05/06/2026
Maxaa kaga baxey Hadii aad tahey Qof af xabashiga yaqaano
Aniga shaqsiyan markaan aqriyey waxaa ii soo baxey in cabashooyinkii iyo cadeymihii arkeen ku celis tahey.
Horeyna waan idinkugu sheegey.
Tuliguled
ማስታወቂያ: በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለተሣተፋችሁ የፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም መከናወኑ ይታወሳል።
ቦርዱ በዕለቱ የፓለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታ ዴስክ በማቋቋም፣ ቀደም ብሎ ባቋቋመው “የምርጫ ቅድመ ማስጠንቀቂያ፣ ጥቆማ ማድረጊያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት” አማካኝነት በስልክ፣ በአጭር ጽሑፍ መልዕክት መቀበያ እና በደብዳቤ ጭምር አቤቱታዎችን ተቀብሏል፤ በዚኽም በዕለቱ መፈታት የሚችሉትን ችግሮችም ሲፈታ ቆይቷል።
የድምፅ መስጫው መጠናቀቅን ተከትሎም ቦርዱ ገለልተኛ የሕግ ባለሞያዎች ቡድን አደራጅቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከተለያዩ አካላት የቀረቡ ቅሬታዎችን በመመርመር ላይ ይገኛል።
ከቀረቡት ቅሬታዎች ውስጥ አንዳንዶቹ በየደረጃው በሚከናወነው የምርጫ ሂደት መቅረብ የነበረባቸው እና በምርጫ ክልሎች ደረጃ የሚቀርቡ ሲሆኑ፤ ሌሎቹ ደግሞ ቦርዱ በምርመራ የሚያያቸው ናቸው።
ምንም እንኳን ቅሬታ አቀራረብን በተመለከተ ቦርዱ ለፓርቲዎቹ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም፤ ከቀረቡት አቤቱታዎች የተወሠኑት የተቆራረጡ፣ ሙሉ መረጃ ያልያዙ እና መካተት የሚገባውን መረጃዎች ያላካተቱ መሆናቸው የምርመራ ሂደቱን ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩን ቦርዱ ተረድቷል።
እስካሁን የቀረቡ አቤቱታዎች ላይ ቦርዱ ማጣራቶችን እያከናወነ ቢሆንም፤ በምርጫው የተወዳደሩ እና በድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ፣ በውጤት ቆጠራ እና አገላለጽ ላይ አቤቱታ ያላቸው ፓርቲዎች ያሏቸውን አቤቱታ በአንድ አጠቃልለው እና የሚከተሉትን ፍሬ ነገሮች እንዲያሟላ አድርገው ቅሬታ ማቅረቢያው እስከሚያበቃበት እስከነገ ቅዳሜ ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ ለቦርዱ እንዲያስገቡ በጥብቅ ያሳስባል።
1. አቤቱታ የቀረበበት የምርጫ ክልል ስም (ቦርዱ ባፀደቀው ስም ብቻ የጻፈ)
2. አቤቱታ የቀረበባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ስም ዝርዝር (ቦርዱ ባፀደቀው ስም ብቻ የጻፈ)
የጣቢያው ዝርዝር ከ20 በላይ ከሆነ በተጨማሪ ወረቀት ላይ ተዘርዝሮ ይያያዝ፡፡
3. አቤቱታ የቀረበበት ምክር ቤት ዓይነት (ለክልል ምክር ቤት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለሁለቱም)
4. የአቤቱታ አቅራቢ ፓርቲ (የአቤት ባዩ ወኪል ሙሉ ስም፣ የአቤት ባዩ ወኪል፣ ኃላፊነት፣የአቤት ባዩ ወኪል ስልክ ቁጥር)
5. አቤቱታው ለቦርዱ ማንኛውም አካል ለመጀመሪያ ጊዜ የቀረበበት ቀን
6. ከድምፅ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ የቅሬታው መነሻ ምክንያት
• መራጮች አንድን የፖለቲካ ፓርቲ ወይም ዕጩ እንዲመርጡ ተገደዋል
• መራጮች የፈለጉትን ፓርቲ ወይም ዕጩ እንዳይመርጡ ገደብ ተጥሎባቸዋል
• መራጮች በምርጫ አስፈጻሚዎች ጫና ተደርጎባቸዋል
• የምርጫው ሚሥጥራዊነት ተጠብቆ ድምፅ የመስጠት ሂደት አልተከናወነም
• ለመራጮች መደለያ ተሰጥቷል
• ምርጫ አስፈጻሚዎች መደለያ ተቀብለዋል
• የምርጫ ጣቢያው ሕጋዊ ባልሆኑ ሰዎች ቁጥጥር ሥር ወድቋል
• ታዛቢዎች እና የዕጩ ወኪሎች የድምፅ አሰጣቱን ሂደት እንዳይታዘቡ ተከልክለዋል
• ሐሰተኛ የምርጫ ሠነዶች ጥቅም ላይ ውለዋል እና መሰል አቤቱታዎች
7. ከድምፅ ቆጠራ ሂደት ጋር የተያያዘ የቅሬታው መነሻ ምክንያት
• በሕግ መሠረት ዋጋ አልባ የሆኑ እና ጥቅም ላይ ያልዋሉ የተበላሹ ድምፅ መስጫ ወረቀቶች ተቆጥረዋል
• ሕጋዊ ድምፅ አላግባብ ዋጋ እንዲኖረው ተደርጓል
• ድምፅ መቆጠሩ እና ማዳመሩ ወቅቱን እና ሥርዓቱን ጠብቆ አለመከናወኑ የውጤቱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል
• የድምፅ መስጫ ሣጥን እሽግ ተቀድዷል፣ ተሠብሯል ወይም ብልሽት ደርሶበታል
• ለምርጫ ጣቢያው ከደረሰው የድምፅ መስጫ ወረቀት ብዛት በላይ የሆነ የድምፅ መስጫ ወረቀት ተገኝቷል
• የድምፅ ቆጠራው የተከናወነው በሕግ ከተፈቀደው ቦታ ውጪ ነው
• የድምፅ ቆጠራው በቂ የተፈጥሮ ወይም ሰው ሰራሽ ብርሃን በሌለበት እንዲከናወን ተደርጓል
• የድምፅ ቆጠራው ሲከናወን ታዛቢዎች የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ አባላት ወይም የዕጩ ወኪሎች እንዳይገኙ ተከልክለዋል እና መሰል ጥሰቶች፡፡
8. ውጤት ይፋ ማድረግን በሚመለከት የቅሬታው መነሻ ምክንያት
• የምርጫው ውጤት ለሕዝብ እስከአሁን ይፋ አልተደረገም/አላግባብ እንዲዘገይ እየተደረገ ነው
• የምርጫ ጣቢያው ኃላፊ ለግል ዕጩ ወይም ለፖለቲካ ፓርቲ ወኪል የውጤት መተማመኛ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለም
• የምርጫ ውጤት መግለጫ ቅጾች በአግባቡ እየተሞሉና እየተፈረሙ አይደለም እና መሰል ጥሰቶች፡፡
9. በአስፈጻሚዎች፣ በመራጮች፣ በፓርቲ ዕጩ ወኪሎች ላይ የተፈጸሙ የማስፈራራት፣ ሌላ የኃይል ተግባር ወይም የሥነ-ምግባር ጥሠቶች
• ሕገ-ወጥ እሥራት
• ማስፈራራት እና ዛቻ
• የታጠቀ ኃይል ከመደበኛ መጠን በላይ በጣቢያ አካባቢ እንዲሠማራ መደረግ
• መራጮች አንድን የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የግል ዕጩ እንዲመርጡ ተገድደዋል
• የምርጫ አስፈጻሚዎች መደለያ እየተቀበሉ ነው እና መሰል ጥሰቶች፡፡
ሌሎች ካለ ይጠቀስ
10. ከተራ ቁጥር 5-8 የተፈጸሙ ጥሠቶች ዝርዝር ሃሳብ በአጭሩ
• ለቅሬታው መነሻ የሆነውን ጥሠት የፈጸሙ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ከነኃላፊነታቸው
11. የቀረበው ሠነድ ማስረጃ ዝርዝር
12. የቀረበው የኦዲዮ ወይም ፎቶ-ግራፍ ወይም የቪዲዮ ማስረጃ
13. የቀረበው የሰው ማስረጃ (ስም፣ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር)
14. አቤቱታው ለምርጫ ጣቢያ ኃላፊ ወይም ለምርጫ ክልል አቤቱታ ሰሚ ስለመቅረቡ
15. በመጀመሪያ ደረጃ ቅሬታ ሲቀርብ የተሰጠው ውሣኔ
16. ቅሬታ አቅራቢው ከቦርዱ የሚጠይቀው ዳኝነት (ውጤት እንዳይገለጽ እንዲታገድ፣ ድጋሚ ቆጠራ እና ውጤት ማስተካከል፣ ውጤት መሠረዝ እና ድጋሚ ምርጫ፣ በጥሠት ፈጻሚዎች ላይ አስተዳደራዊ ዕርምጃ እንዲወሰድ)
አቤቱታው በእውነት የቀረበ ስለመሆኑ ቀንና ማረጋገጫ ፊርማ እንዲሁም የፓርቲውን ማኅተም ማካተት።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም.