ኢትዮጵያ Ethiopia

  • Home
  • ኢትዮጵያ Ethiopia

ኢትዮጵያ Ethiopia ትኩስ ዜናዎችን አስተማሪና አዝናኝ መረጃዎችን እናደርሳለን ! (Ethiopia )
(1)

ጫካ ውስጥ አንበሳ ሚዳቆን ሲያሯሩጥ ሩጫውን ብዙ ጊዜ ሚዳቋ የምታሸንፈው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ?‎‎''አንበሳ ለምግብነት ሲያባርር፣ ሚዳቋ ደግሞ ለሕይወት ስለምትሮጥ ነው።''‎‎አላማ (...
29/09/2025

ጫካ ውስጥ አንበሳ ሚዳቆን ሲያሯሩጥ ሩጫውን ብዙ ጊዜ ሚዳቋ የምታሸንፈው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ ?

‎''አንበሳ ለምግብነት ሲያባርር፣ ሚዳቋ ደግሞ ለሕይወት ስለምትሮጥ ነው።''

‎አላማ (Purpose) እና ፍላጎት (Need)

‎እኛ ሰዎች የሆነ ነገር ለማድረግ ስናቅድ/ስንነሳ ''ይህን ለምን አደርጋለሁ ?'' የሚል የምክንያታዊነት ጥያቄ የሁላችን ልብ ውስጥ እንደሚነሳ እርግጠኛ ነኝ።

‎መልሱም፦
‎እንደ አንበሳ ለፍላጎት(ምግብ) ከሆነ ምናልባት ድርጊቱ አስፈላጊ ቢሆን እንኳ በውስጡ ያለው ሀይል ውስንና ከሆነ ጊዜ በኋላ የሚቆም/የሚጠፋ ነው።
‎እንደ ሚዳቆ ለግብ (ሕይወት) ከሆነ ደግሞ ድርጊት በጣም ወሳኝ ነው፣ ጽናትና ትዕግሥቱ የማያቋርጥ ነው፣ ከፍተኛ ሀይል አለው።

‎አንድ ተማሪ ፈተናውን ለማለፍ ብቻ (Need) ከማጥናት ይልቅ አንብቦ/መርምሮ በሚያካብተው እውቀት የራሱና የማህበረሰቡን ሕይወት ለመቀየር/ለማሻሻል ብሎ (Purpose)ቢማር የበለጠ ተነሳሽነት ይኖረዋል።

‎አንድ ካምፓኒ ውስጥ ተቀጥሮ የሚሰራው ሰራተኛ ስራውን ደሞዝ ማስገኛ ብቻ (Need) አድርጎ ከማሰብ ይልቅ ኩባንያውን ትርፋማና ውጤታማ ለማድረግ (Purpose)ቢሰራ የበለጠ እውቀቱን ይጠቀማል።

‎ስናጠቃልል:-
‎አላማ/ግብ ከፍላጎት በላይ ሀይል አለው
‎ለአላማ እንስራ፣ ለአላማ እንኑር !
‎.
‎.
‎እስኪ በጊዜያዊ ነገር ብቻ ለተጠመዱ ሸርርርር አድርጋችሁ አንቋቸው

..አሁን ኮሌታ ያን ያሀል የሚፈጠጥበት የጨረቅ  ክፍል ነዉ? ገብቶኛል፥ በኮሌታየ መቀደድ ዉሰጥ  የኢኮኖሚ  ኩስምናየ አሳስቦት ነዉ።  የገዛ እህቷ  አስተያየት  ስላላማራት  አንባቢና የተማ...
21/09/2025

..አሁን ኮሌታ ያን ያሀል የሚፈጠጥበት የጨረቅ ክፍል ነዉ?

ገብቶኛል፥ በኮሌታየ መቀደድ ዉሰጥ የኢኮኖሚ ኩስምናየ አሳስቦት ነዉ። የገዛ እህቷ አስተያየት ስላላማራት አንባቢና የተማርኩ መሆኔን አተተች። ማንበብና መማሩ አሮጌ ሸሚዙን ካልቀየረለት ምን ይጠቅመዋል? ትል ይሆናል ።

የአለም አንደኛው ና ትልቁ መመዘኛ ጨርቅ ነዉ ። በካፒታሊዝም አለም ቅን ልቦች፣ መልካምነት ፣ እዉቀት ፣ አስተዋይነት፣ .... የሚባሉ ሃሳቦች ገንዘብ ካላመጡ ቦታ የላቸዉም ።

በመኖር በኩል (አድሀኖም ምትኩ )

አንድ ባልና  ሚስት 25 ዓመታትን በትዳር ውስጥ ያለምንም ክርክር አሳልፈው አከበሩ። ሰዎች የዚህ ምስጥርን ለማወቅ ጠየቁት "በሁለታችሁ መካከል ያለምንም ልዩነት 25 አመት እንዴት አለፈ?"‎...
18/09/2025

አንድ ባልና ሚስት 25 ዓመታትን በትዳር ውስጥ ያለምንም ክርክር አሳልፈው አከበሩ። ሰዎች የዚህ ምስጥርን ለማወቅ ጠየቁት "በሁለታችሁ መካከል ያለምንም ልዩነት 25 አመት እንዴት አለፈ?"

‎ባልየውም- በመጀመሪያዎቹ የጫጉላ ሽርሽር ቀናቶች ወደ ገጠር ወጥተን ሁለታችንም ፈረስ እየጋለብን ነበር.. ፈረሱ ግን ሚስቴን ወደ መሬት ጣላት፤ ሚስቴም ተነስታ የፈረሱን ጭንቅላት ዳበሰችውና እንደዚህ አለችው "ይህ የመጀመሪያ ነው" ቀጥሎ በሁለተኛው ሙከራ ፈረሱ እኔን ጣለኝ፤ አሁንም አናቱ ላይ ዳበሰችውና "እናም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው አለች" በሶስተኛው ሙከራም ወደቀች ሚስቴም ተረጋግታ ተነሳችና ቦርሳዋን ከፍታ ሽጉጥ አውጥታ የፈረሱን ጭንቅላት ላይ ተኩሳ ገደለችው።

‎ያየውትን ማመን ስላቃተኝ "ምንድነው ያደረግሽው እብድ ነሽ እንዴ! ፈረሱን ለምን ገደልሽው?" ብዬ ጮውኩባት። ዓይን ዓይኔን እየተመለከተች ወደኔ ጋር መጥታ ጭንቅላቴን በእርጋታ ዳበሰችውና እንዲህ አለችኝ፦ "ናፍቀኸኛል እና ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው.." ከዛ ቀን ጀምሮ በፍቅር፣ በሰላም፣ በደስታ እና በፍፁም መረጋጋት ውስጥ እንኖራለን። ለሁለተኛ ጊዜ አልደረስንም😍

‎ሸርርርር እየተዝናኑ ቁምነገር ለሚፈልጉ

‎ኤሊወች ትልቁ የደህንነት ዋስትናቸው የድንጋይ ልብሳቸው ብቻ አይደለም፤ የቆሙበትን መሬት ቆንጥጠው የመያዝ ብቃታቸውም ጭምር እንጅ። ‎‎ጠላት ሲመጣባቸው ድንጋያቸው ውስጥ ገብተው በቆሙበት መ...
18/09/2025

‎ኤሊወች ትልቁ የደህንነት ዋስትናቸው የድንጋይ ልብሳቸው ብቻ አይደለም፤ የቆሙበትን መሬት ቆንጥጠው የመያዝ ብቃታቸውም ጭምር እንጅ።

‎ጠላት ሲመጣባቸው ድንጋያቸው ውስጥ ገብተው በቆሙበት መሬት በፅናት ከተቸከሉና መሬት ከያዙ ማንም አያነቃንቃቸውም።

‎አንዳንዴ ታዲያ እርስ በእርስ ይጣላሉ። ያኔ አወኩሽ ናኩሽ ድንጋያቸው ውስጥም አይገቡም ፣መሬትም አይዙም። እርስ በእርስ ሲገፋፉና አንዱ አንዱን ለማሸነፍ ሲታገሉ አንድኛቸው ወይም ሁለቱም ይገለበጣሉ።

‎ሲገለበጡ የደህንነት ከለላቸው የነበረው የድንጋይ ልብስ ከታች ስለሚሆን ራሱ ጠላታቸው ይሆናል። እንዳይነሱ በክብደቱ ይይዛቸዋል።

‎ያኔ ከወፍና አይጥ ጀምሮ ቀላል እንስሳት ሳይቀሩ ይጫወቱባቸዋል።
‎አይናቸውን ያወጡታል፣ እግራቸውን እንደድንች ይፈረፍሩታል።

‎በራሳቸው የድንጋይ ሰሀን ለጠላቶቻቸው የቀረቡ ምግቦች ይሆናሉ። በሌሎች ይበላሉ። በቆማችሁበትን ፀንታችሁ ቁሙ፣ በአጉል መናናቅ አትገፋፉ። አንዳንዴ ከተገለበጥን ኋላ መነሳት እንደምናስበው ቀላል አይሆንም። ባለችን ትንሽ ሳንቲምና ግዜያዊ አጨብጫቢዎች በማን አለብኝነት ከስራችን የምንጥለው ዋስትና መከራችን ይሆናል።

ሸርርርርር አድርግለት ትእቢት ወጥሮት ሊጥልህ ለሚታገልህ

‎‎የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ። ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ።‎‎ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ...
17/09/2025


‎የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ። ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ።

‎ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ ፣ እስክሪቢቶውን ወደ ኪሱ እየከተተ ፣ የዛሬው ሌክቸር እዚ ላይ ያበቃል፣ አለና ፈገግ ብሎ ነገር ግን መጀመሪያ አንድ ታሪክ እነግራችኋለው አላቸው። ሁሉም በጉጉት መጠበቅ ጀመረ

‎" ትላንት ቤቴ እንቅልፍ ስላስቸገረኝ ፣ዝም ብዬ ተነስቼ ነዳጅ ሞልቼ በዛውም ልናፈስ ለዛሬም ጊዜ ለመቆጠብ ከመሽ ወጣሁ ነዳጅ ከሞላሁ በኋላ ከትራፌክ ነጻ የሆነው መንገድ ላይ እየተንሸራሸርኩ ከሆነ ድግስ ቦታ የወጣች የምትመስል ቆንጂዬ ወጣት አየሁ።

‎መኪናዬን አዙሬ እርዳታ እንደምትፈልግ ጠየኳት "ታክሲ እንዳጣች እና ቤቷ እንዳደርሳት ጠየቀችኝ"

‎ጋቢና ገባች....ማውራት ጀመርን....ውበት ብቻ ሳይሆን ባወራነው ርእስ ሁሉ በጣም ስማርት ጭንቅላት እንዳላት ከምታወራው መገመት ቻልኩ።

‎ቤቷ እንደደረስን ፣በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ነገረችኝ ፣እኔም ጥሩ አስተሳሰብ እንዳላት ነግሬያት በሌላ ጊዜ ተገናኝተን ሻይ ቡና እንድንል ጠየኳት በሀሳቤም ተስማማች ፣ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር እንደሆንኩ አውርተን ፣ስልክ ተለዋወጥን።

‎ልንለያይ ስንል አንድ ነገር ላስቸግርህ ስትለኝ ፣ምንም ችግር የለውም አልኳት ።"ወንድሜ አንተ የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተማሪ ነው፣ በኛ ግንኙነት እንዳይጎዳ ቃል ግባልኝ" አለችኝ ....ችግር የለም ብዬ ስሙን ጠየኳት ስሙንም ነገረችኝ።

‎ምናልባት ብዙ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ስለሚማሩና ተመሳሳይ ስም ሊኖራቸው ስለሚችል ወንድምሽን እንዴት ልለየው እችላለሁ ? ስል ጠየኳት።

‎እሷም :- ወንድሜ አንድ መለያ ባህሪ አለው በሱ ታውቀዋለህ፣ ፉጨት ማፏጨት ያዘወትራል። አለችኝ

‎ከዛ ሁሉም ተማሪ ወደ አፏጨው ልጅ ዞሮ ማየት ጀመረ

‎ፕሮፌሰሩም :- "የሳይኮሎጂ PHDዬን ተምሬ እንጂ ገዝቼ አይደለም ያገኘውት ና ውጣ ብሎ ጆሮውን ይዞ ከክፍል አስወጣው ።
‎(ፍራሽ አዳሽ)

‎ሸርርርር ማድረግ እንዳይረሱ

‎‎ ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል፡፡ ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በሗላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው፡፡ አስተማሪውም ግራ በመጋባት...
16/09/2025


‎ ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል፡፡ ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በሗላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው፡፡ አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታወስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡

‎ ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት፡፡ "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ፡፡ ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄው ነበር፡፡ እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፣ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን፡፡

‎በዚያን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፣ የምገባበትን አጣሁ፡፡ አስበው ሰዓቱ በእኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ሲሰድበኝ፣ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፣ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ፡፡ በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰማኝ፡፡ በቃ መጥፎ ዜናው ሊነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ሞንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ፡፡ ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን፡፡ እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ፡፡ በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፣ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀው ምንም አልተናገርክም ነበር፡፡

‎በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፡፡ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም፡፡ እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳዳንክልኝና ስብዕናዬን እንደጠበቅክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለሁ፡፡ አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገመትኩም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው፡፡

‎አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘሁ ግን አላስታውስም ፣ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!" አለው፡፡


በህይወታችን_ለምናከናውናቸው_ነገሮች_ሁሉ_ጥበብ_ያስፈልጋል‎፡፡
‎እንደ አስተማሪ እንደወላጅ እንደ መሪ ....ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን፡፡
‎ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም፡፡

‎ሸርርርር በማድረግ ጥበብ ለሚያስፈልጋቸው አስተምሯቸው

‎ መልካም ግዜ ይሁንላችሁ

አንዳንድ ታሪኮች ይገርማሉ እንዳሰብናቸው አያልቁም!!!ለአስቸኳይ ሰርጀሪ ተደውሎ የተጠራው ዶክተር እየተጣደፈ ከሆስፒታሉ ደረሰ፡፡ ልብሶቹን በፍጥነት ቀይሮ ወደ ሰርጀሪ ክፍል ሊገባ ሲል የታማ...
15/09/2025

አንዳንድ ታሪኮች ይገርማሉ እንዳሰብናቸው አያልቁም!!!
ለአስቸኳይ ሰርጀሪ ተደውሎ የተጠራው ዶክተር እየተጣደፈ ከሆስፒታሉ ደረሰ፡፡ ልብሶቹን በፍጥነት ቀይሮ ወደ ሰርጀሪ ክፍል ሊገባ ሲል የታማሚውን ልጅ አባት ከበር ላይ ተክዞ አገኘው፡፡ አባት ዶክተሩን እንዳየው በንዴት ጦፎና ተስፋ ቆርጦ ይናገር ጀመር፡፡
‎''ልጄ በህይወት እና በሞት መሃል ሆኖ ይህን ያህል እንዴት ትዘገያለህ?!!! ምን ዓይነት ሃላፊነት የማይሰማህ ሰው ነህ? የአንተ ልጅ መትረፍ እየቻለ ዶክተር ባለማግኘቱ ቢሞት ምን ይሰማሃል? ምንም የሙያ ስነ-ምግባር የሌለህ ሰው ነህ!!!....''
‎ዶክተሩ ፈገግ ብሎ መለሰ ''ይቅርታ የኔ ወንድም ቅርብ ስላልነበርኩ ነው እንጂ እንደተደወለልኝ ነው የተነሳሁት!!! የሚቻለውን ሁሉ ከፈጣሪ ጋር እናደርጋለን አንተም ፀልይ'' ብሎት ወደ ሰርጀሪ ክፍል ገባ፡፡
‎አባት ግን ብዙ ከመናገር አልተቆጠበም ነበር፡፡
‎ረጅም ሰዓት የፈጀው የሰርጀሪ ውጤቱ አስደሳች ነበር፡፡ ዶክተሩ ከሰርጀሪ ክፍሉ እየተጣደፈ ሲወጣ አሁንም አባትየው አገኘው፡፡ ቆሞ እንዲያናግረው ቢጠይቀውም በምልክት ነርሱን እንዲያናግረው ጠቁሞት በችኮላ ከግቢው ወጣ፡፡ ነርሱም ሁሉም ነገር መልካም እንደሆነ አስረዳው፡፡ አባትየው ግን በዶክተሩ ሁኔታ አዝኖ ለነርሱ እንዲህ አለው፦ "ጉረኛና ሰው የሚንቅ ሰው ነው!!! ስለልጄ ሁኔታ እየጠየቅኩት ጥሎኝ ሲሄድ አይተሃልአይደል?'' አሁን ቆሞ እኔን ቢያናግረኝ ምን ይጎድልበታል?
‎በጣም የሚያሳዝን ሰው ነው!!!''
‎ነርሱ ስለዶክተሩ መናገር ሲጀምር እንባው ባይኑ ሞላ፡፡ ''ዶክተሩ አንዲት እጅግ የሚወዳት ልጁን ዛሬ በመኪና አደጋ አጥቷታል፡፡ ለአንተ ልጅ ህክምና እንዲመጣ ስንደውልለት ወደ ቀብር እየተነሱ ነበር፡፡ የልጁን ቀብር እንዲዘገይ አድርጎ ነው ወደዚህ የመጣው፡፡ አሁን ያንተን ልጅ አክሞ ካተረፈልህ በኋላ ልጁ ቀብር ላይ ለመድረስ፤ ሃዘኑንም ሊያወጣ ነው እየተቻኮለ የሚሄደው'' ሲል መለሰለት፡፡

‎👉 አንዳችን የሌላችንን ህይወት በማናውቅበት አግባብ መፍረድ ውጤቱ ስህተት ነው፡፡ ምናልባትም ፀፀትን የሚወልድ ስህተት፡፡

‎ሸርርርር በማድረግ በችኮላ ሰዎች ላይ እሚፈርዱ ሰዎች እንዲማሩበት እናድርግ።

‎እርሰዎ ቢሆኑ ማንን ይመርጣሉ‎‎ አንድ ቆንጆ ሴትን አራት ወንዶች ለትዳር ጠየቁ‎አንዱ ዘፈኝ ነው‎አንዱ ወታደር‎አንዱ ዓሳ አጥማጅ‎ አንዱ ዶክተር‎አንድ ቀን ልጅቷ ወንዝ ዳር ልብስ እያጠበ...
14/09/2025

‎እርሰዎ ቢሆኑ ማንን ይመርጣሉ

‎ አንድ ቆንጆ ሴትን አራት ወንዶች ለትዳር ጠየቁ
‎አንዱ ዘፈኝ ነው
‎አንዱ ወታደር
‎አንዱ ዓሳ አጥማጅ
‎ አንዱ ዶክተር
‎አንድ ቀን ልጅቷ ወንዝ ዳር ልብስ እያጠበች በአጋጣሚ አዞ ሲመጣ በድንገጤ ወንዙ ወስጥ ወደቀች።

‎ከዛ ዘፋኙ ቶሎ ብሎ ምርጥ ሙዚቃ መዝፈን ጀመረ አዞዎቹ ልጅቷን
‎ትተው ሙዚቃ ለማዳመጥ ከውሃ ወስጥ ወጡ
‎ወታደር ተኩሶ ገደላቸው
‎ዓሳ አጥማጁ ቶሎ ብሎ ልጅቷን ከወንዝ ውስጥ አወጣ
‎ዶክተሩ በጣም ተጎድታ ስለነበረ አከመ።

‎ጥያቄ ፦ ልጅቷን ማግባት ያለበት ማነው ???

‎ሺርርርር አድርጉትና እስ ምርጫ እንይ

ውሳኔ     እና         ተግባርአንድ መምህር ነው አሉ ተማሪዎቹንየዉሳኔ እና ተግባርን ልዩነት እንዲረዱ በማሰብ አንድ ጥያቄ ይጠይቃል፤ ጥያቄዉም "በአንድ ዛፍ ላይ የተቀመጡ ስምንት ወፎ...
14/09/2025

ውሳኔ
እና
ተግባር
አንድ መምህር ነው አሉ ተማሪዎቹን

የዉሳኔ እና ተግባርን ልዩነት እንዲረዱ በማሰብ አንድ ጥያቄ ይጠይቃል፤ ጥያቄዉም "በአንድ ዛፍ ላይ የተቀመጡ ስምንት ወፎች አሉ ብላችሁ አስቡ፤ከነዚህ ስምንት ወፎች መሃል ስድስቱ ለመብረር ቢወስኑ ስንት ወፎች በዛፉ ላይ ይቀራሉ???" የሚል ነበር።

አብዛኞቹ ተማሪዎች "ሁለት ወፎች ብቻ ናቸዉ የሚቀሩት!!" ሲሉ ይመልሳሉ፡፡ አንድ ተማሪ ግን "በዛፉ ላይ የሚቀሩት ወፎች ስምንት ናቸዉ።'' በማለት ይመልሳል፡፡

ምህሩም እንዴት ስምንት ወፎች ሊቀሩ እንደሚችሉ እንዲያብራራ ይጠይቁታል...

ተማሪዉም ''ጥያቄዉ ወፎቹ ለመብረር መወሰናቸዉን እንጂ መብረራቸዉን አይገልፅም!!!ዉሳኔ እና ተግባር ፍፁም የተለያዩ ናቸዉ!!!!"ሲል ያብራራል

መምህሩም ትክክለኛው መልስ ልጁ የመለሰዉ እንደሆነ በመግለፅ .....''ብዙዎች ይህን አደርጋለሁ፣ይህን አላደርግም ሲሉ በተዋቡ ቃላት መወሰናቸውን ሲገልፁ ይሰማሉ፤ይሁን እንጂ ኑሯቸዉን ስትመለከቱ ተናገረዋቸዉ የነበሩ ዉቡ ቃላቶችን አታገኟቸዉም።ብዙዎች ያወራሉ ጥቂቶች ብቻ ይተገብራሉ፤ዉሳኔ አንድ ነገር ነዉ ተግባር ግን መገለጫ ነዉ።"
የዚህ አይነት ሰው ሁነው እያስቸገሯችሁ ላሉ ሸርርር አድርጉላቸው።

ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ። ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡እን...
13/09/2025

ዝሆንና ዉሻ በአንድ ቀን አረገዙ። ከሶስት ወር በኋላ እርጉዟ ዉሻ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኋላ ዉሻዋ እንደገና አርገዘች...ከዘጠኝ ወር በኋላ ሌሎች 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡እንደዚህ እያለች ብዙ ልጆችን ወለደች። በአስራ ስምንተኛዉ ወር ዉሻዋ ዝሆኗን እንዲህ አለቻት "እርጉዝ መሆንሽን ግን እርግጠኛ ነሽ? እኔም አንቺም እርግዝናችን የጀመረዉ አንድ ቀን ላይ እንደነበር አስታዉሳለሁ፡፡

‎ይኸዉ እኔ ሶስት ጊዜ ወልጄ ከደርዘን በላይ ልጆች አሳድጌ ትላልቅ ሆነዉ ልጅ በልጅ ሆኛለሁ።አንቺ ግን አሁንም እርጉዝ ነሽ ችግር አለ??'' ዝሆኗም መልሳ እንዲህ አለቻት “አንድ እንድታዉቂልኝ የምፈልገዉ እኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ።ልወልድ የምችለዉ በሁለት አመት አንዴ ብቻ ነዉ፤ግን ልጄ ገና ተወልዶ መሬቱን ሲረግጥ ሰዎች ተደንቀዉ ይጎበኙታል።የሁሉንም ቀልብ ይስባል ስለዚህ የተሸከምኩት ሃይለኛና ትልቅ ቀልብ የሚስብ ነዉ''

‎እኛም ሰዎች ለጥያቄዎቻቸው እና ለጸሎቶቻቸው መልስ ሲያገኙ አንተ ግን ሳታገኝ ስትቀር ተስፋ አትቁረጥ።በሌሎች ምስክርነት አትቅና፡፡የራስህን የጸሎት መልስ ካላገኘህ ዉስጥህ አይሰበር ይልቅ የራስህ ጊዜ ሲደርስና ልክ እንደ ዝሆኗ ልጁ ተወልዶ መሬት የረገጠ እለት ሰዎች በአድናቆት የተወለደዉን የፀሎት ውጤት በቅርብ ይመለከቱታል፡፡አንተም ለምስክርነት የምትቀርብበት ቀን አለ።መታገስ ዋጋ አለው ትልቅ ሃሳብ አስቦ እና ትልቅ ህልም አልሞ በብርሃን ፍጥነት ውጤቱን ካላየሁ አይባልም፡፡

‎ቸኩለው እየተሰቃዮ ላሉ ሸርርርር አድርጉና አራጋጓቸው!!

ልጅ ሚስት በሚፈልግበት ወቅት አባቱ የሰጠው ምክር።ልጄ ሆይ፣ በጣም ግልጽና ያልተሸፋፈነ ነገር ነው የምነግርህ።ስለ ሴት መቀመጫ ወይም ጡት መጠን አትጨነቅ፤ ነገር ግን ስለ ልቧና አእምሮዋ መ...
13/09/2025

ልጅ ሚስት በሚፈልግበት ወቅት አባቱ የሰጠው ምክር።ልጄ ሆይ፣ በጣም ግልጽና ያልተሸፋፈነ ነገር ነው የምነግርህ።ስለ ሴት መቀመጫ ወይም ጡት መጠን አትጨነቅ፤ ነገር ግን ስለ ልቧና አእምሮዋ መጠን ተጨነቅ። ስለ ፍቅሯና ስለ ትዕግስቷ መጠን ተጨነቅ፡፡ ምክንያቱም ከአምስት ወይም ከአሥር ዓመት በኋላ ዋናው ነገር ጡት ወይም መቀመጫ አይሆንም፡፡

‎እንደምታየው፣ እናትህ አሁን ላይ በፊት የነበራት ውበት የላትም አንተን ከወለደች በኋላ የበፊት ውበቷ፣የሰውነት ቅርጿ የለም፤ ነገር ግን አሁንም በደስታና በፍቅር በስስት እየወደድኳት አብረን እንኖራለን።እኔንም ተመልከት እጆቸ እንደዚህ ሸካራ አልነበሩም ፣የድሮ ደም ግባቴና ወዜ የለም ገርጥቻለሁ፣ጡንቻየ የለም፣ፀጉሬም ተመልጦ ደረቅ ጭንቅላቴ ነው የቀረው ነገር ግን እሷም አሁንም ከድሮው በላይ ትወደኛለች፣ታከብረኛለች።

‎ገንዘብ የምትወድ ሴትን ተጠንቀቅ፡፡ ማለቴ 'ሁልጊዜ' ስለ ፀጉሯ፣ ልብሷ፣ ጫማዋ፣ ቦርሳዋ፣ የውስጥ ልብሶቿና ሜካፕ የምታወራ ሴትን ስለ ልብ ውበት አታውቅምና ተጠንቀቅ፡፡ጋብቻ ሙሉ በሙሉ ስለ እነዚህ ነገሮች አይደለም፡፡ ያለ ሜካፕ፣ ልብስ፣ ጫማና የውስጥ ልብስ ጥሩ ትዳር ይቆማል፤ ነገር ግን ያለ ፍቅር ምንም ትዳር ሊቆም አይችልም፡፡

‎እናትህን ሳገባ መኪናም ሆነ የራሴ ቤት አልነበረኝም።የተማርኩም እንኳን አልነበርኩም። ነገር ግን ህልሞች ነበሩኝ።እሷም በማንነቴ አድንቃ ደግፋኛለች።ህልምህን የማትደግፍ ማንኛዋም ሴት ለአንዲት ደቂቃ እንኳ ከጎንህ እንድትሆን አትፍቀድላት፡፡ ካንተ በተሻለ ህልምህን የሚያዩ ሴቶች አሉ፤ አንዷን ካገኘህ እድለኛ ነህ!

‎ልጄ ሆይ፣ ጆሮህን በደንብ ክፈት፤ ልትርቃት የሚገባ አይነት ሴት አለች፤ እንዲህ አይነቷን ሴት የማግባት ስህተት እንዳትሠራ፤አለበለዚያ ትጸጸታለህ። ማለቴ ሁልጊዜ ስለ ሁሉም ሰው መጥፎ ነገር የምትናገር ሴት ናት። እንዲህ አይነቷን ሴት ካየህ ሸሽ አምልጥ፡፡ልታገባቸው ከምትችላቸው እጅግ መጥፎ ሴቶች መካከል አንዷ ስለ ሁሉም ነገር የምታማርር ናት፡፡ ይህን ከገዛህ ያኛውን መግዛት ነበረብህ ትላለች፤ ይህን ካደረክ ያኛውንም ማድረግ ነበረብህ ትላለች።ይችን አይነት መቸም ልታስደስታት አትችልምና እባክህን ራቅ ፡፡

‎አብዛኞቹ ሴቶች ማውራት ያስደስታቸዋል፤ ነገር ግን ለሁለት ሰዓት አውርታ ለሁለት ደቂቃ የምታዳምጥ ሴት ለወደፊቱ 'አደጋ' ልትሆን የምትችል ናት። ብልህ ሁን! አስመሳይ አጋርን በጣም ተጠንቀቅ፡፡ አስመሳይ ሴትን ማወቅ ከባድ አይደለም። ሁልጊዜ ስለ ሁሉም ነገር ሁሉን አውቃለሁ ትላለች፤ ጥንቁቅ ትሆናለች። አይንህን ዝም ብለህ ዝጋና ልብህን ክፈት ያኔ ታያታለህ!

‎ፍጹም ነትን አትጠብቅ ፍፁም የሆነች ሴት የለችም፡፡ የምታፈቅርህ፣በህልምህ የምታምን፣የምታከብርህ፣ ቁርጠኛ የሆነች እና ስለ ራሷ ብቻ የማታስብ ሴት ካገኘህ አትልቀቃት፡፡

‎ነገር ግን አስታውስ፣ አንተም ባለጌ ወንድ መሆን የለብህም።ጥሩ ሴት አግኝተህ አንተ ግን መጥፎ ወንድ ከሆንክ ጥሩ ትዳር አይኖርህም!ሚስት አልመርጥልህም፤ ነገር ግን ምክሬን ሰጥቼሃለሁ፡፡ ስታገኛት ለምርቃቴ አምጣት።የምትጨምርልህን እንጂ የምትቀንስብህ ያልሆነች ሴት ያጋጥምህ በማለት የአባትነት ምክሩንና ምርቃቱን ለገሰው፡፡

‎ፈጣሪ ማስተዋልን ጥበብን እውቀትን ከፍቅር ጋር ይስጠን አሜን ፡፡

‎እስኪ ሸርርርርር በማድረግ ለምትወዷቸው እንተም ይህንን ምርቃት አጋሯቸው።መልካም ግዜ

ይህንን ፁሁፍ አንድ ተከታታያችን በውስጥ ልካልን ነው ልብ የሚነካ ፁሁፍ ነው አንብቡት።አባቴ የጉልበት ሰራተኛ ነው፤አዘውትሮ የሚለብሳቸው ውስን ልብሶች ብቻ ነበሩት፤እኔን ግን ምንም ሳያጓድል...
12/09/2025

ይህንን ፁሁፍ አንድ ተከታታያችን በውስጥ ልካልን ነው ልብ የሚነካ ፁሁፍ ነው አንብቡት።
አባቴ የጉልበት ሰራተኛ ነው፤አዘውትሮ የሚለብሳቸው ውስን ልብሶች ብቻ ነበሩት፤እኔን ግን ምንም ሳያጓድል አቀማጥሎ አሳድጎኛል፤በለስ ቀንቶት ያገኘውን ገንዘብ በሙሉ አንድም ሳይቀንስ ለእናቴ ይሰጣትና "የዛሬ ዘመን ልጆች መከፋታቸውን የሚሸሽጉት በሆዳቸው ነው" እስካለሁ ምንም እንዳይጎድልባቸው ብሎ ወደ ሰርክ ስራው ያቀናል፤አባቴን ዘወትር ሰበብ እየፈጠርኩ ገንዘብ እጠይቀዋለሁ፤ገንዘብ ከመጠየቅ በስተቀር አንድም ቀን ግን ስለስራው ጠይቄው አላውቅም ፤ዛሬም አንደወትሮው ወደ ስራ ከመሔዱ በፊት ለትምህርት ቤት ፕሮግራም ትንሽ ብር እንደምፈልግ ነገርኩት፤ትንሽ አሰብ አደረገና "ልጄ ለምን ነገ አልሰጥሽም አለኝ?" ዛሬ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ አልኩት፤ትንሽ አሰብ አደረገና ያልኩትን ብር ሳያጓድል ቦርሳውን አራቁቶ ሰጠኝና በርትተህ ተማር ብሎኝ ሔደ ፤የሚያሳዝነው ግን አባቴ ያን ቀን ጨምሮ ለተከታታይ ቀናት በታክሲ ሁለት ሰአት የሚፈጀውን መንገድ ወደ ስራ ሲመላለስ የነበረው በእግሩ ነበር፤ምክንያቱም ለእኔ የሰጠኝ የትራንስፖርቱን ብር ነበርና፤ከዚያን ቀን ጀምሮ አባቴን አምስት ሳንቲም ጠይቄው አላውቅም፤ከዚህ ይልቅ ሙሉ ትኩረቴን ትምህርቴ ላይ አደረግኩ።

‎ማስታወሻ፦ክብር በአስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ እያለፉ ለልጆቻቸው መስዕዋትነት ለሚከፍሉ ወላጆች ይሁን።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮጵያ Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share