
21/07/2025
በከተማዋ በ2017 የተሰሩ ስራዎች አብዛኞቹ በስኬት ተጠናቀዋል ፦ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ
በከተማው በ2017 በጀት ዓመት ለመፈፀም ከታቀዱት የመሠረተ ልማትና ሌሎች ስራዎች አብዛኛዎቹ በስኬትና በውጤታማነት መጠናቀቃቸውን የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ ገለፁ።
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አመራሮችና አባላት በከተማው የተሰሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች አፈፃፀም ጥሩና አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ ከንቲባ አቶ አብዱ አህመድ በበጀት ዓመቱ ከዕቅድ በላይ መፈፀም ተችሏል ብለዋል።
የተመዘገበው የተሻለና አበረታች ውጤትም የአመራሩ፣ የባለሞያዎች ፣ የባለድርሻ አካላትነ እና የማህበረሰቡ ቁርጠኝነትና በኃላፊነት የመትጋት ውጤት መሆንንም አንስተው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል
በከተማው አንዱ ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራው የከተማዋ "መገለጫ የሆነው የሰላም ጉዳይ ነው"።
ሰላምን አስጠብቆ ለማስቀጠል ከህዝባችን እና ከፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት በቁርጠኝነት ተሰርቷል፤
የ24 ሰዓት ያልተገደበ እንቅስቃሴ ያለበት መሆኑን እና ሰላምን አስጠብቆ ማስቀጠል ተችሎል።
25 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ለመስራት ታቅዶ በመጀመሪያው ምዕራፋ 17.5 ኪ.ሜ መካከል 13.17 ኪ.ሜትሩ ወደ ተግባር ተገብቶ እየተገነባ ነው።ከዚህም መካከል 8.35 ኪ.ሜትር አብዛኛው ስራ ማጠናቀቅ ተችሏል ።
ሌላው ከንቲባ አቶ አብዱ በከተማው ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራው የምዕራፍ ሁለት በ150 ሚሊየን ብር የአስፓልት ግንባታ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ የተቻለ መሆኑንም ገልፀዋል።
በከተማው በ334 ሚሊየን ብር የአስፓልት ግንባታም እየተሰራ ይገኛል።
በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት የህዝቡ ጥያቄ የነበረውን የማህበረሰብ ዓቀፍ መድሃኒት መደብር ደረጃውን በጠበቀና ስታንዳርድ ባሟላ ሁኔታ በሁለት ወር ተሰርቶ መድሃኒት መሟላቱንም አስታውቀዋል።
ሰው ተክር የሆኑ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ መሆኑን አንስተው ከውሃ ልማት ፣የማብራት አቅርቦት በተመሳሳይ በቁርጠኝነት እየተሰራ ነው።
በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች 1600 ለቅድመ አንደኛ ተማሪዎች የምገባ አገልግሎት መስጠት ተችሏል።
በ1.3 ቢሊየን የአስተዳደር ህንፃ እየተሰራ መሆኑንና 680 ሚሊየን በመጀመሪያው ምዕራፍ ወጪ የሚደረግ መሆኑን ከንቲባ አብዱ ገልፀዋል።
ከንቲባ አብዱ በከተማው ትላልቅ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለመገንባትም ታቅዶ ተገብቷል ብለዋል፤የአዳሪ ትምህርት ፣ ቡታጅራ ፓርክ በቀጣይ ይሰራል።
ከተማው ከዚህ በላይ ለምቶና አድጎ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከአመራሮቻችን ከባለሙያዎች እና ከማህበረሰቡ በቁርጠኝነት እንሰራለን።
የተመዘገበው የተሻለና አበረታች ውጤትም የአመራሩ የባለሞያዎችና የማህበረሰብ ቁርጠኝነትና በኃላፊነት የመትጋት ውጤት መሆኑንም አንስተው በከተማ አተዳደሩና በራሳቸው ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
(ሐምሌ 14/2017 የመንግስት ኮሙኒኬሽን)