መንክር ሚዲያ-Menker Media

መንክር ሚዲያ-Menker Media ዝማሬ፤ስብከት፤ወቅታዊ መረጀ ማስተላለፊያ ገፅ

04/11/2025

በአርሲ ዞን አቦምሳ ከተማ ወጣ ብሎ በምትገኝ ገዶ ቀበሌ ውስጥ የተገደሉት 5ቱ ኦርቶዶክሳውያን ስርዓተ ቀብር።

መንክር ሚዲያ-Menker Media

ሌላ 5 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ!!!በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከአቦምሳ ከተማ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትኘው ጋዶ በምትባል ቀበሌ ውስጥ በአጨዳ ላይ እያሉ ትናንት ጥቅምት 24/2018 ዓ/...
04/11/2025

ሌላ 5 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ!!!

በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከአቦምሳ ከተማ 12 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትኘው ጋዶ በምትባል ቀበሌ ውስጥ በአጨዳ ላይ እያሉ ትናንት ጥቅምት 24/2018 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ 5 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ተገድለዋል። በግፍ የተገደሉት ዛሬ አቦምሳ እንደተቀበሩ ከስፍራው መረጃውን አግኝተናል።

የተገደሉት ኦርቶዶክሳውያን ስም ዝርዝር
1.ይርጋ ሲሳይ
2.የሺጥላ ሲሳይ
3.ጥበቡ ዝቅአርጋቸው
4.አሞኜ ኃይልዬ
5.ንጉሴ ከበደ

ከታች በምስሉ እንደምታዩት ስርአተ ቀብራቸው ሲፈፀም ነው
ይሄን ግፍ #ሼር በማድረግ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያድርሱ።

መንክር ሚዲያ-Menker Media

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ...
04/11/2025

ይኼንን ጽሑፍ ቁጭ ብለህ እያነበብህ ያለኸው በዚህ ሰዓት ምሥራቅ አርሲ ገጠር ውስጥ ስላልተገኘህ ብቻ ነው:: በዚህች ቅጽበት በሥጋት ውስጥ ሆነው "ከአሁን አሁን ምን ይመጣብን ይሆን?" እያሉ ያሉ የኦሮሚያ ምእመናን ቁጥራቸው ብዙ ነው:: ከቀናት በፊት የተገደሉትን ተናግረን ሳናበቃ አሁን ደግሞ ሌላ ቦታ አምስት እንደተገደሉ እየሰማን ነው::

ሰሞኑን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ሔሮድስ ስላሳደዳት እመቤታችን "ሰቆቃወ ድንግል" እያልን እያዘንን ነው:: ከሰይፍ ልጅዋን ማስጣል ያልቻለች የአርሲዋን እናትስ እንዴት ዝም እንበላት? ይህንን የማያቆም ሞት ዜና ሰምተን ወደ ጉሮሮአችን የሚወርድ ምግብና መጠጥ የምንተኛውም እንቅልፍ የለም:: የእነርሱ ሞት የእኛ ሞት ነው:: የእነርሱ መቁሰል የእኛ ቁስል ነው:: የቦታ ለውጥ እንጂ በእነርሱ የደረሰው በእኛም ሊደርስ ይችላል::

ቤተ ክርስቲያን ምሕላ እንድታውጅ ፣ ለተሠዉት ተገቢውን ክብር እና ጸሎተ ፍትሐት እንድታደርግ እንጠብቃለን:: ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ቦታ የንጹሐን ደም ዳግመኛ እንዳይፈስስ እንደ ራሔል ዕንባዋን የምትረጭበት ጊዜ አሁን ነው::

የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ትኩረት ያልሠጠውን ችግር ሌላ አካል ሊጨነቅበት አይችልም:: ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን በአስተዳደራዊ መዋቅርዋ መንግሥት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ በሙሉ ትኩረት የምትሠራበት ጊዜም አሁን ነው:: ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ዓይነት ጊዜ የሚያሳየው ምላሽ ከሌለ ሌላ ቀን ቢጣራ የማይሰማውን ቤተ ክርስቲያን አልባ ክርስቲያን በራሱ ላይ ይፈጥራል:: ሐዋርያዊትዋ ቤተ ክርስቲያንም በክህነት የማትመራ የመሆን አደጋ ይገጥማታል:: ክህነት ከሌለ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንም ምሥጢራትም የሉም::

ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ይህንን ጊዜ ለመካሰስ ፣ አባቶችን ለመሳደብ ፣ አንዱ ሌላውን ለማስጠቆርና ለመናቆር ሳይሆን ለጸሎት ለምሕላና ለሰብአዊ ሥራና መሬት ላይ ቢወርዱ ችግሮችን የሚፈቱ ዘላቂ መፍትሔዎች ላይ በትብብር ለመሥራት ምክንያት ብናደርገው የተሻለ ነገር ማምጣት እንችላለን::

የሌላ እምነት ተከታዮች ሆነው ይህ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ጥቃት ብለው ጉዳዩን በተቋምም በግልም ያወገዙ ሰዎችን እናከብራለን:: "ይበላችሁ" ብለው የተሳለቁትን እና በክፉ ቀን ክፋታቸውን ላሳዩን ደግሞ እውነተኛ ማንነታቸውን ስላሳዩን እያመሰገንን "አቤቱ፥ በኢየሩሳሌም ቀን የኤዶምን ልጆች አስብ፦ “እስከ መሠረትዋ ድረስ አፍርሱ አፍርሱ፡” ያሉአትን" ብለን ለሰማያዊው ዳኛ ሠጥተናቸዋል:: መዝ. 137:7






© Henok Haile

መዝሙር
03/11/2025

መዝሙር

ቀሲስ መንግስቱ የእናቴ ልጅ
01/11/2025

ቀሲስ መንግስቱ የእናቴ ልጅ

ይሄ ነው የአባትነት ርህራሄብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በግፍ ከተገደሉት መካከል በተዓምር የተረፉትን በወላይታ ሆስፒታል ተገኝተው አፅናንተው 70 ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋ...
01/11/2025

ይሄ ነው የአባትነት ርህራሄ

ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በግፍ ከተገደሉት መካከል በተዓምር የተረፉትን በወላይታ ሆስፒታል ተገኝተው አፅናንተው 70 ሺ ብር ድጋፍ አድርገዋል። እንዲህ አይነቱን ስናይ ፈፅሞ በአባቶቻችን ተስፋ እንዳንቆርጥ ያደርገናል።

መንክር ሚዲያ-Menker Media

እነኚህ ሁሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቅርቡ በምንጃር አረርቲ በድንገት ሕይወታቸውን ላጡ ምእመናን የሀዘን መግለጫ ያስተላለፉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። በአርሲ ሀገረ ስብከት በጨካኞች ለተገ...
30/10/2025

እነኚህ ሁሉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በቅርቡ በምንጃር አረርቲ በድንገት ሕይወታቸውን ላጡ ምእመናን የሀዘን መግለጫ ያስተላለፉ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው። በአርሲ ሀገረ ስብከት በጨካኞች ለተገደሉት ምእመናን ግን ከሁለት ጳጳሳት ውጪ ሌሎቹ ምንም ማለት አልፈለጉም። ምናልባት የልጅ እና የእንጀራ ልጅ ልዩነት ይኖር ይሆን? እንደውም በሰው በጭካኔ ለተገደሉት ቅድሚያ መሰጠት አልነበረበትም?

በእርግጥ መግለጫ መስጠት የችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ባይሆንም መንግሥት በጉዳዩ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ፣ የሟች ቤተሰቦች "የሚሳሳልን ሀዘናችንን የሚጋራን አባት አለን" ብለው ተስፋ እንዲያደርጉ እንዲፅናኑ ይረዳል።

መንክር ሚዲያ-Menker Media

30/10/2025

በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ስለተገደሉ ምእመናን የቋሚ ሲኖዲሱ መግለጫ

ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው እንደጻፈቺው!!! "ምንም ማለት እኮ አቃተን።ይህ ተገድሎ፣  ተሰዶ፣ ታግቶ የማያልቀው ምእመን ባለቤቱ ማነው? አለሁ ሚለው አባቱ ማነው?በየዓመቱ ገቢ አስገኘን ብላችሁ...
29/10/2025

ጋዜጠኛ መስከረም ጌታቸው እንደጻፈቺው!!!

"ምንም ማለት እኮ አቃተን።

ይህ ተገድሎ፣ ተሰዶ፣ ታግቶ የማያልቀው ምእመን ባለቤቱ ማነው?

አለሁ ሚለው አባቱ ማነው?

በየዓመቱ ገቢ አስገኘን ብላችሁ ምትሸላለሙት እኮ ይህ ነፍስ እና ሥጋውን አስይዞ በሚወጣ በሚገባ የምእመን ላብ ነው።

መቼ ነው ምትደነግጡት? ስንት ልጆችን ስታጡ ነው ሕመሙ ሚደርሳችሁ? የዚህ ጠባቂ የሌለው ምእመን እንባ ግፍ አይሆንም ወይ?

ምእመኑ ከማኅበራዊ ሚዲያ ጩኸት ባለፈ ደፍሮ እንዳይጥይቃችሁ የያዛችሁት ሥልጣነ ክህነት ነውና በጥቅስ ተተብትቦ እያየ ነው።

ቀስ በቀስ የመካከለኛው ክርስቲያኖች እጣ ፋንታ ጋር ገጥመናል።

ሌላው አካባቢ ይቅር በ2 ዓመት ያውም በምሥራቅ አርሲ በአንድ ወረዳ ብቻ 115 ልጆቻችሁን መገደል ሰምታችሁ ይሆን? በእውነት ነገ ፐርሰንት ብላችሁ ፊቱ የመቆም ሞራል አላችሁ? ለነገሩ እስከዛ ካላለቁ ነው።

ኧረ በእንተ ማርያም ብላችሁ ስለጠራችኋት እመብርሃን ይሁንባችሁ።

ባለቤቱን ባይንቁ ይህ ባልሆነ። ለራሳችሁ ክብር በእግዚአብሔር ፊት ምእመኑን ልጠብቁት ስለገባችሁት ቃል ኪዳን ብላችሁ አባቶቻችን አለሁ በሉ።

እኛም አባቶቻችንን ወቃሽ አታሰኙን።

ያረፉትን ወገኖች እግዚአብሔር የሰማእታቱን ዋጋ ያድልልን። ቤተሰቦቻቸውን ያጽናልንም - ያጽናናልንም።"

ሌላ አሳዛኝ ዜና!!!አሁን በደረሰን መረጃ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሌ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ 5 ምእመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ...
29/10/2025

ሌላ አሳዛኝ ዜና!!!

አሁን በደረሰን መረጃ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሌ ዋቤ ወረዳ በቀቅሳ ቀበሌ ጥቅምት 18 ለ19 አጥቢያ 5 ምእመናን በታጣቂዎች መገደላቸውን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በስልክ አድርሰዋል።

መረጃ ሰጭዎቻችን አሁንም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ገልጸዋል።

MK

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መንክር ሚዲያ-Menker Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share