Dilla town culture , tourism & Gov,com

Dilla town culture , tourism & Gov,com Promotion and public figure page

‎ የተነቃቃ የባለሙያዎች ንቃተ ሂሊና ለዕቅድ አፈጻጸም ስኬቶች ጉልህ ሚና አለው፤‎‎ #ዲላ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (ጌዞባቱ)‎‎በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በዲላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የታክሲ ህግ...
03/07/2025

‎ የተነቃቃ የባለሙያዎች ንቃተ ሂሊና ለዕቅድ አፈጻጸም ስኬቶች ጉልህ ሚና አለው፤

‎ #ዲላ ሰኔ 26/2017 ዓ.ም (ጌዞባቱ)

‎በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በዲላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የታክሲ ህግ ማስከበር ዋና የሥራ ሂደት በተግባር አፈጻጸም ላይ የቆዩት ባለሙያዎች የጌዴአ ዞንን ታሪካዊ የቱቲቲ እና ቱቶፈላ መካነቅርስ ስፍራዎችን ጉብኝት አድርገዋል።

‎በዲላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት የታክሲ ህግ ማስከበር ዳይረክቶሬት ዳይረክተር ወ/ሮ አዶናይት ጥላሁን እንደተናገሩት በዞናችን በዩኔስኮ የተመዘገቡ ባህላዊ መልካዓምድር ውስጥ የተደበቁ በርካታ የቱሪስት መዳረሻዎች የቱሪዝም ዕምቅ ሃብቶቻችን ዓለም ዓቀፋዊ ትኩረት በማግኘት ከሀገር ውጪ እና ከሌሎች የሀገራችን የጉብኝት ማዕከላት እየሆኑ መጥተዋል።

‎እንደ ዞናችን የጉብኝት ባህላችንን በማዳበር የዞኑን የቱሪስት መዳረሻዎች አውቆ ከማስተዋወቅና መረጃዎችን ከማዳረስ አንጻር በሁሉም ተቋማት የጉብኝቱ ባህል መዳበር እንዳለበት ገልጸዋል

‎አክሎም ይህ የስራ ሂደት በዲላ ከተማ ውስጥ ከታክስ ህግ ማስከበር ሥራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የስራ ውጥረት የምታይበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በዓመቱ የሴክተሩን ዕቅድ ከግብ በማድረስ የተሻለ አፈጻጸም እንድናስመዘግብ ባለሙያዎቻችን በእጅጉ ተግተዋል ብለዋል።

‎በበጀት ዓመቱ በስራ ሂደቱ የሥራ አፈጻጸም ስተጉ የቆዩ ባለሙያዎች ለቀጣይ የስራ ዘመን ዕቅዱን በተነቃቃ አዕምሮ ተግባራትን ለመፈጸም ዝግጁ በመሆን ንቃተ ህሊናቸውን እንድያድሱ ታስቦ የተደረገ የዞኑ የቱሪስት መስህቦች ጉብኝት ጉዞ እንደሆነ አስረድተዋል።

‎በጉብኝቱ የተሳተፉ አጠቃላይ የዳይረክቶሬቱ ባለሙያዎች በተመለከቱ መስህቦች ታሪካዊነት እና ከዞኑ የቱሪዝም ፕሮሞሽን ባለሙያ በኩል ባገኙት ብርቱ ገለጻ ባገኙት ግንዛቤ መደሰታቸውን መናገራቸውን የገለጸው፦

‎ የጌዴኦ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ቱሪዝም ፕሮሞሽን ነው።

 #ጥሩ መሪ አከባቢን ብሎም ሀገርን ይቀይራል። የአንድ ጥሩ መሪ 10 ዋና ባህሪዎቹ*******************************1. ታማኝነት/Integrity/2. የመወከል ችሎታ/Abili...
01/07/2025

#ጥሩ መሪ አከባቢን ብሎም ሀገርን ይቀይራል።
የአንድ ጥሩ መሪ 10 ዋና ባህሪዎቹ
*******************************
1. ታማኝነት/Integrity/
2. የመወከል ችሎታ/Ability to delegate
3. መግባባት/Communication
4. ራስን ማወቅ/Self-awareness
5. ምስጋና/Gratitude
6. የመማር ችሎታ/Learning agility
7. ተፅዕኖ/Influence
8. ርኅራኄ /Empathy
9. ድፍረት/Courage
10. አክብሮት/Respect

12/06/2025
በኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ2017 ዓ.ም የውድድር ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን የይርጋጨፌ ቡና ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ሁለት ጫወታዎች እየቀሩት ወደ 2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪመር ...
17/05/2025

በኢትዮጵያ ሴቶች ከፍተኛ ሊግ የ2017 ዓ.ም የውድድር ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን የይርጋጨፌ ቡና ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ሁለት ጫወታዎች እየቀሩት ወደ 2018 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪመር ሊግ የገባ በመሆኑ እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላችሁ !! እያልን
በነገው ዕለትም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ ደማቅ አቀባበል ስነስርዓት ስለምደረግ መላው ህዝብ በጋራ ወጥተን እንድንቀበላቸው የጌዴኦ ዞን ስፖርት ሞክር ቤት እና የጌዴኦ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ መልዕቱን ወደ እናንተ ያስተላልፋል !!

Address

Dilla

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dilla town culture , tourism & Gov,com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share