Lafto Prosperity Media

  • Home
  • Lafto Prosperity Media

Lafto Prosperity Media ኢትዮጵያ ረቂቅ ሚስጥር ያላት ሀገር ነች።

    #አመሰግንሃለሁ 🙏 አንተ የትውልድ ብርሃን ነህ  ዘመንን የቀመርህ ፣ ዘመናት እንደ ስፍር በእጅህ የተጨበጡ ፣ ሳትቸገር ዕድሜን የምትቸር ፣ ለዘመኑ የሚሆን ሰው ፣  ለሰውም የሚሆን ዘ...
18/07/2025

#አመሰግንሃለሁ 🙏
አንተ የትውልድ ብርሃን ነህ
ዘመንን የቀመርህ ፣ ዘመናት እንደ ስፍር በእጅህ የተጨበጡ ፣ ሳትቸገር ዕድሜን የምትቸር ፣ ለዘመኑ የሚሆን ሰው ፣ ለሰውም የሚሆን ዘመንን የምትሰጥ ፣ ሁሉን ስታደራጅ ቅሬታ ፣ ሁሉን ስትሠራ እንከን የማይወጣልህ ፣ ይህችን ቀን ያየሁብህ ወዳጄ ሆይ ተመስገን 🙏

ልፋቱ ብዙ ፣ ዕረፍቱ ጥቂት ከሆነው ዓለም ፤ ልፋቱ ጥቂት ዕረፍቱ ብዙ ወደሆነው የቃልህ ገበታ መልሰኝ ፡፡ ሰዎችን ላለመጥላት እየተጠነቀቅሁ እንጂ መውደድ አልቻልኩም 🙏

አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ ነህ ብዬ በአደባባይ መስክሬአለሁ ፡፡ እንደ ጴጥሮስ አላውቅህም እንዳልልህ ፣ በአንድ ምላሴ ሁለት እንዳልናገር እርዳኝ🙏
የፈረቃ ማንነቴ ወደ ወጥ ጨለማ እንዳይሄድ ፣ ቦግ ጭልም ሲል ያበሳጨኝ እኔነቴ ፈጽሞ ቀጥ እንዳይል እባክህ መልሰኝ ፡፡ ወደፊት ስሄድ የተከፈለልኝ ቀይ ባሕር ስመለስ አይከፈልምና መቃብር እንዳይሆንብኝ እባክህ እርዳኝ🙏

የተሻገርኩት እንዳያሰጥመኝ ፣ አንተን እያየሁ መጓዝ ይሁንልኝ🙏 ቃልህን ሰምቼ ስወጣ የሚመራ ሙሴን ሰጠኸኝ ፤ ወደ ኋላ ስል አለቃ እንዳይገጥመኝ እባክህ መልሰኝ ፡፡ ለምለም ሰውነቴ የጨው ሐውልት እንዳይሆን ፣ ተልሶ የሚያልቅ ድንጋይ ፣ ሟሙቶ የሚፈርስ የጨው ቅጥር እንዳይሆን ወደ ፊት መጓዝን ስጠኝ🙏

እውነተኛ የንስሐ ልብ አድለኝ 🙏ጭቃ ላይ ተቀምጬ የምታጠብ ነኝ🙏

ያየሁትን የምመስል ፣ አካባቢውን የምለውጥ ሳይሆን አካባቢ የሚለውጠኝ ፣ ስምህን የጠራ ሁሉ በተቀባ ውሸት የሚያታልለኝ ስስ ሰው ነኝ 🙏
ከምጠላው ብዬ አልዋሽም እባክህ ከምወደው ኃጢአት አድነኝ🙏ለይሉኝታ ሳይሆን ለጽድቅ አኑረኝ 🙏🙏

ሰው ምን አለ ⁉️ሳይሆን እግዚብሔር ምን አለ⁉️ ማለትን አስለምደኝ 🙏
ለመንፈስ ቅዱስ ወቀሳ ከሚጸና ፣ ለሰይጣን ክስ ከሚፈራ ልብ አውጣኝ ፡፡

አንድ ቀን በሞት የሚታሰረው እጄ ቀድሞ በስስት እንዳይታሰር ፣ አንድ ቀን የሚዘጋው አንደበቴ ሰዎችን እንዳይሰብር ጠብቀኝ🙏

ዘላለም ገና ላርፍ ዕረፍት አጣሁ እንዳልል አግዘኝ ፡፡ ያንተን ድምፅ ከእኔ ድምፅ በቃልህ ፣ የጠላትን ድምፅ ካንተ ቃል በመንፈስህ ለይልኝ 🙏

እጆቼ ለመዝራት ፣ አፌም ለምስጋና እንዳይደክም መቅረዜን ይዤ እንድጠብቅህ እርዳኝ🙏🙏
ስጨርስ እንደ ጀመርኩት በፍቅር ግለት ይሁንልኝ 🙏🙏

   #አመሰግንሃለሁ 🙏አንተን መከተል ለእኔ መልካም ሆኖልኛል የጠላቴ ድቆሳ ይበልጥ ወዳንተ አቅርቦኛልና አመሰግንሃለሁ🙏 አንተ ለእኔ የገነት ምንጭ ፣ የሕይወት ፈሳሽ ፣ ብዙ ዘመን ተጠምቼ ያ...
09/07/2025

#አመሰግንሃለሁ 🙏
አንተን መከተል ለእኔ መልካም ሆኖልኛል
የጠላቴ ድቆሳ ይበልጥ ወዳንተ አቅርቦኛልና አመሰግንሃለሁ🙏

አንተ ለእኔ የገነት ምንጭ ፣ የሕይወት ፈሳሽ ፣ ብዙ ዘመን ተጠምቼ ያገኘሁህ እርካታዬ ነህና አመሰግንሃለሁ🙏

ዓይኔ በራስዋ ብርሃን የላትም፡፡ ማስተዋሌም ርቆ አያይም፡፡ ለዓይኔ ብርሃኑ፣ ለማስተዋሌ ኃይሉ አንተ ነህና አትለየኝ፡፡🙏

አንተን መከተል ስጀምር ጠባዬን የሚያውቁ ሁሉ አትዘልቅበትም አሉኝ፡፡ ያንተን ጠባይ አያውቁምና ትንቢታቸው ከሰረ፡፡ አንተ ወላዋዮችን በማይለቅ ፍቅር ትወዳለህና ይኸው ዛሬም በቤትህ አለሁ፡፡ በማልተውህ ሳይሆን በማትተወኝ ጌታ እደሰታለሁ🙏

የማደንቃቸው ፈላስፎች የቢታንያ ድንጋዮች ያወቁህን ጌታ አያውቁምና በራሴ አፈርሁ🙏
የምናገርላቸው ተናጋሪዎች ስለ አንተ አይናገሩምና ከበለዓም አህያ አነሡብኝ 🙏

አንተ የሌለህበት ትዳርና ጉባዔ የመቃብር ስፍራ ሆነብኝ🙏
ወገኖቼ የተሸከሙት የመከራ ቀንበር በሩቅ ሳየው ከበደኝ🙏
አንተ ግን ሸክም ሰጥተህ አቅም አትነሣምና ደግሞም ከእኔ በላይ ለእነርሱ ደግ ነህና በመጽናናት አመሰገንኩህ፡፡ ለዓመታት የናፈቅሁት፣ ላየው የተመኘሁት የአእምሮ ስዕሌ የሆነውን ወዳጅ ፈልጌ አጣሁት፡፡‼️
ለካ ስምህን ሳልጠራ ስፈልግህ የኖርኩት አንተን ነውን?

ለዚያ ወዳጄ የገዛሁትን ውድ ሽቱ በፊትህ እሰብራለሁ🙏
ለማንም አልሰጥም ብዬ የደበቅሁትን ውድ ላንተ እሠዋለሁ🙏 ሌላ እስከማያምረኝ ባንተ ረክቻለሁ🙏 በፈሰሰው ደምህ ለዘላለሙ አሜን🙏

   #አመሰግንሃለሁ 🙏የእስትንፋሴ መሠረት ፣ የመኖሬ ምሥጢር ፣ የመንገዴ ቀያሽ ፣ የሃይማኖቴ አስረጂ ፣ የጥያቄዬ መልስ ፣ የራሴ ራስ ፣ የኑሮዬ ኑሮ ፣ የነፍሴ ነፍስ ፣ ያልተፈጠርህ ሕይወ...
29/06/2025

#አመሰግንሃለሁ 🙏
የእስትንፋሴ መሠረት ፣ የመኖሬ ምሥጢር ፣ የመንገዴ ቀያሽ ፣ የሃይማኖቴ አስረጂ ፣ የጥያቄዬ መልስ ፣ የራሴ ራስ ፣ የኑሮዬ ኑሮ ፣ የነፍሴ ነፍስ ፣ ያልተፈጠርህ ሕይወት ፣ የምስቅልቅሉ አስተካካይ አንተ እግዚአብሔር ነህና አመሰግንሃለሁ 🙏

የፀጥታው ወደብ ፣ የሰማይ መነጽር ፣ የመንፈሳዊ ዓለም ብርሃን ፣ መካኑን ባለፍሬ የምታደርግ ፣ የጸጋ ባለቤት ፣ የሀብታት ምንጭ አንተ እግዚአብሔር ነህና አመሰግንሃለሁ 🙏

የቤተ ክርስቲያን መሥራች ፣ የአገልጋዮች አንደበት ፣ የካህናት ሞገስ ፣ ሳልኖር የምታውቀኝ ፣ ኖሬ የምታበረታኝ ፣ ሞቴን በትንሣኤ የምትለውጥ ፣ በዘላለም ከተማ የምትቀበለኝ ፣ የምትሠራኝ ፣ የምትሠራብኝ አንተ እግዚአብሔር ነህና አመሰግንሃለሁ 🙏

የምታግዘኝ ወዳጄ ፣ ያለነቀፋ የምታስተምረኝ መምህር ፣ የምደገፍብህ ምርኩዝ ፣ የበረሃው ጥላ ፣ ሳላይህ ያየኸኝ ፣ የሕፃንነቴ አሳዳጊ ፣ በሚወዱኝ ውስጥ ሆነህ የወደድከኝ አንተ እግዚአብሔር ነህና አመሰግንሃለሁ 🙏

ዘመን ሲያባርር መጠጊያ ፣ ያከበረ ሲያዋርድ አንተ ንጹሕ ካባ ፣ ቀኑ ሲከፋ መጠጊያ ፣ የእናት ደጅ ሲዘጋ መጽናኛ ፣ መነሻ ሲጠፋ የአልፋው ፊደል ፣ መድረሻው ጭልም ሲል የዖሜጋው ማኅተም ፣ ጠባዬ ሲበላሽ አዳሽ ፣ ስቆሽሽ አጣቢዬ አንተ እግዚአብሔር ነህና አመሰግንሃለሁ 🙏

ሰይጣን ሲከሰኝ የስርየት ቃሌ ፣ ስሜ ሲጠፋ ስሜ ፣ ከጭቃ ስወድቅ ንጽሕናዬ ፣ ፍጥረት ሲያምፅብኝ ተዋጊዬ ፣ ከራሴ ስጣላ ሰላሜ አንተ ነህ ጌታ መንፈስ ቅዱስ ተመስገን 🙏

ላንተም ከዘላለም እስከ ዘላለም ፣ ከልቤ እስከ አርያም ክብር ምስጋና ይሁን 🙏
አሜን 🙏

እድሜ ጨምረህ ለዛሬው ቀኔ ስላደረስከኝ እመስግንሀለው🙏
Biniam Chifraw Sisay

   #አመሰግንሃለሁበአካል ሦስት ፣ በመለኮት አንድ መባል ገንዘብህ የሆነ ፤ አንድነትህ ሦስትነትህን ያልጠቀለለው ፣ ሦስትነትህ አንድነትህን ያልከፈለው በዘላለም ክብር ውዳሴ ያለኸው አብ ወል...
24/06/2025

#አመሰግንሃለሁ
በአካል ሦስት ፣ በመለኮት አንድ መባል ገንዘብህ የሆነ ፤ አንድነትህ ሦስትነትህን ያልጠቀለለው ፣ ሦስትነትህ አንድነትህን ያልከፈለው በዘላለም ክብር ውዳሴ ያለኸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ጌታዬ ፣ በእቅፍህ ለዘላለም በፍቅርህ እስከ ወዲያኛው ባሪያህን ሸሽገው🙏

አላመሰገኑኝም ብለህ የማትከፋ ፤ ባለማመስገናችን ግን የኀዘን ጥላ የሚያጠላብን ፣ ራሳችንን በመጥላት የምንሞገት እኛው ነን ።
ተፈላጊ ነኝ ብለህም ራስህን ገሸሽ አላደረግህም ። ብዙ ሠራዊት አለኝ ብለህም አትመካም ። ሠራዊትህንም የምትጠብቀው ንጉሥ አንተ ነህ🙏
ለክብርህ ፍጥረታትን ፈጠርህ እንጂ ክብር ለማግኘት ያበጀኸው አንድም ፍጡር የለም ። የሰገዱልህ ሲያምፁብን ፣ ያመፁብህ ይሰግዱልሃል 🙏
በቃልህ የተማሩ በሰላም ሲመጡ ፣ በመከራ የተማሩም እያለቀሱ ይመጡብሃል 🙏

አንድም ቀን የምሽት ወዳጅ ነኝ ወይ ? ብለህ በርህን ዘግተህ አታውቅም 🙏የመሸበት አሳዳሪ ፣ ከራሱ ለወጣም ራስህን የምትሰጥ አንተ ነህ ። ከስፍራችን ስንናወጥ መልሰን የምናገኝህ ከስፍራህ ስለማትናወጥ ነው 🙏።

በምስኪኑ ቤት ስታድር ክብሬ ይጎድላል አትልም ፣ ድሀውን ስትወዳጅ የልብሱ መቀደድ አያሳስብህም ። አንዱን በመስጠት ሌላውን በመንሣት ትባርከዋለህ ። ሁሉን እንደ አመሉ ታሳድረዋለህ 🙏

የሌለህበት ጊዜና ቦታ የለም ። የሌለሁበት ጊዜና ቦታ ግን እኔ አለኝ ። ውስኑ ማንነቴ ጽንፍ አልባ ለሆነው ጌትነትህ ይገዛል ። ለመቅረብ ለሚያስፈራው ግርማህ ምስጋና ፣ ሊርቁት ለሚያሳሳው ሞገስህ ውዳሴ ይሁን 🙏

የቆለፍከውን የሚከፍት ለሌለ ፣ የከፍትከውን የሚዘጋ ለሌለ ቅዳሴ ይሁን 🙏
በኋለኛው ቀን አገኘዋለሁ የምለው ዘመድ የለም ፣ ከሞት በኋላ የማገኝህ ዘመዴ አንተ ነህ 🙏

ጥቂት ደቂቃ ለማመስገን ጊዜ እያጣሁ ለዘላለም ለማመስገን ገነትን እናፍቃለሁ 🙏
ወገንነቴ ካንተ ጋር ነው 🙏
ሌላውን የወገኑ አፍረዋል ፣ አንተ ያሉ ድነዋል 🙏
ለዘላለሙ አሜን 🙏
🙏❤️🙏❤️🙏🙏❤️🙏🙏❤️🙏🙏❤️🙏🙏

ሰውዬው ዛሬም በቃሉ የፀና ነው!!!ዛሬ ሰኔ 16 ቀን ነው!የዛሬ 7ዓመት በዛሬዋ እለት በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ፍቅር፣ መፃኢ እድል፣ ህብረ ብሔራዊነት ያተየበት ወቅት ነበር...
23/06/2025

ሰውዬው ዛሬም በቃሉ የፀና ነው!!!
ዛሬ ሰኔ 16 ቀን ነው!
የዛሬ 7ዓመት በዛሬዋ እለት በመስቀል አደባባይ የኢትዮጵያን አንድነት፣ ፍቅር፣ መፃኢ እድል፣ ህብረ ብሔራዊነት ያተየበት ወቅት ነበር፡፡ በእለቱ ሚሊዮኖች የተሳተፉበት ድንቅ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ በእለቱ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድ(ዶ.ር) በእለቱ ምን ብለው ነበር፡፡ በእለቱ የተናገሩትን ዛሬ ሰኔ 2017ዓ.ም ሆነን በምዕናብ ወደ 2010ተመልሰን እያየን ነው፡፡
1. ሰልፉ ላይ የተገኘሁት ለሳየችሁኝ አለኝታነት ላከብራችሁ ነው፡፡
2. ኢትዮጵያ የሰው ልጆች የእስትንፋስ የመጀመሪያ፣ የጥቁር ህዝቦች የነፃነትና የአይበገሬነት አገር ናት፡፡
3. ዓላማችን ሩቅ ነው ግባችንም ሰፊ ነው፡፡
4. አገራችንን ከወደድን ለሚንገላታው ለእያንዳንዱ ዜጋ ልንቆምለት፣ ለምትባክን ለእያንዷንዷ ሰዓት ልንቆረቆርላት፣ በየትኛውም የአገራችን ክፍል መብቱ ሲጣስ ማንነቱን ሳንመለከት ወገኔ ነው ብለን ልንቆምለት ይገባል፡፡
5. አንዱ ሌላውን ከአከባቢዬ ውጣልኝ የሚለው ከሆነ ከቅኝ ገዥዎች በምን እንለያለን?
6. ኢትዮጵያን በጋራ እንገንባ፣ ለኢትዮጵያ ሁላችንም እናስፈልጋታለን፣ ለሁላችንም ታስፈልጋናለች ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞ ገናናቷ እንደምትመለስ ቅንጣትም ያህል ጥርጣሬ አይኑራችሁ፡፡
7. የእምነት አባቶች ዘረኝነትንና ሙስናን አጥፍተችሁ ደሃ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ በሉ፡፡
8. ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያለፈውን እርሱና ለመደመር ትጉ፡፡
9. አገራችን ከወደድን ስልጣን ኃላፊነት እንጂ ገዥነት አይሁን፣ ሹመት ማገልገያ እንጂ መገልገያ አይሁን፡፡
10. ኢትዮጵያ ከ2000 ዓመታት በላይ የዘለቀ የስነ ጽሑፍ ታሪክ ያላት አገር ናት፡፡
11. ግለሰቦችን ከህዝቦች እንለይ፣ እሾህን ከጽጌረዳ እንለይ፣ አይጥ በበላ ዳዋ አይመታ፣ በአንድ ጠማማዛፍ ምክንያት ደኑ አይለቅ፡፡
12. ላለፈው አንድ መቶ ዓመት ጥላቻ ቀልዶብናል፣ ጥላቻ ሸብቦናል፣ ግለኝነት ጎድቶናል፣ ይህንን ሁሉ ችግር አሸንፈን እንድንሻገር የሚያደርገን ይቅርታና ፍቅር ብቻ ነው፤ኢትዮጵያኖች አንበገርም በፍቅር እናሸንፋለን፡፡
አዎ ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩ ቃላቸውን አክብረው ከዚህ ደርሰናል፡፡ በቀጣይ ደግሞ መሰል ድንቅ የድጋፍ ሰልፍ እናደርጋለን!

#ብልፅግና
#ሰላም
#ኢትዮጵያ

ሰኔ 16 የጠላት ተንኮል ወደ ማንቂያ ደወል የተቀየረበት ቀን ነውሰኔ 16 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ቀላል ቀን የምትታይ አይደለችም። ይህች ቀን የጠላትን ተንኮልና ሴራ እንደ ትልቅ ማንቂ...
23/06/2025

ሰኔ 16 የጠላት ተንኮል ወደ ማንቂያ ደወል የተቀየረበት ቀን ነው

ሰኔ 16 በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እንደ ቀላል ቀን የምትታይ አይደለችም። ይህች ቀን የጠላትን ተንኮልና ሴራ እንደ ትልቅ ማንቂያ ደውል የተጠቀምንባት፣ ለሀገራችን አንድነትና ህልውና ወሳኝ ምዕራፍ የነበረችበት ዕለት ናት። የጥፋት ኃይሎች የራሳቸውን የጥላቻ አጀንዳ ለማስፈጸም የፈፀሙት ድርጊት፣ ሳያውቁት ግን የኢትዮጵያ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ እንዲነቃና እንዲተባበር ምክንያት ሆኗል።

በዚህች ቀን የጠላት ተንኮል ፍርሃትን ከመዝራት ይልቅ ለጋራ ዓላማ የምንቆምበትን ብርታት ሰጠን። የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የተሰነዘረው ጥቃት፣ በተቃራኒው ህዝቡን ከዳር እስከ ዳር በማነቃቃት፣ ለአንድነትና ለፍቅር ያለውን ቁርጠኝነት በግልጽ አሳይቷል። ይህ ደግሞ በጠላቶች የተጠነሰሰው ሴራ የከሸፈበት፣ እውነትና ፍቅር ደግሞ ያሸነፉበት አስደናቂ ትዕይንት ነበር።

23/06/2025
አረንጓዴ ኢትዮጵያ፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ አምራች ኢትዮጵያና ፅዱ ኢትዮጵያ ባለቤትየሚሰራው ሁሉም ለኢትዮጵያ ነው። አረንጓዴ ኢትዮጵያ የእሱ ራዕይ ነው። እውን አድርጎ ቢሊዮን ችግኞችን ተክሎ አ...
23/06/2025

አረንጓዴ ኢትዮጵያ፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ አምራች ኢትዮጵያና ፅዱ ኢትዮጵያ ባለቤት

የሚሰራው ሁሉም ለኢትዮጵያ ነው። አረንጓዴ ኢትዮጵያ የእሱ ራዕይ ነው። እውን አድርጎ ቢሊዮን ችግኞችን ተክሎ አሳይቶናል። ሌላ ደግም አምራች ኢትዮጵያን ለአለም እና ለአፍሪካ እውን ለማድረግ ለአመታት ተግቶ ሰርቶ በተግባር አረጋግጧል። ኢትዮጵያ በግብር አምራች፣ በኢንዱስትሪ አምራች እንድትሆን አደረጋት።

ፅዱ ኢትዮጵያ በማለትም ከከተሞች እስከ ገጠር ብዙ ስራዎችን ሰርቷል። ፅዱ እና ለነዋሪዎች ምቹ፣ ለቱሪዝም ሳቢ የሆነን ሃገር መፍጠር ችሏል። አሁንም ይህ ራዕይ የዐቢይ አሕመድ ነው። ይሄንፅዱ ኢትዮጵያ፣ አምራች፣ ኢትዮጵያ እና አረንጓዴ ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ ለማስተሳሰርና አቅም ለመስጠት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ ችሏል።

የዚህ ሰው ራዕይ ኢትዮጵያን ንፁህ አድርጓል። ኢትዮጵያን አምራች አድርጓል።አረንጓዴ አድርጓል። በተጨማሪም ከዘመን ጋር እንድትራመድ ዲጂታል እያደረጋት ነው።

ሰኔ 16 በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በደማቅ ቀለም የተቀረጸች፣ በታሪክም በወርቃማ ቀለም የምትመዘገብ ልዩ ቀን ነች። ゚viralfbreelsfypシ゚viral
23/06/2025

ሰኔ 16 በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ በደማቅ ቀለም የተቀረጸች፣ በታሪክም በወርቃማ ቀለም የምትመዘገብ ልዩ ቀን ነች።
゚viralfbreelsfypシ゚viral

እግድ ተጣለባቸው!የአቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ የሐብታሙ አያሌውና የዘመድኩን በቀለ ዳዲንን ቤት ማገዱን መንግስት አስታወቀ። መንግስት በኢትዮ 360 ሚዲያ አዘጋጅ በሀብታሙ አያሌው ስምና ዘመድ...
15/04/2025

እግድ ተጣለባቸው!
የአቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ የሐብታሙ አያሌውና የዘመድኩን በቀለ ዳዲንን ቤት ማገዱን መንግስት አስታወቀ። መንግስት በኢትዮ 360 ሚዲያ አዘጋጅ በሀብታሙ አያሌው ስምና ዘመድኩን በቀለ ስም በአዲስአበባ ከተማ በስማቸው የተመዘገበ ቤት ማግኘቱን አስታውቆ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ እግድ ጥያለሁ ብሏል። ከእነኚህ ሁለት ግለሰቦች በተጨማሪ በላሊበላ የሚገኘውን የፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው ቤት አግጃለሁ ብሏል።

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ጀግና መሪ ነው 👍 ለምን በል ሃበሻ  ****- ስልጣን ሊቀሙት ያሴሩ ሃይሎችን- ጦር የሰበቁ እና በግል የሰደቡት ግለሰቦችን- የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ የተጠረጠሩ...
15/04/2025

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ጀግና መሪ ነው 👍 ለምን በል ሃበሻ
****
- ስልጣን ሊቀሙት ያሴሩ ሃይሎችን
- ጦር የሰበቁ እና በግል የሰደቡት ግለሰቦችን
- የጦር ወንጀል ፈጽመዋል ተብሎ የተጠረጠሩ
- ያጣጣሉትን እና የናቁትን ሃይሎች በይቅርታ እና በምህረት የተቀበለ መሪ ነው። የቀደምት ነገስታት ብልጠት ወርሷል፤ ጠሚው ከጃንሆይ በኋላ ተዘጋጅቶ የመጣ መሪ ነው ያልኩትን በተደጋጋሚ በተግባር አሳይቷል።
ጠሚውን ብትንቅ፣ ብትሰደብ እና ልታጣጥለው ብትሞክር ልትፍቀው የማይቻል ትልቅ ታሪክ እየሰራ ይገኛል እናም በቅናት እና ምቀኝነት ተቃጥለህ ተንገብግበህ ከምትሞት ይልቅ ምራቅህን ዋጥና መሬት የያዘ የፖለቲካ አዘጋጅ እና ተራህን ጠብቅ። የተሻለ ፖሊሲ እና አስተዳደር አዘጋጅ፤ በርእዮተ አለም እና አላማ ካንተ አንድ የሆኑ ግለሰቦች ከሁሉም አካባቢ መርጠህ ሰብስብ። ብልጽግና መንግስት በግምገማዬ ያየሁት አንድ ክፍተት አለው፤ እሱም የኢኮኖሚ ፖሊሲ ነው። ያንን ወደ ውስጥ አይተው ያስተካከሉ ቀን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ተቃዋሚ እንደቁራ እየጮህ ይቀራል።
ለማንኛውም ጠሚው የሚቀጥለው ምርጫ አሸንፎ ተጨማሪ አምስት አመት እንዲያስተዳድር ድጋፍ እናደርጋለን። ይሄን እብድ እና ቅጥረኛ ተቃዋሚ ሃይል አይኔ እያየ የሃገሬ ጉዳይ አሳልፌ አልሰጥም።
****
ስለኢኮኖሚ እድገት እና ልማት ለመንግስታችን ሃሳብ ማዋጣት እንቀጥላለን።
Biniam Chifraw Sisay

28/01/2025

1713 ኢትዮጵያዊያን ከአሜሪካን ወደ
ወደ ሃገር ቤት ተጠርዝው ሊላኩ ነው !

ባባ ትራምፕ ተው ግን ተው ኧረ ተው ⁉️

Address


Telephone

+251944722567

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafto Prosperity Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Lafto Prosperity Media:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share