Abrsh Daily

Abrsh Daily New info, New tech, new media

" ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር አይቻልም " - ትምህርት ሚኒስቴርትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ/ም ለሁሉም የመንግስት...
20/10/2023

" ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር አይቻልም " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ/ም ለሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ በ2015 ትምህርት ዘመን የሬሜዲያል ትምህርት ተከታትለው 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች የፍሬሽማን ኮርስ እንዲማሩ መወሰኑን አስታውሷል።

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ፦

- ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከአንድ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ ሌላ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር እንደሚችሉ፤

- ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተዛውሮ መማር #የማይችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስገንዝቧል።

ተማሪዎች ከአንድ ተቋም ወደ ሌላ ተቋም ሄደው መማር የሚፈልጉ ከሆነ መረጃቸው በአግባቡ ተደራጅቶ እንዲሰጣቸው ትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ አሳስቧል።

28/09/2023
በአሜሪካ የአዞ መንጋጋ ውስጥ የአንዲት ሴት አስክሬን ተገኘበአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ 4 ሜትር ርዝመት ባለው አዞ መንጋጋ ውስጥ የአንዲት ሴት የሰውነት ቅሪት መገኘቱን ተከትሎ አዞው መገደ...
25/09/2023

በአሜሪካ የአዞ መንጋጋ ውስጥ የአንዲት ሴት አስክሬን ተገኘ

በአሜሪካ ፍሎሪዳ ግዛት ውስጥ 4 ሜትር ርዝመት ባለው አዞ መንጋጋ ውስጥ የአንዲት ሴት የሰውነት ቅሪት መገኘቱን ተከትሎ አዞው መገደሉን ፖሊስ ገልጿል።

በአካባቢው በሚገኝ የውሃ መፋሰሻ ውስጥ አዞው የጉዳቱ ሰለባ የሆነችውን ሴት የታችኛውን የሰውነት ክፍል ይዞ መመልከቱን አንድ የአይን ዕማኝ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግሯል።

በፍሎሪዳ ፒኒሌስ ካውንቲ የጸጥታ መስሪያ ቤት ባልደረባ አዞው እንደተገደለና የ41 ዓመቷ ሳብሪና ፒክሃም ቀሪ አስክሬን በውሃ ላይ መገኘቱን ተናግረዋል።

የሳብሪና ፒክሃም አሟሟትን በተመለከተ ምርመራ እየተደረገ ይገኛል።

ባለፈው አርብ በአዞ መንጋጋ ላይ የሰው ቅሪት መታየቱን ተከትሎ ወደ ፖሊስ ሪፖርት ተደርገል።

ክስተቱን ለፖሊስ ሪፖርት ያደረገው ጃማርከስ ቡላርድ ለስራ ቃለ መጠይቅ እየተጓዘ ሳለ አዞው አፉ ውስጥ መጀመሪያ ላይ የልብስ መሸጫ ቤቶች አሸንጉሊት የሚመስል ነገር መመልከቱን ተናግሯል።

“የሰው ታችኛው የሰውነት ክፍል አስክሬን በአፉ ውስጥ እንደሚገኝ አስተዋልኩ። ያንን እንደተመለከተኩ ወደ እሳት አደጋ መቆጣጠሪያ መስሪያ ቤት ገሰገስኩ” ሲል ለአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ተናግሯል።

“አዞን ፊት ለፊት ሳይ ይህ የመጀመሪያ ነው። ስለዚህ ሳየው እንደጥሩ ነገር ነው የተመለከትኩት። ነገር ግን ያየሁት ነገር ሳይ ‘ይሄ የልብስ መሸጫ አሻንጉሊት ነው?’ አልኩ” ይላል።

ቀጥሎም “በአፉ የያዘው የገረጣና ነጭ ነው” ብሏል።

በሌላ ቃለ መጠይቁ ደግሞ “ከአፉ ጋር ተጣብቋል። ከዚያም ዞሮ ሄደ። እውነት ነው ብዬ ለማመን ተቸገርኩ” ሲል ገልጿል።

የሟቿ ቤተሰቦች የገቢ ማሰባሰቢያ አዘጋጅተዋል። ፒክሃም በሞተችበት አቅራቢያ በሚገኝ የቤት አልባ ሰዎች መጠለያ ውስጥ ትኖር እንደነበር ቤተሰቦቿ ተናግረዋል።

የጉዳቱ ሰለባ የሆነችው ሴት ልጅ እንደሆነች የተናገረች ብሪውና ዶሪስ “ወደ መጠለያው እየሄደች ወይም ከመጠለያው ወጥታ እየተጓዘች ሳለ ከውሃ የወጣው አዞ ጥቃት አድርሶበት ሊሆን እንደሚችል ይታመናል” ስትል በፌስ ቡክ ገጿ ጽፋለች።

BBC amharic

 #ከዚህ የሕንፃ ባለቤት ትልቅ ትምህርት አግንችያለሁ። ሌሎችን ሳያጠፉ በህይወት ውስጥ መሻሻል ይችላሉ። በግባችን ላይ ብቻ እናተኩር። ከላይ የምንመለከተውን ዛፍ የቤቱ ባለቤት ያኔ ቤት ስሰራ...
02/08/2023

#ከዚህ የሕንፃ ባለቤት ትልቅ ትምህርት አግንችያለሁ።
ሌሎችን ሳያጠፉ በህይወት ውስጥ መሻሻል ይችላሉ። በግባችን ላይ ብቻ እናተኩር። ከላይ የምንመለከተውን ዛፍ የቤቱ ባለቤት ያኔ ቤት ስሰራ ቆርጦ ቢያጠፋ ኖሮ ንጹህ አየር እና ጥሩ ጥላ አያገኝም ነበረ። ከዚ ምንማረው ነገር ቢኖር እራሳችንን ለመገንባት ሌሎችን ከጎዳን በእርግጠኝነት በስኬት ቦታ የምንደርስ ቢመስለንም መጨረሻችን ጉዳት ነው ምሆነው።
#መልካም ምሽት

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የስራ መልቀቂያ አስገቡአዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “ጤናየን በሚገባ ለመጠበ...
26/06/2023

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ የስራ መልቀቂያ አስገቡ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “ጤናየን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ እረፍት ያስፈልገኛል” በማለት በፈቃዳቸው የሥራ መልቀቂያ አስገቡ፡፡

በዚህም “ከ ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፈቃዴ መልቀቄን ለተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባዔ ጽሕፈት ቤት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሳውቄያለሁ” ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

“ማሕበረሰቤን የማገልገል እድል እንዳገኝ ቦርዱን በሰብሳቢነት ለመምራት በእጩነት ላቀረቡኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም እምነቱን ጥሎ ኃላፊነቱን ለሰጠኝ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡

“የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ቦርዱን እንደ አስተዳዳሪ እና እንደተቆጣጣሪ ከማየት ይልቅ በጋራ እንደሚሰራ ቤተሰብ በመቁጠር የማያስደስታቸውን ውሳኔ በምንወስንበት ወቅት ጭምርም እምነታቸውን ስላልነሱን አመሰግናለሁ” ነው ያሉት፡፡

በቀጣይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የሚያወጣው ዝርዝር መረጃ ካለ ተከታትለን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

በ2011 ዓ.ም ታኅሣሥ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል፡፡

 ዶ/ር ማቴ ማጋኔ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደር ተደርገው ተሾሙዶ/ር ማቴ ማጋኔ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደ...
26/06/2023


ዶ/ር ማቴ ማጋኔ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደር ተደርገው ተሾሙ

ዶ/ር ማቴ ማጋኔ በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳደር ተደርገው የተሾሙ ሲሆን በተጨማሪ ዞኑን የሚመሩ የካቢኔ አባላት የተሾሙ ሲሆን በዚህ መሰረት:-
1. የዞኑ የብልፅግና ፖርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ባናታ
2. የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ ፎልካ
3. የዞኑ የብልፅግና ፖርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሰለሞን ቃዋቶ
4. የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሙልዬ ኦዶላ
5. የዞኑ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አሰፋ ኪኣ
6. የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ታደሰ ቱንሲሳ
7. የዞኑ የገጠር ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አርቦ ጃልደሳ
8. የፋይናንስ ዘርፍ መምሪያ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ጮራ

ሆነው ተሹመዋል።

ሰኔ 19-2015 ዓ.ም
ሀዋሳ

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 20 ደረሰ *********************** የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ...
21/05/2023

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 20 ደረሰ
***********************

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱ ተገለጸ።

የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ የ15 መምህራን ሕይወት ማለፉ ተገልጾ ነበር።

ተሸከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል በመግባቱ በተፈጠረው በዚህ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር በአምስት ጨምሮ 20 መድረሱን ኦቢኤን ዘግቧል።

ከአደጋው በሕይወት የተረፉት ሌሎች ሰዎች በአደባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢብራሂም ከሊል ተናግረዋል።

 #መኪና ተገዛለት!  Abinet Kebede በእናንተው በደጋግ ኢትዮጵያውያን ምክንያት ይህው መኪናው ተገስቶለታል።ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣችሁ🙏ወንድም ማስተር አብነት ላንተ ከዚህ በላይ ይገባሀል ...
11/05/2023

#መኪና ተገዛለት!

Abinet Kebede በእናንተው በደጋግ ኢትዮጵያውያን ምክንያት ይህው መኪናው ተገስቶለታል።

ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣችሁ🙏

ወንድም ማስተር አብነት ላንተ ከዚህ በላይ ይገባሀል በርታ ተበራታ።

ዕድሜ ከጤና ጋር ይስጥልን በርታ ሁሌም ከጎንህ ነን
🙏🙏🙏

የ2 ልጆች ገዳይ ተያዘች 🙏🙏🙏❤️❤️❤️ነጋሴ ከበደ ጫካ ውስጥ ተያዘች የ2 ልጆች ገዳይ ቡራዬ ሳንሱሲ ጫካ ውሰጥ አሁን ተይዛለችአሁን በአስቸኳይ ፍትህ ከመንግስት እንጥብቃለን ሼር አድርጉት ...
10/05/2023

የ2 ልጆች ገዳይ ተያዘች 🙏🙏🙏❤️❤️❤️

ነጋሴ ከበደ ጫካ ውስጥ ተያዘች

የ2 ልጆች ገዳይ ቡራዬ ሳንሱሲ ጫካ ውሰጥ አሁን ተይዛለች

አሁን በአስቸኳይ ፍትህ ከመንግስት እንጥብቃለን

ሼር አድርጉት በደንብ 🙏

08/05/2023

#አካልህን እና አእምሮህን በሚገባ ተንከባከብ፡፡ በምድር ላይ ስትኖር የሚኖርህ አንድ አካል እና አንድ አእምሮ ስለሆነ በትጋት ጠብቀው ተንከባከበው፡፡

ምንጭ:- Book Land(warren buffett)

ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የ106 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙአዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ የግብርና...
08/05/2023

ኢትዮጵያና ዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የ106 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (አይ ኤፍ ኤ ዲ) የ106 ነጥብ 54 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ እና የዓለም አቀፉ የግብርና ልማት ፈንድ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ሳራ ምባንጎ-ቡን ፈርመውታል።

ድጋፉ አሳታፊ ግብርናና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችል መርሐ-ግብር ተግባራዊ ለማድረግ የሚውል መሆኑም በሥምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ በተመረጡ ቀበሌዎች የሚገኙ 150 ሺህ የገጠር አባወራዎች ገቢን በዘላቂነት እንዲያሻሽሉ ማስቻል፣ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥና የአየር ንብረት መዛባትን የመቋቋም አቅም መፍጠር እንደሆነ ተመላክቷል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abrsh Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abrsh Daily:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share