
10/08/2025
የትግራይ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ፣ በትግራይና አፋር ክልሎች አዋሳኝ የሚንቀሳቀሰው የትግራይ አፈንጋጭ TDF እና ከህወሓት የተገነጠሉ ታጣቂ ቡድን ዛሬ በክልሉ ጸጥታ ኃይሎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቃት አድርሷል በማለት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከሷል።
ቢሮው፣ ታጣቂ ቡድኑ “ጠብጣብ” በተባለ ቦታ ላይ አደረሰው ባለው ጥቃት የአንድ የክልሉ ጸጥታ ኃይል አባል ሕይወት መጥፋቱን ገልጧል። ይህ አጥፊ ተግባር ከቀጠለ ቡድኑን በሚመሩና በሚያስተባብሩ አካላት ላይ ርምጃ እወስዳለሁ በማለት ያስጠነቀቀው ቢሮው፣ ደም መፋሰሱ ባስቸኳይ ይቁም በማለት ጥሪ አድርጓል።