Wollo Addis

Wollo Addis The official page of Wollo Addis Website www.wolloaddis.com

"ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር" - ሮዛባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ...
22/09/2026

"ቪድዮውን እንዳጠፋው እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ ቀርቦልኝ ነበር" - ሮዛ

ባሳለፍነው ሳምንት፣ ከዓርብ መስከረም 8/2019 ዓ.ም ጀምሮ አንድ የሃይማኖት አባት የሚታዩበት ፀያፍ ነውረኛ ቪድዮ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተለቆ ብዙዎችን አስደንግጧል ፤ ጉድ አሰኝቷል።

ቪዲዮው እውነተኛ ነው ? እውነተኛ አይደለም፣ በአርቴፊሻል ኢንተሌጀንስ (AI) የተቀናበረ ሐሰት ነው ? የሚሉ ክርክሮችም ተነስተዋል። "በኋላ ላይ ግን " እኔ ተበዳይ ነኝ " ያለች ግለሰብ ወደ ሚዲያ ወጥታ ቪዲዮው እውነተኛ መሆኑን አፍረጥርጣ መስክራለች።"

" ተበዳይ ነኝ " ያለችው ስሟ ሮዛ እንደሚባል፣ የአክሱም ነዋሪ እንደሆነችና በከተማው በሚገኝ ደረጃውን የጠበቀ ሆቴል በአስተናጋጅነት እንደምታገለግል ተናግራለች።

ሮዛ " ሱርያል " ለተባለ የዩቲዩብ ሚዲያ እሁድ መስከረም 10/2019 ዓ.ም በድምፅ በሰጠችው ማብራሪያ፣ ከአንድ ዓመት በፊት የ " ትግራይ መንበረ ሰላም ጳጳስና ዋና ጸሐፊ የሆኑት አቡነ አረጋዊ " በሥራ ቦታዋ መጥተው ባገኙት የመስተንግዶ እርካታ መነሻ እንደተዋወቋት ገልጻለች።

ከዚያም የሮዛና የጳጳሱ መቀራረብ ተጠናክሮ በመቀጠሉ፣ በኋላ ላይ ራሷን እስከ መጥላት ወደ አደረሰ ጾታዊ ግንኙነት ማደጉን ተበዳይ ነኝ ባይዋ በጸጸት ተናግራለች።

ሮዛ እንደምትለው፣ ጳጳሱ በተደጋጋሚ ጊዜ " ጾታዊ ጥቃት እንዳደረሱባት " ይህንን መግቻ እንዲሆን ለጳጳሳት መኖሪያ ወደ ተፈቀደ ቤታቸው በመሄድ ጾታዊ ግንኙነት እየፈጸሙ ቪዲዮ በድብቅ መቅረጿን ተናግራለች።

የቀረጸችውን የቪዲዮ ማስረጃ ወደ ጳጳሱ ልካ ግንኙነታቸው እንዲቆም ብትማጸንም እንዳልተሳካ ተናገራለች። "በድብቅ የቀረጸችውን ቪዲዮ እንድታጠፋ ከጳጳሱ እስከ 5 ሚሊዮን ብር ወሮታ እንደቀረበላትም ገልጻለች።"

ሆኖም ብር ከመቀበል በላይ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህ መሰል ጸያፍ ተግባር ከሚፈጽሙ የሃይማኖት አባቶች እንድትላቀቅ ባሳየችው አቋም፣ እስከ የመግደል ሙከራ ዛቻ እንደተደረሰባት አብራርታለች።

በዚህ ሁኔታ የቀረጸችው ቪዲዮ ከቁጥጥሯ ውጭ ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ ሊለቀቅ ችሏል። ይግም ፍርሃትና ስጋት እንደፈጠረባትም አልደበቀችም።

ሮዛ፣ “ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ መጽሐፍ ሕግ በጽኑ በሚገዙ የሃይማኖት አባቶች መመራት አለባት” ስትል በአጽንኦት አሳስባለች። "በተጨማሪም በአክሱምና ከአክሱም ውጪ እሷን ጨምሮ የጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸው 4 ሴቶችን እንደምታውቅና እንደምታጋልጥ አረጋግጣለች።"

ከዚህ ቀደም ጳጳሱ ለጵጵስና በታጩበት ጊዜ " ወልደዋል " ተብሎ በቪዲዮ የተደገፈ ምስል በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተሰራጭቶባቸው የነበረ ሲሆን የሰጡት መልስ አልነበረም።

በአሁኑ የቪድዮ ጉዳይም ፣ እንዲሁም ሮዛ ላወረበችው የጾታዊ ጥቃት ክስ እስካሁን በይፋ የሰጡት መልስ የለም። "በደል ደርሶብኛል" ባይዋ ሮዛ በአሁኑ ሰዓት በቂ የሕግ አገልግሎት እየተሰጣት በአክሱም ከተማ እንደምትገኝ ገልጻለች።

መቀመጫቸው አክሱም የሆኑት አቡነ አረጋዊ በአሁኑ ጊዜ የት እንዳሉ አይታወቅም።

Via:- ቲክቫህ ኢትዮጵያ
:
:
:
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

"አፄ ቴዎድሮስን የገደለችው ወርቂት የምትባል የወሎ ኦሮሞ ናት! «የታሪክ ስህተት ወይንስ የታሪክ ድፍረት?» — በነፃነት ጣሰው የተሰነዘረውን አሳዛኝ ንግግር"ስሙ «ነፃነት» ይሁን እንጂ፣ ከ...
22/09/2026

"አፄ ቴዎድሮስን የገደለችው ወርቂት የምትባል የወሎ ኦሮሞ ናት! «የታሪክ ስህተት ወይንስ የታሪክ ድፍረት?» — በነፃነት ጣሰው የተሰነዘረውን አሳዛኝ ንግግር"

ስሙ «ነፃነት» ይሁን እንጂ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚያወጣቸው ንግግሮች የሀሳብ ነፃነትን ሳይሆን የታሪክና የሞራል ዝቅተኝነትን የሚያንፀባርቁ ሆነዋል።

በአደባባይ የሚናገራቸው የወረዱ ንግግሮች ሳያንስ፣ አሁን ደግሞ «በቅርቡ የሚመረቅ አዲስ መጽሐፍ አለኝ» በማለት የሀገሪቱን የታሪክ መሠረት የሚያናጉ የፈጠራ ወሬዎችን በስፋት አዘጋጅቼላችኋለሁ እያለ ይገኛል።

አቶ ነፃነት ጣሰው በመጽሐፉ ሊያስተላልፍ የዛተው አደገኛና የተሳሳተ ትረካ፡-
፩. «ወሎ አማራ አይደለም» የሚል የታሪክና የማህበራዊ እውነታን የካደ ባዶ መላምት፤

፪. «አፄ ቴዎድሮስ ራሳቸውን አላጠፉም» በማለት፣ የእንግሊዝ ጦርን ሳይቀር ያስደመመውንና ለአገራቸው ክብር ሲሉ የከፈሉትን ታላቅ መስዋዕትነት ዝቅ ለማድረግ መሞከሩ፤

፫. «አፄ ቴዎድሮስን የገደለችው ወርቂት የምትባል የወሎ ኦሮሞ ናት፤ በመቅደላ ስለነበረች እሷ ናት የገደለችው» የሚል ምንም ዓይነት የታሪክ ማስረጃና ሰነድ የሌለው የፈጠራ ታሪክ ይዞ መቅረቡ።

፬. «አማርኛ ቋንቋ የአማራ አይደለም፤ የአፄ ዮሐንስ ነው፤ አፄ ዮሐንስ ደግሞ ትግራይ ናቸው» በማለት የቋንቋን ዕድገት፣ የታሪክ ሰነዶችንና ሳይንሳዊ እውነታዎችን ያላገናዘበ አስቂኝ የፈጠራ ታሪክ ማሰራጨቱ፤

• ይህ ዓይነት ሙከራ የታሪክ አላዋቂነት ብቻ ሳይሆን፣ ለሀገርና ለታሪክ ጀግኖች የሚገባውን ክብር የመንሳት፣ እንዲሁም የትውልድን የታሪክ ግንዛቤ የመበከል እኩይ ተግባር ነው። "ሀገርን በደም እና በአጥንታቸው ያቆዩ የጀግኖቻችንን ታሪክ እየደለዙ የፈጠራ ትረካዎችን ማስረፅ ትልቅ የታሪክ ወንጀል ነው።"

«አቶ ነፃነት ጣሰውን» አሁንም ጊዜው ሳይረፍድ እና የጀመሩት የታሪክ ማደናገር መንገድ ከመስመሩ ሳይወጣ፣ በዙሪያቸው ያሉ ዘመዶቻቸውና ወዳጆቻቸው ቢመክሯቸውና መላ ቢሉላቸው መልካም ነው።

"ታሪክ በስሜትና በፈጠራ ሳይሆን በእውነትና በማስረጃ ብቻ የሚጻፍ መሆኑን ልንገራቸው እንወዳለን!"

#ወሎ
:
:
:
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

"ከህወሓት ጋር የሚደረጉ ድብቅ ስምምነቶች እንዲጣሩ እንጠይቃለን! የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ"የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ከህወሓ...
22/09/2026

"ከህወሓት ጋር የሚደረጉ ድብቅ ስምምነቶች እንዲጣሩ እንጠይቃለን! የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ"

የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነትና የወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ከህወሓት ጋር የሚደረጉ ድብቅ እንቅስቃሴዎችና ስምምነቶች እንዲጣሩ ጠየቀ።

ኮሚቴው በሰጠው አስቸኳይ የአቋም መግለጫ፣ ከህወሓት ጋር የሚደረግ ትብብር በወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ጉዳይ ላይ የአማራ ሕዝብ ያነሳቸውን ጥያቄዎች ሊጎዳ ይችላል በሚል ስጋቱን ገልጿል።

ኮሚቴው በተለይ ከህወሓት ጋር በትብብርና በጥምረት ስም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመቃወም፣ ማናቸውም የጀርባ ስምምነቶች ካሉ በግልጽ እንዲታወቁ ጠይቋል።

እንደ ኮሚቴው ገለጻ፣ የወልቃይት ጠገዴ የማንነትና የወሰን ጥያቄ በሕጋዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኝ ለዓመታት ሲሰራ ቆይቷል ያለ ሲሆን፤ ኮሚቴው በዚህ ዙሪያ ያለው ጥያቄ በሌሎች የፖለቲካ ትብብሮች ሳይወሰን በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እንደሚፈልግ ገልጿል።

በተጨማሪም ኮሚቴው የአማራና የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጣናዊ የፖለቲካ አሰላለፎች ላይ በጥንቃቄ እንዲከታተል ጥሪ አቅርቧል። በተለይም በተለያዩ ኃይሎች መካከል የሚፈጠሩ ትብብሮች የሀገሪቱን ሰላምና መረጋጋት እንዳይጎዱ በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስቧል።

ኮሚቴው በመግለጫው መጨረሻ፣ ከህወሓት ጋር የሚደረጉ የተለያዩ የትብብር እንቅስቃሴዎች በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ላይ ሊያሳድሩ የሚችሉት ተፅዕኖ በጥንቃቄ እንዲታይ እና የአካባቢው ሕዝብ ጥያቄ እንዳይዘነጋ ጥሪ አቅርቧል።
:
:
:
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

"መቐለ ላይ የተካሄደው ጥምረት፡ የመደመር ፍሬ ወይስ የብሶት ውጤት? " ሀሳብዎን ያካፍሉን?ሰባት የታጠቁ አደረጃጀቶች ወደ አንድ ጠረጴዛ መምጣታቸው ይፋ ሆኗል። በጉዳዩ ላይ የማህበራዊ ሚዲያ...
21/09/2026

"መቐለ ላይ የተካሄደው ጥምረት፡ የመደመር ፍሬ ወይስ የብሶት ውጤት? " ሀሳብዎን ያካፍሉን?

ሰባት የታጠቁ አደረጃጀቶች ወደ አንድ ጠረጴዛ መምጣታቸው ይፋ ሆኗል። በጉዳዩ ላይ የማህበራዊ ሚዲያውና የፖለቲካው አየር በሁለት ተከፍሏል፦

🔹 አንዳንዶች፦ “የጠመንጃ ዘመን ያብቃ፣ ልዩነትን በውይይት መፍታት የመደመርና የሰላም አስተሳሰብ ውጤት ነው!” ይላሉ።

🔻 ሌሎች ደግሞ፦ “ይህ በረጅም ጊዜ ራዕይ የተገነባ ሳይሆን በጊዜያዊ ብሶትና የፖለቲካ ስሌት የመጣ ጥምረት ነው!” ሲሉ ይጠራጠራሉ።

የእርስዎ እይታ ምንድን ነው?
• ይህ ስምምነት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም መንገድ የሚከፍት የመደመር ውጤት ነው?

• ወይስ በጊዜያዊ ብሶትና ስጋት የተፈጠረ ጥምረት?
💬 ሀሳብዎን በኮመንት ያካፍሉን!

#ኢትዮጵያ
:
:
Stop civil war in Ethiopia
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

የትግራይ ቴሌቪዥን (Tigray TV) በድጋሚ ተታገደ!የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ከዛሬ ጀምሮ ለላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መጣሉን አስታወቀ። • የእገዳው...
21/09/2026

የትግራይ ቴሌቪዥን (Tigray TV) በድጋሚ ተታገደ!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በትግራይ ቴሌቪዥን ላይ ከዛሬ ጀምሮ ለላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።

• የእገዳው ምክንያት፡ ጣቢያው የሀገርንና የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ ወደ ግጭት የሚገፋፉ እና ፅንፈኝነትን የሚያበረታቱ ይዘቶችን በተከታታይ አስተላልፏል ተብሏል።

• ከዚህ ቀደም፡ በፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት መሠረት ተጥሎበት የነበረው እገዳ ተንስቶ፣ ባለሥልጣኑ ለጋዜጠኞቹ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ መቆየቱ ይታወሳልም ብሏል።

• ማስጠንቀቂያ፡ ማንኛውም የብሮድካስት፣ የሕትመትም ሆነ የዲጂታል ሚዲያ የትግራይ ቴሌቪዥንን እንደ መረጃ ምንጭ መጠቀም ወይም ይዘቶቹን አሰራጭቶ መገኘት በጥብቅ የተከለከለ ነውም ተብሏል በመግለጫው

መመሪያውን በማይከበሩ ሚዲያዎች ላይ ባለሥልጣኑ ጠንካራ ሕጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወስድ አሳስቧል።

ሀሳንዎን ያካፍሉን?
:
:
Stop civil war in Ethiopia
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

«ጥምረት የፈጠሩት ታጣቂዎች የኤርትራን ተልዕኮ ለመፈፀም ነው!» የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይድረስልን" — አቶ ጌታቸው ረዳኤርትራ እና ግብፅ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎችን በመደገፍ እና...
21/09/2026

«ጥምረት የፈጠሩት ታጣቂዎች የኤርትራን ተልዕኮ ለመፈፀም ነው!» የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ይድረስልን" — አቶ ጌታቸው ረዳ

ኤርትራ እና ግብፅ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ታጣቂዎችን በመደገፍ እና በማሰባሰብ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጦርነት እንዲከፍቱ እያደረጉ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ፣ የህወሓት የቀድሞ ምክትል ሊቀመንበር እና የአሁኑ የስምረት ፓርቲ ሊቀመንበር ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

ከመንግስታዊው ጣቢያ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጌታቸው ረዳ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

• ኤርትራ ከግብፅ በሚደረግላት ድጋፍ የቀጣናውን አለመረጋጋት የኃይል የበላይነት ማረጋገጫ መንገድ አድርጋ እየሰራችበት ይገኛል።

• የኤርትራ ሰራዊት የኢሳያስን ስልጣን ለመጠበቅ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ እና ሀገሪቱ በወጣቶች ስደት በደረሰባት የስነ-ሕዝብ ውድቀት ምክንያት ሰራዊቷን የመላክ አቅም የላትም።

• በመሆኑም ኤርትራ የራሷን ጦር በቀጥታ ከማሰለፍ ይልቅ እንደ አማራ ፋኖ፣ ኦነግ እና ሕወሓትን የመሳሰሉ አካላትን «የጉዳቱ ሰለባ እንዲሆኑ ጥቅም ላይ የሚውሉ ሞኞች» በማድረግ ጦርነቱን ወደ ኢትዮጵያ እየገፋች ነው።

⚠️ ቀደም ሲል ለሞት የሚፈላለጉ ጠላቶች የነበሩት ሕወሓት እና የኤርትራ መንግሥት፣ የጋራ ጠላታቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት ለመጋፈጥ ሲሉ ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ብለው ተሰልፈዋል።

ሕወሓት የመጀመሪያ ዓላማውን በመተው በኤርትራ ትዕዛዝ ወጣቶችን ምንም በማያውቁበት የሱዳን ጦርነት ውስጥ እንዲያልቁ እያደረገ ይገኛል ሲሉም ከሰዋል።

🔥 የፌዴራል መንግሥት እስካሁን ከፍተኛ ትዕግሥት ማሳየቱን የጠቆሙት አማካሪው፤ ሕወሓት በኤርትራ መረብ ተይዞ በደቡብ ትግራይ፣ በሰሜን ወሎ ወይም በአፋር በኩል ጥቃት የሚሰነዝር ከሆነ ሊቆጣጠሩት የማይቻል ሰፊ ጦርነት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

🌍 ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኤርትራ እና በሌሎች የሰላም እንቅፋት በሆኑ አካላት ላይ ጠንካራ ጫና በማሳደር ቀጣናው ወደ ሌላ አጥፊ ጦርነት እንዳይገባ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ምን ያስባሉ? ኤርትራ እና ግብፅ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት እና የታጣቂዎች ጥምረት በቀጣናው ሰላም ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምንድን ነው? አስተያየትዎን ያካፍሉን!



:
:
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

"ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ከ4አመታት እስር በሗላ በዚህ መልኩ ጨርሰው ከቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል"ታዋቂው አንጋፋው የታሪክ አዋቂ እና ጋዜጠኛ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በብልፅግና መንግስት ተፈርዶባቸው የ...
20/09/2026

"ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ ከ4አመታት እስር በሗላ በዚህ መልኩ ጨርሰው ከቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል"

ታዋቂው አንጋፋው የታሪክ አዋቂ እና ጋዜጠኛ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በብልፅግና መንግስት ተፈርዶባቸው የነበረውን የ4 ዓመት ከነፍስ ወከፍ (4 ዓመት ተኩል) የእስር ጊዜያቸውን በሙሉ አጠናቀው ዛሬ ወደ ቤታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል።

በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜያት በርካታ ውጣ ውረዶችን ያሳለፉት አቶ ታዲዮስ፣ በመጨረሻም የፅናትና የትግል ውጤት በሆነው ሁኔታ የእስር ጊዜያቸውን ፈፅመው በነፃነት ወደ ቤታቸው በመመለሳቸው ለቤተሰቦቻቸው፣ ወዳጆቻቸው እና ለደጋፊዎቻቸው ትልቅ ደስታ ሆኗል።

በድጋሜ እንኳን ለዚህ ቀን አበቃዎት! ለቤተሰቦቻችሁም እንኳን ደስ አላችሁ!
:
:
:
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

"ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ግዙፍ የፖለቲካ እና የጦር ትብብር ተመሠረተ!"በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ 7 አማፅያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች “አካታች የሽግግር መንግሥት” ለመመስረት ያለመ የጋራ...
20/09/2026

"ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ግዙፍ የፖለቲካ እና የጦር ትብብር ተመሠረተ!"

በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ 7 አማፅያን ኃይሎች እና የፖለቲካ ድርጅቶች “አካታች የሽግግር መንግሥት” ለመመስረት ያለመ የጋራ ትብብር መሥረታቸውን ዛሬ እሁድ (መስከረም 10፤ 2019 ዓ.ም) በትግራይ ክልል ዜና ማሰራጫዎች በኩል በይፋ አስታወቁ።

«የኢትዮጵያ ህዝባዊ ኃይሎች ትብብር ለህልውና» (በአጭሩ "ትብብር ለህልውና") የሚል ስያሜ የተሰጠውን ይህን ትብብር ከመሰረቱት ውስጥ

1. አፋብን (የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ)
2. ኦነሰ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት)
3. ህወሓት (ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ)
4. ኦህነግ (የኦጋዴን ህዝብ ነጻነት ግንባር)
5. አብአአግ (የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር)
6. ቤህነን (የቤንሻንጉል ህዝቦች ነጻነት ንቅናቄ)
7. ጉህዲን (የጉሙዝ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ)

ይህ የተገለጸው ዛሬ እሁድ መስከረም 10፤ 2019 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዜና ማሰራጫዎች በኩል በተላለፈ መግለጫ ነው። መግለጫውን በንባብ ያቀረቡት በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሰው አፋብንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት አቶ ዘመነ ካሴ ናቸው።

አቶ ዘመነ “ትብብር ለህልውና” የሚል አጭር መጠሪያ የሚጠቀመው የጋራ ትብብር ሰብሳቢ መሆናቸውም በቪዲዮ በተሰራጨው መግለጫ ላይ ተመልክቷል።

📌 ይህ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ በሃገሪቱ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ የሚያሳድር ይመስላችኋል? አስተያየትዎን ያጋሩ!
#ለህልውና #ኢትዮጵያ #ሀገርአቀፍዜና

ሰላም ለሀገራችን
ሰላም ለህዝባችን
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ

"ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪው ታዴዎስ ታንቱ ከእስር ተለቀቁ"ታዋቂው ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ የተወጣጣባቸውን የእስር ጊዜ በማጠናቀቅ ከእስር ነጻ መውጣታቸው ተገለጸ።በተለ...
20/09/2026

"ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪው ታዴዎስ ታንቱ ከእስር ተለቀቁ"

ታዋቂው ጋዜጠኛና የታሪክ ተመራማሪ ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ የተወጣጣባቸውን የእስር ጊዜ በማጠናቀቅ ከእስር ነጻ መውጣታቸው ተገለጸ።

በተለያዩ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ታሪካዊ ጉዳዮች ላይ በሚሰጡት ጠንከር ያሉ አስተያየቶቻቸውና ትንተናዎቻቸው የሚታወቁት ጋሽ ታዴዎስ፣ ላለፉት ጊዜያት በህግ ጥላ ስር ቆይተው የነበረ ሲሆን፣ የቅጣት ጊዜያቸውን ጨርሰውወደ ቤተሰቦቻቸው ተቀላቅለዋል።

ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ "እንኳን ለቤትዎ አበቃዎት"
:
:
:
ሰላም ለሀገራችን!
ሰላም ለህዝባችን!
ወሎ አዲስ የህዝብ አድማስ!

20/09/2026

"ቢኒያም እና ሀገረሰላም፤ ስፖርታዊ ጨዋነት የታየበት ከባለፉት MMA ETHIOPIA ፍልሚያዎች የተሻለ ድንቅ ውድድር"

Address


Telephone

+251929332211

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Addis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wollo Addis:

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share