06/06/2026
ተተኳሽ ጭኖ የሚጓዘውን ቡድን ሲመራ የነበረው ኮሎኔል ህይወቱ አለፈ!
በሰሜን ምዕራብ ትግራይ ዞን ታሕታይ ኣድያቦ ወረዳ “ሰንብል” በተባለ አካባቢ ትናንት ምሽት በተፈጸመ የድሮን ጥቃት፣ ወደ ባደመ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ የነበረ ወታደራዊ ኮንቮይ መመታቱ ተነግሯል።
እንደ ምንጮች መረጃ፣ ኮንቮዩ ከአደሚቲ ጣቢያ ተነስቶ በ27 ተሽከርካሪዎች የተደራጀ ሲሆን፣ ሙሉ ሎጅስቲክስ እና ተተኳሽ ጥይት ጭኖ በጉዞ ላይ እንደነበር ተገልጿል።
ጥቃቱ በደረሰበት ወቅት ቡድኑን በመምራት ላይ የነበሩት ኮሎኔል ሀጎስ አብርሃ ህይወታቸው ማለፉን ምንጮቹ አስታውቀዋል።