
05/08/2025
የዓሳ እራት መሆን ማብቂያው መቼ ይሁን?
===========
በሕገወጥ መንገድ የሚደረግ ስደት የብዙ ወጣቶች ሕይወት እያስገበረ መጥቷል፤ አሁንም እያስገበረ ይገኛል።ባለፈው እሁድም ከወደ የመን አሳዛኝ መርዶም መሰማቱ ይታወቃል።
ወደ አውሮፓ ተሻግረን ያልፍልናል የሚል ተስፋ ሰንቀው፣ ረጅም እና ስበዛ አሰልቺ ጉዞን ሲጓዙ የነበሩ… ውድ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን አሁንም የዓሳ ሲሳይ መሆናቸው… በህዝብ ላይ ከፍተኛ ሀዘን እና ቁጭትን ፈጥሯል።
አንዳንድ ስደተኛ ወጣቶች ሕይወታችሁን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ አሳልፋችሁ አደገኛ ጉዞ ለማድረግ ምን አስመኛችሁ? ተብለውም ሲጠየቁ "ሀገር ቤት" በረሐብና በጦርነት ከመሞት ዕድልን ሞክሮ መሞት ይሻላል" የሚሉ አሉ።
በርካታ ወጣቶች ደግሞ ስለአውሮፓ እና አሜሪካ ያለውን ነባራዊ ሁኔታና የስደተኞች አያያዝ ፖሊሲያቸው ግልጽ መረጃ እንደሌላቸው ይነገራሉ።
በዚህ ዓይነት አደገኛ ጉዞ የሰው ሕይወት መገበራችን ግን አሁንም እየቀጠለ ይገኛል። ለመሆኑ የዓሳ እራት መሆን ማብቂያው መቼ ይሁን ?