Siltie Media House ስልጤ ሚዲያ ሃውስ

  • Home
  • Siltie Media House ስልጤ ሚዲያ ሃውስ

Siltie Media House ስልጤ ሚዲያ ሃውስ I need ALLH in my life.
(1)

በዚህ የፌስቡክ ፔጅ የስልጤን ማህበረሰብ ባህላዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ ና ፖለቲካዊ ኩነቶችን እንዘግባለን!!

የyoutube ቻናለችንን
SUBSCRIBE👇
https://youtube.com/?si=Za4dsOAiXwbc2VqT

ፔጃችንን FOLLOW በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇

የዓሳ እራት መሆን ማብቂያው መቼ ይሁን?===========በሕገወጥ መንገድ የሚደረግ ስደት የብዙ ወጣቶች ሕይወት እያስገበረ መጥቷል፤ አሁንም እያስገበረ ይገኛል።ባለፈው እሁድም  ከወደ የመን ...
05/08/2025

የዓሳ እራት መሆን ማብቂያው መቼ ይሁን?
===========
በሕገወጥ መንገድ የሚደረግ ስደት የብዙ ወጣቶች ሕይወት እያስገበረ መጥቷል፤ አሁንም እያስገበረ ይገኛል።ባለፈው እሁድም ከወደ የመን አሳዛኝ መርዶም መሰማቱ ይታወቃል።

ወደ አውሮፓ ተሻግረን ያልፍልናል የሚል ተስፋ ሰንቀው፣ ረጅም እና ስበዛ አሰልቺ ጉዞን ሲጓዙ የነበሩ… ውድ ኢትዮጵያውያን ዜጎቻችን አሁንም የዓሳ ሲሳይ መሆናቸው… በህዝብ ላይ ከፍተኛ ሀዘን እና ቁጭትን ፈጥሯል።

አንዳንድ ስደተኛ ወጣቶች ሕይወታችሁን በአደገኛ ሁኔታ ውስጥ አሳልፋችሁ አደገኛ ጉዞ ለማድረግ ምን አስመኛችሁ? ተብለውም ሲጠየቁ "ሀገር ቤት" በረሐብና በጦርነት ከመሞት ዕድልን ሞክሮ መሞት ይሻላል" የሚሉ አሉ።

በርካታ ወጣቶች ደግሞ ስለአውሮፓ እና አሜሪካ ያለውን ነባራዊ ሁኔታና የስደተኞች አያያዝ ፖሊሲያቸው ግልጽ መረጃ እንደሌላቸው ይነገራሉ።

በዚህ ዓይነት አደገኛ ጉዞ የሰው ሕይወት መገበራችን ግን አሁንም እየቀጠለ ይገኛል። ለመሆኑ የዓሳ እራት መሆን ማብቂያው መቼ ይሁን ?

ይህ እጅግ አሳዛኝ አደጋ ሲሆን፣ በየመን የባህር ዳርቻ የደረሰውን የጀልባ አደጋ በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝሮች ከስደትተኞች አለም አቀፍ ድርጅት (IOM) እና ከሌሎች የዜና ምንጮች የተገኘ መረ...
04/08/2025

ይህ እጅግ አሳዛኝ አደጋ ሲሆን፣ በየመን የባህር ዳርቻ የደረሰውን የጀልባ አደጋ በተመለከተ ተጨማሪ ዝርዝሮች ከስደትተኞች አለም አቀፍ ድርጅት (IOM) እና ከሌሎች የዜና ምንጮች የተገኘ መረጃ እንደሚከተለው ቀርቧል።

* በጀልባዋ ውስጥ በጠቅላላው 154 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ነበሩ።

* በአደጋው 68 ሰዎች እንደሞቱ የIOM የየመን ተወካይ አብዱሰቶር ኢሶቭ ተናግረዋል።

* ከሟቾቹ ውስጥ 54 አስከሬኖች በየመን ካንፋር አውራጃ የባህር ዳርቻ ላይ ሲገኙ፣ ሌሎች 14 አስከሬኖች ደግሞ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሆስፒታል መላካቸው ተገልጿል።

* የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች ቁጥር ወደ 74 አድጓል። እነዚህ ሰዎችም እንደሞቱ ይገመታል።

* ከዚህ አሰቃቂ አደጋ 12 ሰዎች ብቻ በህይወት መትረፋቸው ተረጋግጧል።

* ጀልባዋ የሰመጠችው በደቡብ የመን አብያን ክፍለ ሀገር በምትገኘው በአደን ባህረ ሰላጤ (Gulf of Aden) ውስጥ ነው።

* የአደጋው መንስኤ መጥፎ የአየር ሁኔታ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ ጀልባዋን አደጋ ላይ ጥሏታል።

* ይህ የባህር ጉዞ ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን ከሚደረጉ አደገኛ መንገዶች አንዱ ነው። በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ይህን አደገኛ ጉዞ ያደርጋሉ።

* ስደተኞቹ ወደ የመን የሚጓዙት ወደ ሀብታም ወደሆኑት የባህረ ሰላጤ ሀገራት ለስራ ፍለጋ ለመሻገር ነው።

* እንደ IOM ዘገባ ከሆነ፣ ይህ አሳዛኝ ክስተት በዚሁ መንገድ በቅርብ ወራት ውስጥ በተከታታይ ከደረሱ የጀልባ አደጋዎች አንዱ ነው።

በመጋቢት ወር ብቻ በየመን እና ጅቡቲ የባህር ዳርቻዎች ላይ በአራት ጀልባዎች ላይ በደረሰ አደጋ፣ ሁለት ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ፣ ሌሎች 186 ሰዎች ጠፍተዋል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት በህገወጥ አዘዋዋሪዎች አማካኝነት ለህልም ፍለጋ አደገኛ ጉዞ የሚያደርጉ ስደተኞች የሚገጥማቸውን ከፍተኛ አደጋ በድጋሚ የሚያሳይ ነው።

ነብስ ይማር ወገኖቻችን

Via IOM

አላሁ አክበር ታዋቂው የኦሮሚኛ ዘፋኝ አርቲስት  #እስክንድር ታምሩ ዛሬ ሸዓዳ ይዞ ወደ እስልምና መጥቶዋል።አላህ እኛንም እሱንም በእስልምና ያፅናን
03/08/2025

አላሁ አክበር

ታዋቂው የኦሮሚኛ ዘፋኝ አርቲስት #እስክንድር ታምሩ ዛሬ ሸዓዳ ይዞ ወደ እስልምና መጥቶዋል።አላህ እኛንም እሱንም በእስልምና ያፅናን

የዛሬው ሰልፍ በሲድኒ አውስትራሊያ በሀርቦር ድልድይ ላይ።አንዳንዶች ከ100000 በላይ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል እያሉ ነው!!!👍✊✌️
03/08/2025

የዛሬው ሰልፍ በሲድኒ አውስትራሊያ በሀርቦር ድልድይ ላይ።

አንዳንዶች ከ100000 በላይ ሰዎች ሰልፍ ወጥተዋል እያሉ ነው!!!👍✊✌️

የጋዛ ግፍ ምሳሌም ይሁን ልኬት የለውም። 21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ምጥቀት ሳይሆን ድንቁርናው የታየበት ነው። ዋናው ድንቁርና ልብ እያወቀ የሚሰራ የበደል አቻ ፍለጋ ነው። ጋዛ ላይ የሆ...
03/08/2025

የጋዛ ግፍ ምሳሌም ይሁን ልኬት የለውም። 21ኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ምጥቀት ሳይሆን ድንቁርናው የታየበት ነው። ዋናው ድንቁርና ልብ እያወቀ የሚሰራ የበደል አቻ ፍለጋ ነው። ጋዛ ላይ የሆነው ፈጽሞ አቻ የለውም።በጭራሽ።

ሳውዲ አረቢያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና ስነ-ምህዳሮችን ለመመለስ በአረንጓዴ ኢኒሼቲቭ ስር 10 ቢሊዮን ዛፎችን ለመትከል አቅዳለች።via~Brics
02/08/2025

ሳውዲ አረቢያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና ስነ-ምህዳሮችን ለመመለስ በአረንጓዴ ኢኒሼቲቭ ስር 10 ቢሊዮን ዛፎችን ለመትከል አቅዳለች።

via~Brics

አሜሪካ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ሊወሩኝ ነዉ ! /ሰሜን ኮርያ/‎‎ሰሜን ኮሪያ  አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን ጋር በመጣመር ትንኮሳ እያደረጉብኝ ይገኛል እኔን አጥፋተዉ የኮሪያ ልሳነ ምድ...
02/08/2025

አሜሪካ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ሊወሩኝ ነዉ ! /ሰሜን ኮርያ/

‎ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ እና ከጃፓን ጋር በመጣመር ትንኮሳ እያደረጉብኝ ይገኛል እኔን አጥፋተዉ የኮሪያ ልሳነ ምድር ለእነሱ ምቹ በሆነ መልኩ ለመቆጣጠር ዝግጂት እያደረጉ ነዉ ይህንንም እንደ ነገረኛ የሚያየኝ አለም ይወቅልኝ ስትል መክሰሷ ተሰማ ።

‎የሰሜን ዋና ጋዜጣ ሮዶንግ ሲንሙን ላይ በቀረበው በአንድ መጣጥፍ ላይ ባለፈው ወር በጃፓን አካባቢ በተጀመረው የአሜሪካ የአየር ልምምዶች እና በቅርቡ በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካ የባህር ሃይሎች መካከል የተደረገውን የአየር ሎጂስቲክስ ልምምዶችን በመግለጽ ውንጀላውን አስነብቧል ።

‎"በኮሪያ ልሳነ ምድር እና በአካባቢው ሰላምን ለማረጋገጥ በዩናይትድ ስቴትስ፣ በጃፓን እና በደቡብ ኮሪያ የሚወሰዱት የማያዳግም ወታደራዊ እርምጃ መቆም አለበት።" ሲል ያስነበበው ፅሁፉ በደቡብ ኮሪያ፣ አሜሪካ እና ጃፓን መካከል እየተካሄደ ያለውን የሶስትዮሽ ወታደራዊ ትብብር በመንቀፍ ሰሜንን በጋራ ወታደራዊ ሃይል “ለመጨፍለቅ” ታስቧል ሲል ዮንሃፕ የዜና ወኪል ዘግቧል።

‎የኮሪያ ሴንትራል የዜና አገልግሎት (KCNA) ባለፈው አመት የአሜሪካ-ጃፓን የዩናይትድ ስቴትስ-ጃፓን ምክክር ወደ ሚንስትር ደረጃ ማሻሻሉን እና ሁለቱ ሀገራት በቅርቡ የተራዘመ የመከላከያ መመሪያዎችን ማረጋገጡን የገለፀው የሲኦል ሪፖርት የተራዘመው መከላከያ የሚያመለክተው ዩናይትድ ስቴትስ አጋሯን ለመከላከል ሙሉ ወታደራዊ አቅሟን ጨምሮ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዋን ለመጠቀም የገባችውን ቁርጠኝነት ነው። ብሏል ።

‎አክሎም አሜሪካ የኒውክሌር ስትራቴጂካዊ ንብረቶችን በሃዋይ፣ ጉዋም እና ጃፓን በሚገኙ የባህር ኃይል እና አየር ማረፊያዎች በማሰማራት እና ከ"ትናንሽ አጋሮቿ" ጋር የጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን በማድረግ ክልላዊ ሁኔታውን ወደ "አደገኛ የመነካካት እና የመሄድ" ሁኔታ እያደረሰች ነው ሲል ገልጿል ።

‎በመጨረሻም አሜሪካ እና ጃፓን ትብብራቸውን ወደ አስጊ "የኑክሌር" ጥምረት በመቀየር ላይ እንደሚገኙ በተገለፀበት መጣጥፍ ለእንደዚህ አይነት ተግባራት ምላሽ ለመስጠት ለሰሜን የመከላከያ ሰራዊቱን ማጠናከር "ፍትሃዊ እና ቀና" ብቻ ነው ብሏል።


‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

"በእንግሊዝ እና በወልስ  በርከታ ህፃናቶች ስመቻዉ መሀመድ እንደሆና  ተገለፀ 💁 Muslim Players. 💪
02/08/2025

"በእንግሊዝ እና በወልስ በርከታ ህፃናቶች ስመቻዉ መሀመድ እንደሆና ተገለፀ
💁 Muslim Players. 💪

ረቢዕ መስጂድ😍 @ ወልቂጤ💚   fans
02/08/2025

ረቢዕ መስጂድ😍 @ ወልቂጤ💚

fans

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጅሊስ አመራሮች  ምርጫ መቼ ይካሄዳል?         ================በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።=======የማዕከላዊ...
02/08/2025

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ መቼ ይካሄዳል?
================
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
=======
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምርጫ የሚካሄድባቸውን ቀናት ዝርዝር እና የሚመረጡ ተወካዮች ትውውቅ መቼ እንደሚካሄድ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት፦

✔ የዑለማ ዘርፍ ትውውቅ ነሐሴ 2/17 ከቀኑ 8:30
✔ የምሁራን ዘርፍ ትውውቅ ነሐሴ 4/17 ከጧቱ 3:00
✔ የወጣቶች ዘርፍ ትውውቅ ነሐሴ 4/17 ከጧቱ 3:00 ጀምሮ
✔ የሴቶች ዘርፍ ትውውቅ ነሐሴ 4/17 ከረፋዱ 4:00 ጀምሮ
✔ የስራ ማሕበረሰብ ዘርፍ ትውውቅ ነሐሴ 4/17 ከ8:30 ይካሄዳል።

ከነሐሴ 9 እስከ ነሐሴ 11/17 ዓ.ል በአምስት ዘርፎች የሚደረገው ምርጫ ይደረጋል።

በዚህም መሰረት ፦

✔ የዑለማ ዘርፍ ምርጫ ነሐሴ 9/17 ከጥዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 6:00
✔ የስራ ማህበረሰብ ዘርፍ ምርጫ ነሐሴ 9/17 ከሰዓት 8:00 እስከ 11:30
✔ የምሁራን ዘርፍ ምርጫ ነሐሴ 11/17 ከጧቱ 3:00 እስከ 6:30
✔ የወጣቶች ዘርፍ ምርጫ ከነሐሴ 11/17 ከጧቱ 2:00 እስከ 6:30 ሰዓት
✔ የሴቶች ዘርፍ ምርጫ ነሐሴ 11/17 ከሰዓት ከ8:00 እስከ ቀኑ 10:00 ይካሄዳል

ነሐሴ 9/17 በዑለማ ዘርፍ የሚጀመረው የመጅሊስ ምርጫ በተቀመጠው ቀን እና ሰዓት ላይ መራጩ በመገኘት ኢስላማዊ ኅላፊነታቸውን እንዲወጡ ቦርዱ ጥሪውን አቅርቧል።
===========

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ

የሩሲያን ምድር በድሮን እያደባየሁት ነዉ ! /ዩክሬን /‎‎ዩክሬን የሩሲያን ቁልፍ ስፍራዎች ላይ መብረቃዊ ጥቃት መድረሷን ተናገረች ።‎‎የዩክሬን ጦር ዛሬ ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ በሩሲያ...
02/08/2025

የሩሲያን ምድር በድሮን እያደባየሁት ነዉ ! /ዩክሬን /

‎ዩክሬን የሩሲያን ቁልፍ ስፍራዎች ላይ መብረቃዊ ጥቃት መድረሷን ተናገረች ።

‎የዩክሬን ጦር ዛሬ ቅዳሜ ዕለት ባወጣው መግለጫ በሩሲያ ውስጥ የነዳጅ ማምረቻዎችን ዋና ዋና ማጣሪያ ፋብሪካን እንዲሁም የድሮኖችን እና የኤሌክትሮኒክስ ፋብሪካን ወታደራዊ አየር ማረፊያን ጨምሮ መምታቱን ተናግሯል።

‎በቴሌግራም ላይ በሰጠው መግለጫ የዩክሬን ሰው አልባ ሲስተም ሃይሎች ከሞስኮ በስተደቡብ ምስራቅ 180 ኪሜ (110 ማይል) ርቀት ላይ በምትገኘው ሪያዛን የሚገኘውን የነዳጅ ማጣሪያ በመምታቱ በግቢው ላይ የእሳት ቃጠሎ ዳርገዋል ብሏል።

‎መግለጫው በሰሜን ምስራቅ ዩክሬን በሚያዋስነው በቮሮኔዝ ክልል የሚገኘው የአናኔፍቴፕሮዶክት ዘይት ማከማቻ ቦታ መመታቱን ቢገልፅም ተቋማቱ እንዴት እንደተመቱ ባይገልፅም ከዚህ በተጨማሪ የዩክሬን ኤስቢዩ የስለላ ድርጅት ሰው አልባ አውሮፕላኖቹ በዩክሬን ዒላማዎች ላይ የረዥም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለማጥቃት ያገለገለውን የሩሲያ ፕሪሞርስኮ-አክታርስክ ወታደራዊ አየር መንገድን መምታቱን አስታውቋል።

‎የሩስያ መከላከያ ሚኒስቴር በየእለቱ በሚያወጣዉ ዘገባ እንዳስታወቀው የመከላከያ ክፍሎቹ በአንድ ጀምበር 338 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መውደቃቸውን አስታውቋል።

‎ከዚህም በተጨማሪ በዩክሬን ምስራቃዊ ጦር ግንባር ላይ ቅዳሜ ዕለት የሩስያ ጦር እየገሰገሰ መሆኑን የገለፀዉ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በዶኔትስክ ክልል የሚገኘውን ኦሌክሳንድሮ-ካሊኖቭን መንደር መያዙን አስታውቋል። ሲል የዘገበው ሮይተርስ ነዉ ።

‎ በታዴ የማመይ ልጅ

Breaking News!Dr. Girma Amente, the former Minister of Agriculture of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, appoi...
02/08/2025

Breaking News!

Dr. Girma Amente, the former Minister of Agriculture of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, appointed as the African Union's Permanent Representative to the United Nations and the World Trade Organization in Geneva.

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ዶ/ር ግርማ አመንቴ፥ በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና በዓለም ንግድ ድርጅት የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ ሆነው ተሹመዋል።

Address

New York

Telephone

+251909496980

Website

https://affiliatemarketing650.siterubix.com/welcome-to-your-new-website/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Siltie Media House ስልጤ ሚዲያ ሃውስ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Siltie Media House ስልጤ ሚዲያ ሃውስ:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share