SIMBO KOO

SIMBO KOO Simbo koo is the page that provide news, general knowledge, lifestyles, healthy info and what else

06/11/2025
06/11/2025
06/11/2025
01/11/2025

"ካሳከማችሁኝ ቀና ብዬ መሄድ እችላለሁ!"😭

: ‎ተማሪ ቢንያም ሂታሎ ይባላል ። ትውልድና ኑሮው በጋሞ ዞን ቆጎታ ወረዳ ወሮ ቀበሌ ነው ። እድሜው 12 ሲሆን ፤የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነው ። ጤናማ ሆኖ የተወለደው ቢኒያም ፤ የአንድ ዓመት ህፃን እያለ ዳዴ በሚልበት ጊዜ የመውደቅ አደጋ ይደርስበታል ።

በወቅቱ ሲወድቅ ገደል ውስጥ በመግባቱ ከባድ አደጋ ሊያጋጥመው ችሏል ። በወቅቱ በቂ የህክምና አገልግሎት አላገኘም ። ቤተሰቦቹ በጣም ዝቅተኛ ኢኮኖሚ ደረጃ ላይ ያሉ ስለሆነ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ ማድረግ አልቻሉም ነበር ።
ታዳጊው ቢኒያም በአግባቡ ባለመታከሙ ፤ ከአደጋው በኃላም ከታች በምትመለከቱት መልኩ ቀና ብሎ መራመድ ሳይችል ቀርቷል ። በዚህ መልኩ ዓመታትን መግፋት ቢችልም በጊዜ ሂደት ህመም እየተሰማው ፣ ለመንቀሳቀስ ጭምር እያዳገተው እንደመጣ ቤተሰቦቹ ይናገራሉ ።

ቀና ብሎ ተወልዶ ጎንበስ ብሎ በሚንቀሳቀሰው ልጃቸው በፀፀት የምትንገበገበው እናት ለዓመታት አልቅሳለች ። አሁንም ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ትገኛለች ። አባት ክፉኛ አዝኗል፤ ቢንያም ከጓደኞቹ ጋር መጫወት መማር መራመድ አልቻለም ዕድሜው እየጨመረ ችግሩም አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል።

በጉዳዩ ተስፋ ያልቆረጡት አባት አቶ ሂታሎ ሳጌ ወደ አርባ ምንጭ ሆስፒታል እና ታድሶ ማዕከል ቢንያምን ወስደው ለማሳከም ጥረት ቢያደርጉም ህክምናው አርባምንጭ እንደማይሆን ተገልጾላቸዋል ። ልጃቸውን በአስቸኳይ አዲስ አበባ Cure Hospital ወስደው እንዲያሳክሙ ነግሯቸዋል ።

‎ታዳጊው አስፈላጊው ህክምና ቢያገኝ እንደሚድን ሀኪሞች ተስፋ እንደሰጡት የሚናገረው ታዳጊው ፤ "ካሳከማችሁኝ ቀና ብዬ መሄድ እችላለሁ እኮ ።

እንደ እኩዮቼ ተጫውቼ ቦርቄ ማደግ እችላለሁ " ሲል የመዳን ጉጉቱን እና ተስፋውን አጋርቷል ። ስለሆነ እናንተ መልካምነትና ቅንነት መለያ የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን የተቻላችሁን ሁሉ ድጋፍ እንድታደርጉላቸው ታዳጊው ቢኒያም እና አባት አቶ ሂታሎ ሳጌ ተማጽኗቸውን አቅርበዋል ።

ተማሪ ብንያም ሂታሎን ማሳከሚያ የድጋፍ አካዉንት 1000726892613 በወላጅ አባቱ በሂታሎ ሳጌ ስም ተከፈተ
አስተባባሪ አካላት:-
1, ዘላለም በላቸው 0916700423
2,አቶ በፍቃዱ አበበ 0931321316
3,አቶ ባንጋ በድሉ 0923854474
4,ወ/ሮ ደመቀች ዳርዛ 0923474029

ግራም ወደ ኪሎ ግራም የተሸጋገረበት ተአምርግራም፡፡ ግራም የወርቅ መለኪያ እንጂ የሰው ልጅ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ምን ቢያንስ፤ ምን ጨቅላ ህጻን ቢሆን፤ በግራም አይመዘንም፡፡ መለኪያው ኪሎ...
23/09/2025

ግራም ወደ ኪሎ ግራም የተሸጋገረበት ተአምር

ግራም፡፡ ግራም የወርቅ መለኪያ እንጂ የሰው ልጅ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ምን ቢያንስ፤ ምን ጨቅላ ህጻን ቢሆን፤ በግራም አይመዘንም፡፡ መለኪያው ኪሎ ግራም ነው፡፡ አሜሪካ፣ ማይናማርና ላይቤሪያ በፓውንድ የሰውን ክበደት ይለካሉ፡፡

ወርቅ ብሎ ግራም እንጂ ሰው ብሎ ግራም የለም፡፡ በሕክምና አዲስ የተወለደ ልጅ ጤነኛ ነው ለማለት ቢያንስ 2.5 ኪሎ ግራም መሆን አለበት፡፡ ሲያንስ ውሎ ሲያንስ ቢያድር ግን ከ1 ኪሎ አያንስም፡፡ ካነሰ ግን አይተርፍም፤ ቢተርፍም ዓይኑ፣ አዕምሮው እና ሳንባው በአግባቡ አይሰራም፡፡ ይላሉ የሕክምና ባለሙያዎች፡፡ ደህና ሆኖ ከተረፈ ግን ተአምር ይባላል፡፡

ተአምሩ የተገለጠው በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና እናቶችና ሕጻናት ማዕከል ነው፡፡ ሰብለ ሁለተኛ ልጇን ካረገዘች ሃያ ስድስት ሳምንታት ሞልቷታል፡፡ ልክ ስድስት ወር ላይ ግን ችግር ገጠማት፡፡ ቁጭ ባለችበት የደም መፍሰስ፡፡ ተደናገጠች፡፡ እናትም አይደለች? ወደ ጤና ተቋም ሄደች፡፡ ሐኪሞቹም እንቅስቃሴ እንድትቀንስ፤ እረፍት እንድታደርግ ነግረው አረጋግተው ወደ ቤት መለሷት፡፡ ፡ ቢሆንም ደም መፍሰሱ አልቆመም፡፡

ነገሩ ሲብስ ሰብለ ወደ ሌላ ተቋም ሄደች፡፡ የማኅጸን እና ጽንስ ሐኪሞች ነገርየው ትንሽ ከበደ ያለ ግን የሚያጋጥም እንደሆነ አስረድዋት፡፡ በህክምና ቋንቋ abruption placenta ይሉታል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ከ20 ሳምንት ቀድሞ የተወለደን ጽንስ ሁሉ ውርጃ (Abortion) ሲል ይቆጠረዋል፡፡ እንደየሀገሩ በመለያየት እስከ 28 ሳምንታት ድረስ ውርጃ ሊባል ይችላል፡፡ ይህም ልዩነት ያመጣው ልጅ ከ28 ሳምንታት በፊት ከተወለደ በሕይወት ማቆየት የሚችል ባለሙያ እና መሳሪያዎች በበቂ ሁኔታ አለመሟላት የፈጠረው ነው።

ሰብለ abruption placenta ከተባለች በኋላ ልጁ መወለድ እናዳለባት ይነገራታል፡፡ abruption placenta ማለት የእንግዴ ልጁ ከማኅጸን ግድግዳ ጋር ባልታወቀ ምክንያት ሲላቀቅ ነው፡፡ ይህ ብቸኛ ቀጭን የእናትና የልጅ አገናኝ ድልድይ ምግብ እና የኦክስጅን ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍበት ኮሪደር ነው፡፡

የእንግዴ ልጁ ከማኅጸን ተለያየ ማለት ጽንሱ ይሞታል ማለት ነው፡፡ ነገሩ በጽንሱ ሞት ብቻ አይደመደም፡፡ እናትን ለብዙ ደም መፍሰስ ብሎም ለሞት ያጋልጣል፡፡

አንድ ጽንስ ጤነኛ እና ትክክለኛ ሳምንት የሚባለው ከ37- 42 ሳምንታት በማኅጸን ውስጥ ሲቆይ ነው፡፡ ከዚህ የቀደመም የዘገየም ጽንስ አደጋ ነው፡፡ ከሚቀድም ግን ቢዘገይ ይመረጣል፡፡ ለዘገየ ጽንሽ የሕክምና መፍትሔው ከቀደመው በጣም የተሻለ እና በንጽጽር ቀላል ስለሆነ ነው፡፡

የሰብለ ልጅ ግን በ26 ሳምንት በ6 ቀኑ መወለድ ነበረበት፡፡ ምክንያቱም ብቸኛው አስተሳሳሪው የእንግዴ ልጅ ከማኅጸን ግድግዳ ስለተላቀቀ፡፡፡ የስድስት ወር ልጅ፡፡ ተወለደ፡፡ ሲወለደ 910 ግራም ነበር፡፡

ቢሆንም የእናት ጡት ወተት በአግባቡ መሳብ አይችልም፡፡ ቢችልም ለወተቱ የሚሆን የአደገ አንጀት የለውም፡፡ ስለዚህ ወደ 765 ግራም ወረደ፡፡ ጉዳዩ ግን የኪሎ ብቻ አልነበረም፡፡

የልጁ ሰውነት ስላልጸና ልቡ ላይ ክፍተት ነበረበት፡፡ እድገቱን ስላልጨረሰ ልቡ በግራ መሆን ሲገባው በቀኝ በኩል ሆኗል፡፡ አይኑ የማየት እድሉ በጣም አናሳ ነው ምክንያቱም ሪተና የተባለቸው የአይኑ ክፍል ተጨማሪ የደም ስር እድገት ስለሚኖረው፡፡

በዚያ ላይ IVH ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነው፡፡ IVH ምህጻረ ቃል ሲሆን ምህጻረ ቃሉ ሲፈታም Intraventricular Hemorrhage ማለት ነው፡፡ አለጊዜው የሚወለዱ ህጻናት በጣም ጥቃቅን እና በማደግ ላይ ያሉ የደም ስሮች ስለሚኖሩዋቸው አዕምሮቸው ውስጥ ደም የመፍሰስ እድል አለው፡፡ የሰብለም ልጅ ሁለተኛ ደረጃ IVH ገጥሞት ነበር፡፡

ስለዚህም ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎዳና የእናቶችና የህጻናት ሕክምና ማዕከል ልጇን ይዛ መጣች፡፡

የተወለደው ህጻን 765 ግራም ስለሆነ ሳንባው በአግባቡ ስለማይተነፍስ በማሽን እንዲተነፍስ ማድረግ፤ ረቲና የተባለችው የዓይኑ ክፍል ተጨማሪ የደም ስር በማብቀል ለአይነ ሥውርነት እንዳይጋለጥ Anti-VEGF የተባለ መድኃኒት ተሰጠው፡፡

በመቀጠል ሳንባው ለሰለስ ብሎ በተለይም አየር ከሳንባ ሲወጣ አተነፋፈሱ እንዲስተካከል ሰርፋክታንት በመስጠት ጥብቅ ክትትል በፅኑ ሕሙማን ክፍል እንዲደረግለት ሆነ፡፡

ከጽኑ ሕሙማን ክፍል ከወጣ በኋላ በአፍንጫው በኩል (NG tube) ፎርቲፋየር ወተት ከእናት ጡት ጋር እየተሰጠው በኦክስጅን ላይ ሆኖ አተነፋፈሱ እንዲሰምር caffeine citrate እየተሰጠው ለሳምንታት ቆየ፡፡

ተአምር በየካቲት፤ ተአምር በአበበች ጎበና የህጻናት እና እናቶች ማዕከል ተፈጠረ፡፡ ከ765 ግራም ወደ 1.6 ኪሎ ግራም ከፍ አለ፡፡ ኪሎ ግራም ትክክለኛው የሰው ልጅ መለኪያ፡፡

ይሞታል ሲባል፡፡ ተረፈ። ሳንባው በአግባቡ አይተነፍስም ሲባል። በትንሽ ኦክስጅን ድጋፍ ተነፈሰ፡፡ ዓይነ ሥውር ይሆናል ሲባል ዓይናማ ሆነ፡፡ አእምሮው በአግባቡ አይሰራም ሲባል አእምሮው መደበኛ ሥራውን ቀጠለ፡፡ በእናት እመነትና ጸሎት በየካቲት 12 የአበበች ጎበና የእናቶችና ሕጻናት አጠቃላይ ባለሙያዎች ያለሰለሰ ጥረትና ትጋት ተአምር ተፈጠረ፡፡ ይሁን አሉ ሐኪሞች። በትጋትና በጥረት ሆነ። የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና እናቶችና ሕጻናት ማዕከል
ሆነ!

ሰብለ “ምጡን እርሽው፤ ልጁን አንሽው” አልተባለችም፡፡ በሀገር ባህል ወግም በቅጡ “እንኳን ማርያም ማረችሽም” ተብላ አልተጠየቀችም፡፡ አራስ ቤቷን ሆስፒታል ከረመች፡፡ ከሀምሌ 11 2017 የጀመረ እስከዛሬ በእናት እንክብካቤ፤ በቤት በቤተዘመድ አጀባና ሽርጉድ ሳይሆን በአስጨናቂ የሕክምና መንገድ አሳለፈች፡፡ ዛሬ ግን ከሆስፒታል ወጥታ ወደ ቤት ልትመለስ ነው፡፡ ልጇ በጥሩ ጤንነት ላይ ነው፡፡ ምጡን ረስታ ልጁን ልታነሳ።

እናት ሰብለ ለልጇ ስም አወጣች፡፡ ተአምር ከፈለኝ፡፡ እውነትም ተአምር ከፈለ፡፡ የፈጣሪ ተአምር፡፡ ያለሰለሰ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ማዕከል ባለሙያዎች ተአምራዊ ትጋትና ጥረት ተአምር ፈጠረ፡፡

"ይሁን አለ ሆነም"

እውነትም ተአምር ከፈለኝ!

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካ ኮሌጅ አዲስ አበባ መስከረም 13/2018 ዓ.ም ( ኮሚኒኬሽን ቡድን)

17/09/2025

Address


45500

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when SIMBO KOO posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to SIMBO KOO:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share