Nolot Media

Nolot Media START WHERE YOU ARE. USE WHAT YOU HAVE. DO WHAT YOU CAN.

♡ ㅤ ❍ ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ share

DON'T TRUST TOO MUCH
DON'T LOVE TOO MUCH
DON'T HOPE TOO MUCH
BECAUSE THAT TOO MUCH CAN HURT YOU SO MUCH

You can also follow on Instagram to see more.
23/12/2025

You can also follow on Instagram to see more.

"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና!" (2ኛ ቆሮ. 9:7)▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬በምስሉ ላይ የምታዩት በዎላይታ ሀገረ ስብከት፣ በካዎ ኮይሻ ወረዳ የምትገኘውን የኮይሻ ዋሙራ ሳጋዶራ በዓታ ማ...
17/12/2025

"እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና!" (2ኛ ቆሮ. 9:7)
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በምስሉ ላይ የምታዩት በዎላይታ ሀገረ ስብከት፣ በካዎ ኮይሻ ወረዳ የምትገኘውን የኮይሻ ዋሙራ ሳጋዶራ በዓታ ማርያም ቤተክርስቲያንን ነው። በእንዲህ ያለ ሁኔታ ውስጥ ሆነው ቅዳሴ የሚቀደስባት፣ ማኅሌት የሚቆምባትና ምእመናን በፀሐይና በዝናብ እየተጠበሱ የሚጸልዩባት የእመቤታችን ቤት ናት።

ይህንን ሁኔታ አይቶ ዝም ማለት ለሕሊና ይከብዳል። ቤተክርስቲያኗን ወደ ተሻለ ደረጃ ለመቀየርና ቋሚ ግንባታ ለመጀመር የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል።

ለግንባታው የሚያስፈልጉ፡ ቆርቆሮ፣ ሲሚንቶ፣ ምስማርና ሌሎች የግንባታ ቁሳቁሶች ጠቅላላ ግምት፡ 500,000 ብር በላይ።

ዲያቆን Esahun Tekle 500 ብር ዛሬ ገቢ አድርጓል ። እናንተም እንደ እሱ "ለቤተክርስቲያን መታደስ የበኩሌን አደርጋለሁ" ካላችሁ፣ በዚሁ የባንክ አካውንት ገቢ በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እጠይቃችኋለሁ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE): 1000707796026

📌 የአካውንት ስም: የኮይሻ ዋሙራ ሳጋዶራ በዓታ ማርያም ቤተክርስቲያን

🙏 እባካችሁ! ገቢ ስታደርጉ Screenshot (ደረሰኝ) በመላክ ሌሎችን አበረታቱ። ይህንን መልእክት Share በማድረግ ለብዙዎች እንዲደርስ በማድረግም ተባበሩን።
Nolot Media

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን🙏▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬"ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መ...
16/12/2025

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን🙏
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"ስጡ ይሰጣችሁማል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ይሰፈርላችኋልና፥ የተጨቈነና የተነቀነቀ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በእቅፋችሁ ይሰጣችኋል።" የሉቃስ ወንጌል 6:38

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በዎላይታ ሀገረ ስብከት፣ በካዎ ኮይሻ ወረዳ ቤተ ክህነት ሥር የምትገኘው ኮይሻ ዋሙራ ሳጋዶራ በዓታ ማርያም ቤተክርስቲያን ታላቅ ራእይ ይዛላችሁ ቀርባለች።

አሁን ያለችው መቀኛችን (የጸሎት ቦታችን) ወደ ቤተ መቅደስ እንድትለወጥ፣ ነገር ግን ቦታው አጥሮ፣ ቤተክርስቲያኒቱ የጥገናና የግንባታ እጁን እንድትዘረጋ እየተማፀነች ነው።

የእኛ ተጋድሎ፣ የእናንተ በረከት
ይህንን መንፈሳዊ ምኞት እውን ለማድረግ ቤተክርስቲያኒቱ አስቸኳይ የሆኑ ተግባራት ይጠብቋታል። የቦታ ማስፋፊያ ሥራዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም ለግንባታ የሚያስፈልጉ ወሳኝ ቁሳቁሶችን፣ ከእነዚህም መካከል፦ቆርቆሮ (ለጣራ) ሚስማር፣ (ሲሚንቶ)

የተለያዩ ነዋያተ ቅዱሳት (ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት)
ለመግዛትና ግንባታውን ለማስኬድ 500,000 ብር በላይ የሚያስፈልግ ግምት ተቀምጧል።

እኛም፣ እናንተን—ደጋግና ቸር የኢትዮጵያ ልጆችን—በእግዚአብሔር ስም ልንጠይቃችሁ ተነስተናል!

🤲 በትንሹ ዘርቶ ታላቁን በረከት ይሰብስቡ! 🤲

በዚህ የተቀደሰ ሥራ የበኩላችሁን አስተዋጽዖ ስታደርጉ፣ የምትሰጡት ገንዘብ ሳይሆን፣ ለክርስቶስ አካል የዘረጋችሁት ፍቅር መሆኑን እወቁ። በትንሽ እርዳታችሁ፣ ትልቁን እና ዘላለማዊውን በረከት ከልዑል እግዚአብሔር ዘንድ እንድትወስዱ በፍቅር እንማፀናለን።

የእርዳታችሁን እጅ ዘርጉ፣ ለትውልድ የሚሻገር ሃይማኖታዊ ቅርስን አብረን እንገንባ!

የቤተክርስቲያን አካውንት መረጃ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE)1000707796026 ሳጋዶራ በዓታ ማርያም

✍️ለበለጠ መረጃ እና ማረጋገጫ፣ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ይደውሉ:

0916 14 14 39
0915 53 64 25

እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥልኝ! 🙏

💔 ልብ የሚሰብር ዜና እና የሐዘን መግለጫ 💔የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሁለት ቁልፍ አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ!በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ታላቅ ሐዘን ደርሷል። የሀገረ ስብከቱ ...
14/12/2025

💔 ልብ የሚሰብር ዜና እና የሐዘን መግለጫ 💔

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ሁለት ቁልፍ አመራሮች በታጣቂዎች ተገደሉ!

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ሀገረ ስብከት ታላቅ ሐዘን ደርሷል። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና ካህን ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ በሕገ ወጥ ታጣቂዎች እጅ በጭካኔ መገደላቸው ተረጋግጧል።

መልአከ ኤዶም ቀሲስ ዱጉማ ኡፋ እና ካህን ቀሲስ ደሳለኝ ነሞምሳ።

ሁለቱ ካህናት ከበርካታ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች ጋር የኅዳር ጽዮን ማርያምን በዓል አክብረው ሲመለሱ ጥቃት ደርሶባቸዋል።

ታጣቂዎቹ ካህናቱን ከሌሎች ሰዎች ለይተው ከያዙና ካገቱ በኋላ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸዋል። ሌሎቹ ታጋቾች በጊዜ ሂደት ተለቀዋል።

ይህ ኢሰብአዊ እና ኢ-ሃይማኖታዊ ድርጊት በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ታላቅ ድንጋጤንና መሪር ሐዘንን ፈጥሯል።

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሀገረ ስብከቱ ምእመናን እና ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ መጽናናትን እንመኛለን። ነፍስ ይማር!

መንግሥት የፀጥታ ችግሩን በአስቸኳይ እንዲፈታ እና ይህን ኢሰብአዊ ድርጊት የፈጸሙ አካላትን ለሕግ እንዲያቀርብ ጠንካራ ጥሪ እናቀርባለን። በሃይማኖት አባቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት ይቁም!

#ኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ሆሮጉዱሩወለጋ #ፍትህይሁን #ነብስይማር

Nolot Media©

✨ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ እና የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ! ✨የሦርቶ ቅድስት አርሴማ ገዳም (በታላቅ ደስታና ፍጹም መንፈሳዊ ቅንዓት) የሰማዕቷን የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ የን...
12/12/2025

✨ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ እና የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ! ✨

የሦርቶ ቅድስት አርሴማ ገዳም (በታላቅ ደስታና ፍጹም መንፈሳዊ ቅንዓት) የሰማዕቷን የቅድስት አርሴማ ዓመታዊ የንግሥ በዓል አስመልክቶ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ መዘጋጀቱን ለመላው ኦርቶዶክሳዊ ምእመናን ይፋ ያደርጋል!

ይህ ታላቅ መንፈሳዊ በዓል ከታኅሣሥ 4 እስከ ታኅሣሥ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ቀናት በድምቀት ይካሄዳል።

_____በዕለቱ_____
የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች
የመዝሙርና የጸሎት መርሃ ግብሮች

⛪ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም:

ከመንፈሳዊ በረከት ባሻገር፣ ይህ በዓል በተለየ ሁኔታ ለተጀመረው የሦርቶ ቅድስት አርሴማ ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ ማጠናቀቂያ የሚሆን ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የሚካሄድበት ይሆናል።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ግንባታ በመደገፍ፣ ዘላለማዊ በረከት እና ምንዳ ለማግኘት በቅንነት የተዘጋጀ ሁሉ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ቤተክርስቲያኑ ቅዱስ ጥሪውን ያቀርባል!

በተለይም፣ ለመንፈሳዊ በዓሉ ተሳታፊነትና ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግንባታ ድጋፍ ለማድረግ ለሚፈልጉ ሁሉ ምቹ እንዲሆን:

የጉዞ ቀን: በዕለተ እሑድ፣ ታኅሣሥ 5 ቀን 2018 ዓ.ም.

ዓላማ: ወደ ሦርቶ ቅ/አርሴማ ገዳም ታላቅ ጉዞ ስለተዘጋጀ፣ ምእመናን በጉባኤው እንዲሳተፉ እና የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ነው።

🙏 ጥሪ ለሁላችንም!

መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፣ የሰማዕቷን በረከት ለመካፈል፣ በታላቁ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ ለመገኘት እና የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታን በመደገፍ ታሪካዊ ሥራ ለመሥራት በብዙ ፍቅርና አክብሮት ጥሪ ቀርቦላችኋል!

ልብ ይበሉ! ይህ ጉባኤ የእምነት መሠረት የሚጸናበት፣ ታላቅ በረከት የሚገኝበት እና ዘላለማዊ ዋጋ የሚያስገኝበት መልካም አጋጣሚ ነው።

ኑ! የበዓሉ ተካፋይ ይሁኑ! የሰማዕቷ ቅ/አርሴማ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን! አሜን!

📍 ቦታ: የሦርቶ ቅድስት አርሴማ ገዳም

🗓 ጊዜ: ከታኅሣሥ 4 እስከ 6/2018 ዓ.ም

የሦርቶ ቅ/አርሴማ ቤ/ያን ሕንፃ ግንባታ የንግድ ባንክ አካዉንት 1000660345136

Nolot Media

✝️ የይቅርታ ጥሪ ከጎንደር ሙሉ ወንጌል አማኞች! 🕊️በጎንደር ከተማ የተካሄደውን የኮንፍራንስ መርሃግብር ተከትሎ፣ የብዙዎችን ልብ የነካ እና ውዝግብ የቀሰቀሰ ክስተት ተፈጠሮ ነበር። በዚህም...
11/12/2025

✝️ የይቅርታ ጥሪ ከጎንደር ሙሉ ወንጌል አማኞች! 🕊️

በጎንደር ከተማ የተካሄደውን የኮንፍራንስ መርሃግብር ተከትሎ፣ የብዙዎችን ልብ የነካ እና ውዝግብ የቀሰቀሰ ክስተት ተፈጠሮ ነበር። በዚህም መሰረት፣ የጎንደር ሙሉ ወንጌል አማኞች ማህበር ባጋጠመው ሁኔታ ጥልቅ ይቅርታ ጠይቋል።

የይቅርታ ጥያቄው መንስኤ በቅርቡ በጎንደር ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አስተባባሪነት በተካሄደው የኮንፍራንስ ፕሮግራም ላይ የተከናወነው ድርጊት ነው። በዝግጅቱ ላይ፣ መስቀል አንገታቸው ላይ ያደረጉ ግለሰቦች በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምእመናን ማስመሰል በማሳየት፣ የብዙዎችን ስሜት የሚዳፈር እና የቤተክርስቲያኗን ክብር የሚነካ የሚመስል ተግባር ተፈጽሞ ነበር።

ይህ ድርጊት በበርካታ ወገኖች ዘንድ ቅሬታና ቁጣን ያስነሳ ሲሆን፣ በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮችን ስሜት በእጅጉ ነክቷል።

የጎንደር ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን አስተባባሪዎች እና አማኞች ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች የይቅርታ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ቤተክርስቲያኒቱ፣ የተፈጠረውን ሁኔታ ተገንዝባ፣ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ክብር የሚነካ ምንም ዓይነት ድርጊት የመፈጸም ፍላጎት እንዳልነበራት ገልጻለች።

"በዚህ ድርጊት ሳቢያ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ምእመናን እና የቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ላይ ለተሰማው መረር ስሜት ሁሉ፣ ከልብ የመነጨና ቅን የሆነ ይቅርታ እንጠይቃለን። ዓላማችን ፍቅርንና አንድነትን መዝራት እንጂ መለያየትንና ንቀትን ማምጣት አልነበረም።" ብለዋል።

ይህ ድርጊት በጎንደር ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት ተቋማት እና አማኞች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር፣ የጋራ መከባበርን ለመጠበቅ እና የይቅርታን ባህል ለማስረፅ እንደ አንድ አዎንታዊ እርምጃ ተወስዷል። የይቅርታው ጥያቄ ለሃይማኖታዊ ተቋማት የሚሰጠውን ከፍተኛ ክብር እና የጋራ ሰላምን የመጠበቅን አስፈላጊነት በድጋሚ አጉልቶ አሳይቷል።
media

11/12/2025

Big shout out to my newest top fans! Asnakech Odiro Asi, Abisrat Abis

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 🙏የሆርባቢቾ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ራጉኤል  ቤተክርስቲያን የአትክልት ግምት ጥሪ!ክቡራን ምዕመናን እና ኦርቶዶክሳውያን ወዳጆች!የሆርባቢቾ...
11/12/2025

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! 🙏

የሆርባቢቾ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን የአትክልት ግምት
ጥሪ!

ክቡራን ምዕመናን እና ኦርቶዶክሳውያን ወዳጆች!

የሆርባቢቾ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ለረጅም ጊዜ ሲያገታት የነበረውን የቦታ ችግር የሚፈታ ታላቅ እድል አግኝታለች።

የነበረው የደብሩ ይዞታ 1000 ካሬ ሜትር ለዘመናት ለሚኖረው እድገት፣ ለመካነ መቃብር፣ ለሰንበት ትምህርት ቤት እና ለመንፈሳዊ አገልግሎቶች መስፋፋት በቂ አልነበረም።

በሰበካ ጉባኤ ጥረት ምክንያት፣ ቤተክርስቲያኒቱን ሙሉ ለሙሉ የሚያስፋፋ 30,000 ካሬ ሜትር (3 ሄክታር) ሰፊ መሬት በስጦታ መልክ ተገኝቷል!

🔴 ይህንን ታሪካዊ ቦታ በሕጋዊ መንገድ ለመረከብ እና የደብሩ ንብረት ለማድረግ፣ በላዩ ላይ ለሚገኙ አትክልቶች ግምት ብር 10,000,000 (አሥር ሚሊዮን ብር) በአስቸኳይ መክፈል ይጠበቅባታል!

ይህ ክፍያ በአፋጣኝ ካልተፈጸመ፣ ቤተክርስቲያኒቱ ይህን የዕድገት ዕድል ልታጣ ትችላለች።

🏦 የድጋፍ መስጫ ብቸኛ እና ሕጋዊ የባንክ ሂሳብ ቁጥር:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ : 1000497958087

⚠️ ማሳሰቢያ: ማንኛውንም አይነት ድጋፍ የሚደረገው በዚህ ሂሳብ ቁጥር ብቻ ነው።

ይህን መልዕክት በስፋት ሼር በማድረግ እና በገንዘብዎ በመርዳት፣ የቅዱስ ራጉኤል ወኤልያስ ቤተክርስቲያንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ይቀይሩ! የበረከት ተካፋይ ይሁኑ!

እግዚአብሔር ይስጥልን! አሜን!

መጋቤ ሚስጥር መምህር አበራ ንጋቱ

 #አርቲስቶች እና  #ቲክቶከሮች  #ተጨማሪ  #የቤተ  #ክርስቲያን  #መከራ ሆነዋል።                            -------***-------ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መሥራት እግ...
09/12/2025

#አርቲስቶች እና #ቲክቶከሮች #ተጨማሪ #የቤተ #ክርስቲያን #መከራ ሆነዋል።
-------***-------
ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን መሥራት እግዚአብሔር የሚወደው ሥራ ነው። ሰው ሳይሠራ ግን ሕንጻ ተሠርቶ ምን ያደርጋል? አዕምሮ ሳይገነባ ፎቅ ደርድረን ምን እንጠቀማለን?

ምእመናን የመጣው ጐርፍ ሁሉ እየወሰዳቸው፥ #ዕቅበተ እምነት ላይ ሥራ ሳይሠራ #ሕንጻ ቢከመር፥ ምእመናን ሲወሰዱ ሕንጻውም በሌሎች ይወረሳል። "እንወርሰዋለን" ብለው አይደል።

አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች #ከሸቃጭ ዘማሪያን ጋር ተጃምለውና ተሰብስበው ለሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገቢ አሰባሰቡ ተብሎ እልልልል ይባላል። ምእመኑ ደግሞ የዋሕ ነው። ዝም ብሎ ይሰጣል። አያጣራም።

እነሱ ሆዬ #የሚሰበስቡት #በፐርሰንት ነው። #አንድ #ሦስተኛን ገንዘብ (30%ቱን) #ለራሳቸው ሐም ያደርጉታል። ቀድሞውንስ ሳይሰበሰብ ገንዘቡ የቤተ ክርስቲያን አልነበረምን? ንጹሕ ወንጌል አስተምረን ይህንን አድርግ ብነው ሕዝቡ ለመስጠት እጁ ተጨብጦ ያውቃል?

ቤተ ክርስቲያን ማቅ በለበሰችበት በዚህ ጊዜ #ተሰብስቦ መጨፈር፣ በቀጥታ ስርጭት እልል ማለት፣ መቦረቅ ከየት የመጣ ነው? የቤተ ክርስቲያንን ወተት በፐርሰንት አልቦ መሔድስ ከማን የተገኘ ነው?

ትንሽ እንኳ ስቅጥጥ አይላቸውም'ኮ። #ከዐየር ማረፊያ ጀምሮ ልብሰ ተክህኖ በለበሱ ካህናት አቀባበል ይደረግላቸዋል። የቤተ ክርስቲያን ጥላ ይዘረጋላቸዋል። የቀጥታ ስርጭት ሽፋኑ በእጃቸው ነው። በከበሮ በጭብጨባ በሞቅታ በግርግርታ በጩኸት በፉጨት ሲለምኑ ውለው ሲለምኑ ያድራሉ። ፐርሰንት ጎርደው ይሔዳሉ። ኸረ እግዚአብሔርን እንፍራ።

እውን ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ ልማት የምታስቡ ከሆነ አዕምሮ ከሚለማበት አብነት ት/ቤት ላይ አትሳተፉም? የጣና ቂርቆስ የመጻሕት ትርጓሜ ጉባኤ ቤት መምህር፥ የኔታ አባ ገብረ ኪዳን የነደፉት ፕሮጀክት ዞር ብሎ #ያዬው ታዋቂ የሚዲያ ሰው አለ?

የደብረ ታቦሩ የኔታ #በጽሐ ዓለሙ #የነደፉት አስገራሚ የቤተ ጉባኤ ፕሮጀክትስ ማን ደረሰለት? ይህንን አታስተባብሩም ነበር? ይህ ብቻ አይደለም፤ በእጅጉ ርዳታ የሚናፍቃቸው ገዳማት አሉ'ኮ። ገዳማትን መርዳት አይቻልም ነበር?

ዓላማው #ለራስ #ገቢን በፐርሰንት መሰብሰብ የሆነ፥ እንዲህ ያለ ዘመን ተሻጋሪ ሥራ አይሠራም። ብትችሉ ነውራችሁን በልክ አድርጉት። እምቢ ካላችሁ ግን ዋጋችሁን ከባለቤቱ ትቀበላላችሁ። ይኸው ነው።
Getinet
media

Address


19958

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Nolot Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Nolot Media:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share