ስልጤ—ታይምስ/siltie-Times

  • Home
  • ስልጤ—ታይምስ/siltie-Times

ስልጤ—ታይምስ/siltie-Times we provide latest global&local news

18/09/2025
18/09/2025
07/09/2025
07/09/2025
የሰላም ሚኒስቴር የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቁን አስመልክቶ ያስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት!የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ...
07/09/2025

የሰላም ሚኒስቴር የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቁን አስመልክቶ ያስተላለፈው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2017 ጠቅላላ ምርጫ በሰላምና በሕዝበ ሙስሊሙ የነቃ ተሳትፎ በመጠናቀቁ ለዕምነቱ ተከታዮች እንኳን ደስ አላችሁ።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠቅላላ ምርጫውን በዛሬው ዕለት አጠናቅቋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ መሪውን በድምፁ በመምረጥ ተቋሙን በነፃነት ለመምራት ለዘመናት ሲታገል የቆየ ሲሆን÷ ለውጡን ተከትሎ በተፈጠረው መልካም ዕድል ጠቅላይ ም/ቤቱ በአዋጅ ሊቋቋም ችሏል።

በዚህ መነሻ ሕዝበ ሙስሊሙ በነፃነት ለቀጣይ 5 ዓመታት ተቋሙን የሚመሩ መሪዎችን በነቃ ተሳትፎ፣በብልህነት፣ በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜትና ኃላፊነት፣አካታችና የመላው ሕዝባችንን ሰላምና ሀገራዊ የአብሮነት መንፈስን በሚያጠናክር መልኩ በመጠናቀቁ የተሰማንን ደስታ እንገልጻለን።

በየደረጃው ተቋሙን ለመምራት ኃላፊነትን ከተረከቡት የዕምነቱ አባቶች ጋር ተቀራርበን እንደምንሠራ እናስታውቃለን፡፡

ጠቅላይ ምክር ቤቱ በሰላም፣በማኅበራዊ ልማት እና በሀገር ግንባታ ዙሪያ የጀመረውን በጎ ተግባርን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተስፋ እናደርጋለን።

የሰላም ሚኒስቴር

ጳጉሜ 2/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባ

02/09/2025
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ እና የምክር ቤት ስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ አካሄደ!- ሀሩን ሚዲያ፣ ነሃሴ 27/2017፣ ደቡብ ስቱዲዮየማዕከላዊ ኢ...
02/09/2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ እና የምክር ቤት ስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ አካሄደ!

- ሀሩን ሚዲያ፣ ነሃሴ 27/2017፣ ደቡብ ስቱዲዮ

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ባካሄደው የምስረታ ጉባዔና የስራ አስፈጻሚ ምርጫ ኢማም ሃጂ አብዱልሃዲ አህመድ ቡርሃንን የከፍተኛ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት አድርጎ ሰይሟል።

በዚሁ በመስራች ጉባዔ መሰረት
1- ኢማም ሀጂ አብዱልሃዲ አህመድ - ፕሬዚደንት (ከኡለማዕ)
2- ኡስታዝ ባህጃ አብዱልጀሊል ምክትል ፕሬዚደንት (ከኡለማዕ)
3- ሸህ ኡመር ሙስጠፋ - ጸሃፊ (ከምሁራን)
4- ኡስታዝ ሳዲቅ ወጌቦ አባል ከኡለማዕ
5- ሸይኽ ሙስጠፋ ጀማል አባል ከኡለማ
6- ሸይኽ ሙክታር ሀሰን አባል ከኡለማ
7- ኡስታዝ ናስር ሙሐመድ አባል ከኡለማዕ
8- አባዝናብ አባዋሬ አባል ከስራ ማህበረሰብ
9- ሸይኽ አህመድ አበቴ አባል ከኡለማ
10- ኢስማኢል ሻሜቦ አባል ከወጣቶች
11- ዙበይዳ ሀቢብ አባል ከሴቶች ተመርጠው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

በሌላም በኩል

1-ሸይኽ አብዱልከሪም ሸይኽ በድረዲን
2- ሀጂ ሽፋ ሙሐመድ
3- ሸይኽ አዩብ ሙሐመድ
4- ኡስታዝ ሰኢድ ጅላሉ
5- ሸይኽ ረሻድ ከድር
6- ሸይኽ አብዱሰላም ከድር
7- ሸይኽ ሙስጠፋ ሙሐመድ
8- ሁሴን ሙሐመድ
9- አብዱረሂም ሁሴን
10- መሐመድ ሱልጣን እንዲሁም
11- ሙንተሃ ሀያቱ ክልሉን ወክለው ለፌዴራል ተመርጠዋል።

በምርጫና መስራች ጉባኤው ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የህግና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ጽ/ቤት የህግ ጉዳዮች አማካሪ ወ/ሮ መቅደስ ማቴዎስ፣ የፌዴራልና የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫ አስፈጻሚ አመራሮች፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የስራ ሀላፊዎች፣ የዞንና የልዩ ወረዳ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት ስራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

- ሀሩን ሚዲያ ደቡብ ስቱዲዮ ስፍራው ተገኝቶ ያጠናቀረውን የቪዲዮ ዘገባ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚዲያ

ትንሿ የሞት ደሴት +++++++ ደሴቷ በብራዚል የባህር ዳርቻ እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ትገኛለች።በሳኦ ፓሎ ግዛት ውስጥ የኢታንሃም ማዘጋጃ ቤት አካል ሆና የምትተዳደር ትንሽ  ደሴት ...
31/08/2025

ትንሿ የሞት ደሴት
+++++++



ደሴቷ በብራዚል የባህር ዳርቻ እና በአትላንቲክ ውቅያኖስ ውስጥ ትገኛለች።

በሳኦ ፓሎ ግዛት ውስጥ የኢታንሃም ማዘጋጃ ቤት አካል ሆና የምትተዳደር ትንሽ ደሴት ናት።

የቆዳ ስፋቷም 43 ሄክታር ብቻ ሲሆን፤ ሞቃታማ የአየር ንብረት፣ አለቶች እና ትልልቅ የደን ዛፎች መገለጫዎቿ ናቸው።

ደሴቲቱ በቀድሞ ዘመን ከብራዚሏ ሳኦ ፖሎ ጋር የነበረች ቢሆንም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ቀስ በቀስ ከሳኦ ፖሎ ግዛትነት የተነጠለች ሆናለች።

በዚህም ምክንያት ነበር በደሴቷ ውስጥ የነበሩ አራዊቶች እንደልባቸው መራባት የጀመሩት።

በተለይ ደግሞ ቁጥራቸ በውል የማይታወቅ የተለያዩ መርዛማ እባቦች በደሴቷ መራባት ጀመሩ። ይህም ደሴቲቱ አደገኛ እና የሞት ደሴት አስባላት።

አሁን ላይ "የእባብ ደሴት" በሚል ስያሜም ትጠራለች። እባቦቹ የሰውን ሥጋ ማቅለጥ የሚችል መርዝ ያላቸው ሲሆን፤ በአንድ ሰዓት ውስጥም የሚገድሉ ናቸው።

የብራዚል መንግስት አሁን ላይ ወደ ደሴቷ ማንም ሰው እንዳይገባ ከልክሏል። ይህን ያደረገውም ሰዎች በእባቦቹ ተነድፈው እንዳይሞቱ እንዲሁም ለእባቦቹም ደህንነት ነው ተብሏል።

ፈቃድ ያላቸው ተመራማሪዎች ብቻ የሚጎበኟት እቺ ደሴት በምድር ላይ ካሉት በጣም አደገኛ ቦታዎች አንዷ ሆና ተመዝግባለች።

በዳግማዊት አበበ
+++++++++++++++++++++++


#ኢትዮጵያ #ደሴት #እባብ #ሳኦፖሎ #ቱሪዝም

31/08/2025

Address


Telephone

+251927171974

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስልጤ—ታይምስ/siltie-Times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ስልጤ—ታይምስ/siltie-Times:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share