Adane Yisma Baruda Page/ አዳነ ይስማ ባሩዳ ፔጅ

  • Home
  • Adane Yisma Baruda Page/ አዳነ ይስማ ባሩዳ ፔጅ

Adane Yisma Baruda Page/ አዳነ ይስማ ባሩዳ ፔጅ " ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ::" ፊል 4:13

☞ ዳግመኛ የተወለደ አማኝ!!
☞ የወንጌል አገልጋይ!!
☞ የአንዲት ሚስት ባል!!
☞ የልጅ አባት!!
☞ የመንፈሳዊ መጽሐፍቶች ጸሐፊ!!
☞ ቴዎሎጂ ዲግሪ(EVANGLICAL CHRISTIAN UNIVERSTY)!!
ፔጁን ፎሎው፡ ላይክና ሼር በማድረግ መንፈስንና አዕምሮን የሚገነቡ አስደናቂ መልዕክቶችን ያገኙ ዘንድ እጋብዛችኃለሁ!!

Isaiah 28:7-12 But they also have erred through wine, and through strong drink are out of the way; the priest and the pr...
15/07/2025

Isaiah 28:7-12
But they also have erred through wine, and through strong drink are out of the way; the priest and the prophet have erred through strong drink, they are swallowed up of wine, they are out of the way through strong drink; they err in vision, they stumble in judgment.
For all tables are full of vomit and filthiness, so that there is no place clean.
Whom shall he teach knowledge? and whom shall he make to understand doctrine? them that are weaned from the milk, and drawn from the breasts.
For precept must be upon precept, precept upon precept; line upon line, line upon line; here a little, and there a little:
For with stammering lips and another tongue will he speak to this people.
To whom he said, This is the rest wherewith ye may cause the weary to rest; and this is the refreshing: yet they would not hear.

 ...!!! !!
15/07/2025

...!!!

!!

15/07/2025

"ኑ በመዳን እኛን ምሰሉ!!"
(የዘሪቱ ከበደ መልዕክት)

በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ወደሕይወት የመጣ ሰው ሁሉ ካመለጠበት የጥፋት ጉድጓድ ሌሎችም እንዲያመልጡ ይናገራል። የሰዎችን አቋምና እምነት አክብሮ ወደማይወጣበት ሞት እንዲሸኛቸው የሚያስችለው አሮጌ ማንነት በክርስቶስ ከእርሱና ከእርሷ ተወግዷልና በማይመች ሁኔታና በከፋ ምላሽ ውስጥ ሁሉ "ጌታን ተቀበሉ" እያለ ይናገራል፤ ኑ! በመዳን እኛን ምሰሉ በማለት ወደዘላለም ሕይወት ይጣራል።
"ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው" ዮሐንስ - 1፥12

 #የኤልዛቤል መንፈስ አሰራር በጋብቻ ውስጥ  🙌ኤልዛቤል ማን ነች ? 🔷 ኤልዛቤል የሲዶናውያን ንጉሥ የኤትበአል ልጅ ናት ። ኤልዛቤል ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ የተወለደች ጣኦት አምላኪ ነች ።...
15/07/2025

#የኤልዛቤል መንፈስ አሰራር በጋብቻ ውስጥ 🙌

ኤልዛቤል ማን ነች ?

🔷 ኤልዛቤል የሲዶናውያን ንጉሥ የኤትበአል ልጅ ናት ። ኤልዛቤል ከጣኦት አምላኪ ቤተሰብ የተወለደች ጣኦት አምላኪ ነች ። ኤልዛቤል በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱ ክፉ ሴቶች መካከል አንዷ ነች ።
አክዓብ የእግዚአብሔርን ህግ ተላልፎ ከእግዚአብሔር ህዝብ ካልሆነች ጋለሞታ ሴት የሆነችውን ኤልዛቤልን አገባ ። ኤልዛቤል እና አክዓብ ወደ ንግስና ከመጡ በኋላ ለእስራኤላውያን የሞራልና መንፈሳዊ ውድቀት ምክንያት ነበሩ ።
1ነገ 16:21

👉በብሉይ ኪዳን በአካል ኤልዛቤል የምትባል ሴት ነበረች በአዲስ ኪዳን ግን የኤልዛቤል መንፈስ ሆኖ ተገልጧል በጣም ክፉ አደገኛ አጋንንት ነው።

የኤልዛቤል መንፈስ አሰራር በዛሬይቱ ቤተክርስቲያን ትዳር ላይ ያለው ባህሪያት (The spirit of Jezebel)

* ኤልዛቤል የባልን ራስነት የማትቀበል ሴት ነች ።

1/ “ሚስቱም ኤልዛቤል፦ አንተ አሁን የእስራኤልን መንግሥት ትገዛለህን?
— 1ኛ ነገሥት 20፥7

🔷 በዚህ ክፍል ላይ የሚናገረው ኤልዛቤል ባሏን በንቀት በስድብ ቃል ዝቅ አድርጋ ስትናገር ያሳያል ።

በትዳር ላይ ባልን መናቅ ፤ ማዋረድ ፥ መሳደብ ፥ የኤልዛቤል መንፈስ ባህሪ ነው ።

በጋብቻ ውስጥ የባልን ራስነት አለመቀበል በኤልዛቤል መንፈስ መጠቃትን ያሳያል ። የባልን ውሳኔ ሀሳብ አለመቀበል የዚህ መንፈስ መገለጫ ነው ።

👉በትዳር ላይ ወንድን ሴት ፤ ሴትን ወንድ የሚያደርግ አጋንንት ነው ።
የወንድ ቦታ ላይ ሴትን የሚያስቀምጥ እና ሴትን አንባገነን(ፈላጭ ቆራጭ) አድርጎ እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚያስብል የኤልዛቤል መንፈስ ነው ።

🔷 በዚህ መንፈስ አሰራር ውስጥ የወደቀ ትዳር ባልና ሚስት ቋንቋቸውን ይደበላልቃል ። ቤተሰቡን ባለመግባባትና ግጭት ያውካል ። ዓላማው አንድ ነው ባልና ሚስት መለያየት ልጆች መበተን ነው ።

2/ “ ተነሣ እንጀራም ብላ፥ ልብህም ደስ ይበላት የኢይዝራኤላዊውን የናቡቴን የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ አለችው።”
— 1ኛ ነገሥት 20፥7

🔷 በዚህኛው ክፍለ ደግሞ የተሳሳተ ውሳኔ በማሳለፍ በግፍ የናቡቴን የወይን ቦታ ቀምታ እንደምትሰጠው ይናገራል ።
* ኤልዛቤል ግፈኛ ሴት ነች ።

👉ሴት በጋብቻ ውስጥ የበላይ ሆነው በመታየት የተሳሳተ አመራር በመስጠት ጋብቻን መበጥበጥ የኤልዛቤል መንፈስ መገለጫ ነው ።

* ኤልዛቤል ባልን የምትነዳ ሴት ነች ።

🔷 አክአብም በመንፈሱ ተመቶ በእርሷ ሀሳብ እና ውሳኔ ሲነዳ እና በመንግስታዊ ስራም ሆነ በትዳሩ ላይ በእርሷ ሲመራ እንደነበር የእግዚአብሔር ቃል ይናገራል ። በዚህም ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ክፉ ነገር መጥቶበታል።
1ነገ 20:21

3/ “በእግዚአብሔር ፊት ክፋት ለመሥራት ራሱን እንደ ሸጠ፥ ሚስቱም ኤልዛቤል እንደ ነዳችው፥ እንደ አክዓብ ያለ ሰው አልነበረም።”
— 1ኛ ነገሥት 20፥25

🔷 ሚስት በባል ላይ መሰልጠን ለቤተሰቡ መርገም ነው ።
በዚህ ዘመን በርካታ ትዳሮች በዚህ ክፉ መንፈስ ስር የወደቁ ናቸው ። በዚህ አሰራር ውስጥ ላላችሁ እፀልያለሁ ትዳራችሁ በኢየሱስ ስም ነፃ እንዲወጣ እፀልያለሁ ።

ዛሬ ነፃ መውጣት ይሆናል ፀልዩ ፀልዩ ባለትዳሮች ቤታችሁ ከኤልዛቤል መንፈስ እንዲፈታ አጥብቃችሁ ተቃወሙ ።

በኢየሱስ ስም የኤልዛቤል መንፈስ የተመታ ይሁን !!! አሜን

ሻሎም

11/07/2025

☞ 10 መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንየቶች!

1. ጌታ ኢየሱስ ብቻ አዳኝና አስታራቂ እንደሆነ ስለማምንና ከርሱ ውጪ እንዳልሰብክ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር 1ኛ ቆሮ 1፥23

2. መዳን በጸጋ እንጂ በሰው ጥረት እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ኤፌ 2፥1

3. ልጅነት በእምነት እንጂ በ40 እና 80 ቀን ጥምቀት እንደማይገኝና ጥምቀት ያመኑ ሰዎች ብቻ የሚፈጽሙት ስርአት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር። ዮሐ 1፥12

4.የጌታ እራት(ቁርባን) የሞቱ መታሰቢያ ከክርስቶስና ከአማኞች ጋር ህብረት የምናደርግበት ስርአት እንጂ ሀጥያትን የሚያስተሰርይ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ማቴ 26፥26

5. እግዚአብሔር ኃጥያታችንን ለማስተስረይ በልጁ ደም ኪዳን እንደገባ እንጂ ለየትኛውም ፍጡር ቃልኪዳን እንደገባና የፍጡርን ምልጃ እንደሚቀበል መጽሐፍ ስለማያስተምር ዕብ - 8

6. ስግደት ለእግዚአብሔር እንጁ በእጅ ለተቀረጸ ምስል (መስቀል ታቦት ስዕል) እንድንሰግድ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ሐዋ 7፥29

7.መዝሙር የሚገባው እግዚአብሔር እንጂ ፍጡራን እንዳልሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር መዝ 9፥11

8. በየቀኑ በልባችን ጌታ ኢየሱስ ብቻውን እንዲነግስ እንጂ ቀን ተመድቦላቸው ፍጡራን እንዲነግሱ መጽሐፍ ቅዱስ ስለማያስተምር ቆላ 2፥16

9.ጸሎት በኢየሱስ ስም ወደእግዚአብሔር እንጂ ወደ ፍጡራን እንዳልሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ዮሐ 16፥24

10. ሰዎች በህይወት ዘመናቸው በኢየሱስ በማመናቸው ምክንያት እንደሚድኑ እንጂ ከሞቱ በኋላ የሚኖር ፍትሀት እንደማይጠቅም መጽሐፍ ቅዱስ ስለሚያስተምር ዮሐ 3፥16

አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፤ እኔም እጅግ ተቸገርሁ።
መዝ 116፥10

እባካችሁ ሁላችሁም ሼር!!

11/07/2025

ምክር ፤ ተረጋጋ!

ሥራ ቦታ በዕረፍት ሰዓቴ ነው የምጽፍልህ። ለአዲስ ክርስቲያን የሚሆን ኬክና ንፍሮ ላካፍልህ አልችልምና ያንን ሳይሆን ለሩቅ ተጓዥ ስንቅ ነው የምተውልህ። ምክር ነው የምመክርህ። ምክሬም በአጭር ሁለት ቃል፥ ነው።

ያኔ ለጥቂት ወራት ሙስሊም የሆነህ ጊዜ እንደ ዑስታዝ ነገር ሲያደርግህ የነበረ ሰሞን፥ ስለ ማታውቃቸው ወይም በጣም ጥቂትና በአባሮሽ ያገኘሃቸው ነገሮች ላይ ነበር የምትናገረውና ዝም እንድትል ሲነግሩህ ዝም አልክ። እንዲያውም ጨርሶውኑ አቆምክ፤ ደግ አደረግህ።

ግን ዝም ማለት ስለማትችል ነው መሰለኝ ሌላ መናገር የምትችልበትን ሃይማኖት ቀየርክና እዚያም የሰማሃቸው ነገሮች ብቻ ላይ እየተናገርክ (ተናጋሪ ሳትሆን አናጋሪ እየሆንህ) ብዙ አስቆጣሃቸው፤ ብዙም አበላሸህ።

አሁን የኛ ተራ ነው። እኛጋ ይህኛው ሁለተኛ ዙርህ መሰለኝ። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ። ስለ እኛ የአሁኑ ዘመን ትግል የምታውቅ አይመስለኝም። ለዚህ ነው የምመክርህ። መቼም ምክር የምትሰማ ትመስለኛለህ።

አውሮፕላን ስንሳፈር ከጉዞ መጀመር በፊት የሚነገሩ ማሳሰቢያዎችና ማስጠንቀቂያዎች አሉ። ይህ የሚነገረው በተለይ አደጋ ቢከሰት ምን ማድረግ እንደሚገባ እንዲታወቅ ነው። ከቀበቶ መታጠቅ አንስቶ እስከ ውኃ መንሳፈፊያ ምንም ሳያስቀሩ ይነግሩናል።

በክርስትናም እንዲሁ ነው። እኔ በክርስቶስ ሳምን የተነገሩኝ ነገሮች አሉ። 'በቃ አምነሃል፤ ድነሃል፤ ተደሰት!' ብለው አልለቀቁኝም። ለማደግ ማድረግ ያለብኝን ነግረውኛል። ያኔ ጊዜው የስደት ነውና ስለ ዋጋ መክፈል አስተምረውኛል። ቃሉን እንዳነብብና እንዳጠና፥ በጸሎት እንድተጋ፥ ከቅዱሳን ኅብረት እንዳልጠፋ፥ እምነቴን ላልዳኑ እንዳካፍል አስተማሩኝ። ስለ ደቀ መዝሙር ምንነት አብርተውልኛል። 'ጉዞው ቀላል አይደለም፥' ብለውኛል። ልክ ነበሩ። ቀላል አልነበረም።

ወደ ቤቱ እንኳን ደህና መጣህ። የመጣህበት ጊዜ ውስብስብ ጊዜ ነው። ቢሆንም የጌታ ቃል በእጅህ፥ የጌታ መንፈስ በውስጥህ፥ የታመኑ ቅዱሳን በዙሪያህ ካሉ ታድጋለህ፤ ትበስላለህ። ያለዚያ ግን ትመስላለህ፤ ትቀነጭራለህ።

#እኛጋ አሁን ተቀምጠው ሳይማሩ ቆሞ ማስተማር በሽ ነው። ግን ልክ አይደለም። በነገራችን ላይ፥ ይህ ሳይማሩ ማስተማር ወይዘሮ ብርቱካን ጣሰውንም ይመለከታል። አደራ ሳትማር አስተማሪ ለመሆን አትሞክር።

#እኛጋ አሁን ነቢይ ነቢይ መጫወት የአዘቦት ልማድ ነው። እነዚህ፥ 'ነቢይ ነኝ!' የሚሉ ሰዎች በቃሉ ውስጥ የተጻፉትን ነቢያት ቢያዩ ኖሮ አፈር ላይ ተቀምጠው ይጸጸቱ ነበር። እነዚህ ነቢያት ሳይሆኑ መንፈሳዊ ሲራራ ነጋዴዎች ናቸው። በነገራችን ላይ፥ ይህ ሲራራ ነጋዴነት ወይዘሮ ብርቱካን ጣሰውንም ይመለከታል። ብርቱካን ነጋዴ ብቻ አይደለችም፤ ተራጋሚ ሴት ናት። የቲ. ቢ. ጆሹዋ የጥንቆላና የሟርት መንፈስ ወራሽ ሴት ናት። ቲ. ቢ. ጆሹዋ የሚቃወሙትን ሰዎች ፎቶ በወስፌ እየወጋ የሚራገም ተራጋሚ ነበረ። የአገራቸው ጥንቆላ ነው። እግረ መንገዴን እንድትጠነቀቅ ነው።

#እኛጋ ሐዋርያ ሐዋርያ መጫወት ልክ ጆተኒ እንደ መጫወት ነው። ሐዋርያ ማለት የተላከ ማለት ነው። ማንም ሳይልካቸው ሐዋርያ ብሎ ራስን መሾም ቱባ ባለ ሥልጣንና መሆንና ረብጣ ደመወዝ ማግኛ ነው።

ሐዋርያው ጳውሎስ በክርስቶስ እንዳመነ ወዲያው ሊሰብክና ሊያስተምር ጀመረ። ግን እ! እ! የጌታ አሳብ ሌላ ነበር። ከጌታው ጋር ለብቻው ሳምንታትና ወራት ሳይሆን ዓመታት አሳለፈ። ዓመታት። አንተም ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ጊዜ ውሰድ።

20/06/2025

Address

Hossana

Telephone

+251932655168

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Adane Yisma Baruda Page/ አዳነ ይስማ ባሩዳ ፔጅ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Adane Yisma Baruda Page/ አዳነ ይስማ ባሩዳ ፔጅ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share