Discover South Ethiopia

Discover South Ethiopia The Land of Diversity and Peace❗

👉https://www.facebook.com/profile.php?id=61550826170135

👉South Ethiopia❗

አርባምንጭ : ደግ ልጇን አጥታለች   | በአርባምንጭ ከተማ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚታወቀው  ወጣት ተወዳጅ መኮንን ለድሆች የመኖሪያ ቤት እንዲሁም ሙሉ የህክምና ወጪ በመሸፈን አ...
10/07/2025

አርባምንጭ : ደግ ልጇን አጥታለች

| በአርባምንጭ ከተማ በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች የሚታወቀው ወጣት ተወዳጅ መኮንን ለድሆች የመኖሪያ ቤት እንዲሁም ሙሉ የህክምና ወጪ በመሸፈን አርባምንጭ ሁሌም የምታመሰግነው ወጣት በድንገት ማረፉ ተሰምቷል።

ለቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመዶቹ መጽናናትን እንመኛለን።

የአርባምንጭ በጎ ፍቃደኞች ማህበር

የወላይታ ዞን ምክር ቤት ባደረገው 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፦ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በም/ማዕረግ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፤ዶ/ር አማሬ አቦታ የወላይታ ዞን ...
08/07/2025

የወላይታ ዞን ምክር ቤት ባደረገው 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ፦

ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በም/ማዕረግ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፤

ዶ/ር አማሬ አቦታ የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ ፤

አቶ ተስፋሁን ታዲዮስን የፓለቲካ ስበት ማዕከልና የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አድርጎ ሾሟል።

የክልል ክለቦች ሻምፕዮና ምድብ ድልድል
04/07/2025

የክልል ክለቦች ሻምፕዮና ምድብ ድልድል

በክልሉ እየተደረገ ያለው የአንድነት መድረክ ልምድ የሚወሰድበት ነዉ ፦ አቶ አደም ፋራህ ሰኔ 24/2017 ዓ.ም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ያለው  የሠላም፣ የአን...
01/07/2025

በክልሉ እየተደረገ ያለው የአንድነት መድረክ ልምድ የሚወሰድበት ነዉ ፦ አቶ አደም ፋራህ

ሰኔ 24/2017 ዓ.ም

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ያለው የሠላም፣ የአንድነት እና የልማት ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።

በወቅቱ የተገኙት የኢፌድሪ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ክልሉ በታሪክ በባህልና በተፈጥሮ ፀጋ የታደለ መሆኑን ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያ ብዝሃ ማንነት የሚኖሩባት መሆኑን የገለፁት አቶ አደም ፋራህ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙት ብሔር ፣ብሔረሰቦች ይህንኑ የሚያሳዩ ናቸው ብለዋል።

በክልሉ 32 ብሔሮች ፣ብሔረሰቦች እንደሚገኙ የገለፁት አቶ አደም ፋራህ ክልሉ ፣በተመሰረተ አጭር ጊዜ ውስጥ፣ ከነባር ክልሎች ጋር መሰለፍ መቻሉን ገልጸዋል ።

በክልሉ ያሉት የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ እምቅ ፀጋዎች ክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የብልጽግና ተምሳሌት መሆኑን ገልጸው፤ ለም መሬቱ፣ የተፈጥሮ ሀብቱ እና ታታሪ ሕዝቦቹ የልማት ምሰሶ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በፖለቲካ መስክ የክልሉን ተቋማት አደራጅቶ ወደ ሥራ በማስገባት፣ የሕዝብ ንቅናቄ እና የአመራር አንድነት የሚያመጡ ተግባራት መከናወናቸውን ለክልሉ ትልቅ አቅም ነው ብለዋል።

በዚህም ፣በክልሉ እየተከናወኑ ያሉት የልማት ስራዎች አንዱ ማሳያ መሆናቸውን አቶ አደም ፋራህ ጠቁመዋል ።

በኢትዮጵያ ህብረ ብሔራዊ አንድነት ለማጠናከር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሰረት ነዉ ያሉት አቶ አደም ፋራህ ፣በቀጣይም በክልሉ ህዝብ ዘንድ ያለዉን አብሮነት በዘላቂነት ለማስቀጠል መስራት እንደሚገባም አስረድተዋል ።

በክልሉ ያሉት የጋራ ማንነትቶች እንዲጎለብቱ የተጀመሩት ስራዎች መጠናከር እንዳለባቸውም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል ።

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የመደመር ፍልፍስና ዉጤት በሀገሪቱ ሁለንታዊ ብልጽግና እንዲረጋገጥ ስለማስቻሉ የገለፁት አቶ አደም፣ በክልሉም ይህንኑ ማጠናከር እንዳለበት አስገንዝበዋል ።

በክልሉ የተጀመሩ የገዢ ትርክት ዕሳቤዎች እንዲጠናከሩ የኢፌድሪ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል ።

በቀጣይ በክልሉ ያለዉን ታሪክ ባህልና ቋንቋ እንዲሁም የተፈጥሮ ፀጋ ለጋራ ብልጽግና መጠቀም እንደሚገባም አስረድተዋል ።

ጉባዔው ''ጠንካራ ክልላዊ አንድነትና አብሮነት ለዘላቂ ሠላምና ብልጽግና" በሚል መሪ ቃል ተካሂዷል ።

በጉባኤው ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ በተጨማሪ ፣የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ተሳታፊ ሆነዋል ።

ቀጣዩ ምዕራፍ እስካሁን በተፈጠረው መግባባት ላይ የሚገነባና በወንድማማችነት እሴት ላይ የሚፀና መሆኑን አምኖ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ተብሏል ።

እንዴት ማመን እችላለሁ። ዉድ ወንድሜ አሊ ከድር ዛሬ ጠዋት አብረን ስብሰባ ዉለን ለምሳ ተለይተን ከሰዓታት በኃላ ሲያጣህ አሊዬ። በጣም ልብ ሰባሪ። የቀድሞ የሲልጤ ዞን ዋና አስተዳዳርና የማ...
28/04/2025

እንዴት ማመን እችላለሁ።
ዉድ ወንድሜ አሊ ከድር
ዛሬ ጠዋት አብረን ስብሰባ ዉለን ለምሳ ተለይተን ከሰዓታት በኃላ ሲያጣህ አሊዬ። በጣም ልብ ሰባሪ።

የቀድሞ የሲልጤ ዞን ዋና አስተዳዳርና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ አሊ ከድር ባጋጠማቸው እጅግ ልብ ሰባሪ ድንገተኛ የመኪና አደጋ ህልፈተ ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን ለመግለፅ እወዳለሁ።

ነፍስህ በገነት ከደጋጎች አጠገብ ያሳርፍ ፈጣሪ።
ለመላዉ ቤተሰቦችህ፣ ሥራ ባልደረቦችህ እና ጓደኞችህ መጽናናትን ተመኘሁ።

አቶ ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር

ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ቁልፍ ጉዳዮች እንዲሁም በፓርቲ ተኮር ጭብጦች ላይ ለመጪዎቹ ሁለት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።
25/04/2025

ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ቁልፍ ጉዳዮች እንዲሁም በፓርቲ ተኮር ጭብጦች ላይ ለመጪዎቹ ሁለት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቢሮ ጋር በመሆን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ማዕድ አጋራየክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ከክልሉ ፋይናንስ ቢ...
19/04/2025

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቢሮ ጋር በመሆን ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ማዕድ አጋራ

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመሆን በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚገኙ ከ400 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ማዕድ አጋርቷል።

በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ መረዳዳት ለአብሮነትና ለአንድነት እጅግ ወሳኝ በመሆኑ ባህል ሊናደርገው ይገባል ብለዋል።

የለውጥ መንግስት ከመጣ በኃላ በመረዳዳትና በመደጋገፍ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ነው ያሉት አቶ ተፈሪ ይህን በጎ ተግባር ባህል አድርገን በማስቀጠል አቅማችን የቻለነውን ማድረግ ይጠብቅብናልም ብለዋል።

ፓርቲያችን ብልፅግና ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ያሉት አቶ ተፈሪ ፓርቲው የሚመራው መንግስት የዜጎችን ህይወት ለመለወጥ አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

መልካም ነገሮችን በክልላችን በማጠናከር እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ መስራት እንዲሁም የእኛ እገዛ ለሚፈልጉ ወገኖችን መልካምነትንና በጎነትን ማሳየት ይገባል ብለዋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱፄ ታምሩ በበኩላቸው ትንሳኤ በዓልን ስናከብር በጎነትንና መልካምነትን ለሌሎች በማሳየት ሊሆን ይገባል።

ሁሉም ህብረተሰብ ክፍል ካለው ሌላው በማካፈል በዓሉን በጋራ ማክበር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ዱፄ አቅም የሌላቸውን የመደገፍ ስራ ባህልን ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ጋር በመተባበር ከ400 በላይ አቅመ ደካሞች ማዕድ ማጋራት ፕሮግራም መካሄዱንም አስታውቀዋል።

በየአካባቢው ያሉ አቅም ደካምችንና አረጋዊያን መጠየቅና መደገፍ በምድራዊ ህይወት ብቻ ሳይሆን ከፈጣሪ ዘንድም ዋጋ ያለው መልካም ተግባር በመሆኑን ማጠናከር ይገባናል ሲሉም አሳስበዋል።

ሁሉም በየአካባቢው መልካም ተግባር በመፈጸም አብሮነትንና ፍቅርን እንዲያሳዩ ጥረ በማቅረብ በዓሉ የሠላምና የፍቅር እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱሰ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!   ብርሃነ ትንሣኤው ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ የተሻረበት፤...
19/04/2025

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱሰ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!

ብርሃነ ትንሣኤው ሞተ ሥጋና ሞተ ነፍስ የተሻረበት፤ መርገም የተወገደበት፤ ነፃነት የተገኘበት በመሆኑ፤ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት የሚከበር ደማቅ በዓል ነው፡፡

በዓለ ትንሣኤው የዕርቅ፤ የይቅርታና የሰላም ተምሳሌትም ነው፡፡ በሰውና በፈጣሪ መካከል የነበረ የጥል ግድግዳ በአምላክ ይቅር ባይነት የፈረሰበት፣ ዕርቅና ሰላም ወርዶ አዲስ የምሕረት ምዕራፍ የተከፈተበት በመሆኑ በዓሉ ስከበር ቂም፤ ቁርሾና በቀልን በይቅርታ በመሻገር የምከበር ነዉ።

ክርስቶስ ለሰው ልጆች ድኀነትና ፍጹም ሰላም ሲል ጽኑ መከራና ስቃይን ተቀብሎ ቤዛ የሆነበትን ሚስጢር በማሰብ የሚከበረው በዓል ፤ ሰላም ከፈጣሪ የተቸረን ፀጋ መሆኑን አውቀን፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም ትብብራችንን የምናጠናክርበት አጋጣሚ መሆን ይኖርበታል፡፡

ብርሃነ ትንሣኤው የተስፋ፤ የፅናት እና የድል በዓል ነው፡፡ ክርስቶስ በሰሞነ ሕማማቱ የመከራን ቀንበር ተሸክሞ፤ በፈተና በመፅናት የተስፋውን ቃል ይጠበቅ ለነበረው አዳም ድኅነትንና ዘላለማዊ ህይወትን ያጎናፀፈበት የፅናትና የድል ተምሳሌት ነው፡፡

በዓለ ትንሣኤውን ስናከብር ከመጓተት ይልቅ አብሮ መቆምን፤ ከመገፋፋት ይልቅ ትብብርን፤ ከመለያየት ይልቅ ህብረትና አንድነትን ይበልጥ አጠናክረን፤ ፈተናዎችን በፅናት በመሻገር ለክልላዊና ሀገራዊ የሰላምና የልማት ትልሞቻችን በጋራ በመረባረብ የኢትዮጵያን የመንሰራራት ጎዞ ለማፅናት በመነሣት ሊሆን ይገባል፡፡

የክርስቶስ ትንሣኤ የፍቅርና የእውነት ኃያልነት የተገለጠበት በመሆኑ ብርሃነ ትንሣኤውን ስናከበር፤ በጥላቻና በሀሰት ዘመቻዎች ሳንጠለፍ ፍቅርን በመስበክ፤ አብሮነትንና አንድነትን በማጠናከር እና የጋራ ሰላማችንን የበለጠ በመጠበቅ መሆን ይኖርበታል፡፡

በዓሉ ከክርስቶስ የፍቅርና የሰላም መንገድ ትምህርት በመውሰድ በክልላችን ለክልላዊ የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት ራዕያችን ስኬት አብረን በመቆም ማስፈን የቻልነውን ሰላም ለማፅናት ከመቼውም ጊዜ በላይ በጋራ የምንነሣበት ሊሆን ይገባል፡፡

ትንሣኤ የፍጹም ትህትናና የመታዘዝ ተምሳሌት ነው፡፡ በዓሉን ስናከብር ክርስቶስ ዓለምን የማዳን ታላቅ ገቢር በትህትና መፈፀሙን በማሰብ፤ በየተሰማራንበት መስክ ሀገራችንና ህዝባችንን በፍጽም ትህትናና ቅንነት ለማገልገል በመነሳት እንዲሆን አደራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

አንድነትና ኅብረት፤ መደጋገፍና መረዳዳት በክርስትና ልዩ ስፍራ እንደሚሰጠው የእምነቱ አስተምህሮ ያስረዳል፡፡ በመሆኑም በዓሉን በትንሣኤ ልቦና ተነሥተን የመተሳሰብ፤ የመጠያየቅና የመደጋገፍ እሴቶችን በማንገብ፤ ያለንን ለለሌው በማካፈል፤ አቅመ ደካሞችንና ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በመደገፍ እና ራስን ለበጎ ተግባራት በማዘጋጀት ማክበር ይጠበቅብናል፡፡

በተለይ ትንሣኤው ለመልካም ስራ እንድንነሳ የሚያደርግ መሆኑን ተረድተን፤ መረዳዳቱና መደጋገፉ በዕለተ ፋሲካው ሳይገደብ ተባብረን በያለንበት የተቸገሩ ወገኖችን በዘላቂነት ራሳቸውን እንዲችሉ ለማስቻል በመስራት ማክበር ይገባናል፡፡

በድጋም መልካም የትንሣኤ በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈአዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 20ኛ መደበ...
18/03/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 20ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎቸ ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የኢንቨስትመንት አሥተዳደርን ለማስፈፀም በወጣ ደንብ፣ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ ሲለቀቅ የሚከፈል ካሳ እና መልሶ ማቋቋምን በተመለከተ በወጣ መመሪያ እንዲሁም በክልሉ ማዕከላት የሚገነቡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሕንጻ ግንባታን በተመለከተ የቀረበ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቷል፡፡

በቀረቡ ረቂቅ ደንቦችና መመሪያዎች ላይ ተወያይቶ በየዘርፉ የሚሠሩ ሥራዎችን በሕግ ማዕቀፍ በመምራትና በአሠራር በመደገፍ ለተሻለ ውጤት ለማብቃት የሚያስችሉ መሆኑን በማመን ከነማሻሻያቸው አፅድቋል፡፡

በክልሉ ማዕከላት የሚገነቡ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሕንጻ ግንባታ በተመለከተ በቀረበ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በመወያየት አቅጣጫ ማስቀመጡን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

እንዲሁም በክልሉ የማዕድን ልማት ዘርፍ ያሉ አበረታች ሥራዎችን አጠናክሮ የግሉን ዘርፍ በስፋት በማሳተፍና ክልሉ ባለው እምቅ ዐቅም ልክ በማልማት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በቡና ጥራት አጠባበቅና አቅርቦት ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛልየደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር አስተ...
16/03/2025

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በቡና ጥራት አጠባበቅና አቅርቦት ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር አስተግባሪ ግብረ ሀይል የ2017 ግማሽ ዓመት የቡና ጥራት አጠባበቅና አቅርቦት ዙሪያ በወላይታ ሶዶ ከተማ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የለውጡ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲውን ከአንድ ዘርፍ ወደ ብዝሃ ዘርፍ ሲያሻግር፥ ግብርናን ዋነኛ የኢኮኖሚው መሠረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የክልሉ መንግስትም ግብርናን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ የክልሉ ኢኮኖሚ መሠረት በማድረግ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ የኤክስፖርት ምርቶች በማምረት የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ የክልሉን እምቅ አቅም በመለየትና በመጠቀም የቡና እና ቅመማ ቅመም ምርት ጥራትና ምርታማነት በማሳደግ ወደ ውጪ መላክ ቀዳሚ ተግባር በማድረግ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ክልሉ የይርጋጨፌ፥ የአማሮ እና ሌሎችም ባለ ልዩ ጣዕም ጥራት ያላቸው ቡናዎች የሚበቅሉበት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ዘርፉ የውጪ ምንዛሬ በማስገኝት ለሀገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ብለዋል።

የቡና ማሳን በማስፋትና በመጠንና በጥራት ተወዳዳሪ መሆን የሚችል ቡና በማምረት አርሶ አደሩ ባመረተው ልክ ተጠቃሚ መሆን እንዲችል መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።

ታአማኒ፥ በገበያ ተፈላጊና ተወዳዳሪ የሆነ ጥራት ያለው ቡና በደቡብ ኢትዮጵያ አርሶ አደሮች በስፋት እንዲመረት የቡና ጥራትና ግብይት ቁጥጥር አስተግባሪ ግብረ ሀይሉ ተጠናክሮ መስራት አለበት ብለዋል።

በቅርቡ በኢትዮ ቻይና የልማት ትብብር በተፈጠረ የንግድ ትስስር ጥራት ያለው የይርጋጨፌ ቡና ወደ ቻይና ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀው፥ ተሞክረው ወደ ሌሎች ቡና አምራች አካባቢዎች መስፋት አለበት ብለዋል።

በምክትል ርዕለ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ ( ዶ/ር) በበኩላቸው፥ ክልሉ ቡናን ኤክስፖርት በማድረግ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

አክለው የቡና ምርት በሁሉም ስነምህዳሮች የሚበቅል ብቻ ሳይሆን በእርሻ ላይ ለሌሎች የግብርና ስራዎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሰብል መሆኑን ተናግረው፥ በክልሉ በ2017 25 ሺህ 884 ቶን ቡና ለገበያ መቅረቡን አስታውቀዋል።

#ርዕሰመስተዳድርጽቤት

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ክልል አቀፍ የአመራር የዉይይት መድረክ እያካሄደ ነዉመጋቢት 6/2017 ዓ.ም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በቀ...
15/03/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ክልል አቀፍ የአመራር የዉይይት መድረክ እያካሄደ ነዉ

መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በቀጣይ ወራት በሚከናወኑ ዕቅድ ዙሪያ ክልል አቀፍ የከፍተኛ አመራር የዉይይት መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል ።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ጥላሁን ከበደ ፣የዉስጥ አንድነትን በማጠናከር የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።

ለዚህም በቀጣይ ጊዜያት የሚከናወኑ ተግባራትን በአግባቡ በመምራት ያሉትን ሁሉንም አማራጮች መጠቀም እንደሚገባም ነዉ ርዕሰ መስተዳደሩ የገለፁት ።

መድረኩ በክልሉ በቀጣይ ሶስት ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ስነድ በክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ ቀርቦ ዉይይት የሚደረግ መሆኑ ተመላክቷል።

በመድረኩም ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ፣የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አለማየሁ ባዉዲን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል ።

ከክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ተጨማሪ ክልላዊና ሃገራዊ መረጃዎችን ለማግኘት ተከታዮቹን ገፆቻችንን ይጎብኙ
Follow South Ethiopia Government Communication pages for more information
**
facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61550826170135
***
Website http://www.segocom.gov.et/
**
Twitter/X https://x.com/Segovcom
*
YouTube https://www.youtube.com/
*
Tik Tok https://www.tiktok.com/

Address

Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Discover South Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share