13/11/2021
‼ #የአሜሪካኖች ጩኸትና ጫና መሠረታዊ ዓላማው #በጅቡቲ ያለውን #የቻይና የጦር ሰፈር እንዲዘጋ ማድረግ ነው......
#በቻይና እና #አሜሪካ መካከል የሚካሄደው ማሳያ አሁን #በኢትዮጵያ እያካሄዱት ያለው የተልዕኮ ጦርነት ነው ‼
በአፍሪካ ቀንድ የሰይጣን መልዕክተኛ የሆነው ሰውዬ ጠዋት ማታ ወደ ኢትዮጵያ የሚመላለሰው፤ የኢትዮጵያ ወዳጆች የሆኑትን ቱርክ እና የተባበሩት የአረብ ኤምሬትስን አቋም ለማስቀየር የሚታትረው፣ የአሜሪካ ተላላኪ የሆኑት ሳውዲ አረቢያ እና ግብፅ፣ እንዲሁም የእነሱ ተላላኪ የሆኑት ሱዳን እና ኬኒያ የሚሯሯጠው ለምንድነው? መልሱን ትላንት በጅቡቲ የአሜሪካን የጦር አዛዥ ስለ ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት ላይ ታገኙታላችሁ።
የአሜሪካኖች ጩኸትና ጫና መሠረታዊ ዓላማው በጅቡቲ ያለውን የቻይና የጦር ሰፈር እንዲዘጋ ማድረግ ነው። የአሜሪካው የጦር አዛዥ ትላንት የተናገረው ነገር ሙሉ በሙሉ ባዶ ቀረርቶ መሆኑን የምታውቁት ከጎናቸው የሚገኘው የቻይና የጦር ሰፈር 10,000 ወታደሮችን መያዝ የሚችል ሲሆን የራሱ ሆነ ወደብ እና Naval Base አለው። በአንፃሩ የአሜሪካ የጦር ሰፈር 4,000 ወታደሮችን የመያዝ አቅም አለው። ይህም ሆኖ አሜሪካኖቹ የሚፈሩት ከጎናቸው ካለው የቻይና የጦር ሰፈር ይልቅ በምዕራባዊ ቻይና ከሚገኙት 100 የሚጠጉ የሮኬት ማስወንጨፊያዎች የሚተኮሰውን "Hypersonic Missile" ነው።
የቻይና Hypersonic ሚሳኤል በሰዓት 4ሺህ ማይል የሚመዝገዘግ ሲሆን ከቻይና ቤጂንግ ተነስቶ አሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ ለመድረስ 100 ደቂቃዎች (1 ሰዓት ከ40 ደቂቃ) ብቻ ነው። በቅርቡ ቻይና ይህን እጅግ ዘመናዊ የሆነ የጦር መሣሪያ ሙከራ አድርጋለች። ሚሳኤሉ የምድርን ወገብ በሚገርም ፍጥነት ከዞረ በኋላ ኢላማውን መምታቱን በከባድ ድንጋጤ ውስጥ ሆነው የነገሩን የአሜሪካ ኢታማዦር ሹም ናቸው። ቻይና Hypersonic Missile ሙከራን በተሳካ ሁኔታ ያደረገችው የአሜሪካ ጦር በተመሳሳይ መንገድ ያደረገው ሙከራ በከሸፈ ማግስት ነው።
የአሜሪካው የጦር ጄኔራል እንደተናገሩት አዲሱ የቻይና Hypersonic Missile በዓለም ላይ የመጀመሪያው ከመሆኑም በተጨማሪ በምድር ወደብ ላይ ሲሽከረከር ከላይ ወደታች ገላምጧቸው ካለፉት ሀገራት አንዷ አሜሪካ መሆኗ በ1957 ሩሲያ የመጀመሪያውን ሳተላይት ወደ ህዋ ስታመጥቅ የተፈጠረውን አይነት ድባብ በአሜሪካ ነጩ ቤተመንግሥት እና ፔንታጐን ውስጥ ዳግም መፈጠሩን የራሳቸው ሚዲያዎች ሳይቀሩ በስፋት ዘግበውበታል።
ዋናው ቁምነገር ከ60 አመት በፊት ለቀዝቃዛው ጦርነት መነሻ የሆነው በአሜሪካ እና ሩሲያ መካከል የነበረው የጦር መሣሪያ እሽቅድድም ዛሬ በአሜሪካ እና ቻይና መካከል ተከስቷል። ሩሲያ እና አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ሲያካሂዱት የነበረውን "Proxy war" ዳግም በኢትዮጵያ እያካሄዱት ይገኛሉ። በቅርቡ ጠ/ሚ አብይ አህመድ እንደተናገሩት 2ኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረው ናዚ ፖላንድን ከመውረሩ የተወሰኑ አመታት ቀደም ብሎ ነው። በተመሣሣይ 2ኛው ቀዝቃዛ ጦርነት የተጀመረው ከስድስት አመት በፊት በፈረንጆች አቆጣጠር በ2015 ነው።
ይህ በቻይና አሜሪካ መካከል የሚካሄደው ቀዝቃዛ ጦርነት ማሳያ ደግሞ አሁን በኢትዮጵያ እያካሄዱት ያለው የተልዕኮ ጦርነት ነው። ችግሩ የዶ/ር አብይ ከቻይና መንግስት ይልቅ ፊቱን ወደ ሩሲያ እና ቱርክ ማዞሩ ላይ ነው። አሜሪካኖች በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እና ግፊት የሚያቆሙት እኛ ስንሸነፍ ወይም የእነሱ ተላላኪዎች ስንሆን ብቻ ነው። ዳግም የኢምፔሪያሊስቶች ተላላኪ ከመሆን ይልቅ ጓዛችንን ጠቅልለን ከቻይናዎቹ ጋር መጣመር እና አይቀሬውን 3ኛው የዓለም ጦርነትን ቀድመን እንጀምረው።
https://youtu.be/xyaq7S05HQs
በፌስቡክ የማይለቀቁ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት በዚህ የቴሌግራም ቻናል በመግባት ይመልከቱቨ
https://t.me/joinchat/g9j2Vfso_XhiNWZk