Desalegn Asmare

  • Home
  • Desalegn Asmare

Desalegn Asmare ሳያውቁኝ በወሬ በመነዳት፡ እያወቁኝ በምቀኝነት የሐሰት ወሬ የሚያወሩብኝን ሁሉ፡ ከተፈጥሮ ደካማነትና በስንፍናቸው ከሚጭወትባቸው ድንቁርና እግዚያብሔር እንዲያድናቸው እመኝላቸዋለሁ፡፡

ከ አቤ ጉበኛ የተወሰደ

27/05/2025

"የምድሪቱን ሞኝ ፍለጋ"!!
💫⚜️💫

አንድ ሰው ለመሞት በሚያጣጥርበት ሰዓት የመጨረሻ ኑዛዜ እንዳለው ተጠይቆ ወንድ ልጁን እንዲጠሩለት ያዛል። ወንድ ልጁም ወደ እሱ በቀረበ ጊዜ እንዲህ አለው:- «ልጄ ሆይ ከፊት ለፊትህ ያስቀመጥኩት መቶ መሐለቅ ወርቅ ነው፡፡ ይኸን ወርቅ ትወስድና በዚህ ምድር ላይ እጅግ ሞኝ ሰው ያጋጠመኸ ዕለት ለእሱ ስጠው። ይኸ አደራዬ ነው» በማለት ይሞታል።

ልጁም በአባቱ ኑዛዜ መሠረት ይኸን ወርቅ ተሸክሞ የምድሪቱን ሞኝ ፍለጋ ሲዞር ይከርምና አንድ ቀን አንዲት ከተማ ይደርሳል። በዚያች ከተማም ሕዝብ የተሰበሰበበት አደባባይ ይመለከትና ተጠግቶ የሚሆነውን ሲጠይቅ የሃገሪቱ ሚኒስትር ንጉሠ ነገሥቱ ስላዘነበት አንገቱን ተቆርጦ እንዲሞትና በእሱም ሬሣ ላይ አዲሱ ሚኒስትር እንዲራመድ ስላዘዘው ይኸው ሥርዓት የሚፈፀምበት ዕለት ነው ይሉታል፡፡

ወጣቱም ከሕዝቡ ጋር ተቀላቅሎ የሚሆነውን ሲጠብቅ ንጉሡን ያሳዘነው ሚኒስትር በወታደሮች ተከቦ በሕዝቡ ፊት ይቆምና አንገቱን አስጐንብሰው በሰይፍ ሲቆርጡት ይመለከታል፡፡ ይኸም ብቻ አልነበረም። አዲሱ ሚኒስትር ደግሞ በፈገግታ ተሞልቶ አንገቱ ተቆርጦ የወደቀውን ሚኒስትር ሬሣ ተራምዶ ሲያልፍ ሕዝቡ በዕልልታና በጭብጨባ ያጅበዋል። ይኸን ጊዜ ወጣቱ ወደ አዲሱ ሚኒስትር ሲገሰግስ ሄዶ የተሸከመውን መቶ መሃለቅ ወርቅ ተረከበኝ ይለዋል።

አዲሱ ሚኒስትር በነገሩ ግራ ተጋብቶ:- «በእርግጥ በእኔ ሹመት ተደስተህ ነው ይኸን ሁሉ ወርቅ የምትሰጠኝ?» ቢለው «የለም! አባቴ በኑዛዜው ሰዓት በዓለም ላይ እጅግ ሞኝ ሰው ፈልገህ ይኸን ወርቅ ስጥልኝ ባለኝ መሠረት ነው የምሰጥህ..» ይለዋል። ሚኒስትሩ ግራ ተጋብቶ «እንዴት እንዲህ ትለኛለህ?» ቢለው «ይቅርታ ድርጉልኝና ዛሬ ተራምደውት የተሾሙትን ሚኒስትር ሬሣ ነገ የእርስዎን ሌላ እንደሚራመደውና እንደሚሾምበት ሳያውቁ የቀሩ በመሆንዎ ለእኔ ከዚህ በላይ ሞኝ ሰው ላገኝ አልችልም..» በማለት ወርቁን ጥሎለት
ሄደ። የሀገሬ ሰው ነገ በኔ ማለቱ ያለምክንያት እንዳይመስለህ ጎበዝ ።
*============
⚜️ጥበብ ከጲላጦስ

24/02/2025

Address

Wolaita

Opening Hours

Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Telephone

+251918106981

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Desalegn Asmare posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Desalegn Asmare:

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share