
23/07/2025
ቱርክ አዲስ የጦር ቴክኖሎጂ ለዓለም አስተዋወቀች :-
=====
ቱርክ በጦር ሜዳ ላይ የሚደርሰውን የድሮን ስጋቶችን ለመመመከት ለመከላከልና ለማክሸፍ የሚያስችል አልካ-ካፕላን የተባለውን በቴክኖሎጂ የረቀቀ ጸረ ድሮን ተሽከርካሪ ሰርታ ይፋ አደረገች።
በዓይነቱ ልዩ የሆነውና የመጀመሪያው የተባለው ከአየር፣ ከመንገድ ዳር የሚደርሱ ቦምቦችን፣ ፈንጂዎችንና ያልተፈነዱ ቦምቦች ብሎም በውጊያ ዞኖች የሚመጡ ስጋቶችን በማነፍነፍ ለማስወገድ ይረዳል የተባለ ዘመናዊ ተሽከርካሪ አንካራ የደረሰችበትን የቴክኖሎጂ ልህቀት ያሳያል ተብሏል ።
ዓለም እየተጠቀመባቸዉ ካሉ ወቅታዊ የአየር መከላከያ ዘዴዎች በተሻለ ድሮኖችን፣ ሄሊኮፕተሮችን እና በራሪ የጦር መሳሪያዎችን ለመለየት ለመመከት ለማጥቃትና ለማምከን የሚያስችል ኤሌክትሮማግኔቲክና ጠንካራ ሌዘርን ስራ ላይ ያውላል። ይህ ዘመናዊ ተሽከርካሪ የአየር ላይ ስጋቶችን ለማስወገድ የሚያስችል ቀሰድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት እንዳለውም ተጠቅሷል ።
ተሽከርካሪው በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በታገዘ ክትትል የጠላት አቅጣጫዎችን መለየት የሚችል የሚችልና የላቀ የአሰራር ስርዓት ጠቋሚ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ከራዳር እይታ ውጭ የሆኑ ሰዉ አልባ ድሮኖች፣ ተወንጫፊ ፈንጂዎችን በፍጥነት ለማወቅ እና ለማስወገድ የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት ነው። በተጨማሪም የከተማ ከባቢዎችን፣ ክፍት ቦታዎችን እና ተንቀሳቃሽ ኮንቮይዎችን ለመጠበቅ የሚያስችል ሁለገብ አማራጭን በመጠቀም ሊሰማራ ይችላል ።
Reuters UK