ያለውለት ገላዬ

ያለውለት ገላዬ የመረጃ የክተት አዋጅ- ቱዩብ /tube/

New new world
08/02/2025

New new world

በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት ሲፈጽሙባቸው የሚያሳዩ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተሠራጭተው መነጋገሪያ ሆነዋል።ከእነዚህ ታጋቾች መካከል ነሒማ...
09/01/2025

በሊቢያ ታጣቂዎች በርካታ ስደተኞችን አግተው የማሰቃየት ድርጊት ሲፈጽሙባቸው የሚያሳዩ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተሠራጭተው መነጋገሪያ ሆነዋል።
ከእነዚህ ታጋቾች መካከል ነሒማ ጀማል አንዷ ናት። ነሒማ ከኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ በመሰደድ ነው ወደ ሊቢያ ያቀናችው።
'ሬፊዩጂስ ኢን ሊቢያ' የተሰኘው ተቋም በኤክስ ገፁ እንዳስታወቀው ነሒማ እና ሌሎች ስደተኞች ኩፍራ በምትባለው የሊቢያ ግዛት በታጣቂዎች ቁጥጥር ሥር ይገኛሉ።
ነሒማ በፎቶዎቹ እና በቪዲዮዎች ላይ አፏ በጨርቅ ተለጉሞ ስቃይ ሲደርስባት ትታያለች።
የነሒማ ቤተሰቦች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች ተልኮላቸው የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዲከፍሉ ማስጠንቀቂያ ደርሷቸዋል።
የነሒማ እህት ኢፍቱ ጀማል፤ ነሒማ ከስምንት ወራት በፊት ነበር ከሻሸመኔ ከተማ የ11ኛ ክፍል ትምህርቷን አቋርጣ ወደ ሊቢያ የተሰደደችው ስትል ለቢቢሲ ትናገራለች።

በሊቢያ "ለባርነት ጨረታ" የቀረበችው ኢትዮጵያዊቷ ነሒማ

 #ቡግና  የምርጫ ድምፅ የሽክፈበት ሰፈር ዘሬስ ማን ወክሎት ይሆን?አንብቡት!ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ችግር በትክክል ሳትረዱ ገንዘብ ለመሰብሰብ የምትሯሯጡ ሰዎች የነገ...
21/12/2024

#ቡግና
የምርጫ ድምፅ የሽክፈበት ሰፈር ዘሬስ ማን ወክሎት ይሆን?
አንብቡት!

ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ የተከሰተው አስከፊ ችግር በትክክል ሳትረዱ ገንዘብ ለመሰብሰብ የምትሯሯጡ ሰዎች የነገርየውን አስከፊነት የተረዳችሁት አይመስለኝም።

ለማንኛውም ከ60ሺ በላይ ሕዝብ አስከፊ ችግር የወደቀበት ነው። ብርድልብስና ስንዴ ዱቄት ተወርውሮ የሚመለስበት ጉዳይ አይደለም።

የተከሰተው ነገር እንድታውቁት
ድርቅ ተከሰተ፤ ድርቁ ወደ ርሃብ ተቀየረ፤ ርሃቡ ደግሞ የከፈ የህይወት አደጋ፣ የወባ በሽታ፣ እከክና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን አስከትሏል።

አንድ ቀበሌ ላይ 780 ሰው Screen ተደርጓ 720 ሰው ተጠቂ ሁኖ የተገኘበት ነው።

ስለዚህ ልዩ ትኩረት የሚያሻ ጉዳይ ስለሆነ ጠንካራ ልጆችም ጉዳዩን ይዘውት እየሰሩበት ስለሆነ መረጋጋት ይኑር።

ሁሉም የጉዳዩን አሳሳቢነት ተረድቶ መፍትሔዎችን እያሰላሰለ ይጠብቅ።

የመንግስት ሚድያዎች የትናንቱን የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ዜና እንዳይሰሩ እንደተነገራቸው ታወቀ (መሠረት ሚድያ)- አሜሪካ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ለተከሰተው ድርቅ እና የምግብ እጥረት ምግብ...
21/12/2024

የመንግስት ሚድያዎች የትናንቱን የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫ ዜና እንዳይሰሩ እንደተነገራቸው ታወቀ

(መሠረት ሚድያ)- አሜሪካ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ለተከሰተው ድርቅ እና የምግብ እጥረት ምግብ እየተላከ መሆኑን አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል በትናንትናው እለት ያሳወቀችበትን መረጃ የመንግስት ሚድያዎች እንዳይዘግቡ እንደተነገራቸው ታውቋል።

በሁለት የተለያዩ የመንግስት ሚድያዎች ውስጥ የሚሰሩ የሚድያ ባለሙያዎች ስማችን አይጠቀስ ብለው ለመሠረት ሚድያ እንደተናገሩት "ከላይ በመጣ ትእዛዝ" የአሜሪካ ድጋፍ ማድረግ እንዳይዘገብ ትእዛዝ ተላልፏል።

"ዜናውን መስራት ጀምረን ነበር፣ በኤዲተራችን በኩል ግን ተዉት ተብለናል" ያለው አንደኛው ምንጫችን ጉዳዩ "የመንግስትን የሰብል ምርት ስኬት ያኮስሳል" ተብሎ እንደተነገረው ገልጿል።

ሌላኛው ጋዜጠኛ ደግሞ "ጉዳዩ ለሀገር ገፅታ አንፃር ይቅር" እንደተባለ ተናግሯል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ትናንት በኦፊሴላዊ የፌስቡክ ገፁ እንዳስታወቀው በወረዳው ድርቅ እንደተከሰተ ከሰሞኑ እየወጡ ያሉ ሪፖርቶች ላይ ክትትል አድርጌያለሁ ብሏል።

"የኢትዮጵያ ህዝብን ለመደገፍ አጋሮቻችን ምግብ እና አልሚ ምግቦችን ወደተጠቁት ስፍራዎች እየላኩ ነው" ያለው ኤምባሲው ሁኔታውን በቀጣይም በመከታተል ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሰራ አስታውቋል።

መሠረት ሚድያን ጨምሮ አንዳንድ ሚድያዎች ከሰሞኑ በሰሜን ወሎ ቡግና ወረዳ ስለተከሰተው ድርቅ ሲዘግቡ ቆይተዋል።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ እጥረት እንዳጋጠማቸው እና በርሀብ እጅግ የተጎዱ ህፃናት ምስልም በማህበራዊ ሲዘዋወር ነበር።
መሰረት ሚዲያ

የጎንደርን ህዝብ ሳስብ  !  / መሳጭ ወግከአፄዎቹ ድምፅ የራዲዮ ፕሮግራም የተቆነፀለ!  ከእንግዳ ፕሮግራም ሌጀንድ ታደለ ባይሳ(ታዴ) ጋ ከነበረው ቆይታ..።የፋሲል ሚዲያ ክፍል ጋዜጠኛ Wo...
16/12/2024

የጎንደርን ህዝብ ሳስብ !
/ መሳጭ ወግ
ከአፄዎቹ ድምፅ የራዲዮ ፕሮግራም የተቆነፀለ! ከእንግዳ ፕሮግራም ሌጀንድ ታደለ ባይሳ(ታዴ) ጋ ከነበረው ቆይታ..።

የፋሲል ሚዲያ ክፍል ጋዜጠኛ Wondimu Eyayu :- ታዴ በፋሲል ቤት የማትረሳው ገጠመኝ ?

ታደለ ባይሳ :- ወደ ፕሪሚየር ሊግ ባደግንበት የደስታ ምሽት ማታ ሰለብሬት እያደረግን አንድ የብልኮ አካባቢ ደጋፊ አሽኮኮ አድርጎኝ ጭፈራ ቤት ገባ ይዞኝም ወጣ እና አሽኮኮ ላይ እንዳለሁ ተኩስ ብሎ ሽጉጥ ሰጠኝ😁 እኔም ተኮስኩና ነዝሮኝ ለቀኩት😁😁

Wondimu eyayu :- የፋሲልን ደጋፊ እና የጎንደርን ህዝብ ስታስብ/ስታስታውስ ምን ይሰማሀል ?

ታደለ ባይሳ :- የጎንደር ህዝብ እና ፋሲል ከነማ ከልቤ አልፍቀውም❤ የጎንደርን ህዝብ ሳስብ እንባዬ ይመጣል😓
በየሄድኩበት አወራለሁ የፋሲል ከነማ ማልያ ስትለብስ አትፈራም ትጀግናለህ🔥💪
ከአፄዎቹ ገፅ የተውደ

🇦🇹 ሌጀንድ ታደለ🇦🇹 ካፒቴን🔥

👉 ሸር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ።
👍 የአፄዎቹ ገፅን Like ያድርጉ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቻይና የመጀመሪያዋን ደብር በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች   I ለሁለተኛ ምዕራፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በ...
08/12/2024

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቻይና የመጀመሪያዋን ደብር በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ አከናወነች

I ለሁለተኛ ምዕራፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት ቻይና የገቡት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ በዕለቱ ከተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በማስከተል የአስተዳደር ሥራዎችን ሲያከናውኑ ከቆዩ በኋላ በዕለተ እሑድ በቻይና ምድር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመጀመርያዋን ቤተ ክርስቲያን ደብረ ምሕረት መድኃኔዓለም ብለው በመሰየም ሥርዓተ ቅዳሴ በመፈጸም ምዕምናንን አቁርበዋል።

በዕለቱም፣ አንዲት በሌላ ሃይማኖት ትኖር የነበረችን እኅት እና ሕፃን በማጥመቅ የሥላሴን ልጅነት እንዲያገኙ ያደረጉ ሲሆን በቻይና የመጀመሪያውን አንድ ኢትዮጵያዊ ዲያቆን ሾመዋል። በዕለቱም ከቻይና የተለያዩ ክፍላተ ግዛት የተሰባሰቡ ምዕመናን፣ ቻይናውያን እና ትውልደ ቻይናውያን በሥርዓተ ቅዳሴው የተሳተፉ ሲሆን መጋቤ ሐዲስ ቀሲስ ለይኩን ብርሃኑ "ሔዶም ታጠበና እያየም ተመለሰ" በሚል ርዕስ ስብከት አስተምረዋል።

ከሥርዓተ ቅዳሴው በኋላ ብፁዕነታቸው ለቀጣይ አገልግሎት ወደ ቤይጂንግ ከተማ አቅንተዋል።

የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት

 #ኦርቶዶክሳዊ  #እስላማዊ  #ጴንጢያዊ የተባለ ኢትዮጵያዊ የሚዘፍንለት  #የግብረሰናዊ አለም!በእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ከሚገኙ ክለቦች ብቸኛው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚደግፈውን አርምባ...
02/12/2024

#ኦርቶዶክሳዊ #እስላማዊ #ጴንጢያዊ የተባለ ኢትዮጵያዊ የሚዘፍንለት #የግብረሰናዊ አለም!
በእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ ከሚገኙ ክለቦች ብቸኛው የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነትን የሚደግፈውን አርምባንድ የማያደርገው የኢፕሲዊች ታውኑ አምበል ግብፃዊው ሳም ሙርሲ ነው።ሳም ሙርሲ ሀይማኖቴና ባህሌ ስለማይፈቅድ ይህንን አርምባንድ አላደርግም ያለ ሲሆን ክለቡም ውሳኔውን እንደሚደግፍ አስታውቋል።

ሲዲ ስፖርት/CD Sport

35ቱ ተራሮች🏞   | በአማራ ብሔራዊ ክልል የሚገኙ 35 ተራሮች (ስም፣ ከፍታው በሜትር፣ የሚገኙበት ዞንና ወረዳ)❶ ራስ ዳሽን ( 4620 ሜትር ከፍታ፣ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣❷ አናሎ  ( ...
14/11/2024

35ቱ ተራሮች🏞

| በአማራ ብሔራዊ ክልል የሚገኙ 35 ተራሮች (ስም፣ ከፍታው በሜትር፣ የሚገኙበት ዞንና ወረዳ)

❶ ራስ ዳሽን ( 4620 ሜትር ከፍታ፣ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

❷ አናሎ ( 4473 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደባርቅ)፣

❸ ወይኖበር ( 4465 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

➍ ቅዱስ ያሬድ ( 4453 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር በየዳ)፣

➎ አባት ደጀን ( 4445 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

❻ ጠፋው ለዘር ( 4449 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

❼ ቧሂት ( 4430 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ጃናሞራ)፣

➑ ሲሊኪ ( 4420 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደባርቅ)፣

❾ አባ ያሬድ ( 4409 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

❿ መሳረሪያ ( 4355 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

⓫ ደግረዋ ( 4316 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደባርቅ)፣

⓬ ቦርጭ ውሃ ( 4272 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ በየዳ)፣

⓭ ዋልያ ቀንድ (4249 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጃናማራ)፣

⓮ ሽዋና ( 41 13 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጃናሞራ)፣

⓯ እናትየ ( 4070 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደባርቅ)፣

⓰ ጓዘመቀርቀቢያ ( 4063 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጃናሞራ)፣

⓱ ትልቅ አምባ ( 4044 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደባርቅ)፣

⓲ ጨነቅ (4000 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ጃናሞራ)፣

⓳ ጉና ( 4231 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ጎንደር፣ እስቴ፣ፉርጣ፣ ላይጋይንት)፣

⓴ አደባባይ (4261 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሳይንትና ተንታ)፣

21. ጠና (4208 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣ መቅደላ)፤

22. አንጦት (4108 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣ለጋንቦ)፣

23. የወል ( 3832 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣ ደሴ ዙሪያ)፣

24. ልመስክ ( 3710 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣ መሃል ሳይንትና ቦረና)፣

25. ወፋጮ (3651 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣አባሰል)፣

26. ወረባያሱ ( 3598 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሎ፣ ወረኢሉ)፣

27. መሆነኛ ( 3463 ሜትር ከፍታ፣ ደቡብ ወሉ፣ ኩታበር)፣

28. ጦሳ ( ከ2500 ሜትር ከፍታ በላይ፣ ደሴ፣ ደሴ ዙሪያ)፣

29. አዳማ 3533 ሜትር ከፍታ፣ ምዕራብ ጎጃም)፣

30. መገዘዝ (3596 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ሽዋ፣
አሳግርት)፣

31.ጓሳ (3400 ሜትር ከፍታ፣ ሰሜን ሽዋ)፣

32. ጮቄ (4100 ሜትር ከፍታ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ ቢቡኝ)፣

33. አባ ሚኒዮስ (3664 ሜትር ከፍታ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ እነብሴ ሳርምድር)፣

34.የጎፍ (ከ2400 ሜትር ከፍታ በላይ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ ዙሪያ)

35. አራት መከራክር (3537 ሜትር ከፍታ፣ ምስራቅ ጎጃም፣ቢቡኝ ናቸው።

(አማራ ባህል ቱሪዝም ቢሮ)

በጀርመን የ250 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት በወፍ ጎጆ ምክንያት መቋረጡ እያነጋገረ ነው።በጀርመን የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ...
28/10/2024

በጀርመን የ250 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት በወፍ ጎጆ ምክንያት መቋረጡ እያነጋገረ ነው።
በጀርመን የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ

በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ አንዲት ወፍ ጎጆዋን ቀልሳ መኖር ከጀመረች ከራርማለች። ይህች ወፍ እንደሌሎች ዝርያቸው በመጥፋት አደጋ ላይ ከሚገኙ የወፍ ዓይነቶች አንዷ ናት። የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩ የሕንጻ ማስፋፋት ሥራ ለማከናወን በተሰናዳበት አጋጣሚ በጣሪያው ጎጆዋን ቀልሳ የምትኖረውን ወፍ ይደርሱባታል። ክሊኒኩም በማስፋፋት ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ይገታል። 250 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣው ፕሮጀክትም ለዘጠኝ ዓመታት ባለበት ቆመ። በአካባቢው የሚገኘው ደን ጥበቃውም ቀጠለ፤ ወፏም ያለ ስጋት በጣሪያው ላይ ትኖር ጀመር። የወፎን ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ታዲያ ድንገት ወፏ ትሰወርባቸዋለች።

ዘሯ ሊጠፋ ነው የተባለላት ወፍ አለመኖር ግን ወዲያው የታቀደውን የሕንጻ ማስፋፋት ፕሮጀክት መጀመር አላስቻለም። በጥንቃቄና በትዕግሥት ወፏ ወደ ቀለሰችው ጎጆዋ ትመለስ ይሆናል በሚል ተጠበቀች። ጉዳዩ የግዛቷ ፖለቲከኞችና ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ድመት በልቷት ይሁን ወይም አካባቢውን ለቃ ባልታወቀ ምክንያት የወፏ ከጎርጎሪዮሳዊው 2022 ጀምሮ አለመታየት በደስታ የማስፋፋት ሥራውን ለመጀመር አላጣደፈም። ይልቁንም የለመደችው አካባቢ ነውና ተመልሳ ብትመጣ ጎጆዋ ከፈረሰ የት ትገባለች የሚል ክርክር አስነሳ።

የከተማዋ ከንቲባ ወፏ አሁን እኛ ሳናባርራት ቦታውን ስለለቀች ሥራው መቀጠል ይችላል ቢሉም የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ሕግ ባለሙያዎች ግን አንቀጽ እየጠቀሱ ሞገቱ። የአእዋፍ ጥናት ባለሙያዎችም በዚህ እየተሳተፉ ነው።

ይህች ወፍ ፈጣሪ አድሏት ጀርመን ሀገር በመኖሯ ጎጆዋ ሳይፈርስ የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጓተተ። ግንባታውን ለማድረግ በአካባቢው ከሚገኘው ደን የተወሰነው ይወገዳል መባሉም ሌላ ሙግት አስነስቷል። በጀርመን ወፍም መብት አላት።
via DW Amaharic

ይህ ምስጊን ጀግና የጠለምት ገበሬ ደግ ህዝባችን ከመለመን ሞትን የሚመርጥ ሁኖ ሳለ  የእድሜ ልክ ቤት ንብረቱ : የደረሰ ሰብሉ : የልጅ ያክል የሚወዳቸው የቤት እንስሳቶቹ  ውድ ልጁን ሚስቱ...
29/08/2024

ይህ ምስጊን ጀግና የጠለምት ገበሬ ደግ ህዝባችን ከመለመን ሞትን የሚመርጥ ሁኖ ሳለ የእድሜ ልክ ቤት ንብረቱ : የደረሰ ሰብሉ : የልጅ ያክል የሚወዳቸው የቤት እንስሳቶቹ ውድ ልጁን ሚስቱን አባቱን ወንድሙን ከእነ ነብሳቸው ክፉ ቀን መጦ በናዳ ተዳፍኖ አፈር ለብሶበት የሰው አይን ለማዬት ከቀዬው ዕርቆ ለመመፅወት ደጅ ጠና 😭😭😭

አይዞህ ወገኔ 🙏 ሁላችንም በቻልነው አቅም ድጋፍ እናድርግ 🙏

በጎንደር ከተማ ያላቹህ በሙሉ ከነገ አርብ ጀምሮ በተመረጡ ቦታዎች ድንኳን ተጥሎ የአይነት ስጦታዎች ልባሽ ልብሶችን ስለምንሰበስብ በመኪናም ወደ ሁላቹህም መንደር እየዞርን ቸርነታቹህን ስለምንሻ ከአሁኑ ዝግጁ ሁናቹህ ጠብቁን🙏🙏🙏

አካውንት ቁጥር :- 1000575340133

እናመሰግናለን🙏

11/07/2024

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ያለውለት ገላዬ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ያለውለት ገላዬ:

Share