31/07/2025
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ስር ያሉ ድርጅቶች ሀገሪቱን አረንጓዴ በማልበስ ሂደት ላይ የድርሻቸውን ተወጥተዋል፤ ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብርን ተቀላቅለው በተለያዩ የሀገሪቱ ስፍራዎች አሻራቸውን ካኖሩ ድርጅቶች መካከል እነሆ እንልዎታለን፡፡
የኢባትሎ አመራርና ሠራተኞች ዛሬ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢባትሎ ዋ/ሥ/አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) በተገኙበት በገላን ወደብና ተርሚናል አረንጓዴ አሻራ የማኖር ተግባር አከናውነዋል።
በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) መርሃ-ግብሩን ባስጀመሩበት ወቅት የአረንጓዴ አሻራ ልማት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለአካባቢ ጥበቃ እጅግ ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን ፣ የዚህ ታሪካዊ ዘመቻ አካል በመሆናችን ታላቅ ደስታ እና ክብር ይሰማናል ብለዋል።
የኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክረምት በጎፈቃድ ስራዎች የችግኝ ተከላ፣ የአቅመ ደካሞች ቤት እድሳት፣ የተማሪዎች ቁሳቁስ እና መጣቶችን የማነቃቃት ስራ ተሰርቷል ለዚህም የክልሉ መስተዳድር ከፍተኛ እገዛ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ፖስታ ሰራተኞች ‹‹በመትከል ማንሰራራት›› በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ውን ሰባተኛውን ዙር ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሞጆ ከተማ በተዘጋጀው የችግኝ መትከያ ስፍራ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ቤቶች ኮርፖሬሽን የዘንድሮውን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ረሻድ ከማል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ማያ ከተማ ተገኝተው አስጀምረውታል። በአንድ ጀምበር 7 መቶ ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል እየተከናወነ ባለው መርሐ ግብር የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አመራሮችና ሠራተኞች በተለያዩ ቦታዎች ሀገር በቀል ችግኞችን በጉለሌ እፅዋት ማዕከል፣ በቢሾፍቱ ኢባዩ ተራራ፣ በመኖሪያ አፓርትመንቶች፣ በማምረቻ ማዕከላት፣ በመኖሪያ ጊቢዎች ሀገር በቀል ችግኞች ተክለዋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 5,688 ሰራተኞች የተሳተፉበት የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም ያከናወኑ ሲሆን በዚህ ክንውንም 64,640 ችግኞችን በአንድ ጀምበር መትከል ችለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተሳተፈዋል፡፡ የግሩፕ የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች በተለያዩ ስፍራዎች በአንድ ጀንበር 700 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሐ ግብር ላይ ተሳትፈዋል፡፡ የግሩፑ የሥራ መሪዎች እና ሠራተኞቹ የተሳተፉት በምዕራብ አርሲ ዞን በወንዶ ወረዳ እና በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በተከናወኑ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮች ላይ ነው፡፡ በምዕራብ አርሲ ወንዶ ወረዳ በተከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የግሩፑ ከፍተኛ የማነጅመንት አባላት እና የፋብሪካዎቹ የሥራ መሪዎች እንዲሁም የመከላከያ ሠራዊት አባላትና የአካባቢው ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን(ኬ.ኢ.ኮ) በሀገር ደረጃ በተከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ኢ/ሆልዲንግ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች፣ የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች፣ ማኔጅመንት አባላት፣ ሠራተኞች እንዲሁም በሥሩ የሚገኙት ተቋማት ሥ/አስኪያጆችና ሠራተኞች (በኮርፖሬሽኑ ብቻ ከ140 በላይ ሠራተኞችን በማሳተፍ) በተገኙበት ቆቃ በተባለው አካባቢ በሚገኘው ረጅም ከ.ሜ በሚሸፍነው በፈጣን መንገድ ዳርቻ ላይ ከፍተኛ የሆነ የአረንጓዴ አሻራ መ/ግብር አከናውነዋል፡