ለሁሉ

ለሁሉ ይህ ቻናል ከሁሉም በኩል የተገኙ ጥራት ያላቸው መረጃ የሚያገኙበት የርስዎ ቻናል ነው። Like እና Follow በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን።
(1)

ከ368ቱ ተጫዋቾች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ቀርቷል !በ2004 የፖርቹጋል አውሮፓ ዋንጫ ከተጫወቱት 368 ተጫዋቾች ከአንዱ በስተቀር ሁሉም 367 እግር ኳስ አቁመዋል፡፡ 16 ሀገራት በተካፈሉበ...
04/08/2025

ከ368ቱ ተጫዋቾች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ቀርቷል !

በ2004 የፖርቹጋል አውሮፓ ዋንጫ ከተጫወቱት 368 ተጫዋቾች ከአንዱ በስተቀር ሁሉም 367 እግር ኳስ አቁመዋል፡፡

16 ሀገራት በተካፈሉበት 12 ኛው የአውሮፓ ዋንጫ አሁንም በመጫዎት ላይ ሚገኘው ብቸኛው ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ብቻ ነው፡፡

በጊዜው19 ዓመቱ የነበረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአሁን ሰዓት ለሳዑዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር እየተጫወተ ይገኛል፡፡

ከ21 ዓመት በፊት በተደረገው የአውሮፓ ዋንጫ በፍጻሜው ግሪክ አስተናጋጇ ፖርቹጋልን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለመጀመርያም ለመጨረሻም ጊዜ የአህጉሩን ዋንጫ ማንሳቷ ይታወሳል፡፡

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ከ 4 ቀናት በፊት በሴኡል ላይ 7 ጎሎችን አዝንቦ የወጣው ባርሴሎና ዛሬም በዴጉ ላይ 5 ግቦች አስቆጥሯልማርከስ ራሽፎርድ የመጀመሪያ ጎሉን ለባርሴሎና አስቆጥሯል።ብዙ ጎሎችን ካላስቆጠረ ሼም ...
04/08/2025

ከ 4 ቀናት በፊት በሴኡል ላይ 7 ጎሎችን አዝንቦ የወጣው ባርሴሎና ዛሬም በዴጉ ላይ 5 ግቦች አስቆጥሯል

ማርከስ ራሽፎርድ የመጀመሪያ ጎሉን ለባርሴሎና አስቆጥሯል።

ብዙ ጎሎችን ካላስቆጠረ ሼም ስለሚይዘው ባርሴሎና ምን ትላላችሁ?

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ፍቅረኛዋን የደበደበችው አትሌት በቁጥጥር ስር ዋለችየ100ሜትር እና የ200ሜትር የሩጫ የዓለም ሻምፒዮናዋ ሻካሪ ሪቻርድሰን ከፍቅረኛዋ እና አብሯት ከሚሮጠው አትሌት ክርስቲያን ኮልማን ጋር በ...
04/08/2025

ፍቅረኛዋን የደበደበችው አትሌት በቁጥጥር ስር ዋለች

የ100ሜትር እና የ200ሜትር የሩጫ የዓለም ሻምፒዮናዋ ሻካሪ ሪቻርድሰን ከፍቅረኛዋ እና አብሯት ከሚሮጠው አትሌት ክርስቲያን ኮልማን ጋር በተፈጠረ ክርክር ምክንያት፣ በሲያትል-ታኮማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቤት ውስጥ ሁከት ወንጀል ተጠርጥራ በፖሊስ ተይዛለች።

በፖሊስ ሪፖርት መሰረት፣ ሪቻርድሰን ኮልማንን ወደ ግድግዳ እንደገፋችው፣ ቦርሳውን እንደጎተተችው እና እቃ እንደወረወረችበት ተገልጿል።

ሪቻርድሰን ግን ለብዙ ሰዓታት ታስራ ከቆየች በኋላ በሚቀጥለው ቀን ተለቃለች።

ይህ አስደንጋጭ ዜና፣ የዩ.ኤስ.ኤ. ትራክ ኤንድ ፊልድ ሻምፒዮና ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት መሆኑ፣

በቀጣዩ ታላቅ ውድድር ላይ በምትሳተፍበት ጊዜ ዝግጁነቷ እና የአእምሮ ሁኔታዋ ምን እንደሚመስል ጥያቄ አስነስቷል።

በቅርቡ በፍርድ ቤት ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል። አዳዲስ መረጃዎችን ለመከታተል ከእኛ ጋር ይቆዩ!

Via AP

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ሩበን አሙሪም 🗣"ማውንት በአስደናቂ ሁኔታ እየመጣ ነው ፣ የሚያስፈልገንን አየነት ማውንት ለመሆን ጠንክሮ እየሰራ ነው አሁን ያለበት እንቅስቃሴ ወድጄዋው ከዚህ የበለጠ እንደሚያስደምመን ደሞ ...
04/08/2025

ሩበን አሙሪም 🗣

"ማውንት በአስደናቂ ሁኔታ እየመጣ ነው ፣ የሚያስፈልገንን አየነት ማውንት ለመሆን ጠንክሮ እየሰራ ነው አሁን ያለበት እንቅስቃሴ ወድጄዋው ከዚህ የበለጠ እንደሚያስደምመን ደሞ አልጠራጠርም።"

ማውንት ባለፉት 180 ደቂቃዎች ውስጥ 3 የጎል ተሳትፎ አደርጓል 1 ጎል 2 አሲስት

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ዩናይትድ የፕሪሚየር ሊግ ሰመር ሲሪየስ አሸናፊ ሆነ***************ማንችስተር ዩናይትድ በአሜሪካ ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሰመር ሲሪየስ ዋንጫን አንስቷል፡፡የቅድ...
04/08/2025

ዩናይትድ የፕሪሚየር ሊግ ሰመር ሲሪየስ አሸናፊ ሆነ
***************
ማንችስተር ዩናይትድ በአሜሪካ ለ2ኛ ጊዜ የተካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሰመር ሲሪየስ ዋንጫን አንስቷል፡፡

የቅድመ ውድድር ዝግጅት አካል ሆኖ አራት የእንግሊዝ ክለቦች በተሳተፉበት መድረክ ዩናይትድ በመጨረሻው ጨዋታ ከኤቨርተን ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡

በአትላንታ በተደረገው ጨዋታ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ በፍጹም ቅጣት ምት እና ሜሰን ማውንት በጨዋታ የዩናይትድን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡

ኢልማን ኒዴይ እና ኤይደን ሄቨን በራሱ መረብ ላይ የኤቨርተንን ግቦች ያስቆጠሩ ተጫዋቸች ናቸው፡፡

ካደረጋቸው ሶስት ጨዋታዎች ሁለቱን በማሸነፍ በአንዱ ነጥብ የተጋራው ማንችስተር ዩናይትድ በሰባት ነጥብ የተዘጋጀውን ዋንጫው ወስዷል፡፡

በመጨረሻው ጨዋታ ቦርንማውዝን 2 ለ 0 ያሸነፈው ዌስትሀም ዩናይትድ በ6 ነጥብ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ሎስ አንጅለስ ጋላክሲ እና ቶተንሀም ከስምምነት ደረሱ ! ➺ የአሜሪካ የሜጀር ሊግ ሶከር ክለብ የሆነው ሎስ አንጅለስ ጋላክሲ ሶን ሂዪንግ ሚንን ከቶተንሀም ለማስፈረም ከስምምነት ደረሱ ! ➺ ...
03/08/2025

ሎስ አንጅለስ ጋላክሲ እና ቶተንሀም ከስምምነት ደረሱ !

➺ የአሜሪካ የሜጀር ሊግ ሶከር ክለብ የሆነው ሎስ አንጅለስ ጋላክሲ ሶን ሂዪንግ ሚንን ከቶተንሀም ለማስፈረም ከስምምነት ደረሱ !

➺ ከሶን ጋር የግል ስምምነቶች ለመጨረስ የአሜሪካው ክለብ ጥሩ የሆነ ኮንትራትን አቅርቦለታል

➺ ዝውውሩን በዚህ ሳምንት ለመጨረስ እቅድም ተይዟል !

ምንጭ ፡ Ben Jacobs
⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

“ ማንችስትር ዩናይትድን ለ20 አመታት ማሰልጠን እፈልጋለው “ ሩበን አሞሪም ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ የኦልድትራፎርዱን ክለብ ለሁለት አስርት አመታት የማሰልጠን እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል። ...
03/08/2025

“ ማንችስትር ዩናይትድን ለ20 አመታት ማሰልጠን እፈልጋለው “ ሩበን አሞሪም

ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ የኦልድትራፎርዱን ክለብ ለሁለት አስርት አመታት የማሰልጠን እቅድ እንዳላቸው አስታውቀዋል።

" ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ለ20 አመታት መቆየት እፈልጋለው።

አላማዬ ይህ ነው በእዚህ ፅኑ የሆነ እምነት አለኝ " በማለት ተናግረዋል።

የተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ለቡድናቸው ፈታኝ እንደነበር ያነሱት አሞሪም " በአዲሱ ውድድር አመት ወደፊት ለመጓዝ እና የተሻለ ለማድረግ ተዘጋጅተናል" ብለዋል።

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ላይፕዚግ ለቤንጃሚን ሼሽኮ ከኒውካስል ዩናይትድ የቀረበለትን €75M እና €5M ተጨማሪ ክፍያ የያዘውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ❌አርቢ ላይፕዚግ የኒውካስልን ጥያቄ በቂ አይደለም ሲል...
03/08/2025

ላይፕዚግ ለቤንጃሚን ሼሽኮ ከኒውካስል ዩናይትድ የቀረበለትን €75M እና €5M ተጨማሪ ክፍያ የያዘውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። ❌

አርቢ ላይፕዚግ የኒውካስልን ጥያቄ በቂ አይደለም ሲል የገለጸው የሽያጭ ድርሻ (sell-on clause) ስላላካተተ ነው።

ማንቸስተር ዩናይትድ አሁንም በዝውውሩ ውድድር ውስጥ ነው፣ ግን እስካሁን ምንም አይነት ጥያቄ አላቀረበም።

⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

እውነታው ይህ ነው‼️ዋሊያው በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሁለት የአካዳሚ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች አድርጓልአንዱ ባለፈው ማክሰኞ ከስሪ ፖይንት አካዳሚ ጋር አዲስ አበባ ላይ ተጫውቶ 1-0 ...
03/08/2025

እውነታው ይህ ነው‼️

ዋሊያው በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሁለት የአካዳሚ ቡድኖች ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎች አድርጓል

አንዱ ባለፈው ማክሰኞ ከስሪ ፖይንት አካዳሚ ጋር አዲስ አበባ ላይ ተጫውቶ 1-0 አሸንፈ፤ ምሽቱን ወደ አሜሪካ በረረ

ሁለተኛው ትናንት ከዲሲ ዩናይትድ የአካዳሚ ፍሬዎች ጋር ተጫውቶ 3-0 አሽነፈ፤ ከንአን ማርክነህ፣ ዳዋ ሁጤሳና ረመዳን የሱፍ የጎሎቹ ባለቤቶች ነበሩ

ትናንት ዋሊያውን የገጠመው የዲሲ ዩናይትድ ዋና ቡድን አልነበረም፤ ዲሲ ዩናይትድ በሚል ቅብ ስም የክለቡን በርካታ ተለማማጅ የአካዳሚ ታዳጊዎችን ይዞ ነው የመጣው፤ ክለቡ ለጨዋታው ይዞ ከቀረባቸው 25 ተጫዋቾች መካከል 19ኙ የአካዳሚ ተጫዋቾች ናቸው፤ ስድስቱ የዋናው ቡድን አባላት ሲሆኑ አምስቱ በመጀመሪያው 45 ተጫውተው ወጥተዋል፤ አንዱ ግብ ጠባቂ በሁለተኛው አጋማሽ ተሰልፏል፤ ቡድኑ ውስጥ የነበሩት 6 የዋናው ቡድን ተጫዋቾችም ቢሆኑ በሊጉ በቋሚ አሰላለፍ ላይ መግባት ያልቻሉ ናቸው

ትናንት በርካታ ኢትዮጵያዊያን ጥሪውን አክበረው ተገኝተዋል፤ ዋሊያውን ደግፈዋል፤ ብሄራዊ ቡድኑም ግጥሚያውን አክብሮ ተመልካቹን አዝናንቶ አሸንፏል፤ አዘጋጆቹ ደግሞ በቅንነት ጊዜና ገንዘባቸውን አፍስሰዋል፤ ባለሀብቱ ጆ ማሞና አጋሮቻቸው ብዙ ለፍተዋል፤ ለዚህም ምስጋና ይገባቸዋል፤ ሆኖም የብሄራዊ ቡድናችንን ክብር ከዚህ በላይ ማስጠበቅ ነበረባቸው፤ ከክለብ ጋር ከማጫወት ይልቅ አቻ ብሄራዊ ቡድን መፈለግ የተሻለ አማራጭ ነበር፤ ይህ ካልሆነ ደግሞ ዲሲ ዩናይትድ ዋናውን ቡድን እንዲያሰልፍ ውሉ ውስጥ ሊካተት ይገባል፤ ከአካዳሚ ጋር ለመጫወት ዋናውን ብሄራዊ ቡድን ከማምጣት ከ23 ወይም ከ20 አመት በታች ወጣት ቡድን ቢሳተፍ የተሻለ ነበር፤ አዘጋጆቹን ለቀና ልፋታቸው እንዳመሰገንን ሁሉ በቀጣይነት ይህንን ማስተካከል ቢችሉ የተሻለ ይሆናል

ፌዴሬሽኑ ምንም ብር አላወጣም፤ ወጪው ሁሉ ተሸፍኖለታል፤ እንደውም የተጫወተበት 25ሺህ ዶላር፥ ያሸነፈበት 50ሺህ ዶላር በጥቅሉ 75ሺህ ዶላር አግኝቷል፤ ገንዘብ ይዞ መመለሱን እንደ ስኬት ሊያነሳው ይችላል፤ እውነታው ግን ይህ ነው ከዲሲ ዩናይትድ ብር አግኝቶ በዲሲ ዩናይትድ ክብር አጥቷል!

(ታምሩ ዓለሙ)
⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

ዋልያው ከሜዳው ውጪ ወደ አሜሪካ ተጉዞ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የሚሳተፈውን ዲስ ዩናይትድን ገጥሞ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የ 3 ለ 0 ሽንፈት አከናንቦታል 😎😎 🔥🔥🇺🇸 ዲሲ ዩናይትድ 0...
02/08/2025

ዋልያው ከሜዳው ውጪ ወደ አሜሪካ ተጉዞ በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የሚሳተፈውን ዲስ ዩናይትድን ገጥሞ በሜዳው እና በደጋፊው ፊት የ 3 ለ 0 ሽንፈት አከናንቦታል 😎😎 🔥🔥

🇺🇸 ዲሲ ዩናይትድ 0-3 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን 🇪🇹
#ከነዓን 3'
#ዳዋ 20'
#ረመዳን 65'

ብሔራዊ ቡድናችን ጨዋታውን በማድረጉ 25ሺ + ጨዋታውን በማሸነፉ በድምሩ 75ሺ የአሜሪካ ዶላር አጊንቷል !

በዕውነቱ ዲሲ ከበረራ ጀምሮ እስከ ሆቴል + ምግብ ወጪ ሸፈነው ለወዳጅነት ጨዋታ ቢጋብዙንም እነሱን ከማሸነፍ ወደ ኋላ አላልንም 🔥🤯

ሰለ ዋልያዎቹ ምን ይላሉ ?
4 3 3
⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ "ኪሳራም ሥራ ነው" የተሰኘው የከፈለኝ ሐይሉ መጽሐፍ ተመረቀየፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው ከፈለኝ ሐይሉ ያሳተሙት የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ "ኪሳራም ሥራ ነ...
02/08/2025

የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ "ኪሳራም ሥራ ነው" የተሰኘው የከፈለኝ ሐይሉ መጽሐፍ ተመረቀ

የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ባለሙያው ከፈለኝ ሐይሉ ያሳተሙት የቢዝነስ ሀሁ በኢትዮጵያ "ኪሳራም ሥራ ነው" የተሰኘው መፀሐፍ በዛሬው ዕለት በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት አገልግሎት (ወመዘክር) በይፋ ተመርቋል

በኢትዮጵያ ያለው የንግድ ስርዓት በዘርፉ ለተሰማሩ የንግድ አካላት በአሳሪ ቢሮክራሲና በሌሎች ምክንያቶች መታሰሩ፤ ንግድ በኢትዮጵያ እድገቱ በታሰበው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል።

የኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት ንግድ በማያውቁ የመንግስት ሃላፊዎች መመራቱ ዘርፉ በሚገባው ልክ እንዳያድግ ስለማድረጉ በመጽሐፉ ዙሪያ ውይይት በተደረገበት በዚሁ መድረክ ላይ ተነግሯል።

በውይይቱ የተለያዩ የፋይናንስ እና ቢዝነስ ባለሙያዎች፣ ኢንተርፕርነሮች እና በርካታ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን፤ መፀሐፉ ውስጥ በተመረጡ ሃሳቦች ዙሪያ ሙያዊ እይታቸውን አጋርተዋል።

የንግድ ስርዓት፣ የፋይናንስ ፍሰት እና የግብር ስርዓት በኢትዮጵያ ያለው መልክ ከሳይንሱ እና አጠቃላይ የዘፈቀደ አካሄዶች ያላቸው መልክ ምን ይመስላል የሚለው ተዳሶበታል።

(አሐዱ ሬዲዮ) ‌‌‎
ለበለጠ መርጃ:-
⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

አርሰናል የክሪስታል ፓላስ  ኢቤሬቺ ኢዜን ለማስፈረም ከ50 ሚሊየን ፓውንድ በላይ የመክፈቻ ጥያቄ አቅርበዋል።(Transfersdotcom)⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድ...
02/08/2025

አርሰናል የክሪስታል ፓላስ ኢቤሬቺ ኢዜን ለማስፈረም ከ50 ሚሊየን ፓውንድ በላይ የመክፈቻ ጥያቄ አቅርበዋል።

(Transfersdotcom)
⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/lehulu_Media

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ለሁሉ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ለሁሉ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share