
23/05/2025
ጃ-War
ስታፈርስ ኖረህ፣ ደሃውን የቤት ባለቤት ያደረገችውን የመናገር ሞራል የለህም
አስለቃሽ Vs እምባ አፋሽ
አዴን እንዳታስባት፣ የደሃን እናት ልትነካት እንዳትሞክር። አንተ ስንቱን ስታስለቅስ እንዳልኖርክ እሷ ግን የስንቱን እምባ አብሳለች።
አንተ ሙሉ እድሜህን ስታስፈርስ፣ ስታስወድም እንደኖርክ እሷ ደሞ ሚሊዮኖችን የቤት ባለቤት አድርጋለች። አንተ እሷን ስትናገር ጭካ ወርቅን እንደመናገር ነው የተሰማኝ።
ስንት ከተማ ነበር ያስወደምክ? እሷስ ከተማን ምን አስመስላ ገነባች። ደሴት ብለህ የጠራኸው የአዴ የቀን ከሌሊት ልፋት ውጤት ነው። አንተም አምነሃል፣ አው ከተማውን ደሴት አድርጋለች።
አንተ በሻሸመኔ ስንቱን አስወደምክና አሰለቀስ? ስንቱን ንብረት አሳጣህ? እሷ ግን 23 መመገቢያ በከተማችን ከፍታ የሌለውን ሁሉ ሰብስባ እንደ እናት እየመገበች ነው። አታፍርም ይሄን ሁሉ የእሷን ገድል አንተ በተቃራኒው ስትፈፅም መኖርህን አስበህ?
ስንት ሴት ነበር አግብተህ የፈታህ? አግብተህ የፈታኸውን ነው ያልኩ፣ የማገጥከው ቁጥር የለውም። እሷ ግን በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን ከጎዳና ሰብስባ፣ ከሴተኛ አዳሪነት አውጥታ፣ የነገዋ ሴት በማለት አሰልጥና የሙያ ባለቤት አድርጋቸዋለች።
አንተና አዴ ማለት ፋንዲያ እና ወርቅ እንደማለት ናችሁ። የብዙዎች ጠላት ሆነህ የብዙዎችን እናት ልትናገር እንዳትሞክር።