Ethio Social Media Network ኢትዮ ሶሻል ሚዲያ ኔትወርክ

Ethio Social Media Network  ኢትዮ ሶሻል ሚዲያ ኔትወርክ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethio Social Media Network ኢትዮ ሶሻል ሚዲያ ኔትወርክ, Social Media Agency, Addis Ababa.

ይህን 920 ሰብስክራይብ ያለዉን ቻናል ከታች ባለዉ ሊንክ በመግባት ሰብስክራይብ በማድረግ 1K እናድርሰዉ።
26/02/2025

ይህን 920 ሰብስክራይብ ያለዉን ቻናል ከታች ባለዉ ሊንክ በመግባት ሰብስክራይብ በማድረግ 1K እናድርሰዉ።

ዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
26/02/2025

ዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

27/01/2025
21/01/2025

በገፃችን ላይ post እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉትን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ትዝታ ያለበትን ፎቶዎች በinbox አድርሱን



ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የተማራችሁ ተዋወቋቸዉ።
21/01/2025

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የተማራችሁ ተዋወቋቸዉ።

ቦሌ መድኃኒዓለም የሚገኘው ሳውዝ ጌት ሆቴል አፓርትመንት በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን አስታወቀ  I ከተገነባ 6 አመታትን ያስቆጠረው ሳውዝ ጌት ፕላዛ በ1.2 ሚሊየን ዶላር ተሰርቶ አገልግሎት...
04/01/2025

ቦሌ መድኃኒዓለም የሚገኘው ሳውዝ ጌት ሆቴል አፓርትመንት በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን አስታወቀ

I ከተገነባ 6 አመታትን ያስቆጠረው ሳውዝ ጌት ፕላዛ በ1.2 ሚሊየን ዶላር ተሰርቶ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ሲሆን አሁን በአዲስ መልክ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

ሳውዝ ጌት ፕላዛ ሱቆች፣ ባርና ሬስቶራንት፣ ሁሉም ነገር የተሟላላቸው 42 ውብ የእንግዶች ማረፊያ መኝታ ክፍሎች፣ ስፓ እና የውበት ሳሎን አካቶ የያዘ መሆኑ ተገልጿል።

ሳውዝ ጌት ሆቴል አፓርትመንት ከግራውንድ እስከ 3ተኛ ፎቅ ድረስ የተለያዩ ሱቆች፣ ከ4ኛ - 9ኛ ፎቅ አፓርትመንት፣ በ10ኛ ፎሎር የሬስቶራንት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ይሔንን የ 14 አመት ታዳጊ ለማትረፍ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ ።- የተሻለ ህክምና ካላገኘ ከ1 ወር እድሜ በላይ እንደማይኖር ለቤተሰቦቹ ተነግሯቸዋል ።- መላ ቤተሰቡ ከፍተኛ ሀዘንና ድንጋ...
04/01/2025

ይሔንን የ 14 አመት ታዳጊ ለማትረፍ የምንችለውን ሁሉ እናድርግ ።
- የተሻለ ህክምና ካላገኘ ከ1 ወር እድሜ በላይ እንደማይኖር ለቤተሰቦቹ ተነግሯቸዋል ።
- መላ ቤተሰቡ ከፍተኛ ሀዘንና ድንጋጤ ውስጥ ናቸው ።
- በተከፈተው የጎፈንድሚ ወይም በተጠቀሰው አካውንት የምንችለውን ገንዘብ በማገዝ የፅድቅ ስራ እንድንሰራና ከሀገር ውጪ ህክምናውን ተከታትሎ ወደ ሙሉ ጤንነቱ እንመልሰው ዘንድ ድጋፋችሁን በልኡል እግዚአብሔር ስም መላ ቤተሰቦቹ ይጠይቃሉ ።

https://gofund.me/a40bde0f

የኢትዮጵያ አየር መንገድ  በመላው ሀገሪቱ  ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የአቪዬሽን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ ፈተና እየሰጠ ነው።የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች የአቪዬሽን...
04/01/2025

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው ሀገሪቱ ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የአቪዬሽን ዘርፍ እንዲቀላቀሉ ፈተና እየሰጠ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች የአቪዬሽን ዘርፉን እንዲቀላቀሉ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ20ሺህ በላይ ለሆኑ አመልካቾች የጽሁፍ ፈተና እየሰጠ መሆኑን አስታውቋል።

የመግቢያ ፈተናው እየተሰጠ የሚገኘው በአዳማ ፣ አምቦ ፣ አርባ ምንጭ ፣ አሶሳ ፣ ባህር ዳር ፣ ደሴ ፣ ድሬዳዋ ፣ ጋምቤላ ፣ ጎንደር ፣ ሀዋሳ ፣ ጂግጂጋ ፣ ጅማ ፣ መቀለ ፣ ነቀምት ፣ ሮቤ ፣ ሰመራ ፣ ወልቂጤና አዲስ አበባ በሚገ ዩኒቨስርቲዎችና የፈተና ጣቢያዎች መሆኑን ነው አየር መንገዱ የገለፀው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላለፉት በርካታ አመታት አመቺ ትራንስፖርት በሌለባቸው ቦታዎችም ጭምር በሄሊኮፕተር ወደ ስፍራዎቹ በመጓዝ በሁሉም ማዕዘናት ያሉ ወጣቶች ብሔራዊ ሀብት የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቀላቅለው ራሳቸውን፣ አየር መንገዱን እና ሀገርን እንዲጠቅሙ ለማስልቻል ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

04/01/2025

የ10000 እና የ5000 ሜትር የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሞሀመድ ፋራህ ከቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር ጋር በለንደን።

"ኑ በዓለ ልደትን በቅዱስ ላሊበላ እናክብር፤ የበረከቱ ተከፋይም እንሁን" ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ወልድያ: ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ...
04/01/2025

"ኑ በዓለ ልደትን በቅዱስ ላሊበላ እናክብር፤ የበረከቱ ተከፋይም እንሁን" ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

ወልድያ: ታኅሣሥ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለልደት በዓል መልዕክት አሥተላልፈዋል።

በመልዕክታቸውም "በመላው ዓለም ለምትገኙ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን፣ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ" ብለዋል። በደብራችን በቅዱስ ላሊበላ እናንተን ለመቀበል ሁሉንም ሃይማኖታዊ ዝግጅት አከናውነናል፣ ቤተክርስቲያናችን መንፈሳውያን ልጆቿ ሲመጡ እግር በማጠብ ትቀበላለች ነው ያሉት።

ቤተክርስቲያን ሁሉንም ሃይማኖታዊ ዝግጅት ስላደረገች ከየትኛውም የዓለም ክፍል ያላችሁ ወገኖቻችን እግዚአብሔር በፈቀደላችሁ ልክ መጥታችሁ አብረን የጌታችን፣ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት
በዓልን በቅዱስ ላሊበላ እንድናከብር ጥሪያችን ይድረሳችሁ ብለዋል።

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዓለም አቀፍ በዓል ነው፣ በመላው ዓለም ያሉ ክርስቲያኖች እንደየ ሀገራቸው የዘመን አቆጣጠር ያከብሩታል ያሉት ብፁዕነታቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንም በመላ ሀገሪቱ በድምቀት ይከበራል፣ በቅዱስ ላሊበላ ደብር ደግሞ ከሌላው ደመቅ ብሎ ይከበራል ነው ያሉት።

የጌታ አገልጋይ ባለሟል ቅዱስ ላሊበላ ክርስቲያን ወገኖቻችን የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሊያከብሩ እንደሚያጓዙ ያውቅ ነበር፤ ብዙዎቹ በህመም እና በእርጅና መሄድ እያቃታቸው ከበረከቱ ተከፋይ መኾን ሳይችሉ ሲቀሩ አይቷልና በኢትዮጵያ ኢየሩሳሌምን የሚተካ ዳግማዊት ኢየሩሳሌምን ገንብቷል ብለዋል።

ወደ ቅዱስ ላሊበላ ደብር የመጣ፣ የተሳለመ፣ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ያከበረ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በቤተልሔም እንደተሳለመ ስለሚቆጠርለት ልደት በቅዱስ ላሊበላ ደብር ከሌሎች በበለጠ ደምቆ ይከበራል ነው ያሉት።

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ባለሟል የቅዱስ ላሊበላም የልደት በዓል ታኅሣሥ 29 በመኾኑ ተጨማሪ በዓል ነው፣ ጌታችን በመታዘዝ እና በማገልገል አርዓያ እና ምሳሌ የኾነን የቅዱሱ ልደት በዚሁ ቀን ይከበራልና በዓሉ ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ መልኩ ደምቆ እና ገንኖ ይከበራል ብለዋል።

ሁኔታዎች የፈቀዱላችሁ ሁሉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እና የባለሟሉን የቅዱስ ላሊበላ በዓለ ልደትን በአንድ ቀን፣ በአንድ ቦታ እንድናከብር ጥሪ እናቀርብላችኋለን ብለዋል።

በቀደመው ዘመን ኢትዮጵያውያን ለወራት ተጉዘው የልደትን በዓል በኢየሩሳሌም በቤተልሔም ያከብሩ እንደነበር የተናገሩት ብፁዕነታቸው ቅዱስ ላሊበላ ዳግማዊት ኢየሩሳሌምን ሲያዘጋጅም የትራንስፖርት አማራጭ አልነበረም፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች በእግራቸው እየመጡ ነው ሲያከብሩ የነበሩት ብለዋል።

በመድከማቸው፣ በመንከራተታቸው፣ የሚያገኙት ጸጋ እና ክብር አለ፣ ምክንያቱም አምላካቸውን በመውደድ የሚደረግ ስለኾነ ነው ብለዋል። ዛሬም ቢኾን የትራንስፖርት አማራጮች እያሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን በእግራቸው ወደ ቅዱስ ላሊበላ እንደሚመጡ ነው የተናገሩት።

መውጣት እና መውረዳቸው በአምላካቸው ፊት ዋጋ እንደሚያስገኝ ስለሚያምኑ ነው፣ በቤተክርስቲያን ደግሞ ታምኖ የተከፈለ ዋጋ ሁሉ ሰማያዊ ዋጋ ያስገኛል ነው ያሉት።

ብዙ ወገኖች በእግራቸው ተጉዘው ላሊበላ እየተገኙ ነው በዚህም የስጋ እና የነፍስን በረከት እንደሚያገኙ እናምናለን

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Social Media Network ኢትዮ ሶሻል ሚዲያ ኔትወርክ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share