ኦርቶዶክሳዊ ዕይታዎች

ኦርቶዶክሳዊ ዕይታዎች በአንድነት በሦስትነት ለሚመሰገን ለሥሉስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይሁን ።

የሕይወት ተስፋችን የተቀመጠው በሃይማኖት መዝገብ ላይ ነው።"ሃይማኖት እራሱን ለፍጥረቱ በገለጠ በእግዚአብሔር ተስፋ ለምናደርገው ማናቸውንም ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር ሁሉ የሚያስረ...
13/06/2025

የሕይወት ተስፋችን የተቀመጠው በሃይማኖት መዝገብ ላይ ነው።
"ሃይማኖት እራሱን ለፍጥረቱ በገለጠ በእግዚአብሔር ተስፋ ለምናደርገው ማናቸውንም ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር ሁሉ የሚያስረዳና የሚያስገነዝብ እውነታ ነው፡፡
(በተስፋችን የተቀመጠው በዚህ እውነታ ነው።)
ይኸውም ከሁሉ በፊት የነበረ ሁሉን አሳልፎ የሚኖር ፍጠረትን ሁሉ የፈጠረ ማንኛውም ነገር ካለመኖር ወደ መኖር ያመጣ ለእርሱ ግን አስገኝ አሳላፊ የሌለበት በአድነት በሦስትነት ያለ ሁሉን ቻይ የማይለወጥ አምላክ መኖሩን ማመን ነው፡፡ሃይ.መቅ.
በዚህ ማመን ስንጸና ምሥክርነታችን ይገለጻል ተስፋችንም ይጸናል።

11/06/2025

ጾመ ሐዋርያት፦ቅዱሳን ሐዋርያት መድኅን ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ በ፶ ቀን ካረገ በ፲ ቀን ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ወዲያው ሥራቸውን በጾም ጀምረዋል። መድኅን ክርስቶስ ....

ነገረ ክርስቶስ ክፍል፫የነገረ ክረሰስቶስ መሠረቱ ምሥጢረ ሥላሴ ነው።ክርስቶስ ተወለደ ለማለት ተፀነሰ ማለት ይቀድማል፣ተፀነሰ ለማለትም በነቢያት ትንቢት አናገረ ማለት ይቀድማል፣ትንቢት አናገረ...
11/06/2025

ነገረ ክርስቶስ ክፍል፫
የነገረ ክረሰስቶስ መሠረቱ ምሥጢረ ሥላሴ ነው።
ክርስቶስ ተወለደ ለማለት ተፀነሰ ማለት ይቀድማል፣ተፀነሰ ለማለትም በነቢያት ትንቢት አናገረ ማለት ይቀድማል፣ትንቢት አናገረ ለማለትም ሁሉን የፈጠረ ነው ማለት ይቀድማል፣ፈጠረ ከማለትም በቅድምና ነበረ ማለት ይቀድማል።
ምስጢረ ሥላሴን ባጭሩ ለመረዳት፦
፩ .የምንነሣ ከሃይማኖት ነው
፪.ሀልዎተ እግዚአብሔር
፫.ህላውና ሥላሴ(እግዚአብሔር በአካል)
፬.ህልውና አካላት(አንዱ አካል በአንዱ ህልው መሆን)
፭.ስመ አካላት(የማይፋለስ ስም)
፮.ሥላሴ በግብር(የባሕይ ግብር)
፯.አካላት በኩነት(የኩነት ስም)
፯.በኩነት ግብር(የኩነት ግብር)
፰.የባሕርይ አንድነት(ምልክና ሥላሴ)
፱.የአንድነት ሥራ..ናቸው።(ለፍጡራን በሆነው ሁሉየሚነገር)
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱ አንቀጾችን ለይቶ ለይቶ መረዳት መማር የነገረ ክርስቶስ ዋነኛ መሠረት ነው።

አብ ፍጹም አካል፣ፍጹም ገጽ፣ፍጹም መልክ፣ አለው።
በተለየ ስሙ አብ፣በተለየ ግብሩ ወላዲ አሥራጺ፣ በተለየ ከዊኑ ልብ በከዊን ግብሩ ልቡና ነው።
ልበነት በከዊን ስሙ ለራሱ ልቡና በከዊን ተገናዝቦ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ሲሆን።
አለባዊ ለፍጡራን ነው።
አለባዊነት የሦስቱም ያንዲት ባሕርይ ፈቃድ ግብር ናት።ችውም ከዘመን በኋላ በተገለጸው ለፍጡራን በሚደረግ ግብር ጊዜ ነው።

ወልድም ፍጹም አካል፣ፍጹም ገጽ፣ፍጹም መልክ፣ አለው።
በተለየ ስሙ ወልድ፣ በተለየ ግብሩ ተወላዲ፣ በተለየ ከዊን ስሙ ቃል ነባቢ ነው።በከዊን ተገናዝቦ ግብሩ ንባብ ነው፣ ቃል ነባቢ በከዊን ስሙ ለራሱ ነው።
ቃላቸው ንባብ መሆን በከዊን ተገናዝቦ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ነው።
አንባቢ ለፍጡራን ነው።ይኸውም ለዘለዓለሙ ኑሮ ኑሮ ኃይሉን በገለጸበት አፍአዊ ፍጥረት ላይ ለፍጡራን በሚደረግ ያንዲት ባሕርይ የፈቃድ ግብር ጊዜ ነው።
የሥስቱም የመፍጠር ግብር ነው።

መንፈስ ቅዱስ ፍጹም አካል፣ፍጹም ገጽ፣ፍጹም መልክ፣ አለው።
በተለየ ስሙ መንፈስ ቅዱስ፣በተለየ ግብሩ ሠራጺ፣ በተለየ ከዊን ስሙ ሕይወት በተገናዝቦ ከዊኑ ሕይወትና ወይም ሕይወተ አብ ወወልድ ነው።
ሕይወት ለራሱ፣ሕይወትና በከዊን ተገናዝቦ ለአብና ለወልድ ነው።
ማሕየዊ ለፍጡራን ይህም ካላይ በአብና በወልድ እንዳየነው በፍጡራን ላይየተገለጸ ያንዲት ባሕርይ የፈቃድ መገለጫ ግብር ነው።

ማሕየዊነት ለፍጡራን ስለሆነ የሦስቱም ነው።
ምክንያቱም
አብ ልቤን፣ ወልድ ቃሌን፣ መንፈስ ቅዱስ ሕይወቴን ፈጠረልኝ አንልምና።
ለምን ቢባል?መፍጠር ያንዲት ባሕርይ የፈቃድ ግብር ስለሆነ ነው።
በመጻሕፍት ንባብ ጊዜ በፍጥረት ግብር ላይ ከሦስቱ ላንዱ ካንዱ ለሦስቱ ለይቶ የሚናገር ቢኖር አድሎ ሰጥቶ መናገር ልማደ መጻሕፍት ስለሆነ ነው።
በፍጡራን ላይ የተገለጸው የሥላሴ ሥራ ያንድነት ግብር ስለሆነ ላንዱም ለሦስቱም ቢሰጥ ምስጢር አይፋለስም።
አምላክ ሰው ሆነ ለማለት አንድነቱን ሦስትነቱን መረዳት ይቀድማል።

ግሩም ትምህርት
11/06/2025

ግሩም ትምህርት

የእውነት ክርስቲያን ነህ?
፦አንድ እግዚአብሔር ያለው ኦርቶዶክሳዊ ነህ? ኤፌ.፬፥፭
፦አንድ እናት አንድ አባት ያለው ጥሙቅ ነህ? ማር.፲፮፥፲፮
፦አንድ ሙሽራ ያላት አንዲት ሙሽሪት ነህ? ማቴ.፳፪፥፩-፯
፦አንድ መምህር ያላት አንዲት ደቀመዝሙር ነህ? ማቴ.፳፰፥፲፱
፦አንድ መሥዋዕት ያላት አንድ ተቀባይ ነህ?፤ ዕብ.፩፥፩፣ዮሐ፮፥፶፮
፦አንድ ክህነት ያላት አንድት ተባራኪ ነህ? ማቴ.፲፮፥፲፰
፦አንድ ራስ ያላት ህዋስ ነህ? ቆላ.፩፥፲፰
፦ከማይጠፋ ዘር የተወለድህ ልዩ አካል ነህ?፤ ዮሐ.፫፥፬
፦አንድ ዐላማ ያላት ተስፈኛ ነህ?፤ (ግዕዝ ርትዕት) ማቴ.፲፫፥፮
፦ግእዛን ያላቸው ፍጥረታት እና የፈጣሪ ግንኙነት ኅብረት ባለቤት ነህ?
፦አንድ ቀዛፊ ብዙ ተሳፋሪ ባያላት መርከብ ውስጥ ነህ?ዘፍ.፮፥፲፭
፦አንድ የክርስቶስን መስቀል የተሸከምህ ክርስቶሳዊ ነህ? ማቴ.፲፮፥፳፬
፦ሐዋርያዊት፣ቅድስት፣አንዲት፣ኲላዊት በሆነች ቤተ ክርስቲያን ሥር ነህ? ማቴ.፲፰፥፲፯....ይሄንን ሁሉ ከሆንህ በጣም ጥሩ።
ክርስቲያን ከሆንህ እያደረግህ ያለኸው ምንድን ነው?
እየመከርህ ያለኸው ከማን ጋር ነው?
በቤተ ክርስቲናን ላይ እየሆነ ያለውን እንዴት ታየዋለህ?
ክርስቲዮኖቹ ሁሉ አካሌ ናቸው ብለህ ታስባለህ?
ትንሣኤ ሙታንን የማምን ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ ብለህ ታስባለህ?
የምኖርበት ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ነው ብለህ ታምናለህ?
የምታምነውና የምትኖረው አንድ ነው? አፍህና ልብህ የተስማሙ ናቸው?
የእውነት የክርስቶስን መስቀል የተሸከመ ክርስቲያን ነህ?
በመንደር፣በቋንቋ፣በጎሳ፣በሥሁት ፖለቲካ፣በአስመሳይነት፣በግብዝነት፣በስግብግብነት ውስጥ የለህበትም?
አንድ ክርስቶሳዊ ወንድምህን ስታይ ክርስቶስ ይታሰብሀል?
የቤተ ክርስቲያን መዋረድ፣መሳደድ፣በመንደርተኞች ምክንያት መለያየት፣የቀኖናው መጣስ፣የምእመናን መከራ ያስጨንቅሀል?
የእውነት ክርስቲያን ነህ?

ነገረ ክርስቶስ መግቢያ፦          (ክፍል፪)የክርስትና አስተምህሮ ተጠቅልሎ ሲታይ በዋናነት ከዚህ በታች በተቀመጡ ጉዳዮች ላይ የጸና አስተምህሮ ነው፦1.)ተከሥቶአዊ ነው።2.)ቅዱሳዊ ነው...
10/06/2025

ነገረ ክርስቶስ መግቢያ፦
(ክፍል፪)
የክርስትና አስተምህሮ ተጠቅልሎ ሲታይ በዋናነት ከዚህ በታች በተቀመጡ ጉዳዮች ላይ የጸና አስተምህሮ ነው፦
1.)ተከሥቶአዊ ነው።
2.)ቅዱሳዊ ነው።
3.)ኅብረታዊ ነው
4.)ቅብብሎሻዊ ነው።
5.)ዕቅበታዊ ነው።
6.)ቅብብሎሻዊ ነው
7.)ዘለዓለማዊ ነው
1.) ተከሥቶአዊ ነው ማለት፦
የክርስትና አስተምህሮ ተከሥቶአዊ ነው ማለት በሰው ፈቃድ ያልተሠራ ከባለቤቱ ከእግዚአብሔር ለቅዱሳን የተገለጠ እውነት ነው ማለት ነው።
በባሕርዩ ልዑል ሥውር የሆነው እግዚአብሔር ፍጥረቱን ፈጥሮ እንዲሁ የተወው አይደለምና ስሙን ቀድሰው ክብሩን ወርሰው ይኖሩ ዘንድ ራሱን ለሕያዋን ፍጡራን ለመላእክት እና ለደቂቀ አዳም ገልጿል።
2.)ቅዱሳዊ ነው ማለት፦
ይህ የተከሥቶ ወይም የመገለጥ አስተምህሮ የምንለው የተገለጠው ለቅዱሳን ነው እንጂ ለሥጋውያን ለደማውያን አይደለም ማለት ነው።
በመጀመሪያ ለቅዱሳን መላእክት፣ቀጥሎ ለቅዱሳን አበው፣ቀጥሎ ለቅዱሳን ነቢያት፣ቀጥሎ ለቅዱሳን ሐዋርያት የተገለጠ እውነት ነው።ከሁሉም በላይ ፍጻሜው የቅዱሳን ሐዋርያት ነው።እንደ ቀድሞው በረድኤት ያይደለ በኩነት ተገልጾላቸዋልና።
3.)ኅብረታዊ ነው ማለት፦
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ነገር በሙሉ ኅብረታዊ ነው ማለት ነው።
ሁሉም ነገር የሚወሰነው በኅብረታዊ ጉባኤ ብቻ ነው።የመላእክት ኅብረት፣የነቢያት ኅብረት፣የሐዋርያት ኅብረት፣ተጠቃሎ የቤተ ክርስቲያን ኅብረት ይባላል።ሁሉም ከኅብረቱ በታች ነው።ኅብረቱ ግን ከሁሉም በላይ ነው።መዳን የሚቻለውም በዚህ ኅብረት ብቻ ነው ማለት ነው።
4.)ቅብብሎሻዊ ነው ማለት፦
ከላይኞቹ የኅብረት አባቶቻችን የምንቀበለው አስተሳስብ ነው እንጂ በግል ፈቃዳች የምንለዋውጠው አስተሳስብ አይደለም ማለት ነው።ከተቀደሰው ከሐዋርያት ጉባኤ የተቀበልነው እውነት ስለሆነ ዘመን በወለደው ንጉሥ በወደደው አይቀየርም ማለት ነው።
5.)ዕቅበታዊ ነው ማለት፦
ከኅብረቱ በኅብረት የተቀበልነውን የአስተምህሮ እውነት ሰው ሠራሽ ፈቃድ፣ኑፋቄ፣ፍልስፍና፣ክህደት..እንዳይጨመርበት በምሥክርነት የምንጠብቀው እውነት ነው ማለት ነው።በምድር የምንኖርበት ዘመን ሁሉ በዕቅበተ ሃይማኖት እና በዕቅበተ ሕይወት ላይ የተመሠረተ ነው።
6.)ቅብብሎሻዊ ነው ማለት፦
እኛ ከላይኞቹ በኅብረት እንደተቀበልነው እኛም ከእኛ ቀጥሎ ለሚነሡ ትውልዶች ሁሉ"የሰጠኝን ሰጠሁህ"እያልነ የምናስረክበው የአደራ ሃይማኖት ነው ማለት ነው።በዚህ ቅብብሎሽ ከመጀመሪያዎቹ እስከ እኛ እንደመጣ በዚሁ ቅብብሎሽ ከእኛ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ መድረስ አለበት ማለት ነው።
7.)ዘለዓለማዊ ነው ማለት፦
ኦርቶዶክሳዊነት በተስፋ መንግሥተ ሰማያት የተሞላ አስተምህሮ ስለሆነ ከሞት በኋላ ባለው የትንሣኤ ሕይወት በጸጋ በክብር ማኖር የሚችል እውነት ነው ማለት ነው።ኦርቶዶክሳዊነት ዛሬ በጅማሬው ኑረንበት የሚያበቃ አይደለም።ይልቁንም ፍጹም ወደ ሆነው መላእክታዊ ሕይወት የምናድግበት የዘለዓለም ተስፋ ነው እንጂ።

የነገረ ክርስቶስ መግቢያ፦            (ክፍል፩)በዘላቂነት በትምህርቱ ውስጥ የምናገኛቸው፦፩.)ንባብ፣፪.)ትርጉም፣፫.)አረዳድ፣፬.)ኅብረት፣ ፭.)ምሥጢር፣፮.)ሕይወት፣፯.)ጸጋ ክብር፣፰....
09/06/2025

የነገረ ክርስቶስ መግቢያ፦
(ክፍል፩)
በዘላቂነት በትምህርቱ ውስጥ የምናገኛቸው፦
፩.)ንባብ፣
፪.)ትርጉም፣
፫.)አረዳድ፣
፬.)ኅብረት፣
፭.)ምሥጢር፣
፮.)ሕይወት፣
፯.)ጸጋ ክብር፣
፰.)ዘለዓለማዊነት ናቸው።
፩.)ነባብ ማለት፦
በምንም አይነት ሁኔታ ይሁን ስለ አንድ መንፈሳዊ ጉዳይ የምንናገኘው የመጀመሪያው ክፍል ንባብ፣ዘር፣ገጽ፣ጥሬ ይባላል።ስለ ሆነም ከንባብ የሚቀድም ምሥጢር ስለሌለ ቀድመን የምንሰማው ኃይለ ቃል ንባብ ነው።ያ ንባብ ወደ ሁሉም አቅመ ትርጉሞች አድጎ እስኪፈጸም ድረስ መጓዝ መከተል ግድ ይለናል ማለት ነው።
፪.) ትርጉም ማለት፦
ቃል በቃል ያነበብነው ጥሬ ቃል ሲያድግ የሚያገኘው ሂደት ትርጉም ነው።ጥሬ ቃሉ ሲፈጭ ወይም ከንባብነት ደረጃ ወደ መብራራት ሲያልፍ ትርጉም ይባላል።ትርጉም የሌለው ኃይለ ቃል፣ኃይለ ቃል የሌለው ትርጉም የለም ማለት ነው።
፫.) አረዳድ ማለት፦
አንድን ጥሬ ዘር ወደ ትርጉም ካሳደግነው በኋላ ያ ትርጉሙ የሚሰጠን መረዳት ትርጉማዊ አረዳድ ይባላል።ንባቡን መተርጎም ያስፈለገው ለመረዳት ስለሆነ ያለ አረዳት ርቱዕ ኦርቶዶክሳዊነት ሊጸና አይችልም ማለት ነው።
፬.)ኅብረት ማለት፦
ኅብረት የምንለው ርቱዕ አረዳድ የሚገኝበትን ጉባኤ ነው።በኦርቶዶክሳዊነት ውስጥ የግል ንባብ፣የግል ትርጉም፣የግል አረዳድ የለም።
ሁሉም ነገር የሚወሰነው በኅብረታዊት ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ነው ማለት ነው።
ወይም የግል መረዳት የሚባል የለንም።የሐዋርያዊት ጉባኤ አረዳድ አንድነት ነው ያለን ማለት ነው።
፭.)ምሥጢር ማለት፦
ምሥጢር የምንለው ከላይ የተጻፉ ዝርዝሮች ሁሉ የሚካተቱበት ሃይማኖተ ቃል ነው።ወይም ከባለ ቤቱ ከእግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተገለጸውን የተከሥቶ ሃይማኖት መጠበቅ ማለት ነው።የንባብም፣የትርጉምም፣የአረዳድም፣የኅብረታዊነትም ዓላማ ምሥጢር ለመጠበቅ ነው።የምሥጢር ዳኅጽ ኑፋቄ ስለሆነ ማለት ነው።
፮.)ሕይወት ማለት፦
ሕይወት የሚባለው ከላይ ባየናቸው ነገሮች ሁሉ ራስን በኦርቶዶክሳዊ ሕይወት ማኖር መቻል ማለት ነው።ቃለ እግዚአብሔር የምትኖረው ዕውቀት እንጂ የምታውቀው ብቻ አይደለምና።
እያንዳንዷን ንባብ ወደ ትርጉም፣እያንዳንዷን ትርጉም ወደ አረዳድ፣እያንዳንዷን አረዳድ ወደ ኅብረት፣እያንዳንዷን ኅብረታዊ አረዳድ ወደ ምሥጢር፣እያንዳንዷን ምሥጢር ወደ ሕይወት እናሳልፋለን ማለት ነው።
፮.)ጸጋ ክብር ማለት፦
ጸጋ ክብር ማለት ከላይ ጀምረን በተዘረዘረው መሠረት ቃሉን በሕይወት ስንኖርበት ጸጋ ክብር እናገኛለን ማለት ነው።የእግዚአብሔር ቃል ተረድቶ ለሚያደርገው ሁሉ በጸጋ በክብር የሚያሳድግ፣በልጅነት የሚያከብር፣በዚህ ዓለም የጸጋ አማልክት የሚያሰኝ፣በወዲያው ዓለም "በጎ አገልጋይ ታማኝ ባሪያ"የሚያስብል ስለሆነ ነው።
፯.)ዘለዓለማዊነት ማለት፦
ሰው የተፈጠረው ስሙን ቀድሶ ክብሩን ወርሶ ለዘለዓለም ሊኖር ነው።የእግዚአብሔርን ቃል ከላይ በዘረዘርናቸው መሠረት ጠብቆ ለሚኖር ሰው ሁሉ ሞት በሌለው ሕይወት ውስጥ ያኖራል።የእግዚአብሔርን ቃል ሕግ አድርጎ ሕያውነት ያገኘ ሰው በቃለ እግዚአብሔር ምክር የሚኖር ብቻ ያይደለ ራሱን እግዚአብሔርን በማይለይ የጸጋ ተዋሕዶ ተዋሕዶት ለዘለዓለም ይኖራል ማለት ነው።

አስተውሉ፦
ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ርቱዓዊ ኦርቶዶክሳዊ መረዳት የምናገኝባቸው መንገዶች ናቸው።
ወይም ርቱዕ መረዳትን ስናገኝ የምናገኘው መልክአ ሀሳብ ይሄ ነው ማለት ነው።

ጰራቅሊጦስ
08/06/2025

ጰራቅሊጦስ

የዕለቱ ወንጌል
ስለ በዓለ መንፈስ ቅዱስ (ጰራቅሊጦስ)

17፤ ኢየሱስም፦ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ፦ እኔ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ፡ ብለሽ ንገሪአቸው፡ አላት።

ጌታ ኢየሱስ “ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ ዓርጋለሁ” አለ.. “አባቴ” ብሎ ለይቶ ተናገረ አመላክ እንደመሆኑ እርሱ ብቻውን የባህሪ ልጁ ነውና.. “አምላኬ” አለ የእኛን ሥጋ ይዟልና ነው.. ይህም የሱ የሚየው በፈቃዱ ያደረገው መሆኑ ነው.. ሰውን ወድዶ ራሱን ዝቅ አድርጎ በፈቃዱ የባርያን መልክ ይዟልና ሰው እንደመሆኑ አንዱ ጌታ ኢየሱስ “አምላኬ” ይለዋል አብን..

“አላረግሁም” አለ.. አንድ የገባላቸው ቃል አለ ይህም ወደ አብ ቢሄድ ቅዱሱን መንፈስ እንደሚልክላቸው ነው.. እና አላረገምና ያ አልተፈጸመም ነው..

ካረገ በኋላ ግን ቃል እንደገባው መንፈሱን ላከ.. በመንፈሱም አሰራር ቤተ ክርስቲያንን ወለደ.. ዛሬ ይህ ቅዱስ መንፈስ የወረደበትን ቀንን እና የቤተ ክርስቲያናችንን ልደት የምናስብበት ቀን ነው.. ጌታ መንፈሱን ባፈሰሰባት በአካሉ ማለትም በቤተ ክርስቲያን ያጽናን.. መንፈስ ቅዱስ ሁላችንን ይርዳን..

መንፈስ ቅዱስ አዳኝ ሕይወትን የሚሰጥ ጌታ ነው.. መንፈስ ቅዱስ ክርስቶስን በመምሰል ሕይወት ውስጥ እንድናድግ የሚረዳን በዓለም እና ሥጋ ላይ የሚያስጨክነን ነው.."

ዮሐ 20

በራሳቸው ሀገር ቸርቾቻውን በእንዲህ መልኩ እያረከሱ  እኛ ጋር መጥተው መለኮታዊ ጉብኝት ምናምን ይላሉ።  ምን እንበላቸው?
09/03/2025

በራሳቸው ሀገር ቸርቾቻውን በእንዲህ መልኩ እያረከሱ እኛ ጋር መጥተው መለኮታዊ ጉብኝት ምናምን ይላሉ። ምን እንበላቸው?

Viea ድሬ ትዩብ  #ከግማሽ ክፍል ዘመን በላይ ያለምንም ምግብዓይናችን በገለጽንበት ቅጽበት ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፈው ሁሉ አባታችን በተወለዱ ጊዜ አንደበታቸው ከምስጋና የተገኘ፣ ስለ...
12/02/2025

Viea ድሬ ትዩብ

#ከግማሽ ክፍል ዘመን በላይ ያለምንም ምግብ

ዓይናችን በገለጽንበት ቅጽበት ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፈው ሁሉ አባታችን በተወለዱ ጊዜ አንደበታቸው ከምስጋና የተገኘ፣ ስለሀገራችን መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው የጸለዩ፣ ገና በሕጻንነት በ3 ዓመታቸው በገዳም መኖር የጀመሩና ከማሕጸን ጀምሮ ለመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የተለዩ፣ ከተወለዱ ጀምሮ እህል ያልቀመሱ፣ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩ፣ ከጌታችን ጋር መሞት አይገባኝም ብለው የተከራከሩ ታላቅ ቋድቅ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ፡፡

ትውልዳቸው ግብጽ ንሒሳ ውስጥ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ሠላሳ ሦስት ዓመት በትዳር የቆዩት ቅዱሳን በሩካቤ ስጋ የተዋወቁት ለሦስት ቀናት ብቻ ነው፡፡ ይህም ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን እየለመኑ ነው፡፡

በተጋቡ በሰላሳ ዘመናቸው አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን “ክብሩና ሥልጣኑ ከሰማይ ከፍታ ከፍ የሚል ንጽሕናው ከሚካኤል ከገብርኤል የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነቢዩ ኤልያስ የሆነ ልጅ እንቺ ተቀበይ” የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ መጋቢት 29 ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገዶ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምም ባረከችው ቅዱሳን መላዕክት ዘወትር ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡
ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን አባ ዘመደ ብርሃን የተባሉ አባት ወዳሉበት ገዳም ሰጠው፡፡ እርሳቸውም ሕፃኑን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማረ በእንክብካቤ አሳደጉት፡፡ ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ሰጡት፡፡ ፍጹም የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሆነ፡፡ አባ ዘመድ ብርሃንም እንደ ቅዱስ እንጦንስ አስኬማን ሰጡት፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ ወደ ሰማያት አርገው በረከትና ጸጋ የተቀበሉ፣ አጋንንትን የሚያሳድዱ፣ ድውያንን የሚፈውሱበት ታላቅ ታላቅ ጸጋ ተሰጣቸው፡፡

ከሰው ተለይተው ወደ ጫካ ገብተው ከስድሳ አንበሶችና ከስድሳ ነብሮች ጋር የሚኖሩት አባታችን፣ እንስሳቱ እርሳቸውን የረገጡትን መሬት ልሰው ጠግበው ይኖራሉ፡፡ ሰውነታቸው አንድ ክንድ ከስንዝር በሚረዝም ጠጉር የተሸፈነው አባታችን ከትውልድ ሀገራቸው ወደ ሀገራችን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ገዳማቶቻቸው ወዳሉባቸው ወደ ምድረ ከብድና ወደ ዝቋላ ተራራ ወሰዳቸው፡፡ በእነዚህ ገዳማት እየተመላለሱ ሲጸልዩና ሀገራችንን ሲባርኩም ኖረዋል፡፡ ሰው የገዛ ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ በሀገራች ያለውን የኃጢአት ስራ ባዩ ጊዜ በዝቋላ ሐይቅ አንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው መላው ኢትዮጵያንእንዲምርካቸው ጸልየው ቃል ኪዳን ተቀብለዋል፡፡ ገዳማትንና ገዳማውያንን እያሰብን ከበረከታቸው እካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

+++ +እንደ ነነዌ ሰዎች++++    ነነዌ !‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳ...
09/02/2025

+++ +እንደ ነነዌ ሰዎች++++

ነነዌ !

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሦስት ቀን ጾም የጾሙት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው (ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪)፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የሆነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር፡፡ በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶ ነበር (ዮናስ ፬፥፲፩)፡፡ እንግድህ በዚህች ጥንታዊ ከተማ ነው ይህ ታርክ የተፈፀመው ።

ነነዌ በአሁኑ ጊዜ የኢራቅ ክፍል የሆነች ጥንታዊት ከተማ የነበረች ናት ። እግዚአብሔር ዮናስን ወደ ነነዌ ሄዶ ስለ ኃጢአቸውና ስለ መተላለፋቸው ንስሐ እንዲገቡ መልዕክት ላከባቸው ። ነነዌ ከእግዚአብሔር ፊት እንደምትጠፋ ፣ ንሰሐ ካልገቡ በነነዌ ያለው ህዋሳት ሁሉ እንዲሚጠፉ ዮናስ ነገራቸው ።

"ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ የምነግርህንም ስብከት ስበክላት አለው። ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም የሦስት ቀን መንገድ ያህል እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች።"
ዮናስ ከብዙ ማንገራገር በኋላ ነበር እግዚአብሔር ወደ ላከው ወደ ነነዌ ለመኸድ የወሰነው።

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው፡፡ ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይሆን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ፡፡ የነነዌ ሰዎች የተነሳሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ሆኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ነው፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ሁሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች (አስ.፬፥፲፭-፲፮)፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች (ሉቃ.፪፥፵፮)፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መሆኑን ገልጿል (ሉቃ.፲፫፥፴፪)፡፡

ስለዚህ ዮናስን በልዩ ጥበብ ያስተማረ አምላክ እኛንም በይቅርታው ሁሌም ይጠራናል ። እንድሁም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመሆኑንም በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ሆነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡ ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ፣ ከመከራና ስደት ፣ ከሞትና መፈናቀል ፣ ከጦርነትና ግጭት ቅዱስ እግዚአብሔር ይጠብቀን ፡፡

የቅዱሰን በረከት ፣ የእግዚአብሔር ቸርነት በሁላችን ላይ ይሁን ።

የበረከት ፆም ያድርግልን!!!

ዛሬ ተነበበው የወንጌል ክፍል.....የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር...
02/02/2025

ዛሬ ተነበበው የወንጌል ክፍል.....

የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤
ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።

ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤
ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤
የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።
እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው።

እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም። ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።
ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።

ሉቃ 2:42-52

ሠናይ ዕለተ ስንብት 🙏🙏🙏

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኦርቶዶክሳዊ ዕይታዎች posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኦርቶዶክሳዊ ዕይታዎች:

Share