Harari Mass Media Agency

  • Home
  • Harari Mass Media Agency

Harari Mass Media Agency Harari Mass Media Agency is a public media operating in Harar, Ethiopia.
ገፃችንን በመከተል ትኩስ ዜና እና መረጃዎችን ያገኛሉ።

የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት ********የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምስራቅ ሪጅን ቁጥር 3 ሰብስቴሽን ላይ ከቀን 09/12/2017 ዓ.ም እስከ ቀን 12/12/2...
15/08/2025

የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
********
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምስራቅ ሪጅን ቁጥር 3 ሰብስቴሽን ላይ ከቀን 09/12/2017 ዓ.ም እስከ ቀን 12/12/2017 ዓ.ም ድረስ ፓወር ትራንስፎርመር ላይ ታፕ ቼንጀር የማስተካከል ስራዎች ስለሚከናወን በዚህ ምክንያት በሐረር ቁጥር 2 ሰብስቴሽን ላይ የኃይል ዕጥረት ስለሚኖር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ በፈረቃ ስለሚበራ ክቡራን ደንበኞቻችን ቅድመ ጥንቃቄ እንድታደርጉ በትህትና እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

9/12/2017

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀመራል።*********በአለም ዙሪያ ወደ 4 ቢሊየን የሚጠጉ ደጋፊዎች እንዳሉት የሚነገርለት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ሊቨርፑ...
15/08/2025

ተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ዛሬ ምሽት ይጀመራል።
*********
በአለም ዙሪያ ወደ 4 ቢሊየን የሚጠጉ ደጋፊዎች እንዳሉት የሚነገርለት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ሊቨርፑልና ቦርንማውዝ በሚያደርጉት ጨዋታ አንድ ብሎ ይጀምራል።

ክለቦች በአዲሱ የውድድር ዘመን ጠንካራ ሆኖ ለመቅረብ በርካታ የአቋም መለኪያ ጨዋታዎችን ከማድረግ ጀምሮ ረብጣ ገንዘብ አውጥተው ተጫዋቾችን አስፈርመዋል፡፡

ክለቦች ካስፈረሟቸው ተጫዋቾች አንጻር ለዋንጫ የሚደረገው ፉክክር ከቀደሙት አመታት እጅግ ጠንካራ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

የሊጉ ሻምፒዮን ሊቨርፑል እስከ አሁን ከ280 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ወጭ አድርጎ ልዩነት ፈጣሪ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

እንደ ቼልሲ እና ማንቼስተር ሲቲ አይነት ክለቦች ደግሞ ከሊጉ መጠናቀቅ በኋላ በክለቦች ዓለም ዋንጫ ውድድር የተሳተፉ ሲሆን ቼልሲ በፍጻሜው ፒኤስጂን በማሸነፍ ዋንጫውን ማንሳቱ የሚታወስ ነው፡፡

የፕሪሚር ሊጉ ክለቦች ባለፈው ዓመት የነበረባቸውን የቡድን ክፍተት ለመሙላት በርካታ ሚሊየን ፓውንድ በማውጣት በዝውውር መስኮቱ እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ታላላቆቹ ሊቨርፑል፣ ቼልሲ፣ አርሰናል እና ሁለቱ የማንቼስተር ከተማ ክለቦች በዝውውር መስኮቱ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ የሚገኙ ክለቦች ናቸው፡፡

የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በክረምቱ የዝውውር መስኮት እስካሁን ድረስ ጀርሚ ፍሪምፖንግ፣ ሚሎዝ ኬርኬዝ፣ ጆርጂ ማማርዲያሻቪሊ እና ፍሎሪያን ዊርትዝን አስፈርሟል፡፡

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ሊያም ዴላፕ፣ ኢስቴቫኦ ዊሊያን፣ ጄሚ ጊተንስ፣ ዮሬል ሀቶ፣ ዦአዎ ፔድሮ የመሳሰሉ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል፡፡

ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በሊጉ 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው አርሰናል ቪክተር ዮኬሬሽ፣ ኖኒ ማዱኬ፣ ክርስቲያን ኖርጋርድ፣ ክርስቲያን ሞስኬራ እና ማርቲን ዙቢሜንዲን በማስፈረም ይበልጥ ቡድኑን አጠናክሮ ለአዲሱ የውድድር ዘመን ቀርቧል፡፡

በ2024/25 የውድድር ዓመት ደካማ የውድድር ዘመን ያሳለፈው ማንቼስተር ዩናይትድ በበኩሉ ማቲያስ ኩና፣ ዲዮጎ ሊዮን፣ ብሪያን ምቤሞን እና ቤንጃሚን ሼሽኮን በማስፈረም ቡድኑን የማጠናከር ስራ ሰርቷል፡፡

ወደ ሊጉ የተመለሰው ሰንደርላንድ በዝውውር መስኮቱ በንቃት ከተሳተፉ የሊጉ ቡድኖች መካከል አንዱ ሲሆን ግራኒት ዣካን ጨምሮ ሰባት ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

ከወራት በኋላ ዛሬ ምሽት የሚመለሰው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ስታዲየም ቦርንማውዝን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጀመራል፡፡

የመጀመሪያ የመክፈቻ ጨዋታውን ከአምናው ሻምፒዮን ሊቨርፑል ጋር የሚያደርገው ቦርንማውዝ ግብ ጠባቂውን ኬፓ አሪዛባላጋን ጨምሮ ተከላካዮቹን ሚሎስ ኬርኬዝ፣ ዲን ሁይሰን እና ዛባርኒን ለሌሎች ክለቦች አሳልፎ ሰጥቷል፡፡

የፊታችን እሁድ ማንቼሰተር ዩናይትድ ከአርሰናል በኦልድትራፎርድ የሚያደርጉት ጨዋታ ደግሞ የፕሪሚየር ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ከፍተኛ ግምት የተሰጠው ጨዋታ ነው፡፡

የዘ አትሌቲክ ፀሐፊዎች የ2025/26 የውድድር ዓመት የሊጉን ዋንጫ የአምና የሊጉ አሸናፊ ሊቨርፑል በድጋሚ እንደሚያነሳ ግምታቸውን ያስቀመጡ ሲሆን አርሰናል፣ ማንቼስተር ሲቲ እና ቼልሲ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ያጠናቅቃሉ ሲሉም አመላክተዋል፡፡

በ2024/25 15ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ማንቼስተር ዩናይትድ ደግሞ በዚህኛው የውድድር ዘመን 8ኛ ደረጃን ይዞ ይጨርሳል በማለት የዘ አትሌቲክ ፀሐፊዎች ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

9/12/2017

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ እያመረቱ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ጎበኙ*********ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሐዋሳ...
15/08/2025

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ እያመረቱ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ጎበኙ
*********
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ እያመረቱ የሚገኙ ፋብሪካዎችን ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በቬይትናም የቶዮ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ በነበረን ጉብኝት እና ከኩባንያው ፕሬዝደንት ጋር በነበረን ውይይት የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫዎችን በሀገራችን ለማምረት ተስማምተን ነበር ብለዋል።

ዛሬ በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ በነበረን ጉብኝት በፓርኩ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጪያዎችን እያመረቱ በመመልከታችን ደስታ ተሰምቶናል ሲሉም ገልጸዋል።

ማምረቻው በከፍተኛ ጥራት ከፍተኛ ምርት የማምረት አቅም የተላበሰና በዘመናዊ የማሽን ሥርዓት የሚሰራ ሲሆን የምርት ውጤቱ ለማኑፋክቸሪንግ የውጪ ንግድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ይጠበቃል ብለዋል።

ሁለት ተጨማሪ ማምረቻዎች በግንባታ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ወደ ምርት የገባውን ማምረቻ ሥራ ሂደት ተመልክተናል ነው ያሉት።

ይኽ ሥራ እሴት የተጨመረባቸው እና ያስቀመጥናቸውን ግቦች እና ፖሊሲዎች የሚያሳኩ ጨዋታ ቀያሪ ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ከሚያደርገው የኢንቨስትመንት ስትራቴጂያችን ጋር የተጣጣመ ነው ብለዋል።

9/12/2017

15/08/2025

በአጫጭር ስልጠናዎች ለላቀ ውጤት እየተጋ ያለው ተቋም

15/08/2025

የቶዮ የፀሐይ ብርሃን ኃይል ማመንጫ ፋብሪካ በሐዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ።

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች ናቸው፦ ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን**********በኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን የተመራ ልዑካን ቡድን በክልሉ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ...
15/08/2025

በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች ናቸው፦ ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን
**********
በኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን የተመራ ልዑካን ቡድን በክልሉ የተከናወኑ እና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

ኮሚሽነሩ እንደገለፁት በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸዉን በመግለፅ ለሌሎች ክልሎችም እንደ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን አክለዋል።

ወደ ክልሉ ባለሀብቶችን በመጋበዝ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት እንደሚሰሩ አክለዋል።

ልዑካን ቡድኑ የሁለት ሚሊየን ብር ግምት ያላቸዉ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን የተመራዉ ልዑካን ቡድን የአባድር ፕላዛ ግንባታ፤ የጀጎል አለም አቀፍ ቅርስ ፤ የሐረር ቢራ ፋብሪካን ተዘዋዉረዉ ጎብኝተዋል።

ዘጋቢ :- አብስራ አሰግድ
09/12/17

በሀረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ይበልጥ ለማነቃቃት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፦ አቶ ኦርዲን በድሪ  **********የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የኢትዮጵያ ኢን...
15/08/2025

በሀረሪ ክልል የኢንቨስትመንት ዘርፉን ይበልጥ ለማነቃቃት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፦ አቶ ኦርዲን በድሪ
**********

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን ጋር በፅ/ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይቱም ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የኢንቨስትመንት ዘርፉን ይበልጥ ለማነቃቃት ከልማት ስራዎች ጋር በማያያዝ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በተለይ ዘርፉን በሚጠበቀው ልክ ለማጎልበት የህግ ማሻሻያ ከማድረግ ጀምሮ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አክለዋል።

በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለ ሀብቶች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር አስፈላጊው ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በቀጣይም ተቋሙ የተሰጠውን ተልዕኮ ሊወጣ የሚያስችለው ቁመና እንዲኖረው ይበልጥ ለማደራጀት እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዘለቀ ተመስገን በበኩላቸው ባለ ሀብቶችን በመጋበዝ በክልሉ ያለውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ ለማነቃቃት እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ በሀረሪ ክልል ለሚገኙ አቅመ ደካማ ቤተሰብ ተማሪዎች ድጋፍ የሚውል የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ለርዕሰ መስተዳድሩ አስረክበዋል።

9/12/2017

የኢናይ አቢዳ የዕደ ጥበብ ኮሌጅ ተማሪዎች በክረምት ግዜ ከአልባሌ ቦታ እንዲቆጠቡ ትልቅ አሰተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ ። ***************************በኢናይ አቢዳ የ...
15/08/2025

የኢናይ አቢዳ የዕደ ጥበብ ኮሌጅ ተማሪዎች በክረምት ግዜ ከአልባሌ ቦታ እንዲቆጠቡ ትልቅ አሰተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ ።
***************************

በኢናይ አቢዳ የዕደ ጥበብ ኮሌጅ በክረምት መርሀግብር ሲሰለጥኑ ያገኘናቸው ሰልጣኞች እንደገለፁት በኮሌጁ ከዘጠኝ በላይ ሞያዎች እንዳሉ ገልፀዋል ።

በዚህም የፈለጉትን ሙያ በመምረጥ በመማር ላይ እንደሚገኙ እና በክረምት ሰአት ልጆች ግዜአቸውን አልባሌ ቦታ ከማሳለፍ በኮሌጁ በመምጣት ሙያ ቢቀሰሙ የተሻለ ነው ሲሉ ይናገራሉ ።

በኢናይ አቢዳ ዕደጥበብ ኮሌጀ የጌይ ሞት ስልጠና ሲሰጡ ያገኘናቸው ወ/ሮ ሰአዳ አብዶሸ ወጥቶች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን በትርፍ ሰአታቸው በኮሌጁ የተለያዩ ከዘጠኝ በላይ ሙያዎች መኖራቸውን እና እነዚህም የአለላ ሰፌት፣ሴንጀር፣ወርቅ ሰራ፣የእንጨት ሰራ፣ ሸመና፣የቆዳ ውጤቶች በኮሌጁ የሚሰጡ መሆኑን ገለፀዋል ።

ወጣቶች ግዜአቸውን ማሀበራዊ ሚዲያ ና አልባሌ ቦታ ላይ ከማሳለፍ በኮሌጁ በመምጣት ሙያ ቢቀሰሙ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልፀዋል ።

ሌላኛዋ በኮሌጁ የቆዳ ውጤቶች አሰልጣኝ አረቢት ሳይ የተለያዩ ቦርሳዎች ፣ ቀበቶ፣ጫማ፣የመሳሰሉትን በማስተማር ይሄ ሙያ በእኔ ብቻ እንዳይቀር ሲሉ ገልፀው ተማሪዎች በማዕከሉ በመምጣት የተለያዩ ሙያዎችን ቢማሩ ለወደፊት ህይወታቸው እንጀራም ጭምር እንደሚሆን ተናግረዋል ።

በሀረሪ ክልል ባህል ቅርሰና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዳይሮክቶሬት የባህል ባለሙያ ወ/ሮ ኢናሳ መሀመድ ኮሌጁ በተለያዩ ከዘጠኝ በላይ የሙያ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልፀው ስልጠናው ወጣቶች ከአልባሌ ቦታዎች ከመቆጠብ አንጻር ትልቅ አሰተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል ።

በኢናይ አቢዳይ እደጥበብ ኮሌጀ ማንኛውንም ለመማር ፍላጎት ያለው ሰው ያለምንም ክፍያ በኮሌጁ የሚሰጡ ሙያዎችን መቶ መሰልጠን እንደሚችል ተገልጿል ።

አያንቱ አህመድ
9/12/17

ለተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/

ዩቲዩብ :
https://www.youtube.com/

ቴሌግራም:
https://t.me/hararimassmediaagency

በደም እጦት የሚጠፋ ህይወትን ለመታደግ ደም መለገስን ባህል ማድረግ  እንደሚገባ የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።ኮሚሽኑ የደም እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መድረስ የሚያስችል የደም...
15/08/2025

በደም እጦት የሚጠፋ ህይወትን ለመታደግ ደም መለገስን ባህል ማድረግ እንደሚገባ የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።
ኮሚሽኑ የደም እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መድረስ የሚያስችል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል

****
የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የደም እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መድረስ የሚያስችል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

ኮሚሽኑ በደም ልገሳው መሪ በመሆን ሌሎች አርአያነቱን እንዲከተሉ ተግባራዊ ስራ አከናውነዋል።

በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ፣ ለሰው ልጅ ደም መለገስ ለሀገርና ለወገን ያለውን ፍቅርና ሰብዓዊነት የሚያሳይ ነው።

“ይህ የሰብዓዊነት ተግባር ለሰው ልጅ ደኅንነትና ለሀገር ከፍታ የበኩላችንን ድርሻ የምንወጣበት የሕይወት ቅብብሎሽ ነው” ሲሉ ኮሚሽነር አድናን አክለዋል።

በመርሃ ግብሩም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ፣ ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዱላሂ እና የማኔጅመንት አባላት ደም በመለገስ ለሌሎች አርአያነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።

ይህ የበጎ ፈቃድ ተግባር የክልሉን የደም ባንክ አቅም ለማሳደግ፣ አስቸኳይ የደም እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ሕይወት ለመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑም ተጠቁሟል።

የደም ልገሳውም ጤናን የማይጎዳ መሆኑን ለማስገንዘብ እና ኮሚሽኑ መሰል በጎ ተግባራትን እንደሚቀጥልም በእለቱ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ የደም ልገሳው የመጀመሪያ ዙር መጠናቀቁ እና ሁለተኛው ዙር ደግሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የስራ ሰዓቱ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በመራዘሙ ከፍተኛ የስራ ውጤት መመዝገቡን የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ገለፁ።*******የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠ...
14/08/2025

የስራ ሰዓቱ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በመራዘሙ ከፍተኛ የስራ ውጤት መመዝገቡን የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ሰራተኞች ገለፁ።
*******
የሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ ለግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የስራ ሰዓት ማሻሻያ በማድረግ እስከ ምሽት 4 ሰዓት በመስራት ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግኑኝነት ዳሬክተር የሆኑት አቶ ፍፁም ታሪኩ ገልጿል።

ይህም ግብር ከፋዩ በተመቸው ሰዓት ግብሩን እንዲከፍል የሚያስችልና የግብር አሰባሰብ ስራው ውጤታማ እንዲሆን ያስችላል ተብሎ ታምኖበት እንደሆነ ዳሬክተሩ ተናግሯል።

በሐረሪ ክልል ገቢዎች ቢሮ የገቢ አሰባሰብ ዳሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሙና ሁሴን የስራ ሰዓቱ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በመደረጉ በ2017 ሐምሌ ወር 281 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን በመግለፅ የተሰበሰበው የገቢ መጠን 2016 ተመሳሳይ ወር ከተሰበሰበው ጋር ሲነፃፀር የ100 ሚሊዮን ብልጫ እንዳለው ተናግሯል።

ቢሮው በ2017 ሐምሌ ወር ብቻ 280 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በመስራቱ ከእቅድ በላይ ግብር መሰብሰቡን ዳሬክተሯ አስታውቋል።

የተቋሙ የፋይናንስና አስተዳደር ዳሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አልፊያ አብዶሽ በክልሉ መንግስት ቁርጠኛ አመራር የተመዘገበውን ልማት ማስቀጠል የሚቻለው ግብርን በወቅቱና በስርዓቱ መሰብሰብ ሲቻል ነው ሲሉ ተናግሯል።

የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ያለ ተጨማሪ ክፊያ እስከ ምሽት 4 ሰዓት ማገልገላቸው ለሐገር ብልፅግና ቀን ለሊት መስራት የሁሉም ግዴታ መሆኑን ለማሳየት ጭምር ነው ሲሉም ተናግሯል።

በቀን ወደ ተቋሙ የሚመጡ የግብር ከፋዎች ቁጥር በተደረገው የስራ ሰዓት ማሻሸያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የተቋሙ ደንበኞች አገልግሎትና ስልጠና ዳሬክተር አቶ ሬድዋን ሙክታር ናቸው።

በተጨማሪም በተለያዩ የግል ምክንያቶች በመደበኛው የስራ ሰዓት ወደ ተቋሙ መጥቶ ግብር ለመክፈል ለተቸገሩ ደንበኞች ተመራጭ የግብር መክፊያ ግዜ መሆኑን አስረድቷል።

የመክፈያ ግዜው ከመጠናቀቁ በፊት ግብር በወቅቱ በመክፈል ሁሉም ግዴታቸውን እንዲወጡም ሰራተኞቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።

አያይዘውም በተቋማቸው የተጀመረዉ መልካም ተሞክሮ ወደ ሌሎች ተቋማትም እንዲስፋፋ ሰራተኞቹ ጠይቀዋል።

ተቋሙ ከመደበኛ የስራ ሰዓት ውጪ እስከ 4 ሰዓት ‎ለአገልግሎት ክፍት ማድረጉ ግብራቸውን ያለምንም እንግልትና ተጨማሪ ቅጣት በወቅቱ እንዲከፍሉ ማስቻሉን በምሽት የስራ ሰዓት ያገኘናቸው ተገልጋዮች ተናግረዋል።

ግብር በመክፈላችን የተለየ ደስታና ኩራት ይሰማናል ያሉት ግብር ከፋዮቹ ተቋሙ ከቀን የስራ ሰዓት በተጨማሪ እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት በሩን ለስራ ክፍት ከማድረጉም በዘለለ ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት እየሰጣቸው መሆኑን አስረድተዋል።

የሐረሪ ክልል ገቢዎች በ2017 4.6 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ አቅዷል።

ዘጋቢ:- ፋህሚ ዚያድ
8 / 12 /17

ለተጨማሪ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎቻችን ይከታተሉን።

ቲክቶክ፡ https://www.tiktok.com/

ዩቲዩብ : https://www.youtube.com/

ቴሌግራም: https://t.me/hararimassmediaagency

በደም እጦት የሚጠፋ ህይወትን ለመታደግ ደም መለገስን ባህል ማድረግ  ይገባል :-  ኮሚሽነር አድናን አህመድ ********የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የደም እገዛ...
14/08/2025

በደም እጦት የሚጠፋ ህይወትን ለመታደግ ደም መለገስን ባህል ማድረግ ይገባል :- ኮሚሽነር አድናን አህመድ
********
የሀረሪ ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮችና አባላት የደም እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መድረስ የሚያስችል የደም ልገሳ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

ኮሚሽኑ በደም ልገሳው መሪ በመሆን ሌሎች አርአያነቱን እንዲከተሉ ተግባራዊ ስራ አከናውነዋል።

በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ፣ ለሰው ልጅ ደም መለገስ ለሀገርና ለወገን ያለውን ፍቅርና ሰብዓዊነት የሚያሳይ ነው።

“ይህ የሰብዓዊነት ተግባር ለሰው ልጅ ደኅንነትና ለሀገር ከፍታ የበኩላችንን ድርሻ የምንወጣበት የሕይወት ቅብብሎሽ ነው” ሲሉ ኮሚሽነር አድናን አክለዋል።

በመርሃ ግብሩም የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አድናን አህመድ፣ ምክትል ኮሚሽነር ሙራድ አብዱላሂ እና የማኔጅመንት አባላት ደም በመለገስ ለሌሎች አርአያነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።

ይህ የበጎ ፈቃድ ተግባር የክልሉን የደም ባንክ አቅም ለማሳደግ፣ አስቸኳይ የደም እገዛ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ሕይወት ለመታደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑም ተጠቁሟል።

የደም ልገሳውም ጤናን የማይጎዳ መሆኑን ለማስገንዘብ እና ኮሚሽኑ መሰል በጎ ተግባራትን እንደሚቀጥልም በእለቱ ተገልጿል።

በመርሃ ግብሩ የደም ልገሳው የመጀመሪያ ዙር መጠናቀቁ እና ሁለተኛው ዙር ደግሞ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

8/12/2017

የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ለሀረር መምህራን ትምህርት እና ቢዝነዝ ኮሌጅ አበረከተ። ********ለኮሌጁ የኪነጥበብ ማሰልጠኛ ዘርፉን ለማጠናከር ዘመናዊ ...
14/08/2025

የክልሉ ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ዘመናዊ የሙዚቃ መሣሪያዎችን ለሀረር መምህራን ትምህርት እና ቢዝነዝ ኮሌጅ አበረከተ።
********
ለኮሌጁ የኪነጥበብ ማሰልጠኛ ዘርፉን ለማጠናከር ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎቹ ድጋፍ መደረጉ ተገልጿል ።

የሀረሪ ክልል ባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የክልሉን ባህል ና ኪነጥበብ ዘርፍ ለማሳደግ ከሀረር መምህራን ትምህርት እና ቢዝነዝ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰው እየሰሩ ይገኛል።

ቢሮው በኮሌጁ የኪነጥበብ ማሰልጠኛ ዘርፉን ለማጠናከር ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ለኮሌጁ አበርክተዋል።

በስነስርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሐረሪ ክልል ባህል፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ የድጋፉ ዓላማ የኪነ ጥበብና የባህል ታሪክ ለማስተዋወቅና ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሚና ለመጫወት ነው ብለዋል።

የኪነጥበብ ስራን የማስፋፋት ስራ ከግብ ለማድረስ የረጅምና የአጭር ጊዜ እቅድ በማውጣት እየሰራ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

የኮሌጁ ዲን አቶ አብዱልአዚዝ መሃመድ በበኩላቸው ኮሌጃቸው ባህል ና በኪነጥበብ ዘርፍ ለማሳደግ ትምህርት ና ስልጠና እንዲጀምር ከባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ዘመናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ማበርከቱ ትልቅ መነሳሳት የሚፈጥርላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የክልሉን የባህልና የኪነጥበብ ታሪክ ለትውልድ ለማስተላለፍና በዚህ ረገድ የተገኘውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል ትውልድ በመገንባትና በማሰልጠን ኮሌጁ እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በባህል፣ ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ የባህል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እስክንድር አብዱራህማን እንዳሉት ኮሌጁ የክልሉን ባህላዊና ጥበባዊ ታሪክ ለማስቀጠል እና ትውልድን በማሰልጠን የስራ እድል ለማስፋት የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

የክልሉ ባህል፣ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ከሐረር መምህራን ትምህርት እና ቢዝነዝ ኮሌጅ ጋር በኪነ ጥበብና ባህል ልማት ዙሪያ አብሮ ለመስራት ስምምነት ተፈራርሟል።

ዘጋቢ :- አብዲ ኡስማን
8/12/17

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Harari Mass Media Agency posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Harari Mass Media Agency:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share