በጎ ሀሳብ

በጎ ሀሳብ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በጎ ሀሳብ, Digital creator, Dese, Welo.

07/06/2025
14/05/2025

"All religions, arts, and sciences are branches of the same tree. All these aspirations are directed toward ennobling a person's life, lifting it from the sphere of mere physical existence and leading the individual toward freedom." - Albert Einstein

14/05/2025

ማኔጅመንት እወቅ!

ምንም ትምህርት ብትማር ማኔጅመንት/አስተዳደር ልታውቅ ያስፈልግሃል።

ማኔጅመንት፣ አስተዳደር፣ አመራር፣ ቁጥጥር የተባሉት የትምህርት ወይም የእውቀት ዘርፎች አንድነትና ልዩነት አላቸው። መሠረታቸው ግን ማኔጅመንት ነው። ማኔጅመንት ሁሉን-አቀፍ ነው። ማኔጅመንት ውስጥ አመራር አለ፤ ማኔጅመንት ውስጥ አስተዳደር አለ፤ ማኔጅመንት ውስጥ መቆጣጠር አለ።

ማኔጅመንት ገሪነት ነው። ማኔጅመንት ሥራን፣ ሰውን፣ የአሠራር ባህልን ይገራል። ማኔጅመንት የገሪነት ሚናውን የሚጫወትበት ብዙ ሞዴሎች፣ ስልቶች እና ዘዴዎች አሉት።

የብዙ ችግሮች መፍትሔ ማኔጅመንት ውስጥ አለ። ህይወትህን በስርዓት ለመምራት ማኔጅመንት ልታውቅ ግድ ነው። ማኔጅመንት እውቀት ከሌለህ ችግር መዝዘህ እንኳን ሊተገበር ያልታለመ ችግር ውስጥ ትዘፈቃለህ። ግዴለም ማኔጅመንት እወቅ!

መጀመሪያ የተማርከው ምንድን ነው?

የተማርከው ምንም ይሁን ማኔጅመንት ብታውቅ ህይወትህ ለማቃናት ትልቅ እገዛ ያደርግልሃል። ማኔጅመንት ካላወቅህ ግን ሌሎች ይጫወቱብሃል። አንተም ጊዜ ጉልበት እና ገንዘብ ታባክናለህ። ችግርህን ለመፍታት የሚችል ሲስተም ያጥርህና ትግል እና ግጭት ውስጥ ትገባለህ።

ልብ በል! ከዚህ ቀደም እንዳልነው

SYSTEM = Save Your Self Time, Energy Money ማለት ነው።

ለራስህ ይሁን ለሀገርህ ጊዜ፣ ጉልበት እና ገንዘብ የሚቆጥብ ወይም የሚያባዛ ስርዓት ካልፈጠርህ ከንቱ ድካም እና የችግር አዙሪት ቀለበት ውስጥ ነህ።

የተማርከው ህክምና ይሁን ምህንድስና፣ ህግ ይሁን ፍልስፍና ለውጥ የለውም። ማኔጅመንት ልታውቅ ግድ ይልሃል።

ማኔጅመንት ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት፣ እና መቆጣጠር የሚሉ ዋና ተግባራት አሉት።

ለማቀድ ግብን እና የትኩረት አቅጣጫን መምረጥ ይጠይቃል። ማኔጅመንት የሚያውቅ ሰው ያገኘው ጦርነት ውስጥ ነጠላዬን አቀብሉኝ ብሎ ዘው ብሎ አይገባም። ማኔጅመንት የሚያውቅ ሰው ጦርና ጋሻ በእጁ ስላለ፣ ስልጣን ወንበር ላይ ስለተቀመጠ፣ ህግ ስለሚደግፈው ያየውን ችግር ሁሉ በህግና በጉልበት ልፍታ አይልም። ይህ የሚገባህ ማኔጅመንት ስታውቅ ነው። ማኔጅመንት በጠርሙስ ታሽጎ ያለን ጂኒ ክዳኑን ከፍቶ ራሱን ችግር ውስጥ አይጥልም።

ማኔጅመንት ስታውቅ ዋናውን እና ቀላሉን፣ ጠቃሚና ገለባውን፣ ግንድ እና ቅርንጫፉን ለይተህ የምታተኩርበትን ትመርጣለህ፤ ብራንድህን በፈለግኸውና ጠቃሚ በሆነ መስመር ትገነባለህ፤ ለሥራና አገልግሎትህ በቂ ክፍያ የሚያስከፍል ስርዓት ትዘረጋለህ፤ የመቆጣጠሪያ ዘዴ ትዘረጋና አካሄድህን እየለካህ በመገምገም ማስተካከያ ታደርጋለህ።

ማኔጅመንት ከታች ጀምሮ በየትምህርት ሳይክሉ በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን ቢሰጥ ጠቃሚ ነው። በኮሌጅ ደረጃ ላሉም የትምህርት መስኩ ቢያንስ 2 የማኔጅመንት ኮርስ ሊሰጥ ያስፈልጋል ብዬ አምናለሁ። ማኔጅመንት የማያውቅ "አዋቂ" ስራው ስርዝ-ድልዝ ዓይነት ነው።

በነገራችን ላይ በደረጃዎች የተከፋፈለ Mini-MBA የሚባል ስልጠና አለን። ይህ ስልጠና ለብዙዎች አስፈላጊ ነው።

የህግ ሰው ብትሆን፣ ሀኪም ብትሆን፣ መሃንዲስ ብትሆን፣ ኢኮኖሚስት ብትሆን፣ የዩኒቨርሲቲ መምህር ብትሆን፣ ፖለቲከኛ ብትሆን፣ የታክሲ ሾፌር ብትሆን፣ የኳስ አሰልጣኝ ብትሆን፣ ባል ብትሆን፣ ሚስት ብትሆኚ፣ ሚኒስትር ብትሆን፣ ፓስተር ብትሆን፣ ... ማኔጅመንት ካላወቅህ ችግር ውስጥ ነህ። ማኔጅመንት እወቅ!

ችግር የሚፈጠረው ማኔጅመንት ባለማወቅ ነው። ችግር የሚፈታውም የማኔጅመንት ስልት በማወቅ ነው።

የሀገራችን ህዝብ የማኔጅመንት እውቀት ከፍ ሊል የተገባ ነው።

የህዝባችን የማኔጅመንት እውቀትና ልምድ ሲዳብር የመነጋገሪያ አጀንዳችን ይቀየራል፣ የጠራ ግብ ይኖረናል፣ የትኩረታችን አቅጣጫ ይቀየራል፣ ችግርን ለመፍታት ሚና ሚናችንን ለይተን እንደራጃለን፣ አካሄዳችንን ከግባችን አንጻር እየለካን፣ እየገመገምን እና እያስተካከልን ወደ ግባችን እንገሰግሳለን።

ማኔጅመንት የእውቀት ሁሉ መቋጠሪያ ነው።

የማኔጅመንት ትምህርት ስለሲስተም ነው።

ማኔጅመንት ሳይንስም ጥበብም ነው።

እስኪ በዚህ የማኔጅመንት መነጽር ሰሞኑን አየር ላይ የናኙትን የአስጌ ደንዴሾን የመክሰስ ሀሳብ፣ የቅዱስ ጳውሎስ ሀኪሞችን Enough is Enough የሚል የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ፣ የኢሠማኮ የደሞዝ ወለል ይደንገግልኝ ጥያቄ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን "ኢትዮጵያ ታምርት" ንቅናቄ፣ የሰይፉ እና ኩኩ ኢንተርቪው፣ የቴዲ ኮንሰርት እና ሌሎችም ሰፊ ሽፋን ያገኙ የሀገራችን ጉዳዮች ፈትሹት።

የቱ ለዓቅመ-አጀንዳነት ይበቃል? የቱ በየትኛው ስልትና ዘዴ ሊኬድበት ይገባል? የቱ ሰፊ ጊዜ ይፈልጋል? የቱ ሀገራዊ አጀንዳ ነው? የሁሉም ችግር ስረ-መሠረትስ ምንድን ነው?

በጨዋነት እንወያይ።

Get Toughe Zer

02/05/2025

20 የአንስታይን አባባሎች

1. ‹‹ ሠላምን በጉልበት ማስጠበቅ አይቻልም፡፡ ሠላምን ማስጠበቅ የሚቻለው በመግባባት ብቻ ነው፡፡ ››

2. ‹‹ ስህተት ሠርቶ የማያውቅ ሠው ምንም ነገር ሞክሮ አያውቅም ማለት ነው፡፡ ››

3. ‹‹ ሁሉም ሠው ብሩህ ጭንቅላት አለው፡፡ ነገር ግን አሣን ዛፍ መዝለል አይችልም ብለህ ችሎታውን ካጣጣልከው በህይወትህ ሙሉ አሣ ደደብ እንደሆነ ታስባለህ፡፡ ››

4. ‹‹ ዓይነ ሕሊና ከዕውቀት የላቀ አስፈላጊ ነው፡፡ ››

5. ‹‹ ትምህርት አዕምሯችን የበለጠ እንዲያስብ እንጂ ጥሬ ሃቆችን ለመለማመድ አይደለም፡፡ ››

6. ‹‹ ሙከራህን እስከምታቆም ድረስ በህይወት አትሸነፍም፡፡ ››

7. ‹‹ አንድን ነገር በቀላል ቋንቋ መግለፅ ካልቻልክ ነገሩን አልተረዳኸውም ማለት ነው፡፡ ››

8. ‹‹ እብደት ማለት አንድን ነገር በተመሳሳይ ዘዴ ደግሞ ደጋግሞ በመስራት የተለየ ውጤት መጠበቅ ነው፡፡ ››

9. ‹‹ ደስተኛ ሕይወት ለመኖር ከፈለግክ አንተነትህን ከሠዎች ወይም ከነገሮች ጋር ከማወዳደር ይልቅ ከግብህ ወይም ከዓላማህ ጋር ራስህን እሠር፡፡ ››

10. ‹‹ ስኬታማ ለመሆን ከፈለግክ የስኬት ፍላጎትህ እወድቃለሁ ብለህ ከምትፈራው ፍርሃትህ በእጅጉ የበለጠ መሆን አለበት፡፡ ››

11. ‹‹ መቀራረብ በፍቅር ለመውደቅ ዋስትና አይሆንም፡፡ ››

12. ‹‹ ዋጋ ያለህ ሠው ለመሆን ሞክር እንጂ ስኬታማ ብቻ ለመሆን አትሞክር፡፡ ››

13. ‹‹ ምክንያታዊነት ከአንድ ቦታ አንስቶ ወደሌላ ቦታ ሊወስድህ ይችላል፡፡ ዓይነ ሕሊና ግን የትም ይወስድሃል፡፡ ››

14. ‹‹ ጎበዝ ሠው ችግሮችን ይፈታል፡፡ ብልህ ሠው ግን ችግሮቹ መልሠው እንዳይፈጠሩ ያስወግዳቸዋል፡፡ ››

15. ‹‹ ተፈጥሮን በጥልቀት ተመልከት፡፡ ያን ጊዜ ሁሉንም ነገሮች በተሻለ ትረዳለህ፡፡ ››

16. ‹‹ ሴቶች ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ወንዶች ጨርሠው በረሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ወንዶችም ብዙ ጊዜ የሚጨነቁበት ጉዳይ ሴቶቹ በማያስታውሷቸው ነገሮች ላይ ነው፡፡ ››

17. ‹‹ ቅዱሱን ጉጉትህን አትጣለው፡፡ ››

18. ‹‹ የአመለካከት ድክመት እየቆየ ሲሄድ የባህሪ ድክመት ይሆናል፡፡ ››

19. ‹‹ ሞትን መፍራት ማለት ተገቢ ባልሆኑ ፍርሃቶች መንቦቅቦቅ ነው፡፡ ምንም ስጋት የሌለበት ሠው ቢኖር የሞተ ሠው ብቻ ነው፡፡ ››

20. ‹‹ ፍፁም የማይመስለውን የሚሞክሩ የማይቻለውን የሚችሉ ናቸው፡፡

03/04/2025
08/03/2025
30/09/2024

“የሰው ልጅ እንደሚሞት ቢያስብ ኑሮ ለመጨካከን የሚሆነው ጊዜ ባልተረፈው ነበር”

(ጧሪ ቀባሪ የለላቸው ሚስኪኖችን ቀባሪው በጎ ፈቃደኛ አብዱ ከማል ረሺድ)

ደሴ ተወልዶ ያደገው እና ነዋሪነቱም በደሴ ከተማ የሆነው አብዱ ከማል ባለፉት 30 አመታት ውስጥ ብቻ ከ4500 በላይ ቀባሪ የሌላቸውን ሰዎች ደምቡን ጠብቆ ቀብሯል።

ለዚህ በጎ ተግባሩ በገንዘብም ሆነ በጉልበት ከሚያግዙት ጥቂት ሰዎች ጋር በመሆን ከ4500 በላይ ሰዎችን በክብር የቀበረው አብዱ ከማል በእድሜ በመግፋት፣ በድንገተኛ አደጋ እና በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸው ያለፈ እና ቀባሪ የሌላቸው ሰዎችን አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ በማድረግ የቀብር ስነስርአታቸውን ማስፈጸም በደሴ ከተማ የሚታወቅበት የመለያ ምልክቱ ሁኗል፡፡


አብዱ ከአል ዐይን አማርኛ የሚዲያ ተቋም "የተወለድከው መቼ ነው?" ተብሎ ሲጠየቅ “ምኑን አውቀዋለሁ ብለህ ነው፤ ከውልደቴ ይልቅ የምሞትበትን ቀን እያሰብኩ ለዛኛው አለም ስለምጠየቅበት መልካም ስራ ነው የማስበው። ግዴታ ነው ካልክ ግን በግምት 61 ሳልሻገር አልቀርም” ሲል የመለሰው ዓብዱ ከማል ረሽድ በቤቱ ውስጥ ሁሌም ለቀብር ስነስርአት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አሟልቶ በተጠራበት ቦታ ሁሉ ወንድ ፣ ሴት ፣ ክርስቲያን ፣ ሙስሊም ሳይል ሟቾች በተገቢው መንገድ አስክሬናቸው እንዲያርፍ በማድረግ 30 አመታትን አስቆጥሯል፡፡

ቃሬዛ (ስትሬቸር) ፣ መቆፈሪያ ፣ የአስክሬን ከፈኖች እና ለቀብር የሚያስፈልጉ ሌሎች ቁሳቁሶች ሁሌም በቤቱ ዝግጁ አድርጎ ያስቀምጣል፡፡
አብዱ ይህን በጎ ተግባር የጀመረበትን አጋጣሚ ያስታውሳል።
ከዛሬ 30 አመት በፊት በደሴ መነሀሪያ ውስጥ በመኪና ረዳትነት የሚያገለግል ቤተሰብ የሌለው አንድ ልጅ መሞቱን ተከትሎ ጥሪ የደረሰው መዘጋጃ ቤት ልጁን ለመቀበር በመዘግየቱ አብዱ አስከሬኑን አጥቦ እና ገንዞ ከአካባቢው በተሰባሰበ ገንዘብ የቀብር ስነስርአቱ እንዲፈጸም አድርጓል፡፡
ከዚህ ጊዜ በኋላ ቤተሰብ፣ እድር ወይም ቀባሪ የሌላቸው እንዲሁም በተለያየ ምክንያት ለጉዞም ሆነ ለስራ ደሴ ከተማ ውስጥ መጥተው ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ሲኖሩ ቀድሞ የሚጠራው "አብዱ ፋጤ" ሆነ፡፡

“የሰው ልጅ ለመማር ራሱን የሚያዘጋጅ ከሆነ ህይወት ራሷ ትምህርት ቤት ናት። መልካምነት ከቤተሰብ እና ከአካባቢህ ትማራለህ፤ ዋናው ነገር አንተ የምትከተለው መንገድ ነው የሚወስነው፤ስራውን ስጀምር አጋጣሚ ነበር፤ ነገር ግን መጀመርያ እንደቀበርኩት ልጅ ያሉ ቤተሰብ እና ቀባሪ የሌላቸው ሰዎች እንዴት ይሆኑ ይሆን ብየ ማሰብ ጀመርኩ ከዛ ነው ስራየ ብየ የተያያዝኩት”፡፡
በጊዜ ሂደት የሚሰራውን በጎ ምግባር የሚመለከቱ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ሌሎች እሱን የሚያውቁት ሰዎች የቀብር ስነስርአት የሚያስፈጽምባቸውን የተለያዩ መሳርያዎች አሟሉለት፡፡

ቀጥሎም በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የደሴ ከተማ ተወላጆች በወር እና በተለያየ ጊዜ በሚሰጡት ገንዘብ የአስከሬን መከፈኛ ጨርቆችን እና ሌሎች አላቂ እቃዎችን በማሟላት ዛሬ ላይ ሙሉ ጊዜውን ለዚህ በጎ አድርጎት ስራ አውሎት ይገኛል፡፡
አብዱ ይህን በጎ ስራ ይህን ያህል አመት ያለመሰልቸት እንዴት እንዳከናወነ ለጠየቅነው ጥያቄ፦
“እውነቴን ነው የምልህ ስራው በጣም አድካሚ እና ሰዎች አዘውትረው ሊሰሩት የሚችሉት አይደለም፤ ነገር ግን ሜቴን አሳምርልኝ እና ቀባሪ አታሳጣኝ በሚል ማህበረሰብብ ውስጥ አይደለም ብቸኛ ሆነህ በዘመድ ተከበህ ራሱ ምን ያህል ከባድ ነገር እንደሆነ ታውቀዋለህ፤ ዛሬ ላይ እድሜያቸው የገፋ በአልጋ ላይ የዋሉ የሞታቸውን ቀን የሚጠብቁ እና ቀባሪ የሌላቸው ሰዎች በየቤቱ ሞልተዋል። ህመምን ከመታመም እና የሞትን ቀን ከመቁጠር ባለፈ ደግሞ እዚህ ባዶ ቤት ሞቼ ብገኝ ማን ይሆን አንስቶ የሚቀብረኝ በሚል የሚጨነቁ ሰዎች ቁጥር ቀላል እንዳይመስልህ፤ ቢያንስ የእነርሱን ጭንቀት መቅረፍ ችያለሁ ብየ አስባለሁ በዚህ ደግሞ እጅግ ደስተኛ ነኝ” ፡፡

በደሴ ከተማ በስራው ያተረፈውን ዝና ተከትሎ ቀባሪ ከሌላቸው ሰዎች “አብዱ ይቅበረኝ” የሚል ኑዛዜ ጭምር እንደሚደርሰው ይናገራል፡፡
ሟቾች እንደነገሩ አፈር እንዲቀምሱ ማድረግ ብቻ ሳይሆን እንደየ እምነታቸው አስፈላጊውን ሀይማኖታዊ ስርአት በማከናወን በየቤተ እምነታቸው መካነ መቃብር እንዲያርፉ ያደርጋል፡፡
አብዱ ለሶስት አስርተ አመታት ይህን ስራ ሲያከናውን የሟቾችን ስም ፣ የሞቱበትን ቀን ፣ አድራሻ እና የቀበረበትን ቦታ ሁሉ በስነስርአት መዝግቦ ያኖራል፡፡
ይህን የሚደርገው ደግሞ በአጋጣሚ የሟች ቤተሰቦች ቢገኙ እና ሟቹን ወደ ሌላ ቦታ ወስደው ማሳርፍ ቢፈልጉ በሚል ነው፡፡
በቀን ከአንድ ሰው በላይ የቀብር ስነስርአት እንደሚያስፈጽም የሚናገረው አብዱ በአደጋ እና ድንገተኛ ሁኔታ የሞቱ ሰዎች ሲያጋጥሙ ለፖሊስ በማሳወቅ አስፈላጊውን ምርመራ እና ማጣራት እንዲደረግ ሪፖርት ያደርጋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ከእርሱ ጋር የቀብር ስራውን የሚያግዙ አስር በጎ ፈቃደኞች አብረውት ይሰራሉ። በዚህ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ስላጋጠመው የተለየ አጋጣሚ ሲናገር፤ በአንድ ወቅት የቀብር ጉድጓድ እየቆፈረ ባለበት ለረጅም ጊዜ የተቀበረ የጥይት ሳጥን ፈንድቶ እርሱ እና አብረውት የሚሰሩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ለአንድ ወር ሆስፒታል ውስጥ ተኝተው እንደነበር ያስታውሳል፡፡

አብዱ ፋጤ የበጎ አድራጎት ስራውን እያሳደገ መጥቶ ከቀብር ስነስርአት ማስፈጸም ባለፈ በየቤቱ ቤተሰብ እና አስታማሚ የሌላቸውን በጽኑ የታመሙ ሰዎች ማስታመም እና መንከባከብ ፣ አርብ አርብ ደግሞ በሆስፒታሎች ውስጥ ጠያቂ የሌላቸውን ታማሚዎች መጠየቅ እና በተቻለ መጠንም የምግብ እና የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ አጫውቶናል፡፡
ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበረው ቃለ ምልልስ በመጨረሻ የጠየቅነው ጥያቄ ሞትን ትፈራለህ? የሚል ነበር።
“ሞት ምኑ ያስፈራል ብለህ ነው፤ የማይቀርን ነገር ለምን ትፈራለህ ዋናው ነገር ሀይማኖተኛ ከሆንክ ፈጣሪየ ፊት ስቀርብ የምናገረው በጎ ምግባር አለኝ ውይ ብለህ መዘጋጀት ነው፡፡

እኔ ቤት መጥተህ ብታይ መከፈኛ ጨርቅ ተንተርሼ ነው የምተኛው። መጥፎ ሰርተህ ሱፍ ከመልበስ በጎ አድርገህ ጆንያ መልበስ ይሻላል፡፡
ይህ የምታየው መጨካከን ሁሉ የመጣው ፍቅር ከማጣት እና ከስግብግብነት ይመስለኛል፤ እኔ ይህን ስራ ስሰራ በገንዘብም ሆነ በቁሳቁስ የሚረዱኝ ሰዎች መልካም ስራየን ስላዩ ነው። ይህ በጎ ስራ እንደሚጋባ ያሳይሃል፡፡ የሰው ልጅ መሞቱን ቢያስብ ለመጨካከን ጊዜ ባልነበረው ነበር”፡፡
ይህን የበጎ አድራጎት ስራ ወደ ማህበር በመቀየር ተቋማዊ ቅርጽ የማስያዝ ህልም እንዳለው የሚገልጸው አብዱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር ቦታ በመወሰድ የአረጋውያን ማቆያ እና መንከባከቢያ ድርጅት የማቋቋም ህልም ሰንቋል፡፡

04/02/2024

ወይም "ትልልቅ ስኬቶች የተደበቁት ከትልልቅ ሪስኮች ጀርባ ነው" እንደ ማለት ነው።

አዎ ! በህይዎታችን ውስጥ ትልልቅ ለውጦችን እና ስኬቶችን ለማምጣት አልመን ስንሰራ ከትልልቅ ችግሮች (high risk) ጋር መጋፈጣችን አይቀርም ።

ነገር ግን ከችግሮቹ ጀርባ የተደበቀውን ትልቅ ስኬት ለማግኘት ስኬቱን ቆልፈው የያዙብን ችግሮች ጋር ተጋፍጠን በድፍረት መዋጋት ይኖርብናል።

በጎ ሀሳብ-begohasab

Address

Dese
Welo

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጎ ሀሳብ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share