Ethiopia hagerie

Ethiopia hagerie ኢትዮጲያ ሀገሬ

የጀርባ (የወገብ) ህመም የጀርባ ህመም ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ ከሚሹባቸው ወይም ከሥራ ከሚቀሩባቼው በጣም ከተለመዱ የህመም ምክንያቶች አንዱ ነው። የጀርባ ህመም በአለም አቀፍ ደረጃ የአካል ...
25/07/2025

የጀርባ (የወገብ) ህመም

የጀርባ ህመም ሰዎች የሕክምና ዕርዳታ ከሚሹባቸው ወይም ከሥራ ከሚቀሩባቼው በጣም ከተለመዱ የህመም ምክንያቶች አንዱ ነው። የጀርባ ህመም በአለም አቀፍ ደረጃ የአካል ጉዳት ዋነኛ መንስኤ ነው።

የታችኛው ጀርባ ህመም በራሱ በሽታ እይደለም። የበርካታ የተለያዩ የጤና ችግሮች ምልክት ወይም መገለጫ ነው። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው ከአንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ የታችኛው ጀርባ ክፍሎች (መዋቅሮች ) ላይ በሚፈጠር ችግር ነው።

ለጀርባ ህመም የሚያጋልጡ ሁኔታዎች :-

1. • ዕድሜ ( ዕድሜ መጨመር )
2. • የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
3. • ከመጠን ያለፈ ክብደት ( ውፍረት )
4. • ስር የሰደዱ የጤና ችግሮች:- የካንሰር፣ አንጓ ብግነት፣ የኩላሊት ችግር )
5. • ከባድ ነገር ማንሳት
6. • የስነ-ልቦና ሁኔታዎች ( ውጥረት ፣ ጭንቀት )
7. • ሲጋራ ማጨስ

የጀርባ ህመም መንስኤዎች

• የጅማቶችና ጡንቻዎች ችግር
* የጡንቻ ወይም የጅማት ውጥረት፣ ቁስለት (መሸማቀቅ)
• የነርቮች ችግር
* ከአከርካሪ አጥንት ስር የሚወጡ ነርቮች ጉዳት
• የአከርካሪ አጥንት ጉዳት
* ሪሂማቶይድ አንጓ ብግነትና ሌሎችም የአከርካሪ አጥንት አንጓ ብግነት አይነቶች
* የአከርካሪ አጥንት መሳሳት፣ መሰበር፣ መጣመም
* የአከርካሪ አጥንት ኢንፌክሽን
• የድስክ ችግርሮች:-
* የድስክ መዘርጠጥ፣ መንሸራተት፣ መጨማደድና መሰበር
• በአቅራቢያው ባሉ የአካል ክፍሎች
* ኩላሊትና የሽንት ፊኛ ችግሮች (የኩላሊት ጠጠር፣ ኢንፌክሽን )
* የማሃፀን ጫፍ ካንሰር፣ የፕሮስቴት ካንሰር

ለጀርባ ህመም የሚያስፈልጉ ምርመራዎች:-

A, ኤክስሬይ ( X Ray ) :-
- የአከርካሬ አጥንት አንጓ ብግነት
- የአከርካሬ አጥንት ስብራት

B, ኤም አር አይ ( MRI ) ወይም ሲቲ ስካን ( CT-SCAN ):-
- የድስክ መዘርጠጥ፣ መንሸራተት ወይን ማፈንገጥ
- እንድሁም በተሻለ ደረጃ አጥንት፣ ጡንቻዎች፣ ነርቮች፣
- ጅማቶችና የደም ስሮች ጋር ያሉ ችግሮችን ያሳየናል።

C, የደም ምርመራዎች:-
- ኢንፌክሽኖች፣
- የአከርካሬ አጥንት አንጓ ብግነት ጠቋሚዎች
- ቫይታሚን ዲ ፣ ካልሺየም

D, ኤሌክትሮሚዮግራፊ (EMG)፣ የነርቭ አስተላላፊ ምርመራ (NCS ):-
- በተንሸራተቱ ወይም በተዘረጠጡ ዲስኮች ፣ የነርቭ መውጫ ቀዳዳ መጥበብና የተለያዩ የነርቭ ችግሮችንና በነርቮች ላይ ያለውን ጫና ለማረጋገጥ ይጠቅማል።

የጀርባ ህመም አሳሳቢ የሚሆነው መቼ ነው!?

1. ከጥቂት ሳምንታት በላይ ከቆየብዎት፣
2. ከባድ ከሆነና በእረፍት እማይሻሻል ከሆነ፣
3. ህመሙ ወድ አንድ ወይም ሁለቱንም እግሮች ወደ ታች መሰማትና መሰራጫት ከጀመረ ፣
4. በአንዱ ወይም በሁለቱም እግሮች ላይ ድክመት፣ መደንዘዝና መወጠር ካስከተለ፣
5. የጀርባ ህመምዎ ክብደት መቀነስ ጋር ከመጣ ፣
6. ከጀርባ ህመሙ ጋር የአንጀት፣ የፊንጢጣና የሽንት ፊኛ ችግር ካጋጠምዎ፣
7. ከጀርባ ህመሙ ጋር ትኩሳት አብሮ ካለዎት፣
8. የመውደቅ አደጋ ካጋጠመዎት በሗላ የሚመጣ የጀርባ ህመም፣

የጀርባ ህመም መከላከልና ህክምና :-

• የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ:- ፈጣን እርምጃ፣ ሶምሶማ፣ ፕስክሌት ማሽከርከርና ዉሃ ዋና
• የጡንቻ ጥንካሬና ተጣጣፊነትን ( Flexibility) ማጎልበት
• ጤናማ ክብደትን ይጠብቁ
• ማጨስን ያቁሙ

• የተስተካከለ አቋቋምና አቋም ይያዙ:- በሚቆሙ ሰዓት የተስተካከለ ዳሌ አቀማመጥን ይያዙ።

 #ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆሞ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ ኢንጅነር አግኝተው እንዲሰራው ቀጠሩት።  #ኢንጅነሩም ሞተሩን ከታች እ...
04/04/2025

#ትልቅ የንግድ መርከብ ተበላሽቶ ቆሞ ብዙ መካኒኮች ቢሞክሩትም መጠገን አቃታቸው ፣ በኋላም አንድ የ40 ዓመት ጎልማሳ ኢንጅነር አግኝተው እንዲሰራው ቀጠሩት።

#ኢንጅነሩም ሞተሩን ከታች እስከላይ ከገመገመ በኋላ አነስ ያለች የእቃ ቦርሳውን ከፍቶ ትንሽዬ መዶሻ አወጣ፣ ከዛም በጥንቃቄ በመዶሻው አንዷን ስፍራ መታ መታ አረገና ሞተሩ መስራት ጀመረ።

#ከሳምንት በኋላ የሰራበትን ዋጋ አንድ ሚሊዮን ብር ለባለቤቱ ሪሲቱን ሰጠው።

"ምን" አለ ባለቤቱ ጭንቅላቱን ይዞ ምን ሰርተህ ነው ይሄን ያህል ብር የምትጠይቀኝ በል ምን እንደሰራህ ዝርዝሩን ጽፈህ ስጠኝ አለው ተናዶ።

#በቀላሉ እንዲህ ጽፎ ሰጠው
በመዶሻ የመታሁበት 200 ብር
የተበላሸበትን ቦታ ላወኩበት ደግሞ 999800 አለው።

#ይሄን ስራ በ30 ደቂቃ ውስጥ ነው የሰራውት ላለፉት 20 አመታት እንዴት በ30 ደቂቃ መስራት እንዳለብኝ ተምሬ ነው፣ የማስከፍልህ ለተማርኩበት አመታት እንጂ #ለሰራውበት ደቂቃ አይደለም አለው ይባላል።

ሁሉም ውጤት የእረጅም ጊዜ ልፋት ነው።

አላማችን ከተማችንን ከደረቅ ቆሻሻና መሰል አላስፈላጊ ነገሮችን ማፅዳትና ማስዋብ ነው
30/09/2024

አላማችን ከተማችንን ከደረቅ ቆሻሻና መሰል አላስፈላጊ ነገሮችን ማፅዳትና ማስዋብ ነው

11/02/2023
22/12/2022

ብልፅግና የተከበረውን የኦሮሞ ማንነት ወደ አፀያፊ ማንነት አውርዶታል !

ብልፅግና ኦሮሞነትን ወደ አፀያፊ ማንነት ባይቀይረዉ ኖሮ ኦሮምኛ አምጡ ተብላችሁ የምታስተምሩት ቋንቋ ይሆን ነበር።

በዚህ ዘመን ሰዉ ከፍሎ እንግሊዘኛ ይማራል፣ ፈረንሳይኛን ለመማስተማር ለልጁ አሰጠኝ የሚቀጥር ወላጅ አለ፣ ጀርመንኛንና አረብኛን አቀላጥፎ ለመናገር የሚፈልገዉ ወጣት በርካታ ነዉ።

ቻይንኛን መናገር ትልቅ የአስተርጓሚነት የስራ እድል የሆነባት መዲና ናት ሰዉ ግን ኦሮሚኛን ማወቅ ይፀየፋል። ባህሉንም ላለመዉረስ ያምፃል። ምክንያቱ ግልፅ ነዉ! ብልፅግናዎች ኦሮሞነትን ወደ አፀያፊ ማንነት ቀይራችሁታል።

በናንተ ዘመን ኦሮሞነትን ሁሉን ልብላ ባይ ስግብግብነት አርጋችሁታል። አለም አቀፍ ከተማን ኬኛ ብላችኋል
ሚዲያችሁን ጥላቻ መትፊያ ተቋም አርጋችሁታል።

ፍቅር ሰባኪ ኦሮሞን ከሚዲያችሁ ነቅላችኋል
ሰዉ ከኦሮሞ ጋር እንዳይደሰት ለኢሬቻ ተሳደባችሁ፣
ሰዉ ከኦሮሞ ጋር እንዳያዝን በሀጫሉ ሞት ንፁሀንን አሳረዳችሁ።
ዛሬ ሰዉ ኦሮሞነትን ጠላ፣ ቋንቋዉን ተፀየፈ፣ ባህሉን ሸሸ።
ሰዉን የኔን ቋንቋና ባህል ዉሰድ ብሎ ከማስገደድ በፊት እኔ ኦሮሞነትን ምን አርጌ ፃፍኩት ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነዉ።

በቋንቋዉ ፍቅርን ስበኩበት፣ በባህሉ መተቃቀፍን አስተምሩበት፣በስልጣናችሁ ሰዉ ማረድ ትታችሁ አራጅን ቅጡበት፣ በሚዲያችሁ ኬኛ እያሉ ማላዘንን ተዉና! የሁላችን ብላችሁ ፍቅርን ዝሩ።

ወጣቶቻቻችሁን የጥላቻ ሀዉልት ገንቢና የድል ሀዉልት አፍራሽ ደናቁርት አታርጓቸዉ።
ያንግዜ ኦሮሞነት በአጣና የምታስተምሩት ሳይሆን አምጡ ተብላችሁ የምትሰጡት፣ የታለ ተብላችሁ የምታሳዩት ተፈላጊ ማንነት ታረጉታላችሁ።

ከድምፃዊ ጃንቦ ጆቴ የተወሰደ

21/06/2022

ወገን
ወለጋ ላይ አለቀ

21/06/2022

ወለጋ እየሆነ ያለው ይህ ነው
ወጌኔ ወገኔ

Address

Mersa
Welo

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia hagerie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopia hagerie:

Share

Category