
29/08/2025
የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል “የእብድ ውሻ እና ተያያዥ በሽታዎች” ክትባት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ!
******************//******************
AWP 23/12/2017 ዓ.ም|አለታ ወንዶ
ሆስፒታሉ በማህበራዊ ትስስር ገፁ እንደገለፀው፤ ከዚህ ቀደም የአከባቢው ማህበረሰብ ይህን ክትባት ለማግኘት ብዙ ርቀቶችን ይጓዝ እንደነበር ጠቅሶ፥ አሁን ደግሞ በሆስፒታሉ የእብድ ውሻ በሽታ ክትባት እና ተያያዥ ህክምናዎች መሰጠት መጀመሩን አስታውቋል።
የእብድ ውሻ በሽታ የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት መሆኑን የገለፀው ሆስፒታሉ፥ በበሽታው በተለከፉ እንስሳት ንክሻ ማለትም በውሻ፤ በድመት፤ በቀበሮ፤ በተኩላ፤ በጅብ፤ በሌሊት ወፍና በሌሎችም ወደ ጤናማ ሰው ሊተላለፍ የሚችል አደገኛ በሽታ መሆኑን አብራርቷል።
ሆስፒታሉ አክሎም፤ ተጋላጭነት ላለባቸው ሰዎች ለበሽታው ከመጋለጣቸው በፊት አስቀድሞ የመከላከያ ክትባትን መስጠት አንዱ የመከላከያ መንገድ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።
የተነከሰ ሰው ደግሞ በጤና ማዕከላት የሚሰጠውን ክትባትና ተያያዥ ሕክምና በጊዜ መውሰድ አለበት ያለው ሆስፒታሉ፥ የማንኛውንም የእብድ ውሻ በሽታ ሊያስተላልፉ የሚችሉ እንስሳትን ንክሻ ማወቅ ስለማይቻል፣ ንክሻው ካጋጠመን ሳናቅማማ ክትባቱን መውሰድ እንደሚያስፈልግ መክሯል።
መረጃው የሆስፒታሉ የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፅ ነው።
Join us our telegram Channel👇
https://t.me/httpstelegrammealetawendopress
Subscribe our YouTube channel 👇
https://youtube.com/?si=gBoNTIgrGQVo-ErC