Wolaita Intelligence Security

Wolaita Intelligence Security Thank You Always Like Me Ethiopia Prevailing

መንግሥት ጽንፋኞች አመለካከት ማጠን አለበት !! #መንግሥት ሰማያት ሰባክዮች ለምን ይጣላሉ? #ምድር ጊዚያዊ መኖሪያ ነዉ እንጅ ዘላለማዊ መኖሪያ አይደለም ፡፡1. መንግስት የመንግስትነት ሚና...
03/04/2022

መንግሥት ጽንፋኞች አመለካከት ማጠን አለበት !!

#መንግሥት ሰማያት ሰባክዮች ለምን ይጣላሉ?
#ምድር ጊዚያዊ መኖሪያ ነዉ እንጅ ዘላለማዊ መኖሪያ አይደለም ፡፡

1. መንግስት የመንግስትነት ሚናውን በትክክል መወጣት ሳይችል ሲቀር ህገወጥነትና ስርአት አልበኝነት መንሰራፋቱ የማይቀር ነው። የፖሊስና የመከላከያ ኃይሉ ከወገንተኝነት በፀዳ ጥፋተኞችን ማስታገስ ሳይችል ሲቀር ከዛም አልፎ ለህገወጦች ከለላ ሲሆን ደግሞ አደጋው የከፋ ይሆናል። ህዝብም ፍትሃዊ በመሰለው መንገድ መብቱን፣ ንብረቱንና ሃልውናውን ለማስከበር የየራሱን መንገድ መከተል ይጀምራል። ይህ ደግሞ ሃገራችንን ወደ አደገኛ እርስ በርስ ጦርነት ሊያመራት ይችላል። እናም መንግስት ህዝባዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። የተበደለ ሁሉ "መንግስት አለልኝ" ሲል በዳይ ሁሉ "መንግስት አለብኝ" ሲል ያኔ ህገ ወጥነት ቦታ ያጣል።

2. ሃገራችን ያለችበትን ተጨባጭ ግምት ውስጥ በማስገባት ህዝባችን የጥፋት ፊታውራሪዎችን ትንኮሳ ጆሮ ሊነሳ ግድ ይላል። ይህንኑ ሲያደርግም ቆይቷል። በሰላም እጦት አትራፊ እንደሚሆኑ የሚያስቡት ወጥመዳቸውን እዛም እዚህም መዘርጋታቸው አይቀርም፤ ህዝብ ግን በሰላም እጦት የመጀመሪያው ተጎጅ ነውና ወጥመዳቸውን ከመበጣጠስ ውጭ የተሻለ አማራጭ የለውም።

3. ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለማችን ሃገራት የተለየች አይደለችም፤ የተፈጥሮ ህጎች በሌሎች ሃገራት ላይ ተግባራዊ እንደሚሆኑት በኢትዮጵያም ላይ ይሆናሉ፤ ለኛ ሲባል የሚታጠፍ ተፈጥሯዊ ስርዓት የለም። ፍትህ መሰርታዊው ህግ ነው። ፍትህ በእጅጉ ሲዛባ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ዓለማችን በርካታ ምሳሌዎችን አዝላለች። የታሪክ እምብርት የሆኑ ሃገራት ወደ ፍርስራሽ ክምርነት ተቀይረው አይተናል፣ በተፈጥሮ ሃብት የታደሉ ሃገራት የጦርነት አውድማ ሆነው አስተውለናል። "ኢትዮጵያ አትፈርስም" ከሚል እሳቤ ወጥተን የማህበረሰብ ህልውና የሚረጋገጥባቸውን የተፈጥሮ ህጎች እንከተል፤ ያኔ ሃገራችንን ከጥፋት እንታደጋለን፤ ወደ እምርታ ጎዳናም እናመራታለን።

4. የሁሉም ኃይማኖቶች( በተለይም የእስልምናና የኦርቶዶክስ) የኃይማኖት አባቶችና ሰባኪያን በቅርበት የምር መነጋገር ያለባቸው ጊዜ ላይ ደርሰናል። የተጀመሩ ውይይቶች ተጠናክረው ይቀጥሉ። ይህችን ሃገር ለመታደግ የሚጠበቅባችው ቀናኢነት ብቻ ይመስለኛል። የጥላቻ ሰበካዎችን ማስቆም፣ ከፍትህ ጎን በጋራ መቆም፣ የተከታዬቻችውን ስነምግባር ማረቅ፣ ከጭፍን ተከታይነት ይልቅ ምክኒያታዊነትን ዋጋ የሚሰጡ ምእመናን ለማፍራት መትጋት ••• ለነገ የማይባሉ ስራዎች ናቸው። የኃይማኖት ሰባኪያን በወጣቱ አስተሳሰብ ላይ የሚያሳድሩት ተፅእኖ የላቀ ነውና ይህንኑ ተፅእኖ የመፍጠር አቅም ሃገርን ለመታደግ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

5. የመገናኛ ብዙሃን የህዝብን ሃሳብ በመዘወር አቅማቸው አቻ አይገኝላቸውም። በ100 ቀናት ውስጥ ከ800 ሺህ በላይ ህዝብ ያለቀበት የሩዋንዳው አስከፊ እልቂት መነሻ ለረጅም ጊዜ የተዘራውን የጥላቻ ዘር የለኮሰው አንድ የሬዲዮ ጣቢያ መሆኑን መርሳት የለብንም። እጣ ፋንታችንን እየቀረፁ የሚገኙት ማህበራዊ ሚዲያዎችም በጣቶቻችን ስር ያሉ ናቸው። ዘርና ኃይማኖት ሳንለይ ለፍትህ መቆምን እናስተምርባቸው፣ የምንኖርባትን መርከብ በጋራ የምንጠብቅባቸው መሳሪያዎች እንዲሆኑ እንስራ፣ ነውርን የሚፀየፍ ትውልድ ለመቅራፅ ነውርን ተፀይፈን እናሳይ። በመጨረሻም፣ የሚያደርጉት አያውቅምና ይቅር በላቸው

♥ እግ/ር ሆይ! ህዝባችናንና ሃገራችንን ጠብቅ!

26/02/2022
✅የጦና ንቦች የ9 ሳምንታት የሀዋሳ ቆይታ ምልከታ👀🔴ሊጉ በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ለአንድ ወር ከ 20 ቀናት ያህል ይቋረጣል 🔔ይሄ ጊዜ ወላይታ ዲቻ እራሱን በሚገባ እንዲፈትሽ ይረዳው ይሆን?...
25/12/2021

✅የጦና ንቦች የ9 ሳምንታት የሀዋሳ ቆይታ ምልከታ👀
🔴ሊጉ በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ለአንድ ወር ከ 20 ቀናት ያህል ይቋረጣል
🔔ይሄ ጊዜ ወላይታ ዲቻ እራሱን በሚገባ እንዲፈትሽ ይረዳው ይሆን?

📆በጥቅምት ወር መጀመሪያ በሀዋሳ የተጀመረው ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሀዋሳ ቆይታውን በትላንትናው ዕለት አጠናቋል::

✅ሊጉ በቀጣይ ወደ ውድድር የሚመለሰው ከአፍሪካ ዋንጫ መጠናቀቅ በኋላ የካቲት ወር ላይ መሆኑ ታውቋል::

🐝የወላይታ ዲቻ የሀዋሳ ቆይታን ስንመለከት---

✅የጦና ንቦች ሀዋሳ ላይ ባደረጉት የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ በድሬዳዋ በጠባብ የጎል ልዩነት ቢሸነፉም ከዛ በኋላ ባስመዘገቡት ተከታታይ 4 ድሎች ምናልባትም በክለቡ ታሪክ እጅግ መልካም የሚባል አጀማመር በማድረግ ሊጉን እስከመምራት ደርሰው ደጋፊውን ጮቤ አስረግጠዋል::

✅ንቦቹ ጥሩ ከተንቀሳቀሱባቸው ጨዋታዎች መካከል ከ ሰበታ ከተማ ጋር ያደረጉት ጨዋታ የሚጠቀስ ነው:: በጥብቅ መከላከል እና በፈጣን መልሶ ማጥቃት የአጨዋወት ዘይቤ ሰበታን 4-2 በመርታት በዕለቱ አስደሳች ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል::

✅ወላይታ ዲቻዎች ኢትዮጵያ ቡናንም 3-1 ያሸነፉበት ጨዋታ ከ ሰበታው ጨዋታ በመቀጠል ንቦቹ መልካም እንቅስቃሴ ያደረጉበት ጨዋታ ነበረ አዳማ ከተማን እና ሀዋሳ ከተማን በተመሳሳይ 1-0 በሆነ ውጤት የረቱበት ጨዋታ በእንቅስቃሴ ረገድ ከሌሎቹ ጨዋታዎች የወረዱ ሆነው ተገኝተዋል ይሁን እንጂ 3 ነጥብ በሁለቱም ጨዋታዎች ንቦቹ ማግኘት መቻላቸው በጥሩ ጎን የሚታይ ሆኗል::

✅በ6ኛ ሳምንት ንቦቹ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረጉት ጨዋታ 0-0 አቻ የተለያዩ ሲሆን በጨዋታው መከላከልን ብቻ መሰረት ያደረገ አጨዋወት ይዘው የገቡ መሆኑ በአብዛኛው የስፖርት ቤተሰብ ዘንድ ጥያቄን አስነስቷል:: ምንም እንኳን ከጨዋታው 1 ነጥብ ይዘው ቢወጡም በቡድኑ ላይ ጥያቄ መነሳት የጀመረው ከዚህ ጨዋታ በኋላ ነው::
ከ7ኛ ሳምንት እስከ 9ኛ ሳምንት እጅግ አስቸጋሪ ወቅት ያሳለፉት ንቦቹ በ3 ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈትን አስተናግደዋል በባህርዳር በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በሲዳማ ቡና በእነዚህ ጨዋታዎችም ወላይታ ዲቻን የማይመስል ደካማ የቡድን እንቅስቃሴ ታይቷል:: ቡድኑ ምን አይነት አጨዋወትን እንደሚከተል እንኳን በውል ለማወቅ አስቸጋሪ የሆኑ 3 ጨዋታዎችን አስመልክቶናል መሸነፍ አንድ ነገር ሆኖ ሳለ በ 90 ደቂቃ ውስጥ የቡድኑ ኳስን የመቀባበል accuracy status + የጎል ሙከራ ጠፍቷል ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ላይ ደርሶ እንደነበረ ማየት ተችሏል::

✅የሀዋሳ ላይ የንቦቹ ቆይታ ሁለት አይነት መልክ የነበረው ሲሆን የጀመሩትን በውጤት የታጀበ መልካው አጀማመር በተከታታይ ሽንፈቶች በማጣፋት በደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ አካባቢ ላይ ሆነው ቆይታቸውን አጠናቀዋል::

✅በዚህ ሰዓት ሊጉ መቋረጡ ከሚጠቅማቸው ቡድኖች መካከል ወላይታ ዲቻ አንዱ ነው:: የዕረፍቱን ጊዜ በሚገባ የሚጠቀሙበት ከሆነ ማለት ነው:: ምንም አይነት ጊዜ ማባከን ሳያስፈልግ ከቀናት ዕረፍት በኋላ ቡድኑ ወደ ልምምድ መመለስ ይኖርበታል:: ከፍተኛ የቅንጅት ችግር እና የስነልቦና መውረድ ንቦቹ የታየባቸው በመሆኑ በዚህ ረገድ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል::

✅ክፍተት በሚታይባቸው ቦታዎች ላይ በውድድሩ አጋማሽ የዝውውር መስኮት ሲከፈት የተጫዋች ግዢ በማድረግ ቡድኑን ማጠናከር ያስፈልጋል::

✅ባሳለፍነው የክረምት የዝውውር መስኮት ቡድኑን ከተቀላቀሉ ተጫዋቾች 60% የሚያህሉት በተጠባበቂ ወንበር ላይ 9ኙን ሳምንት አሳልፈዋል::

  Abinet Kebede # ሀዋሳ ሴንተራል ሆቴል vs የዘማሪዉ ህልፈት ምክንያት********************************ወንድሜ እዚህ ሆቴል ላይ እዚህ ቦታ ነዉ ለህልፈት የተዳረገ...
22/12/2021

Abinet Kebede

# ሀዋሳ ሴንተራል ሆቴል vs የዘማሪዉ ህልፈት ምክንያት
********************************
ወንድሜ እዚህ ሆቴል ላይ እዚህ ቦታ ነዉ ለህልፈት የተዳረገው ::ታዲያ አይምሮ ላይ ብዙ ጥያቄዎች ስመላለሱብኝ ለምን ቦታው ድረስ ሄጄ አላጣራም ብዬ ወሰንኩኝ። ስገባ እንደማንኛውም customer(ደንበኛ ) ነበረ የገባሁት።
ታዲያ እንኳንስ ሰዉ የሞተበት ቀርቶ የሞት መርዶ የሰሙ ሁሉ አይመስሉም ...መደበኛ ሥራቸዉ ላይ ናቸዉ።ሆቴሎ ዉስጥ 1ኛ ፎቅ ላይ ነዉ ጋንዳዉ ያለዉ ስደርስ ጅም ቤት አጠገቡ አለ የሆቴሉ ሰራተኞች ክፍልም እዛው ላይ ነዉ። በተጨማሪ ለዋነዉ ሆነ ለጂም የሚመጡ ተጠቃሚዎች ሂሳብ የሚከፍሉት እዛው ዋናው ጋንዳዉ አጠገብ ነዉ።ጥያቄዬን እዛዉ ጋንዳዉ አጠገብ ያለዉ ቢሮ ላይ የምትሠራ ልጅ እንዲህ ብዬ ጠየኳት..ትላንትና እዚህ ቦታ ሰዉ በዋና ላይ እያለ አደጋ ደርሳል ይበላል? አይ እኛ አልነበርንም ... ጥልቀቱ ስንት meter ነው ? 2 meter.
እሸ ዋና ማነጀሩን ጥርልኝ ? የለም ..
እሺ እንዴትስ ይህ ሁሉ ቢሮ ክፋት ሆኖ አንድ ሰዉ አልነበረም በሰዓቱ ? እኔ እንጃ .... ብላኝ ትንሽ ለማፅናናት ሞክራ ትታ ወደ ዉስጥ ገባች ። ሁሉም የሰራተኞች ዓይን ከሩቅ ሆኖ እኔን መከታተል ጀመሩ። በጣም የገረመኝ lifesaver እኔ ውሃው ላይ የሚወድቅ መስሎት እኔን መረጋጋት ጀምረ ከዛ ትላንት እንዳልነበረ ነግሮኝ ከሩቅ ቁጭ
አለ። መልስ የለም ጥያቄ እንጂ ... # የኔ_ጥያቄ ......
# 1ኛ/ እንዴት ትልቅ ሆቴል ህይወት አድን (Lifesaver) ሰራተኛ በቦታው አንዴት አይኖርም ?
# 2ኛ/ ጋንዳዉ አጠገብ ብዙ ቢሮዎች አሉ ጂም ቤትም አለ እንዴትስ 1ሰዉ ማየት አልቻለም ?
# 3ኛ/ ሆቴሉስ ሰዉን የሚያክል ነገር ሞቶ እንዴትስ መሥራት ይችላል?
# 4ኛ/ በሆቴሉ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተተከሉ ካሜራዎች አሉ እነዚህ ካሜራዎች የምመለከተው የህግ ክፍል ከሆቴሉ በአስቸኳይ መረጃውን ወስዶ በተገቢው ሁኔታ መፈተሽና ውጤቱ ለህዝቡ መቅረብ አለበት። በመጨረሻም መደረግ ያለበት ጉዳዩ እሰከ ሚታወቅ ሆቴሉ ለምን አይዘጋም ? lifesaver በቦታው ባለመኖሩ ምክንያት ለሞተው ወንድሜባይጠቅምም ለሟቹ ቤተሰብ ካሳ መክፈል የለበትም ትላላችሁ?
ህግንና ስርዓትን ተከትሎ ነፍስን ባይተካም ተገቢውን ካሰ መክፈል
እንዳለበት ከሆቴሉ የሚጠበቅ ይሆናል።
# ታስሮ የሚጣራ እንዳለ ሁሉ ሆቴሉም ተዘግቶ ይጣራ ባይ ነኝ ።ሞቱን ያቀረቡት ለፍርድ ይቅረቡ!!መልስ ፥ጥያቄ ለሆነበት ሁሉ ይሰጥ!
የዘማሪ ምትኩ ቶማስ ነብስ ለመመለስ ባይችልም መንግስት የምርመራ ውጤቱን ለህዝቡ ማብራሪያ እንድሰጥ እና ጉዳዮን እንድከታተል እንጠይቃለን
ታህሳስ 13,2014 ዓ.ም

 #ወላይትኛ እንማማር   #80 በላይ ወላይትኛ ስሞች በአማርኛ አሁን አሁን በአማርኛ እየተተኩ ብሆንም ወጣቱ ትውልድ ልዑላዊነትን በጥንቃቄ ከተቀበለ መመለስ ይቻላል። እነዚህ ከአማርኛ ስሞች ...
15/12/2021

#ወላይትኛ እንማማር #80 በላይ ወላይትኛ ስሞች በአማርኛ አሁን አሁን በአማርኛ እየተተኩ ብሆንም ወጣቱ ትውልድ ልዑላዊነትን በጥንቃቄ ከተቀበለ መመለስ ይቻላል። እነዚህ ከአማርኛ ስሞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለቸው ናቸው።

1. PALAHA=ተረፈ
2. GALATA=ተመስገን
3. ANJJA=ብሩክ/በረከት/ተባረክ
4. MAADDA=እርዳቸው
5. GIIGEE=አማረች
6. WOPPEE=ሰናይት
7. LO7ITEE=ቆንጂት
8. MAKKISEE=ድንቅነሽ
9. ASHIKKA=ትህትና
10. DOLA=በቀለ
11. DOSA=ፍቅሩ
12. DAROTA=በዛብህ
13. UFAYISSA=ደሳለኝ
14. MILKKA=ምኞት
15. MAARA=ምህረቱ
16. MAARITEE=ምህረት
17. CIISHSHA=አበበ
18. LA7A=ነጻነት
19. ZAARA=መለሰ
20. XOONA=አሸናፊ
21. MINOTA=ጠንክር
22. YALLISEE=ዘመናይ
23. KAWOTEE=ንግስት
24. GAAGGA=በላቸው
25. TOORA=ጦሩ
26. BARAATA=አንዱዓለም
27. SIIQOTEE=ፍቅርተ
28. ADABEE=ትርፌ
29. BUZEE=የኔነሽ
30. ASHSHA=አዳኔ
31. DAANA=ኑር
32. GAAMMOO=አንበሴ
33. GIFAATEE=አዲስ
34. DEMMA=ተገኝ
35. DUREESA=ሀብታሙ
36. KUMA=ሙሉ
37. KUMETEE=ሙሉነሽ
38. ISHALEE=ፀጋነሽ
39. ANJJITEE=ብሩክታዊት
40. BATALA=ሊቃውንት
41. NAANA=ገኔነ
42. LOOHA=ሥልጣኑ
43. BAASSA=መሠረት
44. KAAFA=ደገፉ
45. SAATA=ሳህሉ
46. FINTTA=አሻግሬ
47. POLA=ፍፁም
48. KALLACHCHOO=ዘውዴ
49. BURAAQA=እንዳሻው
50. SUNTTA=ስሜነህ
51. SINTTA=መሪሁን
52. GAMI"A=ዘላለም
53. DE'A=ኑር
54. DALGGA=ብዙነህ
55. DALGGITEE=ብዙነሽ
56. LEQQA=በለጠ
57. TEQQA=መለሰ
58. DAGATOO=ሰብስቤ
59. KOMBEE=አብይ
60. HODOOTOO=ተስፋዬ
61. ALLEEQEE=ብርቅነሽ
62. WOLQQA=ኃይሉ
63. SHAGGITEE=ውብነሽ
64. BAKKALOO=ንጋቱ
65. DOOGISOO=ማዘንጊያ
66. BAPPITEE=አረጋሽ
67. BAALA=ደጉ
68. BAALOTEE=ደግነሽ
69. MAARITEE=ምህረት
70. ALAAHOO=አሰማኼኝ
71. TUMA=እውነቱ
72. DOOGISOO=አስሬስ
73. GATTA=ደረሰ
74. ODA=ብስራት
75. MERETOO=ሠራዊት
76. MALALOO=ግሩም/ገረመው
77. AMMANOO=ታመነ
78. AMMANEE=ታመነች
79. DIQAASOO=መሳፍንት
80. WOYZEE=ሳምራዊት

አረብ ኤሜሬትስ አሜሪካን ያደነገጠ ውሳኔ አሳለፈች_________________________________የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) ከአሜሪካ ለመግዛት የተስማማችውን የ23 ቢሊዮን ዶላር...
14/12/2021

አረብ ኤሜሬትስ አሜሪካን ያደነገጠ ውሳኔ አሳለፈች
_________________________________
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) ከአሜሪካ ለመግዛት የተስማማችውን የ23 ቢሊዮን ዶላር የድሮን ጦር መሳሪያ ሽያጭ ስምምነት ለመሰረዝ ከጫፍ መድረሷ ተዘግቧል።
ኤሜሬትስ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው አሜሪካ የምትሸጣቸውን የጦር መሳርያዎች በተመለከተ የምታስቀምጣቸው የደህንነት መስፈርቶች ንብረቱን በሚገዛው አገር ሉዓላዊነት ላይ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ እንደሆነ Wall Street Journal ዘግቧል። የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ አሜሪካን ሰራሽ የሆኑትን ኤፍ-35 አውሮፕላኖችን፣ ሪፐር ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ድሮኖችን እና ሌሎች ዘመናዊ ጥይቶችን ለመግዛት የ23 ቢሊዮን ዶላር ውል የነበራት ቢሆንም አሁን ግን ሃሳቧን ሙሉ በሙሉ በመቀየር ሌላ አማራጭ ማማተር ጀምራለች። የስምምነቱ መፍረስ በመካከለኛው ምስራቅ እና ሌሎችም ቦታዎች ለአስርት አመታት የዘለቀው የአሜሪካ የጦር መሳሪያ አቅራቢነት ሚና እየቀነሰ መምጣቱን በግልጽ ያሳየ መሆኑን በርካታ ዓለም አቀፍ ተንታኞች በመግለጽ ላይ ይገኛሉ። የባህረ ሰላጤው ሀገር UAE ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት ብሎም ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖቿን በሌሎች አገራት ግጭቶች ላይ መላኳ ከአሜሪካ ጋር በተደጋጋሚ እሰጣ-ገባ ውስጥ ሲከታት እንደቆየ ይነገራል። ለአብነት UAE ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖቿን በኢትዮጵያ ግጭት ውስጥ አሳትፋለች በሚል ከአሜሪካ በኩል ተደጋጋሚ ወቀሳ ሲሰነዘርባት መጥቷል። የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን ከሰሞኑ በተመሳሳይ አቡዳቢ አቅንተው የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ለኢትዮጵያ መንግስት ድሮን ማቅረቡን ያቁም በሚል መጠየቃቸው መዘገቡ ይታወሳል።
https://www.wsj.com/articles/united-arab-emirates- threatens-to-pull-out-of-23-billion-f-35-drone-deal- with-u-s-11639491997 5 mins · Public

ሰበር ዜናጋሻና እና አምባሳሌ ምን እየሆነ
11/12/2021

ሰበር ዜና

ጋሻና እና አምባሳሌ ምን እየሆነ

 #እጅግ  #በጣም  #ጥንቃቄ  #ለጤንነታችን!!ምንጩ ያልታወቀና በባለሙያ ያልተመረመረ ሥጋ ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ በሕገወጥ መንገድ ሰገባ በፖሊስ ተያዘ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ራሱንና ...
08/12/2021

#እጅግ #በጣም #ጥንቃቄ #ለጤንነታችን!!

ምንጩ ያልታወቀና በባለሙያ ያልተመረመረ ሥጋ ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ በሕገወጥ መንገድ ሰገባ በፖሊስ ተያዘ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ራሱንና የቤተሰቦዎን ጤንነት ይጠብቁ።

የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤትና ጤና ጽ/ቤት ጋር በመሆን መክሰኞ በዋጃ ቄሮ ቀበሌ የፍተሻ ኬላ ላይ ከሆሳዕና ከተማ ምንጩ ያልታወቀና ደኅንነቱ ያልተረጋገጠ በባለሙያ ያልተመረመረ የታረደ የከብት ይሁን የሌላ እንስሳ ያልተለየ ጉበት ወደ ወላይታ ሶዶ ከተማ ሊገባ ሲል በሶዶ ዙሪያ ወረዳ በዋጃ ቄሮ ቀበሌ በጉኑኖ ማዞሪያ ባለው የፍተሻ ኬላ በወረዳው ፖሊሶች ጠንካራ ክትትል ጉበት ለመያዝ ተችሏል። እነዚህ ህገወጥ ነጋዴዎች ከዚህ በፊትም በተለያዩ ጊዜያት ተመሳሳይ ድርጊት መፈጸማቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል። የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ም/ኢ/ር ታመነች ባሳ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ ሥራ ህደት አስተባባሪ ይህ ድርጊት በኅብረተሰቡ ጤንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስና ለከፋ በሽታ ሊዳርግ የሚችል መሆኑ ታውቆ የአካባቢው ህዝብ ጥቆማ በማድረግ ድርጊቱን ማጋለጥና ለህግ በማቅረብ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግና ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ራሱንና ቤተሰቡን ካልተፈለገ የጤና ህመምና ጉዳት መጠበቅ ያስፈልጋል ስሉ አሳሰቡ። ወንጀልን በጋራ እንከላከል።
ምንጭ:- የሶዶ ዙሪያ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ነው

ከታርክ ማህደርወላይታ ዉስጤ ነዉ የኢትዮጵያዊያንን አዱዋ  #ድልን ሲናነሳ የጀግናው  #ካዎ  #ጦና ጋጋ እና የንጉሡ ጦና  # የልብ ጓደኛቸው ጀግናው  # ንጉሥ  # አባ  # ጂፋር ሚና ከፍ...
06/12/2021

ከታርክ ማህደር

ወላይታ ዉስጤ ነዉ

የኢትዮጵያዊያንን አዱዋ #ድልን ሲናነሳ የጀግናው #ካዎ #ጦና ጋጋ እና የንጉሡ ጦና # የልብ ጓደኛቸው ጀግናው # ንጉሥ # አባ # ጂፋር ሚና ከፍተኛ እንደነበር #ታሪክ ያሳያል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በታርክ ፀሃፊት ምንም ትኩረት # ያልተሰጠው በአደዋ ጦርነት ላይ # ጀብድ የፈፀሙ ከወላይታ # በንብ ጦርነት የአፄ # ሚንልክን ጦር #6 ጊዜ በማንበርከካቸው ለአዱዋው ጦርነት # ለመድፊ ውግያ ተመልምሎ አርበኝነታቸውን ያሳዩ ጀግኖችንና # ከወላይታ ተነስቶ የሸዋ ጦርን በመቀላቀል አድዋ ላይ ጠላትን # ያንበረከኩ ጀግኖችን ታርክ ቀኑን ጠብቆ # ይዘከራል የሚል እምነት አለን። ሌላው እምየ # ሚንልክ ወደ አደዋ ይዞ ከዘመቱዋቸው ጦሮችና የጦር አለቆች የወላይታውን ንጉሥ # ካዎ ጦናንና የንጉሡ ጦና የልብ ጓደኛቸው የጅማውን ንጉሥ አባ # ጅፋርን ህዝበንና ሀገረን ጠብቁልኝ በማለት ወደ መሀል ሀገር እንድመለሱ አድርጉቹዋል። ይህ የምያሳየው # የእምነትን ጥግ ነው። እናም አድዋ ላይ ማንም ማንንም ቀጠሮ አላዋጋም ማንም የማንም # ቅጥረኛ አልነበረም። አድዋ ሁሉም # ኢትዮጵያዊ የሀገሩን ሉዐላዊነት የተዋደቀበት፤ በሀገር ፍቅር # ደሙን ያፈሰሰበት አጥንቱን የከሰከሰበት፤ # በመስዋትነት ሀገር ያቆየበት የነፃነት የድል በዓል ነው።አድዋ የኔም ያንተም የኛም # ድል ነው!!ስለዚህ በዚሁ # ታሪካዊ ወቅት ለታሪክ ሰሪው ጀግናው ካዎ # ጦና እና #ሌሎችም ጀግኖች መታሰቢያ ብሰራላቸው #ያንሳቸዋል እንጂ አይበዛም!! #ቅርስ ያለው #ታሪክ አለውና !!

Dawit Lemma

Me


Welayta music plays a prominent role in national entertainment in Ethiopia. The unique and fast-paced Welayta tunes have...
05/12/2021

Welayta music plays a prominent role in national entertainment in Ethiopia. The unique and fast-paced Welayta tunes have influenced several styles and rhythm as it continues to shape the identity of Ethiopian musical diversity. Various famous Ethiopian artists from other ethnic groups have incorporated Welayta musical style into their songs, including vocalists Tibebu Workeye,Teddy afro and Tsehaye Yohannes. Just as influential are Welayta traditional dance forms that are often adopted by musicians and widely visible in Ethiopian music videos

Address

Ethiopia +
Wolkite

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wolaita Intelligence Security posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category