Qebena tv

Qebena tv media & information !

30/07/2026
16/07/2026
10/07/2026

ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርት

" ሰውን መርዳት በህይወት እያለ ነው" በሚል መሪ ቃል ታላቁን የኪነ-ጥበብ ሰው አርቲስት ደገፋ ሳቢርን ለማሳከም እና ቤተሰቦቹን ለመርዳት ታስቦ በቀቤና ልዩ ወረዳ ባህል ቱሪዝም እና በልዩ ወረዳው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን አስተባባሪነት እሁድ በ12/11/2018 ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በወልቂጤ ከተማ በቀቤና ባህል ማዕከል ተዘጋጅቷል።

የፕሮግራሙ ገቢ ሙሉ በሙሉ ለአንጋፋው አርቲስት ደገፋ ሳቢር ህክምና የሚውል ልዩ የበጎ አድራጎት የሙዚቃ ኮንሰርት ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ በነባር እና አዳዲስ አርቲስቶች የተዋቀረው የቀቤና ልዩ ወረዳ ባህላዊ እና ዘመናዊ የኪነት ቡድን ስራዎቹን ለታዳሚው በስፋት የሚያቀርቡ ሲሆን
በተጨማሪም ሌሎችም የአርስቲስቱ አድናቂ የሆኑ ተጋባዥ ድምፃውያንም ይገኛሉ።

በመሆኑም በዚህ ፕሮግራም ላይ በሀገር ውስጥም በውጭ ያላችሁ የአርቲስቱ እና የኪነጥበብ አድናቂዎች በሙሉ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

የመግቢያ ቲኬቱን በቀጥታም ሆነ በኦንላይን መግዛት የሚቻል ሲሆን ለዚህ በጎ ተግባር ሁላችንም እንድንረባረብ ጥሪ እናስተላልፋለን !

"ሰውን መርዳት በህይወት እያለ ነው"
****
የቀቤና ልዩ ወረዳ ባህልቱሪዝም እና የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

03/07/2026

በህብረተሰቡና በመንግስት መካከል ግልጽነት ያለው ግንኙነት በመፍጠር በልዩ ወረዳዉ እየተከናወኑ የሚገኙ ልማታዊ ስራዎችን ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለጸ።

ሰኔ 26/2018(ወልቂጤ)ጽ/ቤቱ የህብረተሰቡን መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ በተያዘዉ 2018 በጀት አመት ወቅታዊና ፍትሃዊ መረጃዎችን በፍጥነት በማድረስ ዉጤታማ ስራ መስራት መቻሉም ተጠቁሟል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድልናስር ሚፍታ እንደገለጹት ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት አመት በልዩ ወረዳዉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁነቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ዉጤታማ ስራዎች መከናወናቸዉን ገልጸዋል።

በበጀት አመቱ የቀቤና ልዩ ወረዳ የልማት፣ የሰላም እና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም የልዩ ወረዳዉ መልካም ገጽታ፣ የቱሪዝም መስህቦችን ጨምሮ ሌሎች የልማት እና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ዌብሳይትን ጨምሮ በተለያዩ 7 የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም መረጃ ማድረስ መቻሉን ጠቁመዋል ።

ጽ/ቤቱ በልዩ ወረዳዉ ከሁሉም የመንግስት ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት እና ከህዝብ የሚነሱ አስተያየቶችን በመሰብሰብ እና በመተንተን ነፃ፣ ተኣማኒ እና ፍትሃዊ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ የህብረተሰቡን ንቁ ተሳትፎ ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለዉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ አብድልናስር ገልጸዋል።

ኃላፊዉ አክለዉም በበጀት አመቱ አላማ ተኮር የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስርአትን ተከትሎ ከመስራት አንፃር ፣ ክልላዊና ሀገራዊ የልማትና የመልካም አስተዳደር አጀንዳዎችን ከማስረፅ ረገድ የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ጠቅሰዋል ።

በልዩ ወረዳዉ የሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለህብረተሰቡ በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊዉ አብራርተዋል።

ዘጋቢ፦ ሪያድ ሙህዲን

  አሰፋ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ረዳት ተጠሪ
26/06/2026

አሰፋ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የመንግስት ረዳት ተጠሪ

ድምቀቶች🥰
25/06/2026

ድምቀቶች🥰

የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት እና የቀቤና ህዝብ የኦገት ሥርዓት በአካባቢያዊ እና በባህላዊ ግንኙነቶች የተሳሰሩ፣ ሁለቱም ማህበረሰቡን በፍትህ፣ በሰላም እና በስነ-ምግባር የሚመሩ የሀገር በቀል አስተ...
22/06/2026

የኦሮሞ የገዳ ሥርዓት እና የቀቤና ህዝብ የኦገት ሥርዓት በአካባቢያዊ እና በባህላዊ ግንኙነቶች የተሳሰሩ፣ ሁለቱም ማህበረሰቡን በፍትህ፣ በሰላም እና በስነ-ምግባር የሚመሩ የሀገር በቀል አስተዳደር ስርዓቶች ናቸው።

ሁለቱም ሥርዓቶች ማህበረሰቡን በዕድሜ ክልልና በኃላፊነት ደረጃ በመከፋፈል፣ ሥርዓትና ሰላምን ማስጠበቅ፣ ግጭቶችን በሽምግልና መፍታት እንዲሁም ለጋራ መግባባትና ለወግ መከበር ቅድሚያ ይሰጣሉ።

የገዳ ሥርዓት የሥልጣን ሽግግርን በየስምንት ዓመቱ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ የኦገት ሥርዓትም በተመሳሳይ መልኩ የሽምግልና እና የአመራር መዋቅሩን በዕውቀት፣ በዕድሜ እና በተሞክሮ ላይ ተመስርቶ የሚመርጥ አሠራር አለው።

የገዳ ሥርዓት በ'አባ ገዳ' አማካኝነት ፍትህን እንደሚሰጥ ሁሉ፣ የኦገት ሥርዓትም በ'ኦገት' ሽማግሌዎች አማካኝነት የህዝቡን የፍትህ ፍላጎት በማሟላት በማህበረሰቡ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል።

በአጠቃላይ፣ እነዚህ ሥርዓቶች በኦሮሞ እና በቀቤና ህዝቦች መካከል የነበረውን ጥልቅ ማህበራዊ ትስስር የሚያሳዩ እና የጋራ የሆኑ የአፍሪካዊ የዴሞክራሲ እሴቶችን የያዙ ናቸው።

21/06/2026

መለቡ 😍 ማር😍

⚽ To day at 4:00 Ethiopian time calendar ⚽France vs Senegal ⚽
16/06/2026

⚽ To day at 4:00 Ethiopian time calendar ⚽France vs Senegal ⚽

የአለም ዋንጫ ምድብ ድልድል ለምትፈልጉ 👌
16/06/2026

የአለም ዋንጫ ምድብ ድልድል ለምትፈልጉ 👌

Address

Central Ethiopia Regional State
Wolkite

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Qebena tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share