EthioInfo

EthioInfo EthioInfo Media brings, social, economic, political and cultural issues to its audience.

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአትሌት ገለቴ ቡርቃ ጎን ይቆማል ።ሰኔ 03/2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ጉዳይ ለቡዙሃን መገናኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷ...
10/06/2025

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአትሌት ገለቴ ቡርቃ ጎን ይቆማል ።

ሰኔ 03/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ጉዳይ ለቡዙሃን መገናኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን አትሌት ገለቴ የገጠማት ችግር ለመፍታት እና እልባት እንዲያገኝ በሁሉም ጉዳይ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

በሴት አትሌቶች ላይ የሚስተዋለው ጥቃት ቀላል የሚባል እንዳልሆነና አትሌቷ ወደ ሚዲያ ወጥታ የገጠማትን ችግር ተናገረች እንጂ ለሀገራቸው ብዙ ዋጋ ከፍለው ብዙ ችግር ውስጥ ያሉ አትሌቶች እንዳሉ ተናግሯል ።

የፌዴሬሽኑ ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋር ከመጀመርያው አንስቶ የገጠማት ችግር ሰፊ መሆኑን በማንሳት ለሀገሯ ስም እና ዝና የከፈለችው መስዋዕትነት ትልቅ መሆኑንና ትክክለኛውን ፍትህ እንዲሰጣት ጠይቀዋል ።

የፌዴሬሽኑ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ቢኒያም ምሩፅ የመገናኛ ብዙሃን በሴት አትሌቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ለመከላከል ከፌዴሬሽኑ ጎን በመሆን እንዲሰሩ ጠይቀዋል ።

የኢትዮጵያ አትሌቶች ማህበር ተወካዮች ሌተናል ኮነሬል አትሌት የማነ ፀጋይ እና አትሌት በላይነሽ ኦልጅራ አትሌቶችን እንደገንዘብ ምንጭ አድርጎ መጠቀም ጉዳዩን ውስብስብ እንዳደረገው እና መንግስን ጨምሮ ሁሉም አካላት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል ።

የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የሕክምና ባለሙያ ዶ/ር አያሌው ጥላሁን የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ በኢትዮጵያ እንዲተገበር እየተሠራ መሆኑን ጠቁመው የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ የአትሌቶችን ጥበቃ የሚደነግጉ ሕጎች ከ2023 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆኑ ውሳኔ ማሳለፋንና የአትሌቶች ሁለንተናዊ ጥበቃ ፖሊሲ በኢትዮጵያ እንዲተገበር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

Via EAF

 #አይዞሽ ገለቴ!  አትሌት ገለቴ ትላንት በእጇ የነበሩትን  መኪናዎችዋን አጥታ በወንድሟ ሱዙኪ ዲዛየር ሲትጓዝ ነበር።ዛሬ አራቱም ዘመናዊ መኪኖቿ  በትላንቱ ባለ ላዳ ታክሲ ሹፌር  እጅ ናቸ...
10/06/2025

#አይዞሽ ገለቴ!
አትሌት ገለቴ ትላንት በእጇ የነበሩትን መኪናዎችዋን አጥታ በወንድሟ ሱዙኪ ዲዛየር ሲትጓዝ ነበር።ዛሬ አራቱም ዘመናዊ መኪኖቿ በትላንቱ ባለ ላዳ ታክሲ ሹፌር እጅ ናቸዉ።

በመዲናዋ የደንብ ልብስ መለያን አስመስለው በመልበስ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉአዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተ...
21/03/2025

በመዲናዋ የደንብ ልብስ መለያን አስመስለው በመልበስ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣንን መለያ አስመስለው በመልበስ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማዋ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ተጠርጣሪዎቹ የደንብ ልብሱን አስመስለው በመልበስ የባለስልጣኑ ሰራተኞች አላስፈላጊ ተግባራትን እንደፈጸሙ በማስመሰል የሱቅ ማስታወቂያ ሰርተዋል፡፡

ግለሰቦቹ በዚህ ሕገ ወጥ ተግባራቸውም በርካታ ሰዎችን ማሳሳታቸውን ነው የገለጹት፡፡

ተጠርጣሪዎቹ አሁን ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡

በመላኩ ገድፍ

19/03/2025
**Job Vacancy: Amharic Script Writer (Multitude of Issues)**  **Location:** Remote **Type:** Full-time/Part-time/Freelan...
04/03/2025

**Job Vacancy: Amharic Script Writer (Multitude of Issues)**

**Location:** Remote
**Type:** Full-time/Part-time/Freelance (Negotiable)
**Salary:** Competitive, based on experience

**About Us:**
We are a dynamic and innovative media production company specializing in creating engaging content across a wide range of topics. From social issues to entertainment, education, and technology, we tackle a multitude of subjects with creativity and impact. We are looking for a talented and versatile Script Writer to join our team and help us craft compelling narratives that resonate with diverse audiences.

**Job Description:**
As a Script Writer, you will be responsible for researching, developing, and writing scripts for various media format videos. You will work on a wide array of topics, ensuring that each script is engaging, informative, and tailored to the target audience.

**Key Responsibilities:**
- Research and develop story ideas on a variety of topics, including but not limited to social issues and entertainment.
- Write clear, concise, and compelling scripts for different media formats.
- Collaborate with directors, producers, and other team members to align scripts with project goals and vision.
- Adapt writing style to suit different tones, audiences, and platforms.
- Revise and edit scripts based on feedback.
- Stay updated on current events, trends, and issues to ensure content is relevant and timely.
- Manage multiple projects simultaneously and meet deadlines.

**Requirements:**
- Proven experience as a Script Writer, Content Writer, or similar role.
- Strong portfolio showcasing a variety of writing samples across different topics and formats.
- Excellent research skills and the ability to write about complex issues in an accessible and engaging way.
- Exceptional storytelling and narrative development skills.
- Ability to work independently and as part of a team.
- Strong communication and collaboration skills.
- A passion for exploring and addressing a wide range of issues through creative writing.

**Preferred Qualifications:**
- Background in journalism, film, media studies, or a related field.
- Familiarity with video production processes.

**How to Apply:**
If you are passionate about storytelling and want to make a difference through your writing, we’d love to hear from you! Please submit your resume and a portfolio of your work to [[email protected]] with the subject line “ Amharic Script Writer Application – [Your Name].”

**Application Deadline:** [March 30, 2025]

Join us in creating stories that matter!

ተወዳጁ አርቲስት አብዱ ኪያር ከሞት አደጋ ህይወቱ ተረፈ:: እንኳን ፈጣሪ አተረፈህ 🙏🏽
16/02/2025

ተወዳጁ አርቲስት አብዱ ኪያር ከሞት አደጋ ህይወቱ ተረፈ:: እንኳን ፈጣሪ አተረፈህ 🙏🏽

ታስራለች።በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ፖሊስ "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ?" በሚል ተወስዳ የታሰረችው ምሥራቅ ተረፈ ላይ ፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁ ተሰማ።ፖሊስ ምሥራቅን አዲስ አበ...
01/02/2025

ታስራለች።

በትላንትናው እለት በአዲስ አበባ ፖሊስ "ለጥያቄ ትፈለጊያለሽ?"

በሚል ተወስዳ የታሰረችው ምሥራቅ ተረፈ ላይ ፖሊስ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ መጠየቁ ተሰማ።

ፖሊስ ምሥራቅን አዲስ አበባ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት እንዳቀረባት፣ ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ያቀረበውን ጥያቄ በመቀበል፣

"ምርመራውን አጠናቆ እንዲያቀርባት" በሚል ለጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ቀጠሮ መስጠቱን ተከትሎ፣ ምሥራቅ አሁን በአዲስ አበባ ፖሊስ እስር ላይ እንደምትገኝ ወዳጆቿ ገልጸዋል።

01/02/2025

🤍🕊

በሜታ ወልቂጤ  በአንዲት ታዳጊ ህጻን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስ...
01/02/2025

በሜታ ወልቂጤ በአንዲት ታዳጊ ህጻን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ሜታ ወልቂጤ ወረዳ አንዲት ህጻን ከቤት ተወስዳ ከተደፈረች በኋላ ተገድላ መገኘቷ ቁጣ ቀስቅሷል። “በኛ የደረሰ በማንም አይድረስ” የሚሉት የተጎጂ ቤተሰብ በታዳጊ ልጃቸው ላይ ለደረሰው ቀሰቃቂ ወንጀል ፍትህ እንሻለለን ብለዋል።
ሲምቦ ብርሃኑ ትባላለች፡፡ የስምንት (8) ዓመት ታዳጊ ህጻን ናት፡፡ የአንደኛ ክፍል ተማሪ፡፡ በዚሁ ባሳለፍነው ሳምንት ባለፈ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2017 ዓ.ም. ከትምህርት ቤት ተመልሳ ምሳ እንደበላች ከመኖሪያ ቤቷ የደረሰችበት ሳይታወቅ ቀርቷል ፡፡ በዕለቱ ፍለጋ የወጣው ቤተሰብ ታዳጊዋን ከነሙሉ ጤንነትና በህይወት ለማግኘት ግን አልታደሉም፡፡
ሮጣ ያልጠገበች ታዳጊዋ ለአዕምሮም በሚከብድ ሁኔታ ከተደፈረች በኋላ “እንዳትናገር በሚል” ከመኖሪያ ቤታቸው ጀርባ በቅርብ ርቀት ላይ ህይወቷ አልፎ መገኘቱን አንድ የቤተሰቧ አባል ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ታዳጊዋ ከተገደለች በኋላ ተሰቅላ መገኘቷን የገለጹት የቤተሰብ አባሉ “ጫማዋን ያወለቁባትና የሰቀሏት ቦታ አንድ አይደለም የ50 ሜትር ገደማ ርቀት አለው” ብለዋል።
በወረዳው የኤላ ከተማ በታዳጊዋ ላይ የተፈጸመው ጥቃት አባት የመንግስት ሰራተኛ መሆናቸው እና በስራ ቦታ መሆናቸው እንዲሁም እናት የ2 ወር እመጫት በመሆናቸው አጋጣሚውን በመጠቀም እንደነበር የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።
የተጎጂ ቤተሰብ አባል የሆኑት አስተያየት ሰጪ ቀጥለው፤ “የታዳጊዋ ቤተሰብ ቤት በፊት ለፊት በኩል ሆቴል በመሆኑ የሚገባውና የሚወታው ብዙ ነው፡፡ በጓሮ በኩል ፑል መጫወቻም አለ፡፡ ደፋሪዎችም በዚያው በጀርባ በር እንደወሰዷት ነው የቤተሰብ ስጋት” ያሉን አስተያየት ሰጪው፤ 2009 ዓ.ም. የተወለደችው ታዳጊዋ ሲምቦ ገና በ8 ዓመቷ ለዚህ ለአሰቃቂው ድርጊት ሰለባ መሆኗን በቁጪት ተናግረዋል፡፡
“ባለሙያዎች በሰውነቷ ላይ የታየውን ፈሳሽ በመውሰድ ምርመራ እያደረጉ ነው” ያሉን የቤተሰብ አባል እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋለ ተጠርጣሪ አለመኖሩንም ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ረቡዕ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ተኩል የተገኘው የታዳጊዋ አስክሬን በትናንትናው እለት ስርዓተ ቀብሩ መፈጸሙን የአዲስ አበባው ወኪላችን ስዩም ጌቱ ዘግቧል።
ዶቼ ቬለ በታዳጊዋ ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ድርጊት እና ቀጣይ እርምጃዎች ለመጠየቅ ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ አጀማ በእጅ ስልካቸው ላይ ቢደወልም ስልካቸው ስለማይነሳ አስተያየታቸውን በዚህ ዘገባ ማካተት አልተቻለም፡፡
ምስል ፤ ከቤተሰብ አባል የተገኘ

12/01/2025

የጠንቋይ ቡና ካዳሚ ነበርኩ

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when EthioInfo posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to EthioInfo:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share