31/08/2024
ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
(መሠረት ሚድያ)- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫው ሌሎች አካላት ቀጠናውን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ ኢትዮጵያ ቆማ እንደማትመለከት አስታውቋል።
መግለጫው የወጣው በትናንትናው እለት የግብፅ የጦር አውሮፕላኖች ወደ ሶማልያ መዲና ሞቃዲሾ ቀሳቁስ እና ወታደሮችን ማጓጓዛቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ነው።
"ኢትዮጵያ ብሄራዊ ፀጥታዋን ሊያውኩ የሚችሉ በቀጠናው እየተከናወኑ ያሉ ድርጊቶችን በንቃት እየተከታተለች ነው" ያለው መግለጫው የሶማልያ መንግስት ከውጭያዊ ሀይሎች ጋር በማበር ቀጠናው ላይ ውጥረት እየፈጠረ ነው ብሎ ከሷል።
መግለጫው አክሎም "ለአጭር ግዜ እና እርባና ቢስ ጥቅም ብለው አካባቢው ላይ ውጥረት የሚነዙ ሀይሎች ለድርጊታቸው ተጠያቂ ይሆናሉ" ብሏል።
ይሁንና መግለጫው በትናንትናው እለት አውሮፕላኖችን ወደ ሶማልያ ያሰማራችውን ግብፅን በስም አልጠቀሰም።
የአፍሪካ ህብረት የሰላም እና ፀጥታ ምክር ቤት ይህን የግብፅ እና ሌሎች ሀገራት ስምሪት ያፀደቀው ሲሆን እ.አ.አ ከጃንዋሪ 1/2025 ጀምሮ በሶማልያ በመሰማራት ሲቪል ዜጎችን ከአልሻባብ ሀይሎች ጥቃት የመከላከል ስራ ተሰጥቶታል።
ሂደቱ ገፍቶ ግብፅ ጦሯን በሶማልያ ካሰፈረች ሀገሪቱ ከደቡብ ሱዳን በመቀጠል በኢትዮጵያ ጎረቤቶች ያላት ሁለተኛ መገኘት ይሆና
via