Amhara fano -አማራ ፋኖ

Amhara fano -አማራ ፋኖ የኢትዮጵያ ብቸኛ መዳኛዋ ፋኖ ነው

01/02/2025

#ሰበር የድል ዜና!

የአማራ ፋኖ በጎጃም የሶስተኛ ጎጃም አገው ምድር ክፍለጦር በግዮን ብርጌድ እና ዘንገና ብርጌድ የትብብር ማጥቃት ትናንት አርብ ጥር 23 ቀን አመሻሽ ላይ የጀመረው ውጊያ እስከ ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24 ቀን 2017 ዓ.ም ቀን 7:00 ሰዓት ድረስ በተደረገ ውጊያ በወራሪው መከላከያ ላይ ሰዋዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሰናል።

#በዚህም:-
1/ ሁለት የመከላከያ ሻለቃ አመራሮች ተደምስሰዋል
2/ 39 ( ሰላሳ ዘጠኝ) የሚሆኑት ተማርከዋል
3/ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁት እግረኞች ተደምስሰዋል
4/ ሶስት ተሽከርካሪዎች በአብሪ ጥይት ነደዋል ( ከጥቅም ውጭ ሆነዋል )
5/ 16 ( አስራ ስድስት ) ክላሽ ተማርኳል
6/ 8,000 ( ስምንት ሽህ ጥይት ተማርኳል ።

በውጊያው የግዮን ብርጌድ መብረቁ ሻለቃ እና ዘንገና ብርጌድ አስደማሚ የሆነ ጥምር ማጥቃት አድርገዋል ።

ተጨማሪ በቁጥር የበዛ ሰራዊት እና የጦር መሳሪያ ወደ ጎጃም በማስገባት እና የፋኖ አባል እና አመራር በገንዘብ በመግዛት ራሴን ከውድቀት እታደጋለሁ የሚል ዕቅድ የያዘው ጨፍጫፊ ስርዓት ነገን ከትናንት መማር ባለመቻሉ አጥፍቶ ለመጥፋት በድጋሜ እያሟሟቀ ነው።

ግብረ አበሮቹ ደግሞ የአማራ ክልል መንግስት ብለው የሚጠሩት ላይ እና ፌደራል መንግሥቱ ላይ ለመሰየም እያሟሟቁ ነው። ( በነገራችን ላይ ባለፉት 34 ዓመታት አማራ ክልል መንግስት ኖሮት አያውቅም )

አዲሱ ትውልድ በመስዕዋትነቱ ህዝብ እና ሐገሩን ለመጠበቅ እየተዋደቀ ነው።
አዲሱ አስተሳሰብ ከአማራ ህዝብ አልፎ ኢትዮጵያውያንን እና የሌላውን ዓለም ትኩረት እየሳበ ነው።
አዲሱ ተስፋ በጉጉት እየተጠበቀ ነው።

አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
( የአማራ ፋኖ በጎጃም )

የሽምቅ ውጊያው እንደ "ድል ለዲሞክራሲው" ቀላል አልሆለትም፡፡ለዚያ ነው ወደ ድርድር የገባው፡፡ አፋሕድን የመሰረተውም ለውጊያ ሳይሆን ለድርድር ነው" ጄ/ል ተፈራ
28/01/2025

የሽምቅ ውጊያው እንደ "ድል ለዲሞክራሲው" ቀላል አልሆለትም፡፡ለዚያ ነው ወደ ድርድር የገባው፡፡ አፋሕድን የመሰረተውም ለውጊያ ሳይሆን ለድርድር ነው" ጄ/ል ተፈራ

የአማራ ፋኖ በጎጃም 6ኛክ/ጦር  ን/ተ/ሀይማኖት ብርጌድ በትላንትናው እለት የብልፅግናን ባንዳ ቀንድሻ የተረከበችው ፒካፕ ነው።
28/01/2025

የአማራ ፋኖ በጎጃም 6ኛክ/ጦር ን/ተ/ሀይማኖት ብርጌድ በትላንትናው እለት የብልፅግናን ባንዳ ቀንድሻ የተረከበችው ፒካፕ ነው።

ይቀጥላል
01/11/2024

ይቀጥላል

10/10/2024

በአማራ ክልል ለተሽከርካሪወች ዝግ ሁኖ የቆየው መንገድ ከነገ ማለትም ከ1-2-2017ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የአማራ ግዛቶች ክፍት እንደሚሆን የአማራ ፋኖ አስታውቋል።

ምርኮኛን መንከባከብ ከትግል ጥበቦች ሁሉ ቀዳሚው ነው።አንዳንድ ሰዎች ሳይገባቸው ይሁን ገብቷቸው ምርኮኛን መቀለብ አያስፈልግም ይላሉ።መሆን ያለበት ግን ምርኮኛን ከሚባለው በላይም መንከባከብ ...
10/10/2024

ምርኮኛን መንከባከብ ከትግል ጥበቦች ሁሉ ቀዳሚው ነው።

አንዳንድ ሰዎች ሳይገባቸው ይሁን ገብቷቸው ምርኮኛን መቀለብ አያስፈልግም ይላሉ።
መሆን ያለበት ግን ምርኮኛን ከሚባለው በላይም መንከባከብ ያስፈልጋል ምክንያቱም ምርኮኛን መንከባከብ ሌሎች ተዋጊዎችን ጥሪ እንደማድረግና ምርኮኛን ማብዛት ነው።ምርኮኛ ሲበዛ ደግሞ የተቃራኒ ሀይል ቋት ይመናመናል።ቋቱ ተመናመነ ማለት ድሉ ቅርብ ይሆናል ማለት ነው።

ባጭሩ ምርቆኛን መንከባከብ የውጊያወች ሁሉ ጥበብ ነው።

የተጠቃለለ!ዘመቻ ፻ ተራሮች፯ኛ ቀንየአማራ ፋኖ በጎጃም ፫ኛ ክ/ጦር ዛሬ በማለዳ ከሠከላ እያስሮጠ ያስወጣውን የዘር አጥፊውን ጠላት ኃይል 6ኛ እዝ 75ኛ ክ/ጦር 4ኛ እና 5ኛ ሬጂመንት ቲሊሊ...
09/10/2024

የተጠቃለለ!
ዘመቻ ፻ ተራሮች

፯ኛ ቀን

የአማራ ፋኖ በጎጃም ፫ኛ ክ/ጦር ዛሬ በማለዳ ከሠከላ እያስሮጠ ያስወጣውን የዘር አጥፊውን ጠላት ኃይል 6ኛ እዝ 75ኛ ክ/ጦር 4ኛ እና 5ኛ ሬጂመንት ቲሊሊ መዳረሻ ከበባ ውስጥ በማስገባት ድሽቃዎችን፣ ብሬንና ስናይፐሮችን፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ክላሾችንና ተሽከርካሪዎችን እንዲሁም የመገናኛ ሬዲዮኖችን ማርኳል።

በተጨማሪም የፖለቲካና ወታደራዊ አመራሮችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠር የጠላት ኃይል ተማርኳል።
እየተካሄደ ያለው ዘመቻ በየቀኑ አዳዲስ አስደናቂ ድሎችን እያስመዘገበ በፍጥነት አየገሰገሰ ሲሆን በጠላት ሰፈር ሽብርና ጭንቀት ተፈጥሮ እርስ በርስ እስከመመታታት አድርሷቸዋል።

በንፁኃን ደም የተጨማለቀው የብልጽግና ስብስብና ወምበር ጠባቂ ኃይሉ እጅ ከመስጠት የተሻለ አማራጭ የለውም።

ከጠላት የተማረኩ ቁሳቁሶች በቁጥር፦
➣ ሁለት ድሽቃ
➣ ሠባት ብሬን
➣ አራት ስናይፐር
➣ 800 የድሽቃ ጥይት
➣ 7400 የብሬን
➣ 15 ሺህ የክላሽ ጥይት
➣ አምስት መኪና
➣ 115 ምርኮኛ
በወገን በኩል ዘንገና ብርጌድ፣ ግዮን ብርጌድ፣ ቀኝ አዝማች ስሜነህ ደስታ ብርጌድ፣ ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ
ብርጌድ እና ከ፭ ተኛ ክ/ጦር አረንዛው ዳሞት ብርጌድ ቢተው ሻለቃ ተሳትፈውበታል ።

#ዘመቻ ፻ ተራሮች
አስረስ ማረ ዳምጤ

08/10/2024

ጥብቅ ማሳሰቢያ
#እስቲበል አለሙ (የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታየ ዮፍታሄ ንጉሴ ክፍለጦር አዛዥ)

በደብረማርቆስ ከተማ በብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ተከቦ የሚውለው ካቢኔ የግል ትጥቅ ሊነጠቅ መሆኑን አረጋግጠናል።
1:መሳሪያ ያለው የማርቆስ ነዋሪ መሳሪያውን በመያዝ ፋኖን መቀላቀል ይኖርበታል።
2: መሳሪያውን ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ አማራ በየትኛውም። አጋጣሚ በተገኘበት እርምጃ የምንወስድ መሆኑን አስቀድመን እናሳውቃለን።
3: ጠላት መሳሪያውን ብቻ ወስዶ የሚቀር አይደለም መሳሪያህን ከነጠቀ በኋላ ልክ የብልፅግና አመራሮችን ተጠቅሞ ሲበቃው ወደ ማጎሪያ እንደጨመረ ሁሉ አንተንም እንደፈለገ እንደሚያደርግህ ልታውቅ ይገባል።
ለጠላት መሳሪያን አሳልፎ የሚሰጥ ጠላት ብቻ ነው።

Address

London

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara fano -አማራ ፋኖ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share