30/08/2026
በሲድኒ ማራቶን አዲሱ ጎበና🇪🇹 ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸነፈ::
ለ24ኛ ጊዜ በተደረገው የሲድኒ ማራቶን ውድድር አዲሱ የገባበት 2 ሰአት 04 ደቂቃ 42 የቦታው ክብረ ወሰን ሆኖም ተመዝግቧል።
ባለፈው ዓመት ሀይለማርያም ኪሮስ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፎ የነበር ቢሆንም በዚህ ዓመት አዲሱ ጎበና ከአንድ ድቂቃ በላይ በማሻሻል አሸንፏል።
በውድድሩ ጭምዴሳ ደበሌ 2ኛ ደርጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ 2 ስዓተ 04 ደቂቃ 46 ሰከንድ የገባበት ስዓት ሆኗል።
ጀማል መኮንን 5ኛ ሲወጣ የባለፈው ዓመት አሸናፊ ሀይለማርያም ኪሮስ ደግሞ 6ኛ ደርጃን ይዞ ውድድሩን ፈጽሟል።
በሴቶች በተደረገው ውድድር ኬንያዊቷ ፒርስ ጅፕችርችር🇰🇪 አሸናፊ ሆናለች። 2:18: የገባችበት ስዓት ሆኗል።
ኢትዮጵያዊያኑ ሹሬ ደምሴ፣ ሄቨን ሀይሉ እና መሰረት አበባየሁ ከ3ኛ እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።