Elite EOTC Nation

Elite EOTC Nation Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Elite EOTC Nation, News & Media Website, United Kingdom, London.

በመላው ዓለም ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን ወደ አንድ ቋት የማሰባሰብ ዘመቻ መጀመሩን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው። የማሰባሰቡ ዋና ዓላማ ቤተክርስቲያንን ከባህል፣ ከቀኖና እና ከዶግማ ጥሰት መከላከል፣ ቤተክርስቲያን ከሚደርስባት ዘርፈ ብዙ ትንኮሳ ራሷን ችላ እንድትቆም ማድረግ ነው። ምዕመናን ይህን ቻናል በመላው አለም ተደራሽ እንዲሆን በባለቤትነት መንፈስ እንድትሰሩ እናሳስባለን።

እጅግ አሳዛኝ ዜና በሸገር ሀገረ ስብከት ዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት  ቄስ ዮሐንስ ግርማ ቅዳሜ ለእሁድ  ለቅዳሴ አገጋግሎት በሎሊት ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ ...
23/06/2025

እጅግ አሳዛኝ ዜና

በሸገር ሀገረ ስብከት ዓለም ገና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆኑት ቄስ ዮሐንስ ግርማ

ቅዳሜ ለእሁድ ለቅዳሴ አገጋግሎት በሎሊት ወደ ቤተክርስቲያን እየሄዱ ባሉበት ወቅት ቤተክርስቲያኑ በር መግብያ በር ላይ በጩቤ ማንነታቸው ባልታወቀ ተወግተው መገደላቸውን የመረጃ ምንጮች አድርሰውናል !

ከቅርብ ግዜ ወዲህ የቅድስት ቤተክርስቲያን ዲያቆናት ካህናትና መነኮሳት ባልታወቁ ሰዎች በሚል እየተገደሉ ነው ::

የአባታችንን ነፍስ ፈጣሪ ከቅዱሳኑ ጋር ይደምርልን ፣ ለቤተሰቡም መጽናናትን ያድልልን ፣

በአስቸኳይ ይፈቱ፣ #አባታችን ሊቀ ብርሃናት የኔታ ይባቤ በላይ ለምን ታሠሩ? የቅኔ፣የ፹፩መጻሕፍት፣የአቡሻኽር፣የጥበባት መምህሩ፣ የናዳ ገዳም አበ ምኔት (አስተዳዳሪ)ለበርካታ ዓመታት ደከመኝ ...
21/06/2025

በአስቸኳይ ይፈቱ፣

#አባታችን ሊቀ ብርሃናት የኔታ ይባቤ በላይ ለምን ታሠሩ?
የቅኔ፣የ፹፩መጻሕፍት፣የአቡሻኽር፣የጥበባት መምህሩ፣ የናዳ ገዳም አበ ምኔት (አስተዳዳሪ)

ለበርካታ ዓመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ወንበር ዘርግተው ደቀ መዛሙርት አብዝተው ሲያስተምሩ የኖሩ እያስተማሩ ያሉ ናቸው።

እንደ አባትነታቸው ትጉኅ አበ ምኔት ናቸው መቆፈሪያ ይዘው ዕርፍ አርቀው ሞፈር ጠርቀው አርሰው ቀፍረው ትሩፋት ሠርተው ገዳም ገድመው የኖሩ የሚኖሩ አባት ናቸው።

እንደ ሰባኪ ዙረው የሚያስተምሩ እያስተማሩ ያሉ ሐዋርያ ናቸው።

የኔታ ይባቤ አይደለም መታሠር በወርቅ ወንበር ተቀምጠው ያስተምሩን የሚባሉ ረቂቅ ሊቅ፣ምጡቅ ባለ አእምሮ ናቸው።

ለየኔታ ይባቤ በላይ የማይሆን ፍትህ ምን አይነት ነው?

መምህራችንን አባታችንን ፍቱልን።
እኔም የየኔታ ይባቤ በላይ ልጅ ነኝ።
እሥራታቸው እሥራቴ፣መከራቸው መከራየ ነው።

አድባር የሆኑትን ትልቅ ሰው ማሠር ትልቅ ስህተት ነው።

ለሀገር ባበረከቱት፣የወንጌል፣የሰላም፣የልማት፣የቅኔ፣የሀገር በቀል ዕውቀት፣የአቡሻህር፣የአርአያነት አስተዋጽኦ ሽልማታቸው እሥራት እና እንግልት ሊሆን አይገባም።

ሊቁ አባታችንን ሲሸለሙ እንጂ ሲታሠሩ መስማት ትልቅ ዕዳ ነው።

ከገዳማቸው ሂዶ በየኔታ ይባቤ ተመክሮ ያልተጽናና፣ተገሥፆ ያልተረጋጋ፣ከመስቀላቸው ተባርኮ ከጸበሉ ተጠምቆ ዕረፍተ ህሊና ያላገኘ ሰው የለም ማለት ይቻላል።

የኔታ ያለ ውግንና የሁሉም መምህር፣የሁሉም አባት፣የሁሉም ዘር ቀለም ሳይለዩ አስተማሪ፣የሁሉም ፊት ደረት ሳይለዩ ገሥፆ መካሪ ናቸው።

እንዲህ ያሉትን የኔታችንን አባታችንን በክብር ወደ ገዳማቸውና ወደ ማስተማሪያ ወንበራቸው መልሱልን።

"ቢያድጥ ቢያድጥ ወደላይ ያድጣል?"

©Elite EOTC Nation

ሰበር መረጃ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በፓስተር ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተች።Elite EOTC Nation
17/06/2025

ሰበር መረጃ፣

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በፓስተር ትዝታው ሳሙኤል ላይ ክስ መሰረተች።

Elite EOTC Nation

በአለም አቀፍ ደረጃ  የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን በአንድ የመሰባሰቢያና Platform ውስጥ እንዲሰባሰቡ የሚያደርግ ፕሮጀክት የተጀመረ መሆኑን ለመግለፅ እን...
03/06/2025

በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞችን በአንድ የመሰባሰቢያና Platform ውስጥ እንዲሰባሰቡ የሚያደርግ ፕሮጀክት የተጀመረ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

አፋጣኝ ምላሽ ስለሚያስፈለግ ኦርቶዶክሳውያን ለጓደኞቻችሁ አድርሱ።

https://t.me/eliteeotcnation
https://t.me/eliteeotcnation
https://t.me/eliteeotcnation

የመሰባሰቢያችን ዋና ዓላማ:-

✅በዋናነት የቤተክርስቲያናችንን ትምህርት፣ ባህል፣ ትውፊት እና ዶግማ በመላው ዓለም ማስፋፋት ሲሆን በሀገር ውስጥ የሚካሄዱ ህገወጥ ፣ ቤተክርስቲያን የማይወክሉ እንቅስቃሴዎችን ማስተካከል እና መግታት፣

✅ በቤተክርስቲያናችን ላይ በየጊዜው የሚነሱ የውሸት ማዕበሎችን ለምዕመናኑ ግንዛቤ እንዲያገኝ በማድረግ መግታት እና ትክክለኛ አስተምሮውን ማስተላለፍ፣

✅ ትክክለኛ አባቶችን ከቆብ ከለበሱ ተኩላ እና ፖለቲከኛ አባቶች በመለየት ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃን በማቀበል የራሱን አቋም እንዲወስድ ማድረግ፣ እንዲሁም ቤተክርስቲያን እንዳይጎዱ መከላከል።

✅ የፈረሱ፣ የታቃጠሉ እና የሚታደሱ ቤተክርስቲያንን በእውቀት፣ በገንዘብ እና በሀሳብ መርዳት።

✅ ምዕመኑ ዘመኑን ዋጅቶ ቤተክርስቲያኑን ከነጣቂ ተኩላዎች እንዲጠብቅ፣

✅ጳጳስ መስለው በቤተክርስቲያን ውስጥ የገቡ በርካታ ፖለቲከኞች እንዳሉ በማስገንዘብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማድረግ፣ አስፈላጊ ከሆነም በስም እና በመረጃ በማጋለጥ ቤተክርስቲያንን ማዳን፣

✅ንዋይ የሚወዱ የቤተክርስቲያን ሰዎችን ወደ ትክክለኛው ስርዓት እንዲመጡ ካልሆነ ግን ለአማኙ ማህበረሰብ አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ማድረግ፣

✅በቤተክርስቲያን ላይ የሚደረጉ ስርቆቶችን በረቀቀ መንገድ በመከታተል ማጋለጥ እና የእርምት እርምጃ መውሰድ፣

✅በቤተክርስቲያናችን ላይ በተጠና መልኩ የተሳሳተ አስተምሮ የሚሰጡ ሀሳዊ መምህራንን እንዲሁም ኢአማንያን በመከታተል አስፈላጊውን የመልስ ትምህርት መስጠት።

✅ በቤተክርስቲያን ላይ ፀያፍ የጥላቻ ንግግር፣ የሚያደርጉ ግለሰቦችን መገሰፅ የማይመለሱ ከሆነ ለህግ ማቅረብ፣ ህግ የማይቀጣቸው ከሆነ አስፈላጊ የሚባለውን እርምጃ መውሰድ።

✅ሌሎች የእምነት ተቋማት የኢኦተቤክቷን አክብረው እና ተከባብረው እንዲኖሩ የሚያስተሳስር አስተምሮን መስጠት፣

✅የመንግስት ባለስልጣናት በቤተክርስቲያናችን ላይ የሚያደርጉት የረቀቀ ሴራ በማጋለጥ ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ ማድረግ፣

✅ መንግስት የዘረጋው የትምህርት ስርዓት ፀረ ኦርቶዶክሳዊ ወይም ኦርቶዶክሳዊ አስተሳሰብን የማይወክል በመሆኑ በተደራጀ መልኩ ምክረሃሳቦችን የያዘ ፕሮፖዛል በማዘጋጀት በማቅረብ የሚመለከተው አካል የእርምት እርምጃ እንዲወስድ ማድረግ፣

✅ ቤተክርስቲያን በምትገኝበት ቦታ ሁሉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ፣ የአብነት ተምህርት ቤቶች እንዲገነቡ፣ማድረግ፣

ሲሆን ሌሎች በዚህ ላይ ያልተጠቀሱ አጀንዳዎች የሚኖሩ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

ስለሆነም በመላው ዓለም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ከላይ የተጠቀሱት ፕሮጀክቶቻችን ከግብ የምናደርሳቸው በጋራ ሆነን በመሆኑ በታሪክ አጋጣሚ አሁን ላይ ቤተክርስቲያን እየደረሰባት ያለውን ግፋ እና እንግልት እንዲሁም መርጦ ግድያ እያንዳንዳችን ሊያሳስበን የሚገባ በመሆኑ የበኩላችንን ስራ እንድንሰራ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን።

በእቅዳችን መሰረት የመጀመሪያው ስራችን ቻናሉን 10,0000 ኦርቶዶክሳውያን አንዲቀላቀሉ ማድረግ ነው።

ሁለተኛው እቅድ በመላው ዓለም ያሉ እና እኛ በምንደርስባቸው አካባቢዎች ተወካዮችን መሰየም፣

እነዚህን ሁለት ስራዎች እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማጠናቀቅ ይጠበቅብናል።

እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

በዚህ ሊንክ መመዝገብ ይችላሉ👇👇👇
https://t.me/eliteeotcnation
https://t.me/eliteeotcnation
https://t.me/eliteeotcnation
https://t.me/eliteeotcnation

02/06/2025

እንኳን ወደ የላቁ እና የተመራመሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ማህበረሰብ መገኛ ፔጅ በደህና መጣችሁ፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ብንኖር ኦርቶዶክሳውያንን በአንድ ቋት ውስጥ አስገብተን ወንጌል እንዲማሩ እና ለቤተክርስቲያናችን ዘብ እንዲቆሙ ይደረጋል፡፡ያቆየን!!

Address

United Kingdom
London
WC1A 1AA

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Elite EOTC Nation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share