Oromia defend

Oromia defend Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Oromia defend, Digital creator, Accra.

01/11/2024
26/09/2024

ለ2017 ዓመት የመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል የሕልም ጉልበት የታየበት በዓል ነው፡፡

ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉን ለማውጣት ያለመችው ምንም አመቺ ነገር ባልነበረበት ጊዜ ነው፡፡ ዙሪያዋ ጨለማ ነበር፡፡ መንገዶች ሁሉ ዝግ ነበሩ፡፡ ነገሮች ሁሉ አስቸጋሪ ነበሩ፡፡ ማንም በማያስበው ጊዜ፤ አይቻልም አይሞከርም በሚባልበት ወቅት፤ አንድ ቀን፤ ፈጣሪዋ ሲፈቅድ፤ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት ሕልም ነበራት፡፡

ሕልሟ እንዲሳካ ሠራች፤ ታገለች፡፡ ጨለማውን እየገፈፈች፤ አስቸጋሪውን ጎዳና እየጠረገች፤ ከውስብስብ ችግሮች ጋር እየተጋፈጠች ወደ ፊት ተጓዘች፡፡ በመጨረሻም ኢየሩሳሌም ተሻግራ፣ መስቀሉን ከተቀበረበት ሥፍራ ለማውጣት በቃች፡፡ ሕልሟ እውን ሆነ፡፡ ታሪክን ቀየረች፡፡ ልዕልናን ዐወጀች፡፡ ደመራ ለሚታገል፤ ተስፋ ለማይቆርጥና እስከ መጨረሻው ለሚጸና ሰው ሕልሙ አንድ ቀን እውን እንደሚሆን የሚያሳይ ትእምርት ነው፡፡

እዮሃ፤ ማለት “ይሄዋ” ማለት ነው ይባላል፡፡

ይሄው ተገኘ፤ ይሄው ተሳካ፤ ይሄው እውን ሆነ ማለት ነው፡፡ ከበረቱ፤ ከታገሉና ከጸኑ የማይሳካ ምን ነገር አለ? ሕልሙን ለሚያውቅ፤ ሕልሙ እንዲሳካ በነገሮች ተስፋ ሳይቆርጥ ለሚለፋ፤ እንደ ንግሥት እሌኒ ሕልሙ እውን ሆኖ አንድ ቀን ማየቱ አይቀርም፡፡ የሕልሙን ደመራ መደመሩ አይቀርም፡፡ “እዮሃ”፤ “ይሄዋ!” ማለቱ አይቀርም፡፡

መስቀል ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በሁለት መንገድ የሚያሳይ በዓል ነው፡፡ ደመራው ከእንጨት ወደ ችቦ፤ ከችቦ ወደ ደመራ የሚያድግበት መንገድ መደመር ምን ያህል ኃይልና ጉልበት እንዳለው ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መስቀል በተለያየ መንገድ፣ በተለያየ ባህልና አከባበር በብዙ ብሔረሰቦች ይከበራል፡፡ ይሄ ደግሞ በኅብረ ብሔራዊነታችን ውስጥ ያለውን ነባር ትሥሥር፣ የወል ትርክትና አንድነት የሚሳይ ነው፡፡

እንዲህ ዓይነት በዓላት ሃይማኖታውያን ብቻ አይደሉም፡፡ የኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን መገለጫዎች ጭምር ናቸው፡፡ በመደመር ውስጥ ያለውን ጥንካሬና ጉልበት የሚሳዩ ትውልድ ለእኛ ትምህርት ያቆማቸው ምልክቶች ናቸው፡፡

ደመራውን በደመርን ጊዜ፤ ደመራውን በለኮስን ጊዜ፤ እንደየባህላችን የመስቀልን በዓል ለማክበር በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ በተሰባሰብን ጊዜ ኢትዮጵያን እናስባት፡፡

የሁላችንም ዕሴቶች፣ ባህሎች፣ ወጎች፣ ዐቅሞች፣ ጸጋዎች፣ ሀብቶች፣ ቋንቋዎች፣ ታሪኮች፣ ወዘተ. ተደምረው ኢትዮጵያን ታላቅ፣ የበለጸገችና የተከበረች ሊያደርጓት እንደሚችሉ እናስብ፡፡ ኢትዮጵያ የእነዚህ ሁሉ ድምር መሆኗን እናስብ፡፡ ከድምሩም በላይ መሆኗንም እናስብ፡፡ ደመራውን እያሳየን ለልጆቻችን ከሃይማኖታዊና ባህላዊ ትርጉሙ በተጨማሪ “እኛ ኢትዮጵያውያን ከተደመርን እንደ ደመራው ብርቱ እንሆናለን፤ እንደደመራው ከፍ ብለን እናበራለን” በሏቸው፡፡

መልካም የመስቀል በዓል ይሁን፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2017 ዓ.ም

13/09/2024
12/09/2024

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔሮች፣ የብዙ ቋንቋዎች፣ የብዙ ባህሎች፣የብዙ እምነቶች፣ የብዙ ሥልጣኔዎች፣ የብዙ ጀግኖች፣ ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ኅብር ናት።

ሁሉም የኛ በእኛ ለእኛ የተሰጡ ናቸው። ሁሉን እናከብራለን፤ በሁሉም እንኮራለን።

ኅብረ ብሔራዊነታችን መልካችን፣ አንድነታችን ደግሞ ህልውናችን ነው። እነዚህ ኅብራዊ ጸጋዎች በአንዲት ሀገር በኢትዮጵያ የሚገኙ ናቸው። ዓላማችን አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ መገንባት ነው። ግባችን የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው። ይህ ነው አንድነታችን።

የተበታተንን ኅብሮች አይደለንም፤ የተጨፈለቅን አንድ ዓይነቶችም አይደለንም። እኛ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ያለን ኢትዮጵያውያን ነን።

Itoophiyaan biyya saboota hedduu, afaanota hedduu, aadaawwan hedduu, amantaawwan hedduu, qaroominoota hedduu, gootota hedduuti. Itoophiyaan daneettiidha.

Hunduu nuyiin unuuf kan kennaman keenyadha. Hundayyuu ni kabajna; hundaanuu ni boonna.

Sabdaneessummaan keenya bifa keenya, tokkummaan keenyammoo waa'ee jiraachuu keenyaati. Kennaawwan danummaa kunneen biyya tookko, Itoophiyaatti kan argamanidha. Kaayyoon keenya hawaasa siyaasaafi dinagdee tokko ijaaruudha. Galmi keenya badhaadhina Itoophiyaati. Tokkummaan keenya kanadha.

Daneessota faffacaane miti; Akaakuu walitti baqne tokkos miti. Nuti Itoophiyaanota tokkummaa sabdaneessa qabnudha.

10/09/2024

ትናንት አልቋል። ዛሬም እየተገባደደ ነው። ነገ ግን ገና አልተነካም። ነገን ለመጠቀም ታድያ ዛሬ መሥራት አለብን።

ሕዳሴ ግድብ፤ የገበታ ለሀገርና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች፤ መንገዶችና ግድቦች፤ የተቋም ግንባታ ሥራዎች፤ አረንጓዴ ዐሻራና ኢትዮጵያ ታምርት፤ የኮሪደር ልማትና የሌማት ትሩፋት ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ እና የትምህርት ቤት ምገባ፤ ሀገራዊ ምክክርና የሽግግር ፍትሕ፤ ሌሎችም.. ነገን የተሻለ ለማድረግ የምንሠራቸው ናቸው።

የነገው ትውልድ እጅግ የተሻለች ኢትዮጵያን እንደሚረከብ ርግጠኞች ነን። ለነገ ዛሬ እየሠራን ነውና።

Kaleessi dhumeera. Har'is xumuramaa jira. Bor garuu ammayyuu hin tuqamne. Boritti fayyadamuuf garuu har'a hojjechuu qabna.

Hidhi Haaromsaa, piroojektoonni Maaddiin Biyyaafiifi Maaddiin Dhalootaaf, daandiiwwaniifi hidhawwan, hojiileen ijaarsa dhaabbilee, Ashaaraa Magariisaafi Itoophiyaan Haa Hoomishtu, Misoomni Kooriidariifi Maaddii Guutuun, Itoophiyaa Dijitaalofteefi sooruun manneen barnootaa, Mariin Biyyaalessaafi Haqni Cehumsaa, kanbiroonis... bor kan wayyu akka ta'uuf hojiilee hojjennudha.

Dhaloonni borii Itoophiyaa baay'ee wayyitu akka dhaalu kan mirkanaa'edha. Boriif har'a waan hojjetaa jirruuf.

10/09/2024

Address

Accra

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oromia defend posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share