26/09/2024
ዛሬ ከዲላ ከተማ ወጣ ብዬ ነበርና በሀድኩበት ከተማ በጣም የሚገርም ነገር አየው፡፡ ይህች ከተማ የአርንጓደ ወርቅ ፤ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና መገኛ ይርጋጨፌ ከተማ ናት ፡፡ ይህችን ከቀርብ ጊዜ ወዲህ እየታየባት ያለው እንቅስቃሴና ለውጥ እጅግ ልብን ይሰርቃል፡፡ የፎቶ ጋጋታ ብዙም አየታይባትም ፤ ሰራን ብሎ ማውራት ብዙም አይቀናቸውም ፤ ነገር ግን በስራ የተወጠሩ ናቸው ፡፡ የገዛ ሙሉ ቀን ቆይታ በዚህች ከተማ ስለነበር ያለስራ ከተማ ውስጥ የሚዞር አመራር አላገኘውትም፡፡ ሁሉም ለተ ተቀን ደፋ ቀና ብሎ እራሱን ፤ ከተማውን አልፎም የዞናችን የአይን መስህብ ለመሆን ይታትራል፡፡
ይህ ፅሁፍ ፤ምንም ዓይነት አጀንዳ የለውም ባየውት በጣም ደስ ስላለኝ ነው፡፡ እኔ በሚኖርበት ዲላ ከተማ እየመጣ ያለውን ለውጥ ብዙም አርክቶኝ ስላለንበረ ብዙ ብዬ ነበር ፤ምክንያቱም የዞኑና የክልሉ ክላስተር አንዱ መቀመጫ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኘው ፤የምስራቅ አፍራካ ትልቁ ገበያ ማለትም ማርካቶ ቀጥሎ ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሰ ያለባት ፡፡እንዲሁም ከተማይቱ ካለው የንግድ እንቅስቃሴ የሚሰበሰበው የገቢ አቅም ከ2 ቢልዮን በላይ የሆነችና ክልሉ በቀጣይ የፖሌቲካ እንቅስቃሴ የዘወራል ብሎ የሚታመንበት ባለ ብዙ ሀብት ባለበት ከተማ ናት ፡፡ የክልሉ ና የፌዴራል ተቋማት መቀመጫ ፤ ለ5 ሚሊዮን ለሚደረስ ህዝብ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የክልሉ የሜድካል ቱርዝም ሃብ ልትሆን ያለቸው እና ባለ ብዙ ተስፋ ባለቤት ናት ፡፡ ታድያ በዚህች ከተማ ስኖር እንደ አንድ ጤነኛ ሰው የሚያየው ልመጥናት የሚችል ስራና ለውጥ ነው ፡፡
ወደ ዛሬ ውሎ ልመለስ ይህች የይርጋጨፌ ከተማ ለውጡን በተገቢ መልኩ የሚመሩ ቁረጠኛ መሪዎች አገኘታለች ፡፡ ይህንን ልል ያሰቻለኝ ነገር ከተማው የባላሃብቶች ጥረት ይበል የሚያሰኝና እዚም እዛም ብቅ ብሎ የሚታዩ ባለብዙ ቀለም ህንፃዎች ዓይኖችን ሳቡኝ፡ይህ ብዬ ትንሽ ራመድ ማለት ሰጀምር የማስተር ፕላን ማስከበር ሳይሆን የከተማይቱን ገጽታ ወደ ተሸለ ደረጃ ከፍ ልያደርግ የሚችል የኮርድር ልማት ቦታዎች ተመለከትኩኝ፡፡ ለእግርኛ ምቹ የሆኑ መንገዶች ያበት እንድሁም የአርንጓደ ቦታዎች አጣምሮ የያዘ ሲሆን አሁን በጅምር ያለ ሆኖ ግን ተስፋ ሰጪ የሆነ ነገር አለው ፡፡
ከዚህ ከተማ ብዙ ልምዶች ተቀምሮ በዞኑ ባሉ የወረዳ ከተሞች ልሰፋ የሚችል በመሆኑ የዞኑ ከተማ ልማት መምሪያና ለሎች የመንግስት አካላት በዚህ ልክ ከአካባቢ የተገኘ ለብዙዎች አስተማሪ ልምድ በመውስድ የተሸሉ የወረዳ ከተሞች እንድፈጠሩ ብሰራበት ባይ ነኝ ፡፡
አደራ ማላት የሚፈለገው የሆነ ጊዜ የመጣውን የፖሌቲካ እሽቅድምድም ለማመለጥ እንደሚሰሩና ዘላቂነታቸው ጥያቄዎች ውስጥ እንድሚያሰገቡ ስራዎች አይሁን ፡፡ የቡና መጠሪያቹ/ችን ገኖ እንደሚጠራ ሁሉ የከተማይቱ ስምም በኢትዮጵያም ሆነ በአለም በተገብ እንድታወቅ እንድተሰሩ አደራ ልባቹ፡፡
በብዙ እጥረቶች ውስጥ ፤የሚሰሩ ስራዎችን ከማድነቅና ውስን የሆነውን የህዝብ አለግባብ እየወጣ የሚሰሩ የህዝብ ቆሽት የሚያቃጥሉ ስራዎች መቃወም አልተውም ፡፡