Bench Sheko Tv

Bench Sheko Tv ይህ የቤንች-ሸኮ ቴሌቪዥን ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው።
መልካም ዕሴትን እንገነባለን!
(1)

አንድነታችን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል አስተማማኝ መሠረት መሆኑን አሳይተናል - ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳሚዛን- አማን ፣መስከረም 24፣ 2019 (ቤሸቴ)፦ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር...
04/10/2026

አንድነታችን ኢትዮጵያን ለማስቀጠል አስተማማኝ መሠረት መሆኑን አሳይተናል - ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ

ሚዛን- አማን ፣መስከረም 24፣ 2019 (ቤሸቴ)፦ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የሆራ ሀርሰዴ ኢሬቻ በዓል በድምቀት እንዲከበር አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ ሀርሰዴ “ኢሬቻ ለብሔራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሀሳብ የተከበረው የኢሬቻ በዓል፤ የኦሮሞ ሕዝብ ባህል፣ ወግ፣ ሥርዓትና እሴቶችን በማንጸባረቅ በስኬት መከበሩን ተናግረዋል።

በዓሉ ለኦሮሞ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለመላው ሀገሪቱ ሕዝብ የሰላም፣ የበረከትና የስኬት መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢሬቻ የአንድነት፣ የሰላምና የፍቅር በዓል መሆኑን ያወሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የዘንድሮው በዓልም የኦሮሞን ሕዝብ አንድነት ከማጠናከር ባለፈ በሕዝቦች መካከል ወንድማማችነትን በማጠናከር ለሀገራዊ መግባባት ግንባታ አስተዋጽኦ ማድረጉን አመልክተዋል፡፡

ኦሮሞነት አንድነት ነው፤ የጋራ ክብራችንንና ፍቅራችንን የምንጠብቅበት እሴት በመሆኑ በመከባበርና በፍቅር በጋራ መኖር ይገባል ነው ያሉት፡፡

የኦሮሞ ባህልና ሥርዓት ሰፊ እና ዓለም አቀፋዊ እሴት ያለው መሆኑን ገልጸው፣ እነዚህ እሴቶች በእውቀትና በጥበብ ተመርተው በትክክል ተረድተው በተግባር መገለጥ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያን ለአፍሪካ ብርሃንና ለዓለም አስደናቂ ሀገር ማድረግ የሚገባበት ጊዜ አሁን ነው ያሉ ሲሆን፤ ለዚህም የሚጠየቀውን ሁሉ መስዋዕትነት በመክፈል የታሪክ ኃላፊነታችንን መወጣት አለብን ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግሥትም ይህንን አንድነት በጠንካራና በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለማጠናከር በትጋት እንደሚሠራም ነው የጠቆሙት።

በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ አባገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የመጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ወጣቶች እና አርሶ አደሮች ታድመዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በዓሉ ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር፣ ወጣቶች፣ የጸጥታ አካላት፣ የሀገር ውስጥና የውጭ መገናኛ ብዙሃን በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ
‎
‎ #መልካም እሴትን እንገነባለን!!
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎📌Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎📌Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎📌https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
‎📌youtube https://www.you tub
‎See less
‎
‎

"የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ በስኬት ተጠናቅቋል" - የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላሚዛን- አማን ፣መስከረም 24፣ 2019 (ቤሸቴ)፦የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ ...
04/10/2026

"የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ ተከብሮ በስኬት ተጠናቅቋል" - የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ

ሚዛን- አማን ፣መስከረም 24፣ 2019 (ቤሸቴ)፦

የሆረ ሀርሰዴ የኢሬቻ በዓል ትውፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት ተከብሮ በስኬት መጠናቀቁን የቱለማ አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ አስታውቀዋል።

አባ ገዳው እንደገለጹት በበዓሉ ላይ የኦሮሞ ሕዝብ በአንድነት በመሆን ባህሉን በጠበቀ መልኩ ወደ ስፍራው በማቅናት ፈጣሪውን አመስግኗል።

በተጨማሪም በዚሁ ደማቅ በዓል ላይ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች መሳተፋቸውን አባ ገዳ ጌቱ ተሊላ ጠቁመዋል።



‎ #መልካም እሴትን እንገነባለን!!
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎📌Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎📌Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎📌https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
‎📌youtube https://www.you tub
‎See less
‎
‎

የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ22ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን  250 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።ሚዛን አማን፤ መስከረም24/2019ዓ.ም(ቤሸቴ)የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ...
04/10/2026

የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ22ኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 250 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ሚዛን አማን፤ መስከረም24/2019ዓ.ም(ቤሸቴ)

የአማን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከሚገኙ ኮሌጆች መካከል አንዱና ተጠቃሽ ነው።

ኮሌጁ መስከረም 25/2019 ሀገር መንግስት በሚመሰረተው ዋዜማ 22ኛ ዙር ሰልጣኞችን ማስመረቁ እንዳስደሰታቸው የኮሌጁ ዋና ዲን መሪ ኢንስትራክተር መስፍን አለማየሁ በንግግራቸው ገልፀዋል።

በ2018 በጀት ዓመት ኮሌጁ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዘገቡን የጠቀሱት ዲኑ ተቋሙ የክህሎት መር እና የተቀናጀ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንና ቴክኖሎጂ ማሸጋገር ላይ ትኩረት አደረጉ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ኮሌጁ በ1994 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን እስካሁን 21ሺህ 559 ተማሪዎችን ማስመረቁን ኢንስትራክተር መስፍን ተናገረዋል።

ኮሌጁ በ25 ዓመታት ጉዞ ሀገራዊ ተልዕኮን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለፁት ዲኑ የዛሬ ተመራቂዎች በ10 የትምህርት ክፍሎች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ 250 ተማሪዎችን በደረጃ 4 ማስመረቁን አብራርተዋል።

ኮሌጁ በተለያዩ የትምህርት ዘርፍ ያስለጠናቸውን 22ኛው ዙር ሰልጣኞችን ተጋባዥ የክብር እንግዶች፣ የኮሌጁ ዲንና የማናጀመንት አካላት እንዲሁም የተመራቂዎች ቤተሰቦች በተገኙበት እያስመረቀ ይገኛል።

በምረቃው የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጅነር ሰለሞን ሌዊን ጨምሮ የዞን፣የክልል እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት መሪዎች የተመራቂ ቤተሰቦች እየተሳተፉ ነው።

አብዲሳ ዮናሰ

#መልካም እሴትን እንገነባለን #
በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
📌‎Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
📌‎Telegram https://t.me/benchshekotelevision 📌https://x.com/Benchshekotv /former twiter /x/
📌youtube https://www.you tub

አዲስ የሚመሰረተዉ መንግስት ህዝቡ የሚያነሣውን የልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመፍታት  መስራት ይገባዋል- የጊዴ ቤንች ወረዳ ነዋሪዎች።ሚዛን አማን ፦ መስከረም 24/2019 ዓ.ም ፦(ቤ.ሸ.ቴ...
04/10/2026

አዲስ የሚመሰረተዉ መንግስት ህዝቡ የሚያነሣውን የልማት ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመፍታት መስራት ይገባዋል- የጊዴ ቤንች ወረዳ ነዋሪዎች።

ሚዛን አማን ፦ መስከረም 24/2019 ዓ.ም ፦(ቤ.ሸ.ቴ)

በ2018 ግንቦት ወር መጨረሻ ላይ በተካሄደው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ድምፅ በማምጣት ማሸነፉ ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም በተካሄደው ስድስተኛ ምርጫ ብልፅግና አሸንፎ መንግስት ከተመረተ በኋላ ሀገሪቷን በመራበት ባለፉት አመስት አመታት በርካታ ልማቶችን ሲሠራ እንደነበር ነው የጊዲ ቤንች ነዋሪዎች የተናገሩት ።

ለአብነት ያህል በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ ወረዳችን ድረስ ዘልቆ በመግባት የዲዙ ከተማ ገፅታ እየቀየረ መቷል ብለዋል።

በትምህርት ፣ በጤና ፣በግብርና እንዲሁም በመሰረተ ልማት በኩል የተከናወኑ ስራዎች ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን ተናግረዋል ።

የጊዲ ቤንች ወረዳ የመዋቅር ጥያቄው ከተመለሰ በኋላ ወደ ልማት መገባቱንም አመልክተዋል።

እንደ ሀገር በርካታ የልማት ስራዎች ቢሰሩም የዋጋ ግሽበቱና የኑሮ ውድነቱ በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለውን ህብረተሰብ እየፈተነው መምጣቱንም ተናግረዋል።

በ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ ህዝቡ ለብልፅግና ፓርቲ ድምፁን መስጠቱን አስታውሰው ይህን ተከትሎ
መስከረም 25/2019 ዓ.ም የሚመሠረተው አዲሱ መንግስትም ለህዝቡ የልማት ተጠቃሚነት አበክሮ መስራት እንደሚገባው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በግብርና ዘርፍ የተጀመሩ ጠንካራ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥበቶ መሠራት እንዳለበት አውስተዋል።

የአርሷደሩን ምርተትና ምርታማነትን የሚያሣድጉ ቴክኖሎጂዎችን ብዛት ማቅረብ እንዳለበት ተናግረዋል።

በየዘርፉ አዳዲስ ኢንሼቲቮችን በማምጣት የአርሷደሩ ተጠቃሚነት የሚያጎለብቱ ተግባራት ማከናወን እንደሚገባው አመልክተዋል።

የኑሩ ውድነቱን የሚያባብሱ ጉዳዮች ላይ ጠንከር ያለ ስራ መስራት እንዳለበት ነዋሪዎቹ አበክረው ገልፀዋል።

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በእንድ ጀንበር መመለስ አይቻልም ያሉት ነዋሪዎቹ ነገር ግን መንግስት ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መሠራት ይገባዋል ብለዋል።

በብዙአየሁ አሣሣኸኝ


በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
http://www.youtube.com/-Mizan-Aman
‎

‎ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት-ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ‎‎ሚዛን- አማን ፣መስከረም 23፣ 2019 (ቤሸቴ)፦ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ...
03/10/2026

‎ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት-ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ
‎
‎ሚዛን- አማን ፣መስከረም 23፣ 2019 (ቤሸቴ)፦ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት አሉ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ፡፡
‎
‎ፕሬዚዳንቱ ከአል አራቢያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላት ሀገር መሆኗን ጠቅሰው
‎በቀጥታ ከቀይ ባህር ጋር ባትዋሰንም የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችላት ህጋዊ መብት አላት ብለዋል፡፡
‎
‎በመሆኑም በአለም አቀፍ የውሃ ህጎች መሰረት ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ ሀገር ልትሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡ኤፍ ኤም ሲ

‎ #መልካም እሴትን እንገነባለን!!
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎📌Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎📌Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎📌https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
‎📌youtube https://www.you tub
‎See less
‎
‎

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደ መርሃ ግብር፤ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ...
03/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደ መርሃ ግብር፤ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት ዛሬ በይፋ አስረክቧል።
‎
‎ይህ የሰነድ ርክክብ፤ በምክክርና በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን የቆዩ ሀገራዊ ፈተናዎች መፍታት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤ በመደመር መንግሥት ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ የተበጀለትን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አንድ ትልቅ ምዕራፍ ያበስራል። ሂደቱ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ስምምነትን ለመፍጠር የሚያስችል አካታች መድረክ መሥርቷል።
‎
‎ባለፉት አራት ዓመታትም ይህ ሂደት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ችሏል። ተሳታፊዎች ባደረጓቸው ሰፊ ምክክሮች እና በተጠናቀቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አማካኝነት እይታዎቻቸውን ለማንጸባረቅ፣ ልዩ ልዩ አመለካከቶችን ለመስማት እና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን መስኮች ለመለየት ዕድል አግኝተዋል። የእነዚህ ውጤቶች በይፋ መቅረብ በምክክሩ የተሰበሰቡ እይታዎችንና የውሳኔ ሐሳቦችን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር የተቀየሰ ትልቅ እርምጃ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክል...
03/10/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት፡-

ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ
ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክልል መንግሥታት በይፋ ርክክብ የተደረገበትን መርሃ ግብር ዛሬ ተከታትያለሁ።
‎
‎ይህ የሰነድ ርክክብ ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚያስመዘግብ ሲሆን የኢትዮጵያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎች አካታች በሆነ ውይይት፣ በሰላማዊ ምክክር እና በራሳችን ሀገር በቀል የመፍትሔ አምጭ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

Today, I attended and oversaw the formal handover of the consolidated agenda items and recommendations emerging from Ethiopia’s National Dialogue to the House of Peoples’ Representatives, the Federal Government, and Regional Governments.

This handover marks an important milestone in the National Dialogue process and reaffirms the commitment to addressing Ethiopia’s longstanding challenges through inclusive dialogue, peaceful deliberation, and nationally owned solutions.

‎ #መልካም እሴትን እንገነባለን!!
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎📌Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎📌Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎📌https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
‎📌youtube https://www.you tub
‎See less
‎
‎

በምዕራብ ኦሞ ዞን በሁለት ወረዳዎች የእንስሳት በሽታ መከሰቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ።ሚዛን- አማን ፣መስከረም 23፣ 2019 (ቤሸቴ)፦በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ጤና ...
03/10/2026

በምዕራብ ኦሞ ዞን በሁለት ወረዳዎች የእንስሳት በሽታ መከሰቱን ተከትሎ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠየቀ።

ሚዛን- አማን ፣መስከረም 23፣ 2019 (ቤሸቴ)፦

በምዕራብ ኦሞ ዞን የዞኑ ጤና መምሪያ ማኔጅመንት በዞኑ በወቅታዊ የጤና ጉዳዮች ላይ ውይይትና ግምገማ ማድረጉ ተገለጸ።

የዞኑ የዋና አስተዳደር ተወኳይ እና የጤና መምሪያው ኃላፊ አቶ ሺማጂ ጉርጭማ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት በመኤኒት ሻሻ እና በሱሪ ወረዳዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች መከሰታቸውን ተከትሎ ህብረተሰቡ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸዉ አስታዉቋል።

የበሽታው ምንነት በምርመራ እስኪረጋገጥ ድረስ በተለይም ከታመሙ ወይም በድንገት ከሞቱ እንስሳት ጋር በቀጥታ ንክኪ ከማድረግና ተያያዥ ተግባራት ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ኃላፊው አሳስበዋል።

የበሽታው ምልክቶች ወደ አንትራክስ የሚያደላ መሆናቸውን ተከትሎ የዞኑና የክልሉ የድንገተኛ የጤና አደጋ ቅኝትና ምላሽ ቡድን በመኤኒት ሻሻ ወረዳ በጋቢ እና ኪሉ ቀበሌዎች በአካል ተገኝቶ ለሁለት ቀናት የመስክ አሰሳ ማካሄዱ ተገልጿል።

በአሰሳውም በአካባቢው በእንስሳት ሞት የተነሳ ሰዎች የእንስሳት ስጋን ለምግብነት መጠቀማቸው በሰው ጤና ላይ ጉዳት መፍጠሩን የመምሪያው ኃላፊ ገልጸዋል።

በመሆኑም ከዛሬ መስከረም 23/2019 ዓ.ም ጀምሮ የበሽታው ምንነት በምርመራ እስኪረጋገጥ ድረስ በተለይም ከታመሙ ወይም በድንገት ከሞቱ እንስሳት ጋር በቀጥታ ንክኪ እንዳይደረግ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በተጨማሪም #ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር በሚደረገው የቁም እንስሳት ዝውውር ላይ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲደረግ መልዕክት ተላልፏል

መረጃዉ የዞኑ ኮሚኒኬሽን ነዉ
‎ #መልካም እሴትን እንገነባለን!!
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎📌Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎📌Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎📌https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
‎📌youtube https://www.you tub
‎See less
‎
‎

Woynten sokam 12:00 - 12:55  Benc’ nonam bucacam kang woyn   soy dosndis no irsnsuwe
03/10/2026

Woynten sokam 12:00 - 12:55 Benc’ nonam bucacam kang woyn soy dosndis no irsnsuwe

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ ሚዛን- አማን ፣መስከረም 23፣ 2019 (ቤሸቴ)፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ...
03/10/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክልሉን አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ

ሚዛን- አማን ፣መስከረም 23፣ 2019 (ቤሸቴ)፦
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ7ኛ ዙር መስራች ጉባዔው ነርዕሰ መስተዳድር የትምጌታ አስራት (ዶ/ር) የቀረቡ የክልሉ አስፈጻሚ የካቢኔ አባላት ሹመት አፅድቋል።
በዚህም መሰረት፡-

1 .አቶ ተመስገን ካሳ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
2 .ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ የሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
3 .አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ የዉሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
4 . አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የጤና ቢሮ ኃላፊ
5 . አቶ ሙስጠፋ ኢሳ የክልሉ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
6 . አቶ ሰላሙ አማዶ የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ
7 . አቶ ሳሙኤል መንገሻ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ
8 . አቶ ተመስገን ጎዴቦ የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮ ቢሮ ኃላፊ
9 . አቶ አሰፋ ደቼ የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ ኃላፊ
10 .አቶ አብዶ አህመድ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
11 . አቶ አብዱል ባሲጥ አባኮ የክልሉ ፕላን እና ልማት ቢሮ ኃላፊ
12 ወ/ሮ ዘይቱና ኢብራሂም የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
13 . አቶደምስ ገብሬ የክልሉ ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
14 ደ/ር ቶፊቅ አጫሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
15. አቶ ገብሬ ጋጌ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
16. አቶ አክሊሉ መኔዶ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ
17 . ዶ/ር ተስፈዬ አጋፋሪ የክልሉ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና የዲያስፖራ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
18 . ወ/ሮ ቀመሪያ ረሻድ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
19 . አቶ ታመነ ገብሬ የክልሉ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል፡፡

የካቢኔ አባላቱ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ በመፈፀም ስራቸውን በይፋ መጀመራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
ኤፍ ኤም ሲ
‎
‎
‎ #መልካም እሴትን እንገነባለን!!
‎በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎📌Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎📌Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎📌Telegram https://t.me/benchshekotelevision
‎📌https://x.com/BENCHSHEKOTV /former twiter /x/
‎📌youtube https://www.you tub
‎See less
‎
‎

Address

Mizan-Aman, South West
Dwa

Opening Hours

Monday 6am - 6pm
6pm - 6am
Tuesday 6am - 6pm
Wednesday 6pm - 6am
Thursday 6am - 8:01pm
Friday 6am - 8pm
Saturday 6am - 8pm
Sunday 6am - 8pm

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Sheko Tv posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category