14/07/2026
ሸህ ያህያ ይማም በታጣቂዎች ተገደሉ‼
በአማራ ክልል የባቲ ወረዳ ባለውለታ፣ የሃይማኖት አባት እና ታዋቂ የሀገር ሽማግሌ የነበሩት ሸህ ያህያ ይማም በታጣቂዎች በግፍ መገደላቸው ተሰማ።
ሸህ ያህያ ይማም ማህበረሰቡን በፍቅር፣ በእርቅና በመቻቻል በማገልገል፣ የተጣሉትን በማስታረቅ እና ወጣቶችን በመልካም ስነ-ምግባር በመምራት የሚታወቁ ትልቅ የሰላም አባት ነበሩ።
ይህ በንጹህ የሀገር ባለውለታ ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሰብዓዊ ሕሊናም ሆነ በሕግ ፈጽሞ የማይቀበል ወንጀል በመሆኑ በፅኑ ተወግዟል።ለቤተሰቦቻቸው፣ መጽናናትን እንመኛለሁ።