
25/08/2025
እናመሰግንሀለን!
📍🙏🏻🇪🇹ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የላቀውን የአመራር ብቃትና ቁርጠኝነት ላሳዩት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን። እርሳቸው በጀመሩት ሀገራዊ ለውጥ ግድቡን ከገጠሙት ውስብስብ የግንባታ መጓተቶችና የሙስና አደጋዎች በመታደግ፣ በጠንካራ የኢትዮጵያዊነት ስሜትና ቆራጥ አመራር ከዳር እንዲደርስ ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍለዋል።
🫡🇪🇹በዲፕሎማሲው መስክም ከውጭ የሚመጡትን ጫናዎች በብቃት በመመከትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ጥቅም በማስጠበቅ፣ ይህ የዘመናት የኩራታችንና የልማታችን ማሳያ የሆነው ግድብ እውን እንዲሆን ላበረከቱት ታሪካዊ አስተዋጽኦ ትውልድ ሲያስታውሰው ይኖራል።