HORN news center

HORN news center Horn News Center is a bilingual digital platform delivering fast reliable updates from the Horn of Africa.

Publishing in both Amharic and English, it provides concise coverage of politics, society, and regional developments to audiences.

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች……..ነሐሴ 20/2018ኦባሳንጆ በትግራይ …….የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ልዑክ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በትናንትናው ዕለት በትግራይ ዋና ከተማ መቐለ ተገኝተው...
25/08/2026

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች……..ነሐሴ 20/2018

ኦባሳንጆ በትግራይ …….

የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ የሰላም ልዑክ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ በትናንትናው ዕለት በትግራይ ዋና ከተማ መቐለ ተገኝተው ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ፡፡ የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ዛሬ ባወጡት መግለጫ፣ የኦሊሴጎን ኦባሳንጆን ጉብኝት አረጋግጠው፣ ከክልሉ ፕረዝደንት ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ጋራ መምከራቸውን ገልፀዋል፡፡ ይሁንና ጉብኝቱ የታቀደና ቀድሞ በተያዘ መርሀግብር መሰረት የተከናወነ አልነበረም፣ ድንገተኛ ነው ብለዋል፡፡ በሰላም ልዑኩ ጉብኝት ደስተኞች እንዳልሆኑ የገለፁት ባለስልጣናቱ፣ ከዚህ ቀደም ሰኔ ወር በመቐለ ተገናኝተው በተነጋገሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ለውጥ እንዳልመጣ ገልፀዋል፡፡ ኦባሳንጆ ግን በጉዳዩ ዙሪያ ከፌደራሉ መንግስት ጋር ተነጋግረው በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ መቐለ እንደሚመለሱ ቃል ገብተዋል፡፡

በትግራይ የድሮን ጥቃት ቀጥሏል…..

በትግራይ ክልል በፌደራሉ መንግስት የሚፈፀመው የድሮን ጥቃት መቀጠሉን የክልሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ እንዳባጉና አካባቢ እና በደቡብ ትግራይ ራያ አካባቢ ሁለት የድሮን ጥቃቶች ተፈፅመዋል፡፡ በጥቃቶቹ የደረሰ ጉዳት አይነትና መጠን በትክክል ባይገልፅም፣ ጉዳት መድረሱን ግን ሚዲያዎቹ አመልክተዋል፡፡ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ ደግሞ በምስራቅ ትግራይ አፅቢ አካባቢ፣ ተመሳሳይ የድሮን ጥቃት እንደተፈፀመ ተገልፆዋል፡፡ በተከታታይ እየተፈፀሙ ስላሉት የድሮን ጥቃቶች እስካሁን ከፌደራሉ መንግስት በኩል የተሰጠ አስተያየት የለም፡፡

የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ውጤታቸውን ከዛሬ 1፡00 ጀምሮ ማየት ይችላሉ…

የ 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ይፋ መሆንን ተከትሎ ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡ የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎችም በተቋሙ ይፋ ሆነዋል፡፡ ውጤታቸውን ለማየትም የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን መጠቀም እንደሚችሉ ተገልፆዋል፡፡
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

በደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት ተገደሉ…

በደቡብ ሱዳን ጆንገሌ ግዛት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት መገደላቸው ተሰማ፡፡ የሰላም ማስከበር አባላቱ ተሽከርካሪ ላይ የታጠቁ ሀይሎች በዛሬው ዕለት በፈጸሙት ጥቃት ሁለት አባላት ሲገደሉ ሰባት አባላት ቆስለዋል ተብሏል፡፡ ከቆሰሉት መካከልም 3 ኢትዮጵያውያን ሰላም አስከባሪ አባላት፣ 2 የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ፖሊስ አባላትና 2 ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ይገኙበታል ተብሏል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ ጥቃቱን አውግዘዋል፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ የተነሳን ድሮን መታሁ አለች….

የሱዳን መንግሥት፣ ከኢትዮጵያ የተነሳ ያለውን ድሮን በትናንትናው ዕለት መጥቶ መጣሉን አስታወቀ፡፡ ድሮኑን የመታው ብሉ ናይል ግዛት ውስጥ እንደሆነም ጠቅሶዋል፡፡ ድሮኑ ተመትቶ የወደቀው የድንበር ከተማ በሆነችው ኩርሙክ አካባቢ መኾኑንም የሱዳን መከላከያ ሚንስቴር ተናግሯል፡፡

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች……..ነሐሴ 18በትግራይ ዛሬ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ…..በሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ ትግራይ በዛሬው ዕለት የድሮን ጥቃት መፈፀሙን የክልሉ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡ ዛሬ ...
24/08/2026

የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች……..ነሐሴ 18

በትግራይ ዛሬ የድሮን ጥቃት ተፈፀመ…..

በሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ ትግራይ በዛሬው ዕለት የድሮን ጥቃት መፈፀሙን የክልሉ ባለስልጣናት አስታወቁ፡፡ ዛሬ ተፈፀመ የተባለው ጥቃት በእንዳባጉና እና በራያ አካባቢዎች እንደሆነም ተገልፆዋል፡፡ በጥቃቱ ስላጋጠመው ጉዳት ግን በይፋ የወጣ መረጃ የለም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ይፋዊ መግለጫም አልተሰጠም፡፡ ከዚህ ቀደም በመቐለ ከተማ ሁለት ቦታዎች ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት 13 ሰዎች መቁሰላቸው ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት በትራፊክ አደጋ 6 ሰዎች ሞቱ…..

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በዛሬው ዕለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ በክፍለ ከተማው ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አካባቢ በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ ሌሎች ሰዎችም ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የከተማው ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል፡፡ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ50 ላይ ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ በመጓዝ ላይ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መካከል የ6ቱ ህይወት አልፏል፡፡

በትግራይ የመውሊድ በዓል በአደባባይ እንዳይከበር ተወሰነ….

በነገው ዕለት የሚከበረው 1501ኛ ዓመት የመውሊድ በዓል በክልሉ እየተስፋፋ በመጣው የድሮን ጥቃት ምክንያት በአደባባይ እንዳይከበር የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ በዓሉ በየመስጊዱ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እንደሚከበርም ገልፆዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ባሉ የድሮን ጥቃቶች የተነሳ የህዝብ በዓላት ተፅዕኖ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡ በዚሁ ችግር ምክንያት በመቐለ ከተማ የአሸንዳ በዓል በስታድየም እንዳይከበር የክልሉ ቱሪዝምና ባህል ቢሮ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የሐላፊነት ቦታ ለወንዶች ያደላ ነው ተባለ…..

ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የኃላፊነት ቦታዎች ለወንዶች ያደሉ መሆናቸውን እንዳረጋገጠ አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ከፍተኛ ቀጣሪ እንደሆነ በሚነገርለት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተያዙ የኃላፊነት ቦታዎች፣ ለወንዶች ያደሉ መሆናቸውን ማረጋገጡን ገልፆዋል፡፡ የዓለም ባንክ በፋይናንስ ዘርፍ ውስጥ በፆታዎች መካከል ያለውን የክፍያ ልዩነት በማስመልከት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ሰነድ ሰሞኑን ይፋ አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ50,000 በላይ ሠራተኞችን መያዙን የገለጸው የዓለም ባንክ ሰነድ፣ ከአገሪቱ የባንክ ዘርፍ ወደ አንድ ሦስተኛ የሚሆነውን ሠራተኛ መያዙን ያስረዳል፡፡ ሆኖም የሐላፊነት ቦታዎች በአብዛኛው በወንዶች መያዛቸውን ገልፆዋል ይላል ሪፖርተር ጋዜጣ፡፡

በጊኒ ክምር ቆሻሻ ተደርምሶ 30 ሰዎች ሞቱ….

በጊኒ ዋና ከተማ ኮናክሪ የቆሻሻ መጣያ ተደርምሶ አጠገቡ ባሉ መኖሪያ ቤቶች ላይ በመውደቁ ቢያንስ 30 ሰዎች መሞታቸውን መንግሥት አስታውቋል፡፡ በከተማዋ ዳር-ኤስ-ሰላም አካባቢ በደረሰው በዚህ አደጋ 22 ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን፥ ከእነዚህም መካከል የስድስቱ ሁኔታ አሳሳቢ ነው። አንዲት እናት ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን እንደተናገሩት አምስት ልጆቻቸው በአደጋው ህይወታቸው አልፏል፡፡ የሟቾች ቁጥር አሁንም ሊጨምር እንደሚችል ሥጋት አለ፡፡

….የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች….በአዲስ አበባ ሕገወጥ ግንባታ የፈጸሙ አካላት ተቀጡ… በአዲስ አበባ ሕገወጥ ግንባታ በፈጸሙ ከ6,000 በላይ ተቋማትና ግለሰቦች ተጠያቂ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡ በ...
23/08/2026

….የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች….

በአዲስ አበባ ሕገወጥ ግንባታ የፈጸሙ አካላት ተቀጡ…
በአዲስ አበባ ሕገወጥ ግንባታ በፈጸሙ ከ6,000 በላይ ተቋማትና ግለሰቦች ተጠያቂ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡ በ2018 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ሕገወጥ ግንባታ በፈጸሙ 892 ተቋማትና ግለሰቦች ሕጋዊ ዕርምጃ እንደተወሰደባቸው የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡ የባለሥልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ተቋሙ ባደረገው የማሳወቅ፣ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ፣ ደንብ መተላለፍን በ81 በመቶ ቀንሶዋል ሲል የዘገበው ሪፖርተር ጋዜጣ ነው፡፡

በሶማሊያ የአየር ጥቃት 7 ሰዎች ተገደሉ…..

በሶማሊያ ፑንትላንድ በሚገኘው የኑጋል ዞን የባህር ዳርቻ አቅራቢያ በአንዲት መርከብ ላይ በተፈጸመ የአየር ጥቃት ሰባት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ ጥቃቱን ማን እንደፈፀመው እስካሁን በግልጽ አልታወቀም፡፡ የአካባቢው ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኤምቪ ሉቱፍ (MV Lutuf) የተባለችው ይህች መርከብ ከጥቂት ቀናት በፊት ወደ አካባቢው መጥታ ነበር፡፡ በካሜሩን ሰንደቅ ዓላማ የምትጓዘው ይህች መርከብ ወደ ቱርክ እያመራች እንደነበረ ተገልፆዋል፡፡

ታንዛኒያ ትልቅ የሀይል ማመንጫ አስመረቀች….

የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ሳሚያ ሱሉሁ 2,115 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለውን እና የታንዛኒያ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ጣቢያ የሆነውን የጁሊየስ ኔሬሬ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ጣቢያን መርቀው ከፍተዋል፡፡ 2.9 ቢሊዮን ዶላር የወጣበት ይህ ጣቢያ አሁን በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ካሉት ትላልቅ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫዎች አንዱ ቢሆንም: ከ 5,000 ሜጋ ዋት በላይ የሚያመነጨው እና የአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ከሆነው የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ (ህዳሴ ግድብ) ያነሰ ነው፡፡ በምስራቅ ታንዛኒያ በሚገኘው ሩፊጂ ወንዝ ላይ የተገነባው ይህ ጣቢያ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ሀብት የተሸፈነ መሆኑን መንግስት ገልጿል፡፡

በናይጄሪያ ከ 100 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች ታገቱ….

በናይጄሪያ ማዕከላዊ ኒጀር ግዛት ውስጥ ባሉ በርካታ መንደሮች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መታገታቸውን ፖሊስ እና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል፡፡ የወታደራዊ አልባሳት የለበሱ እንደሆኑ የተነገረላቸው ጥቃት አድርሾቹ ከአርብ ሶላት በኋላ በቦርጉ አስተዳደር ዞን ውስጥ በሚገኙ ማህበረሰቦች ላይ ኢላማ አድርገዋል፡፡ የፖሊስ ቃል አቀባይ ዋሲኡ አቢዮዱን ጥቃቱን የፈጸሙት የታጠቁ ሽፍቶች እንደሆኑ እንደሚጠረጥሩ ገልጸዋል፡፡

……ዩኔስኮ የዓለም የባርነት ቀን ታስቦ እንደዋለ አስታወቀ……የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ “ለዘመናት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ...
23/08/2026

……ዩኔስኮ የዓለም የባርነት ቀን ታስቦ እንደዋለ አስታወቀ……

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ “ለዘመናት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በየአህጉራቱ እና በየቀጣናው ተይዘዋል፣ በግድ ተፈናቅለዋል፣ ለጥቃት እና ለብዝበዛ ተዳርገዋል፣ እንዲሁም ተበዝብዘዋል” ብሎዋል፡፡ ተቋሙ በመግለጫው በነሐሴ 17 (ኦገስት 23)፣ የባርነት ሰለባዎችን እና የተረፉትን እናስባለን፤ እንዲሁም ዘላቂ ለሆኑ የባርነት ጠባሳዎች እውቅና እንሰጣለን ይላል፡፡ የባርነት ሰለባዎችን ማስታወስ የጋራ ኃላፊነት እና የክብር ተግባር ነው ያለው ዩኔስኮ በትምህርት፣ በምርምር እና በውይይት አማካኝነት ይህንን ትዝታ ለመጠበቅ እና የበለጠ ፍትሃዊ፣ አሳታፊ እና ሰላማዊ ዓለምን ለመገንባት መስራት ይገባል ሲል ገልፆዋል፡፡

አካላቸውን የተጎዱ የፍልስጤም ህፃናት ዋና በመለማመድ ላይ ናቸውበእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እግር እና እጃቸውን ያጡ የፍልስጤም ህፃናት በጋዛ ዋና በመለማመድ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሶስዬትድ ፕረ...
22/08/2026

አካላቸውን የተጎዱ የፍልስጤም ህፃናት ዋና በመለማመድ ላይ ናቸው

በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት እግር እና እጃቸውን ያጡ የፍልስጤም ህፃናት በጋዛ ዋና በመለማመድ ላይ ይገኛሉ፡፡ አሶስዬትድ ፕረዝ እንደዘገበው በፎቶ እንደዘገበው ከጥቅምት 7 ቀን 2023 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ በእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ምክንያት እግር እና እጃቸውን ያጡ የፍልስጤም ህፃናት 'ሂል ፓለስታይን' (Heal Palestine) በተባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት በተዘጋጀ ትምህርት በካን ዩኒስ፣ ጋዛ የዋና ልምምድ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ photo credit: AP

……….የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች…….የ 12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ከ 87 በመቶ በላይ አላለፉም…. የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሠዱ 550 በላይ ተማሪዎች ያ...
22/08/2026

……….የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች…….

የ 12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች ከ 87 በመቶ በላይ አላለፉም….

የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሠዱ 550 በላይ ተማሪዎች ያለፉት 70 ሺሕ 544ቱ ብቻ ናቸው፡፡ ትምህርት ሚንስቴር፣ ማለፊያ ውጤት ያመጡት ከጠቅላላ ተፈታኞች 12 ነጥብ 8 በመቶዎቹ ብቻ መኾናቸውን ማምሻውን በሠጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ከማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች 8 ነጥብ 3 በመቶዎቹ ብቻ ሲያልፉ፣ ከተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ደሞ 16 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ማለፊያ ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

የወባ ትንኝ መድሀኒትን የመቋቋም አቅም ጨምሯል…

በኢትዮጵያ የወባ በሽታ አስተላላፊ ተሕዋሲያን ዘረ መላቸውን በመቀያየር መድሃኒት የመቋቋም አቅማቸው በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን ጤና ሚንስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከአሜሪካ ተመራማሪዎች ጋር ባደረጉት ጥናት አረጋገጡ፡፡ በአገሪቱ ከስድስት ዓመት በፊት 1 ሚሊዮን የነበረው በወባ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በአውሮፓዊያኑ 2024 ወደ 10 ሚሊዮን አሻቅቧል፡፡ መድሃኒቶችን የሚቋቋሙ በርካታ የወባ ተኅዋሲያን ዝርያዎች በስፋት መሠራጨታቸውን ጥናቱ አሳይቷል፡፡

የምክክር ጉባኤው ተጠናቀቀ…

ከ አንድ ወር በላይ የቆየውና 4000 ተመካካሪዎች ተሳትፈውበታል የተባለው የብሔራዊ ምክከር ጉባኤ በዛሬው ዕለት በማጠቃለያ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረ ሥላሴ ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በስኬት መጠናቀቁን አስመልክተው ባደረጉት የማጠቃለያ ንግግር፣ ጉባኤው በኢትዮጵያ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሒደቱ በከፍተኛ አለመግባባትና ውዝግብ የታጀበ እንደነበርና በተለይም በአዲስ አበባ ጉዳይ መግባባት እንዳልተቻለ ሲነገር ቆይቷል፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ለውጭ ሀገር ተቀጣሪዎች የመነሻ ደመወዝ አሳደገች…

የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች፣ በተለያዩ የሙያ መደቦች ለሚቀጠሩ የውጭ ዜጎች ዝቅተኛው ወርሃዊ ደመወዝ አራት ሺሕ ድርሃም ወይም 1 ሺሕ 80 ዶላር ገደማ እንዲኾን ወሠነች፡፡ የአገሪቱ መንግሥት የውጭ ዜጎች የሚሠማሩባቸውን ሁሉንም የሙያ መስኮች በዘጠኝ መደቦች ደልድሏቸዋል፡፡ የውጭ ዜጎች የሚቀጠሩባቸው የሙያ ዘርፎች በዘጠኝ መደቦች የተከፈሉት፣ የዓለም የሥራ ድርጅትን የሙያ ደረጃ መስፈርቶች መሠረት በማድረግ መሆኑ ተነግሯል፡፡

…..የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች……. የአሸንዳ ክብረ በዓል ተሰረዘ….በየአመቱ በመቐለ ከተማ በአደባባዮች የሚከበረው የአሸንዳ ክብረ በዓል በዚህ አመት በትግራይ ስታድየም እንደማይከበር የክልሉ ባ...
21/08/2026

…..የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች…….

የአሸንዳ ክብረ በዓል ተሰረዘ….

በየአመቱ በመቐለ ከተማ በአደባባዮች የሚከበረው የአሸንዳ ክብረ በዓል በዚህ አመት በትግራይ ስታድየም እንደማይከበር የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡ ቢሮው በሰጠው መግለጫ፣ ምንም እንኳን የትግራይ ህዝብና ባህልና እሴቶችን ባከበረ መልኩ በነገው ዕለት ለማክበር ዝግጅቶች ቢደረጉም፣ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች እና በዋና ከተማዋ መቐለ እየተፈፀመ ባለው የአየርና የድሮን ድብደባ ምክንያት የአደባባይ ክበረበዓሉ መሰረዙን አመልክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ጉዳይ በኮሚቴ ሊታይ ነው….

በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ ውዝግብ እና አለመግባባት በፈጠረው የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ላይ አስማሚ ሃሳብ እንዲያዘጋጅ የተቋቋመው አቀራራቢ ኮሚቴ፤ የደረሰበትን ውጤት በዛሬው ዕለት ለተመካካሪዎች እንዲያቀርብ መወሰኑን የጉባኤው ተሳታፊዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ፡፡ ኮሚቴው አስማሚ ሃሳቡን የሚያዘጋጀው፤ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ በተለያዩ ደረጃዎች የተከፋፈሉ ቡድኖች ያቀረቧቸውን ሃሳቦች ከቃለ ጉባኤዎች ላይ ከመረመረ በኋላ ነው ተብሏል፡፡

በኦሮሚያ ጊዳ አያና የታጣቂዎች ጥቃት….

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ ትላንት ረቡዕ ከሰዓት በኋላ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ዋና ሥራ አሥኪያጅ እና የአዋሽ ባንክ ዋና ኦዲተርን ጨምሮ ለጊዜው ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘገበ፡፡ በጥቃቱ የአዋሽ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ኦዲተር ለሚ መንግሥቱ፣ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ጊዳ አያና ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ማሙሽ ማሩን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል ሲሉ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ ከባንኮች የተዘረፈ ገንዘብም እንዳለ ሲገለፅ፣ የጥቃት አድራሾቹ ማንነት እስካሁን አልታወቀም፡፡

የአዲስ አመት ኤክስፖ በአዲስ አበባ ተከፈተ…

በኤግዚቢሽን ማዕከል በተሰናዳው የአዲስ ዓመት ኤክስፖ ከ500 በላይ አምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች፣ የንግድ ወኪሎችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንደሚሳተፉ ተነገረ፡፡ ለመጪው የ2019 አዲስ ዓመት የበዓል ሸመታ የሚከወንበትና በኤግዚቢሽን ማዕከል የተሰናዳው ኤክስፖ በዛሬው እለት ተከፍቷል፡፡ በሴንቸሪ ፕሮሞሽን እና ኤቨንትስ አዘጋጅነት የሚከናወነው የአዲስ ዓመት ኤክስፖ 150 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል ተብሏል፡፡ ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ነሐሴ 15 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለ21 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ሸገር ሬድዮ ዘግቦዋል፡፡

የፋይዳ መታወቂያ ያላወጡ ደመወዝ አያገኙም….

የኦሮሚያ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እስካሁን ላላወጡ የመንግሥት ሠራተኞች ከተያዘው ወር ጀምሮ ደመወዝ እንዳይከፈላቸው ማገዱን ዋዜማ ዘግቦዋል፡፡ ቢሮው የሠራተኞችን ቆጠራ ለማካሄድ ሠራተኞች ፋይዳ መታወቂያ እንዲያወጡ ለበታች ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መዋቅሮች ባለፈው ዓመት ማሳሰቢያ አሠራጭቶ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን መታወቂያውን ያላወጡ ሠራተኞች መኖራቸውን ቢሮው አመልክቷል፡፡

በትግራይ መቐለ ከተማ በድሮን ጥቃት 13 ሰዎች ቆሰሉ….በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ዛሬ ረፋድ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት 13 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለፀ፡፡ ...
20/08/2026

በትግራይ መቐለ ከተማ በድሮን ጥቃት 13 ሰዎች ቆሰሉ….

በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ ዛሬ ረፋድ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት 13 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገለፀ፡፡ የክልሉ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፉት ቀናት እያካሔደ የነበረውን የድሮንና የአየር ጥቃት ቀጥሎበት ዛሬ ነሐሰ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ረፋድ ላይ በዋና ከተማዋ በሁለት ቦታ የድሮን ጥቃት ማካሔዱን አመልክቷል፡፡ የድሮን ጥቃቶቹ የተካሔዱት አንደኛው በሓወልቲ ክፍለ ከተማ ሓወልቲ ሞሞና ቀጣና 27 አካባቢ እና እዳማርያም በሚባሉት ቦታዎች ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ኩሓ አካባቢ መሆናቸውን ገልፆዋል፡፡ የድሮን ጥቃቱ በመኖሪያ ቤቶች ላይ በመፈፀሙ 13 ንፁሃን ሰዎች መጎዳታቸውን ገልፆ፣ ጥቃቱ ሊቀጥል ስለሚችል ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክሯል፡፡

ፕረዝደንት ትራምፕ ለምን ባለሀብቶችን ይሾማሉየአሜሪካው ፕረዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ከሾሟቸው የናጠጡ ባለሀብቶች መካከል የዓለማችን ቱጃሩ ኤሎን መስክ አንዱ ነበር...
19/08/2026

ፕረዝደንት ትራምፕ ለምን ባለሀብቶችን ይሾማሉ

የአሜሪካው ፕረዝደንት ዶናልድ ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው ከሾሟቸው የናጠጡ ባለሀብቶች መካከል የዓለማችን ቱጃሩ ኤሎን መስክ አንዱ ነበር፡፡ አሶሴትድ ፕረስ እንደዘገበው፣ ትራምፕ በሁለተኛው የስልጣን ዘመናቸው፣ በዙሪያቸው ባሰባሰቡዋቸው ባለሀብቶች የሆኑ ባለስልጣናት ብዛት ቀድመው ከነበሩት ሶስት መሪዎች ከነበሩዋቸው ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ ይበልጣሉ፡፡

ለዶናልድ ትራምፕ በሁለተኛው የፕሬዝዳንትነት ዘመናቸው ባለስልጣናትን ለመሾም ከታማኝነት ቀጥሎ ሀብት እጅግ ከፍተኛ ዋጋ የተሰጠው መመዘኛ ሆኗል ይላሉ ተንታኞች፡፡ በሸማቾች መብት ተሟጋቹ 'ፓብሊክ ሲቲዝን' (Public Citizen) ቡድን ዘገባ መሠረት፣ ሪፐብሊካኑ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሾሟቸው የሀብት መጠናቸው ቢያንስ 100 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ሰዎች ቁጥር፣ ቀድመው ከነበሩት ሦስት ፕሬዝዳንቶች ዘመን ከተሾሙት አጠቃላይ ድምር በአራት እጥፍ ይበልጣል፡፡

በአጠቃላይ 57 የትራምፕ ባለሥልጣናት የእያንዳንዳቸው ሀብት መጠን ቢያንስ 100 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ይህም 17 አምባሳደሮችን እና በቀሪዎቹ የሥራ አስፈፃሚ አካላት ውስጥ ባሉ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ያሉ 40 ሰዎችን ያካትታል፡፡ በተለይም ሁለቱ ባለስልጣናት ማለትም የንግድ ሚኒስትሩ ሀዋርድ ሉትኒክ እና የትምህርት ሚኒስትሯ ሊንዳ ማክማሆን ቢሊየነሮች ናቸው፡፡ ራሳቸው ቢሊየነር የሆኑት ፕሬዝዳንቱ፣ እጅግ ሀብታም የሆኑ ሰዎችን ለመሾም ያላቸውን ፍላጎት ለፋይናንስ ስኬት እንደተሰጠ አክብሮት አድርገው ገልጸውታል፡፡

የሪፐብሊካኑ ጆርጅ ደብሊው ቡሽ እና የዴሞክራቱ ጆ ባይደን አስተዳደሮች እያንዳንዳቸው 100 ሚሊዮን ዶላር ወይም ከዚያ በላይ ሀብት ያላቸው አምስት አባላትን ያካተቱ ሲሆን፣ የዴሞክራቱ ባራክ ኦባማ አስተዳደር ደግሞ ሦስት አባላት ብቻ እንደነበሩት የዘገባው መረጃ ያመለክታል፡፡ በብዙ የኢኮኖሚ ባለሀብቶች የተሞላ መንግሥት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ያጋልጣል ሲሉ የዘገባው አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

የፓብሊክ ሲቲዝን' (Public Citizen) ተባባሪ ፕሬዝዳንት ሊሳ ጊልበርት ሲናገሩ፡ “የመንግሥትን ሥልጣን የያዙት ሰዎች እጅግ ከአብዛኛው የሀብታሞች ክፍለ-አካል ብቻ ሲሆኑ፣ ይህ ወደተሳሳተ ተነሳሽነት እና ሙስና የሚያመራ ከመሆኑም በላይ ‘በእርግጥ የማንን ጥቅም ነው የሚያገለግሉት?’ የሚለውን ጥያቄ ያስነሳል” ብለዋል፡፡ የባለህብት ባለስልጣናቱ ዝርዝር 'ፎርብስ' (Forbes) የሀብት መጠናቸውን ከ6 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ የሚገምታቸውን ፕረዝደንት ትራምፕን አያካትትም፡፡

በተጨማሪም ባለፈው ዓመት የፌደራል መንግሥቱን መጠን፣ ወሰን እና የሠራተኛ ኃይል ለመቀነስ በተደረገው ጥረት ትራምፕን ሲያማክሩ የነበሩትን እና ፎርብስ የሀብት መጠናቸውን በግምት 860 ቢሊዮን ዶላር በማድረስ በዓለም ቀዳሚው ባለሀብት እንደሆኑ የገመታቸውን የጠፈር እና የሶሻል ሚዲያ ተቋማት ባለቤቱን ኢሎን መስክን አያካትትም፡፡

በአሜሪካ ታሪክ ፕሬዝዳንቶች የሀገሪቱን ባለሀብቶች ምክር ሲሹና አንዳንዶቹንም ለከፍተኛ የሥራ አስፈፃሚ አመራር ቦታዎች ሲመርጡ ቆይተዋል፡፡ ባለሀብቶችንና ተፅዕኖ ፈጣሪ ደጋፊዎቻቸውን በአምባሳደርነት መሾምም የተለመደ ተግባራቸው ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ከሚጠቀሱት በጣም ታዋቂ ምሳሌዎች መካከል በ1920ዎቹ ውስጥ ከሀገሪቱ እጅግ ባለጠጋ ሰዎች አንዱ የነበሩትና ለሦስት ፕሬዝዳንቶች በፋይናንስ ሚኒስትርነት ያገለገሉት የአሉሚኒየም፣ የነዳጅ እና የባንክ ኢንዱስትሪ ባለቤቱ አንድሩ ሜሎን ይገኙበታል፡፡

የትራምፕ እይታ በግልጽ ይታወቃል፡ የፋይናንስ ስኬት ለአስፈፃሚነት ብቃት እና ለድርድር ጥንካሬ ማረጋገጫ ነው ይላሉ፡፡ ትራምፕ ባለፈው ዓመት ለንግድ ሥራ አስፈፃሚዎች ምክር ትልቅ ቦታ ለምን እንደሰጡ ሲያስረዱ “እነዚያ ሰዎች ከፍተኛ ብቃት አላቸው፡፡ አስደናቂ ብቃት፡፡ ከሁሉ ይበልጥ ብልህ የሆኑ የንግድ መሪዎች ናቸው” ብለው ነበር፡፡ በተጨማሪም የሀብታም ሰዎች ኢንቨስትመንት የወደፊት የኢኮኖሚ ዕድገት ምልክት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

…….የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች…….በትግራይ የሴቶች ግድያ…በዚህ አመት በትግራይ ክልል 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸውን የክልሉ የሴቶች ማህበር አስታወቀ፡፡ ማህበሩ የአሸንዳ በዓል አከባበርን በማስ...
19/08/2026

…….የዕለቱ አጫጭር ዜናዎች…….

በትግራይ የሴቶች ግድያ…

በዚህ አመት በትግራይ ክልል 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸውን የክልሉ የሴቶች ማህበር አስታወቀ፡፡ ማህበሩ የአሸንዳ በዓል አከባበርን በማስመልከት በሰጠው መግለጫ፣ ለሴቶች ፍትህ መጠየቃችንን እንቀጥላለን ብሎዋል፡፡ በትግራይ በተለይም ከጦርነቱ በኋላ ማህበራዊ ቀውስ እየተስፋፋ በመምጣቱ፣ በሴቶች ላይ የሚፈፀም ፆታዊ ጥቃትና ግድያ እየጨመረ መምጣቱ ይታወቃል፡፡ በክልሉ ዋና ከተማ መቐለ የተገደለችው ዘውዱ ሀፍቱ ገዳዮች ናቸው የተባሉት ሁለት ሰዎች በፍርድ ቤት በነፃ እንዲለቀቁ መወሰኑን ተከትሎ በክልሉ ቅሬታ ሰፍኗል፡፡ የመብት ተሟጋቾችም ቅሬታቸውን ለመግለፅ አሸንዳን በጥቁር አልባሳት እናክብር የሚል ዘመቻ የጀመሩ ሲሆን፣ የክልሉ ባለስልጣናት በበኩላቸው ይህ አካሔድ የህግ ተጠያቂነትን ያስከትላል በማለት እንዳይሞክሩት አስጠንቅቀዋል፡፡

በአሜሪካ ለኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ጊዜያዊ ከለላ እንዲሰርዝ ፍርድ ቤት ፈቀደ….

የአሜሪካ ፍ/ቤት የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ጊዜያዊ ከለላ እንዲሰርዝ ፈቀደ፡፡ የአሜሪካ ፌደራል ፍርድ ቤት የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን የጊዜያዊ ከለላ መብት እንዲሰርዝ ወስኗል፡፡ ውሳኔው በኢትዮጵያ ያለውን የጸጥታና የሰብዓዊ ሁኔታ ስጋቶች ግምት ውስጥ ሳያገባ፣ ዜጎቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ፈቅዷል፡፡ ኢትዮጵያውያን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካ ከለላ ያገኙት በፈረንጆቹ 2022 በቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳዳር ዘመን ነው፡፡ በወቅቱ ከለላው የተሰጠው በኢትዮጵያ በነበረው የሲቪል ግጭት እና የሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት ነበር፡፡

በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ለውትድርና የታፈሱ ወጣቶች በመጋዘኖች ይገኛሉ…

በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ ከመንገድ የታፈሱ ወጣቶች በፍየል ማቆያ መጋዘኖች ውስጥ ጭምር ተይዘው ለመልቀቅ ገንዘብ እየተጠየቀባቸው እንደሆነ መሰረት ሚዲያ ዘገበ፡፡ በባህር ዳር ከተማ በተለይም በቀበሌ 13፣ ጎፋ ሰፈር እና ገጠር መንገድ በተባሉ አካባቢዎች በርካታ እናቶች ልጆቻቸውን ፍለጋ በየፖሊስ ጣቢያው ሲንከራተቱ እንደነበርና በርካታ ወጣቶች በሲኖ ትራክ መኪናዎች ተጭነው ሲወሰዱ ታይተዋል ተብሏል፡፡ በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በምትገኘው ድሎሎ ጂላ አካባቢ ደግሞ ሚሊሻዎች ወጣቶችን ከታክሲና ከባጃጅ በማስወረድ እያፈሱ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አሜሪካ ግብፅን እና ኢትዮጵያን ልታደራድር ነው…

አሜሪካ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ላይ ግብፅን እና ኢትዮያን ዳግም ድርድር ለማስጀመር ዝግጁ መሆኗን ገለጸች፡፡ በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን አለመግባባት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት፣ አሜሪካ ድርድር ለማስጀመር ዝግጁ መሆኗን የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ ገለፁ፡፡

ወደ ታላቋ ብሪታንያ ሊተላለፍ የነበረ ኮኬይን በናይጄሪያ ተያዘ…

ወደ ዩኬ ሊላክ የነበረ 28 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ኮኬይን ይዞ የተገኘው ናይጄሪያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ ከዓለም አቀፍ የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር መረብ ጋር ግንኙነት አለው ተብሎ የተጠረጠረ አንድ ናይጄሪያዊ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ፣ ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ሊላክ የነበረ ዋጋው ወደ 28 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኮኬይን መያዙን ተከትሎ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ አፎላቢ ካዜም ማይክል የተባለው ተጠርጣሪ ባለፈው ሳምንት ወደ ፓሪስ ለመብረር በዝግጅት ላይ እያለ በሌጎስ አውሮፕላን ማረፊያ መያዙን የናይጄሪያ የአደንዛዥ ዕፅ ቁጥጥር ኤጀንሲ አስታውቋል ሲል ቢቢ ዘግቦዋል፡፡

በናይጄሪያ 24 ሰዎች በታጣቂዎች ተገደሉ….

በናይጄሪያ ሰሜናዊው የማንፑቱ ግዛት ታጣቂዎች በተፈፀሙት ጥቃት ቢያንስ 24 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡ ነዋሪዎችና የአካባቢው ምንጮች እንደገለፁት፣ ታጣቂዎቹ ሰኞ ማለዳ ወደ ማህበረሰቡ በመግባት በየቤቱ እየዞሩ ነዋሪዎችን ማጥቃታቸውን ተናግረዋል፡፡ በአካባቢው የሚገኘው የማንጉ ልማት ማህበር ፕሬዝዳንት ቡለስ ዳቢት ታጥቂዎቹ ጥቃቱን የፈፀሙት ነዋሪዎች ተኝተው ባለበት እኩለ ሌሊት አካባቢ እንደሆነ አስረድተዋል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ 107 ሰዎች በመሬት ናዳ ሞቱ…

በካሜሩንና በማዕከላዊ የአፍሪካ ሪፐብሊክ መካከል በሚገኝ ዛምቦይ የሚባል የማዕድን ማውጫ ቦታ ባጋጠመ የመሬት መናድ አደጋ 107 ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ፡፡ በካሜሮን ምስራቃዊ ግዛት ባለስልጣን የሆኑት አማዱ አብዶን ለቢቢሲ በሰጡት ቃል፣ አደጋው ያጋጠመው ማክሰኞ እለት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የመሬት ናዳው መንስኤ ግን እስካሁን እንዳልታወቀ ተዘግቦዋል፡፡

Address

Kenya
Nairobi

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when HORN news center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share