Arba Minch FM 90.9 / አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9

Arba Minch FM 90.9 / አርባ ምንጭ  ኤፍ ኤም 90.9 የአርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9 ሬድዮ የህብራዊነት ድምፅ በመሆኑ ያዳምጡታል ይናገሩበታልም !

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ2017  በጀት ዓመት መካከለኛ ዘመን የጤን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸም  ግምገማና የ2018 ዓመት ጤቋሚ ዕቅድ ምክክር መድረክ በአርባ ከተማ እየ...
15/07/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት መካከለኛ ዘመን የጤን ልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 ዓመት ጤቋሚ ዕቅድ ምክክር መድረክ በአርባ ከተማ እየተካሄደ ነው

‎አርባምንጭ ሀምሌ 08፣2017ዓ.ም (ኤፍኤም 90.9)

‎ጤናማ ፣ምርታማና የበለፀገ ህብረተሰብ ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል ።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የእለቱ የክብር ዕንግዳ አቶ ጥላሁን ከበደ የዘጎችን ጤና ለሻሻል ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰሩ ካሉ አበይት ተግባራት መካከል የጤና ስርዓት ተቋም ፣አገልግሎት አሰጣጥ፣ታዓማኝ የመረጃ አሰጣጥና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በማሻሻል ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን በመግለጽጉባኤውን ከፍተዋል ።

‎በቀጣይም ጉባኤው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አድርጉ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።

‎በመርሀ ግብሩም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላሁን ከበደን ጨምሮ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ ፣ የክልል ፣የዞንና የወረዳ አመራሮችና የሚመለከታቸው አካላት እየታደሙ ይገኛሉ ።

‎ዘጋቢ ፡ ማስረሻ ዘውዴ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ሰድስተኛ ምርጫ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 10 ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገለፀ።ምክር ቤቱ በዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አጽንኦት ሰጥቶ...
15/07/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ሰድስተኛ ምርጫ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከሐምሌ 10 ጀምሮ እንደሚያካሂድ ተገለፀ።

ምክር ቤቱ በዚሁ ታሪካዊ ጉባኤ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ አጽንኦት ሰጥቶ እንደሚመክር ተገልጿል።

አርባ ምንጭ ሐምሌ 08_2017 ዓ/ም (አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9 ሬዲዮ)

ከሐምሌ 10,2017 ዓም ጀምሮ የሚካሄደው ስድስተኛ ምርጫ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤ ታሪካዊ ጉባኤ መሆኑን ነው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ ገልፀዋል።

ክልሉ በሁለት ዓመት ቆይታው ባከናወናቸው ተግባራት የታዩ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ያከናወናቸው ስኬቶች ምን እንደሚመስሉ በስፋት ይታያሉ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ።

በጉባኤው ላይ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲት መስሪያ ቤት ዕቅድ አፈፃፀም ቀርቦ በዋና ዋና ጉዳዮች በስፋት ውይይት ይካሄድባቸዋል ነው ያሉት ዋና አፈጉባኤው።

የህዝብን ዘላቂ ሰላም እንዲሁም ልማትን በሚያረጋግጡ እንዲሁም ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ጉባኤው ይመክራል ያሉት የክልሉ ዋና አፈጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲ በ2017 ለተከናወኑ ስኬቶች ዕውቅናም እንደሚሰጥ አመላክተዋል።

የምክር ቤት አባላት የህዝብ ድምፅ ናቸው ያሉት ዋና አፌጉባኤው ከዕቅድ ጀምሮ መሬት ላይ አፈፃፀሙ በትክክል ስለመውረዱና ህዝቡ የልማት ተጠቃሚ ሰለመሆኑ መከታተል ድርሻቸው እንደሆነም አመላክተዋል።

ከሐምሌ 10 ጀምሮ በሚካሄደው በዚሁ ጉባኤ ባለድርሻ አካላት እንደሚገኙና የቅድመ ዝግጅት ሥራው መጠናቀቁን ጭምር አቶ አለማየሁ ባውዲ አብራርተዋል ።

ዘጋቢ ታምሩ በልሁ

15/07/2025

የዞኑን ሕዝብ ሠላምና አንድነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በጋርዱላ ዞን የዲራሼ ወረዳ አስታወቀ።ዘጋቢ ፡ ወ/ገብርኤል ላቀው -ከአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ #ደሬቴድ ...

በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ህዝብ ም/ቤት 4ኛ ዙር  መረሃ ግብር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።አርባ ምንጭ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም(አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም ...
14/07/2025

በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ህዝብ ም/ቤት 4ኛ ዙር መረሃ ግብር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 42ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

አርባ ምንጭ ሐምሌ 07/2017 ዓ.ም(አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9)

በጉባኤዉ የወረዳዉ ም/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9ወር አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ማፅደቅ፣የወረዳዉ አስተዳደር ም/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወር አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ማፅደቅ፣የወረዳዉ ፍ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የ9ወር አፈፃፀም ሪፖርት እና የተለያዩ ሹመቶች የማፅደቅ መርሐ ግብር ይካሔዳል ተብሎ ይጠበቃል።
መረጃው የወረዳው መ/ኮ ነው

በሽታ መከላከልንና አክሞ ማዳን ላይ ትኩረት በማድረግ በድንገተኛ ክስተት ለተጎዱ ወገኖች እና ወረርሽኝ ምላሽ የሚሆን 10 ሚልዮን ብር ግምት ያለውን ግብአት ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል...
14/07/2025

በሽታ መከላከልንና አክሞ ማዳን ላይ ትኩረት በማድረግ በድንገተኛ ክስተት ለተጎዱ ወገኖች እና ወረርሽኝ ምላሽ የሚሆን 10 ሚልዮን ብር ግምት ያለውን ግብአት ማሰራጨቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ አስታወቀ ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት ዘርፍ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ እያካሄደ ይገኛል።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሀኑ እንደገለፁት የማህበረሰቡን ጤና ከማስታጠቅ አኳያ በነህክምና ዘርፉ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል ።

በዚህም በ5 ጤና ጣቢያዎች በቀዶ ህክምና የማዋለድ አገልግሎት መጀመሩን፣ በቀሪ ቦታዎችም ስራውን ለማስጀመር እንዲረዳ የ4 ወር ስልጠና 13 ጠቅላላ ሐኪሞች እየሰለጠኑ ይገኛሉ ብለዋል።

አቶ ናፍቆት አክለዉም በሆስፒታሎች ጥራት ለጥምረት በ5 መሪ ሆስፒታሎች 26 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎችን በማጣመር ከክትትል ባሻገር ያላቸውን የህክምና መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን አንስተዋል።

በበጀት አመቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በተመለከተ የህክምና መሳሪያዎች እጥረት የድጋፍና ክትትል ውስንነት የቦርዶች ጠንካራ አለመሆን የሚጠቀስ መሆኑንና በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባም አቶ ናፍቆት አመላክተዋል ።

በመድረኩ የተለያዪ ዞኖች የዕቅድ ክንዉን ሪፖርታቸውን ያቀረቡ ሲሆን በድክመትና በጥንካሬ ረገድ የተነሱ ጉዳዮችን ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራም በሪፖርታቸው አንስተዋል።

በመድረኩም ከዞን፤ ከሆስፒታሎች ፤የግል የህክምና ተቋማት እና ጥሪ የተደረገላቸው ተቋማት እየተሳተፉ ይገኛሉ ።
‎ዘጋቢ ስምረት አስማማው

የጋሞ ዞን ፖሊስ ሁለገብ አዳራሽ በአባላት  ገንዘብ እና ዕውቀት  የተገነባ ታሪካዊ አዳራሽ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል  ኮሚሽነር ታዬ ጫርጋ  ገለፁ ‎‎አርባምንጭ ...
14/07/2025

የጋሞ ዞን ፖሊስ ሁለገብ አዳራሽ በአባላት ገንዘብ እና ዕውቀት የተገነባ ታሪካዊ አዳራሽ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ታዬ ጫርጋ ገለፁ

‎አርባምንጭ ሀምሌ 07፣2017ዓ.ም (ኤፍ ኤም 90.9)

‎ የሁለገብ አዳራሹ መዝናኛ ክበብ ጠቅላላ አመታዊ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።

‎በመርሀ ግብሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ተወካይ ኮማንደር አንተነህ አበበ የዞኑ ሁለገብ አዳራሽ መዝናኛ ክበብ በቀድሞ አባቶች ከፍተኛ መስዋዕትነት የተገነባ ከመሆኑም ባሻገር ረጅም ታርክ ይዞ ተጠብቆ የቆዬ ነው ብለዋል ።

‎ በመሆኑ የቀድሞ የሠራዊት አባላት በቁጭት ተነሳስተው ህጋዊ መሰረት እና ስርዓት ዘርግተው በርካታ ተግባራትን ስያከናውኑ መቆየታቸውን አመላክተዋል።

‎አክለውም በለውጡ ወቅት መረጃዎች ጠፍተው ባለቤት አልባ ፣ የከብት መዋያ እና ዳዋ የበላው አንደነበር ጠቁመው በሰራዊቱ ተነሳሽነት እና ቁጭት በድጋሚ ተቋቁሞ ወደ ነበረበት ደረጃ ተመልሶ አገልግሎት እየሰጠ እንደምገኝ አመላክተዋል።

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ም/ ኮሚሽነር ታዬ ጫርጋ አዳራሹ በአባላት ገንዘብ እና ዕውቀት የተገነባ የፖሊስን አሻራ ያኖሩበት ታሪካዊ አዳራሽ መሆኑን አብራርተዋል።

‎በወቅቱም ስለ አዳራሹ አጭር ታሪክ በተጧሪ አባት 50 አለቃ ተስፋዬ መለሰ ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል

‎በመጨረሻም ከ2013 ዓም ጀምሮ የተከናወኑ የአዳራሹ ስራ ሪፖርት በኢንስፔክተር መጃ ከርቀላ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

‎በጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ታዬ ጫርጋን ጨምሮ የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ተወካይ ፣ ከፍተኛ መኮንን ማናጅመንት አባላት ፣ከ20 መዋቅሮች የመጡ የወረዳ ፖሊስ አዛዦች ፣የአርባ ምንጭ ከተማ እና የዙሪያ ወረዳ ኃላፊዎች እንዲሁም የቀድሞ ፓሊስ አባላት ተሳትፈዋል።

‎ዘጋቢ ፡ ተዋበች ዳዲ

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 318  ሚሊዮን  542 ሺህ 285 ብር  ብድር ተሰራጭቷል - የኦሞ ባንክ  የአርባ  ምንጭ  ዲስትሪክት‎‎አርባምንጭ ሀምሌ 07፣2017ዓ.ም (ኤፍ ኤም 90.9)‎‎ካ...
14/07/2025

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 318 ሚሊዮን 542 ሺህ 285 ብር ብድር ተሰራጭቷል - የኦሞ ባንክ የአርባ ምንጭ ዲስትሪክት

‎አርባምንጭ ሀምሌ 07፣2017ዓ.ም (ኤፍ ኤም 90.9)

‎ካሰራጨው ብድርም ከ347 ሚሊዮን ,ብር በላይ ማስመለስ መቻሉንም ተናግሯል

‎በኦሞ ባንክ የአርባ ምንጭ ዲስትሪክት 17 ቅርንጫፎች እንዳሉት የገለጹት የዲስትሪክቱ ስራአስኪያጅ አቶ ይርጋለም እሸቴ ናቸው።

‎318 ሚሊዮን 542 ሺህ 285 ብር ብድር አሰራጭቷል ፤ ከዚህም ከ 47 ሚሊዮን ብር በላይ ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚውል ነው ብለዋል ።

‎በበጀ ት ዓመቱ እና ከዚያ ቀደም ከተሰራጨው ገንዘብ 347 ሚሊዮን 724 ሺህ 994 ብር ማስመለስ መቻሉን አቶ ይርጋለም ገልጸዋል ።

‎15 ሺህ 781 የቁጠባ 4ሺህ 755 የብድር ደንበኞች ማፍራት ተችሏልም ብለዋል።

‎ ባንኩ አነስተኛ ብድር አገልግሎት ከሚሰጥበት ፤ የብሔራዊ ባንክን መስፈርት በማሟላቱ ሙሉ የባንክ አገልግሎት ከ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ መሆኑን ገልጸው በክልል ደረጃ ብቻ ታጥሮ የነበረውን በማስፋት በፌዴራል ደረጃ ዋና መ/ቤቱን በመክፈት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።

‎ህብረተሰቡም የተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ የሰፋ መሆኑን በመገንዘብ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል ።

‎ዘጋቢ ፡ አዕላፍ አዳሙ

ባለፈው  በጀት  ዓመት በ 69 አደጋ የ 59 ሰዎች ህይወት  ማለፉን የጋሞ ዞን ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከል  እና ቁጥጥር  ዲቪዥን ገለፀ ‎‎አርባምንጭ ሀምሌ 07፣2017ዓ.ም (ኤፍኤም9...
14/07/2025

ባለፈው በጀት ዓመት በ 69 አደጋ የ 59 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጋሞ ዞን ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ዲቪዥን ገለፀ

‎አርባምንጭ ሀምሌ 07፣2017ዓ.ም (ኤፍኤም90.9)

‎የባለሁለት እግር የሞተር ተሽከርካሪዎች አብዛኛውን አደጋ ማድረሳቸውም ተጠቁሟል

‎ የጋሞ ዞን ፖሊስ የትራፊክ አደጋ መከላከል እና ቁጥጥር ዲቪዥን ኃላፊ ም/ኮማንደር ኢያሱ ፓርዴ ባለፈው በጀት ዓመት በ 69 አደጋ የ 59 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልፀው የባለሁለት እግር የሞተር ተሽከርካሪዎች አብዛኛውን አደጋ ማድረሳቸውን ተናግረዋል ።

‎የደረሰው አደጋ ከ2016 በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር ቅናሽ ቢያሳይም በታቀደው ልክ አለመሆኑንም ጠቁመዋል ።

‎በዞኑ ካሉ መዋቅሮች 31 አደጋ በማስመዝገብ የአርባ ምንጭ ከተማ ቀዳሚ ሲሆን ምዕራብ ዓባያ 9 ብርብር 7 ከምባ ዙሪያ 6 ቁጫ 4 መመዝገቡንም ም/ኮማንደር ኢያሱ ገልጸዋል ።

‎የወደመ ንብረት ግምትም 5 ሚሊዮን 965 ሺህ ሲሆን በ2016 ከደረሰው ጋር ሲነፃፀር በ 499 ሺህ ብር ቀንሷል ብለዋል።

‎እየደረሰ ላለው የትራፊክ አደጋ ምክንያቶቹ ያለመንጃ ፈቃድ ማሽከርከር ፣ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠትና ፍጥነት ተቀዳሚዎቹ መሆናቸውን ም/ኮማንደር ኢያሱ ገልጸዋል ።

‎ዘጋቢ ፡ አዕላፍ አዳሙ

የዞኑን ሕዝብ ሠላምንና  አንድነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በጋርዱላ ዞን የዲራሼ ወረዳ አስታወቀ።በዞኑ የኩሱሜ ብሔረሰብ ምሁራን "በይቅርታ ተሻግረን በፍቅር እንደመራለን"   በሚ...
13/07/2025

የዞኑን ሕዝብ ሠላምንና አንድነት ለማስጠበቅ በትኩረት እየሠራ መሆኑን በጋርዱላ ዞን የዲራሼ ወረዳ አስታወቀ።

በዞኑ የኩሱሜ ብሔረሰብ ምሁራን "በይቅርታ ተሻግረን በፍቅር እንደመራለን" በሚል መሪህ ቃል የአንድነት እና የትውውቅ መርሀ ግብር በጋቶ አካህደዋል።

አርባ ምንጭ ሀምሌ: 06_2017 ዓ_ም (አርባ ምንጭ ሬዲዮ)

በዞኑ ብሎም በወረዳው ባለፉት ጊዜያት የተስተዋለው የጸጥታ ችግር በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ማድረሱ የሚታወስ ነው።
በዚህም የተለያዩ የልማት ሥራዎች በመስተጓጎላቸው ቁጭት ፈጥሮብን ወደ ቀደመ ሠላም ለመመለስ ከመንግሥት ጎን እየሠራን እንገኛለን የሚሉ የአከባቢው አገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ረዳሄኝ ችሎ ናቸው።

የተጀመረውን የሕዝብ ለሕዝብ አንድነትን በማጠናከር የአከባቢውን ሠላማ ለማስጠበቅ ወጣቱ ከጥፋት አጀንዳ መቁጠብ እንዳለበት የተናገረን ደግሞ ወጣት አብርሐም አይላዶ ነው።

የጋቶ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ አስፋው ረጋሳ የአከባቢውን ሠላምንና አንድነትን በማጠናከር በጸጥታ መደፍረስ ጊዜ የተጎዳውን አከባቢ ለመካስ ምሁራን ከመንግሥት ጎን እንዲሆኑ አሳስበዋል።

በወረዳው የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ለመፍታት በሁሉም አከባቢዎች ሰፊ የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት ከተካሔደ ወዲህ አንጻራዊ ሠላም እየታየ መሆኑን የዲራሼ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፍታውራር ታዬ ገልጸው ዘላቂ ሠላም እንዲሰፍን የሁሉም ጥረት ያሻል ብለዋል።

በቀጣይም በጸጥታ ችግር ምክንያት የተጎዱ አካላትን ለመካስ እና አጥፊዎችን በሕግ ለማስጠየቅ ይሠራል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው :ሠላም ወዳዱ የዲራሼ ሕዝብ ሠላም : አንድነትንና ልማትን ምርጫው በማድረግ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጠይቀዋል።

በአንድነት መድረኩ መርሐ ግብር የተገኙ የአከባቢው ተወላጆች የችግኝ ተከላም ተካህዷል።

ዘጋቢ: ወ/ገብርኤል ላቀው

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች የማይበገር የጤና ስርአት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።ይህ የተገለጸው ኢንስቲቲዩቱ  የ2017...
13/07/2025

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለድንገተኛ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች የማይበገር የጤና ስርአት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው ኢንስቲቲዩቱ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ጠቋሚ እቅድ ግምገማ መድረኩን በአርባምንጭ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሸብሩ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት አለምን እየፈተነ ያለውን የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት ምላሽ ስራን ውጤታማ በማድረጉ ሂደት በክልሉ የሚገኙ ዞኖች የተፈተኑበት አመት እንደነበር አስታውሰዋል።

በክልሉ ከ1000 ሰው 38ቱ በወባ የተጠቁበት ወቅት መሆኑን አስታውሰው ይህንንም ለመከላከል በህብረተሰብ ተሳትፎ ቅንጅታዊ ጥረት የጋሞ : ወላይታና የጎፋ ዞኖች ተመስግነዋል።

አርባምንጭ ሶዶና ዲላ ዩኒቨርስቲዎች በክልሉ የት አከባቢ ሰፊ የህብረተሰብ ጤና ችግር አለ የሚለውን በመለየት በጋራ እንዲሰሩ ይደረጋል ብለዋል።

ባለፈው አመት በክልሉ በጎፋ ዞን እና ዳሰነች ወረዳ በተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ የደረሰውን ሰብአዊ ቀውስ ለመከላከል የተሰራውን የጋራ ጥረት አቶ እንዳሻው ተናግረዋል።

በክልሉ በአርባምንጭ እና ጂንካ በመገንባት ላይ የሚገኙ ሪጂናል ላብራቶሪዎች መጠናቀቃቸውን የገለጹት ከኃላፊው ተቋማቱን በሰው ሃይልና ቁሳቁስ ለማሟላት ቢሮው ቁርጠኛ መሆኑን አስረድተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ አጉኔ ኢሹሌ እንዳስረዱት ክልሉ በርካታ ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ያስተናገደችበት ወቅት መሆኑን ተከትሎ ከዚህ ቀደም ያልታዩ በሽታዎች ክስተት በጤና ስርአቱ ላይ ጫና ፈጥሯል።

ወባ ፤ኩፍኝ ኮሌራና ሌሽማንያ የመሳሰሉት በሽታዎች በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ተከስቶ እንደነበር አውስተው በተለይም የወባ ወረርሺኝ በህብረተሰቡ ላይ ያደረሰውን ጫና ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

በበጀት አመቱ 1ሺ529 አዲስ በHIV /AIDS በሽታ የተያዙ ሲሆን 1ሺህ 493 ART መድሃኒት መጀመራቸውን አሰረድተው በመንገድ ላይ መዘግየት እና በከፍተኛ ደም መፍሰስ 71 እናቶች መሞታቸውንም ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል።

ትክክለኛ እና ወቅታዊ የሆነ የጤና መረጃ ለተሻለ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት መጠቀምን ባህል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑምን ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።

የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2018 ጠቋሚ እቅድ ግምገማ መድረክ ላይ በክልሉ የሚገኙ ዞኖች የተገኙ ሲሆን የኮሬ፣ የኮንሶ ዞኖች እና የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አመታዊ ሪፓርት ቀርቦ ጥንካሬና ደካማ አፈጻጸሞች ተለይተው በቀጣዩ በጀት አመት የተሻለ የጤና ስርአት ለመገንባት ከመግባባት ተደርሷል።

ዘጋቢ አሰግድ ተረፈ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ የኩልፎ ወንዝ የጎርፍ መቀልበሻ ስራ  ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረጉ‎‎አርባምንጭ ሀምሌ...
12/07/2025

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ የኩልፎ ወንዝ የጎርፍ መቀልበሻ ስራ ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረጉ

‎አርባምንጭ ሀምሌ 05 ፣2017 ዓ.ም (ኤፍኤም90.9)

‎ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር ሚንስትር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ በአርባምንጭ ከተማ እየተሰራ የሚገኘውን የኩልፎ የኩልፎ ጎርፍ መቀልበሻ ስራ ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አድርገዋል።

‎የኩልፎ ወንዝ በተደጋጋሚ በሚያስከትለው ጎርፍ አደጋ የአርባምንጭ ኤርፖርቱን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ላይ አደጋ በማስከተል ከአቅም በላይ ችግር በመፍጠሩ ምክንያት በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር በኩል ፕሮጀክቱ በመከናወን ላይ ይገኛል።

‎ግንባታውን በአጭር ጊዜ ተሰርቶ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ በመስክ መልከታው ወቅት ተገልጿል።

‎via ፦ ር/መስተዳድር ጽ/ቤት

‎በኮንሶ ዞን "የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ማረጋገጥ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ክብር!" በሚል መሪ-ቃል ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ጀመረ።‎_____‎በስ...
12/07/2025

‎በኮንሶ ዞን "የሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ማረጋገጥ ለሀገር ሉዓላዊነት እና ክብር!" በሚል መሪ-ቃል ለሁለት ቀናት የሚቆይ የአመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠት ጀመረ።
‎_____
‎በስልጠናው መርሃ-ግብር የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራሾ ጎስኬ በዞናችን ያሉና ከ20 ሺ በላይ የሚሆኑ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ከድጋፍ ተላቅቀው እራሳቸውን የሚችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል ያሉ ሲሆን፣ እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች ዳግም ወደተረጂነት እንዳይመለሱና በተዘጋጀላቸው የቢዝነስ ስራዎች መሠረትነት ጠንክረው እንዲሰሩ ማስቻል ያስፈልጋል ብለዋል።

‎የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ተረጂነት በባህሪው የሀገርን ሉአላዊነት የሚያሳንስ እና የዜጎችን ክብር የሚያዋርድ ነው ሲሉ አብራርተው፣ መስራት እየቻልን ተረጂነት ክብራችንን ዝቅ አስደርጎናል በማለት የነገውን የብልጽግና ፋና ለማየት ዛሬ በስራ አርበኝነት ከተረጂነት መላቀቅ ቁልፍ ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

‎አቶ ገለቦ አክለውም ሴፍትኔት የአከባቢያችንን የስራ ባህል አጥፍቶ ልመናን እያስፋፋ ያለ በመሆኑ በቶሎ መቀረፍ አለበት፣ እንደዚሁም ከተረጂነት እሳቤ በመውጣት በታታሪነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የብሄረሰቦች ምክር-ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ ተረጂነት እና ምርታማነት ተቃራኒ ቃላት መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ተረጂነት የድህነት ሌላ ቃል በመሆኑ፣ ይህንን ታሪክ ለመቀየር ምርታማነትን ማሳደግ ግድ ይላል ያሉ ሲሆን፣ መንግስት ይህንን ለማሳካት ከፍተኛ ውሳኔ አድርጎ ውሳኔውንም ለማሳካት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በጥንካሬ የታወቅን ሆነን ስናበቃ ተረጂነትን መቀበላችን ስማችንን የሚያጎድፍና ጥንካሬያችንን የሚያጠለሽ ነው ያሉት አቶ አዳማ፣ ተግተን ሰርተን የጥንካሬን ታሪክ መጻፍ ይገባናል ብለዋል።

‎የሰብአዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት በኢትዮጵያ እሳቤዎች ማስፈንጠሪያዎች እና መለኪያዎች በሚል ርእስ የተዘጋጀን ሰነድ የዞኑ ረዳት የመንግስት ተጠሪ እና የፖለቲካ ርዕዮትና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጉራሾ ለሚታ በሚያቀርቡበት ሰዓት
የሰብአዊ ድጋፍ ዓላማ እራስን መቻል ቢሆንም ዘላቂነት ሲኖረው ተረጂነትን የሚያሰርጽ በመሆኑ ከዚህ ዓይነት እሳቤ መላቀቅ ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል ።

‎በቀጣይም ሌሎች በርካታ ሰነዶች በዝርዝር የሚቀርቡ ሲሆን፣ ሰፋ ያለ ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

በስልጠናው የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬን እና የተከበሩ አቶ ገለቦ ጎልቶሞን ጨምሮ በዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ የተከበሩ አቶ ሐመር ሐንሻ፣ የዞኑ ሕዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ገልገሎ ኦቶማ፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጉራሾ ጎስኬ፣ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ፕረዚዳንት የተከበሩ አቶ ሙሃባ ቃውያ፣ የዞኑ የፊት አስተባባሪዎች፣ ካቢኔና አጠቃላይ ፑል አመራሮች፣ የካራት ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ያቤሎ ኩሴ፣ ከየወረዳው የመጡ አመራሮች፣ የግብርና መምሪያ ማናጅመንት አባላትና ባለሙያዎች፣ እንደዚሁም ከየመዋቅሩ የመጡ የቀበሌ ሊቀ-መናብርትና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
‎መረጃው
‎የኮንሶ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ
‎ ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም

Address

Arba Mintch

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Arba Minch FM 90.9 / አርባ ምንጭ ኤፍ ኤም 90.9 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share