
04/08/2025
68 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በጀልባ መስጠም አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ።
በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ ኢትዮጵያውያን ናቸው " - ዓለምአቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ።
በየመን አብያን ግዛት ስደተኞችን የጫነች ጀልባ በመስጠሟ ቢያንስ 68 ስደተኞች መሞታቸውንና 74 ስደተኞች ደግሞ የደረሱበት እንደማይታወቅ ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል።
በየመን የድርጅቱ ተወካይ አቤዱሳቶር ኢሶቭ ለአሶሼትድ ፕሬስ በሰጡት ቃል " በጀልባዋ የነበሩት 154 ተጓዦች በሙሉ #ኢትዮጵያውያን ናቸው " ብለዋል።
ኢሶቭ በሰጡት ቃል፤ ' ካንፋር ' በተባለ አካባቢ የ54 ስደተኞች አስክሬን በውቅያኖስ ዳር የተለያየ ቦታ ወድቆ መገኘቱን በሌላ ቦታ የተገኘ 14 አስክሬን ወደሆስፒታል መላኩን ተናግረዋል።
12 ሰዎች ደግሞ በህይወት መትረፋቸው ተመላክቷል።
እንደ ተወካዩ ገለፃ ኢትዮጵያውያኑ አደጋው የደረሰባቸው ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመግባት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ነው።
ነፍሳችሁ በሰላም ትረፍ😭