Lbe Amlak Media

Lbe Amlak Media Información de contacto, mapa y direcciones, formulario de contacto, horario de apertura, servicios, puntuaciones, fotos, videos y anuncios de Lbe Amlak Media, Medio de comunicación/noticias, Mexico City.

07/08/2026
ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዓን አባቶችን መደበ።  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ  በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተገኝተው ጉዳት የ...
05/06/2026

ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዓን አባቶችን መደበ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተገኝተው ጉዳት የደረሰባቸውን ኦርቶዶክሳዊያን የሚያጽናኑ ብፁዓን አባቶችን መደበ።

የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በዛሬው ዕለት ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው በችግሩ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ፣ በብፁዓን አባቶች የሚመራ የቤተ ክርስቲያናችን ልዑካን ቡድን ችግሩ ወደ ተፈጠረበት ቦታ በመሄድ ተጎጂዎችን እንዲጎበኝ፣ እንዲያጽናና እና አስፈላጊውን ጊዜያዊ ድጋፍ አንዲያደርግ ወስኗል።

ቋሚ ሲኖዶስ በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል በሚቋቋም ኮሚቴ አስተባባሪነትም በተፈጠረው ችግር ምከንያት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት ጥንታዊው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እንዲያሰራ፣ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በቋሚነት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ፣ በሀገረ ስብከቱ ዳግመኛ መሰል ችግሮች እንዳይፈጠርሩ ጥናት አካሒዶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ዐቢይ ኮሚቴ ተሰይሞ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል።

በትላንትናው ዕለት በምሥራቅ አርሲ አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰተውን ችግር ተከትሎ ፦

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
ብፁ አቡነ ዲዮስቆሮስ
ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ከፌዴራል ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተከሰተው ችግር ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

TV

Dirección

Mexico City

Notificaciones

Sé el primero en enterarse y déjanos enviarle un correo electrónico cuando Lbe Amlak Media publique noticias y promociones. Su dirección de correo electrónico no se utilizará para ningún otro fin, y puede darse de baja en cualquier momento.

Atajos

Compartir