08/02/2026
ሰዎችን ያለማመን ችግር (Paranoid Personality)
"ይህ የኢ-ሴንተሪክ (Ecentric) ማንነት ቀዉስ ዉስጥ የሚመደብ ሰዎችን ያለማመን ችግር ሲሆን ሁሉንም ሰዉ በማንኛዉም ነገር መጠርጠር ፣ እምነት ማጣት ወዘተ...ነዉ፡፡ ይህ ቀዉስ ሰዎችን ካለማመን ባለፈ በጠላትነት መፈረጅ እና ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዲፈጠር የሚያደርግ የአእምሮ መቃወስ ችግር ነዉ፡፡ በዚህ ችግር ዉስጥ ያሉ ሰዎች ከሰዉ የማይግባቡ፣ ቁጡዎች፣ ሌሎች ሰዎችን በጠላትነት የሚፈርጁ፣ እምነት የሌላቸዉ፣ የሰዎችን ደካማ እና ስህተት ብቻ የሚያዩ እና ስህተታቸዉን ብቻ ሚያወሩ ናቸዉ፡፡
መንሰኤ፡ ይህ ነዉ የሚባል መንስኤ ባይኖረዉም በዘር የሚወራረስ እና በአከባቢ ተጽእኖ ሊከሰት እንደሚችል ይነገራል ይህ ሰዎችን ያለማመን ችግር ሰኪዞፌርኒያ (schizophrenia) በተባለ የአእምሮ መዛባት በተጠቁ ሰዎች ዘንድ የተለመደ እና በተደጋጋሚ የሚከሰት ችግር ነዉ፡፡
ምልክቶቹ፡-
ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት እንዳላቸዉ አለመገንዘባቸዉ ትልቁ ችግራቸዉ ነዉ፡፡ በይበልጥ ሰዎችን ላለማመናቸዉ ምክንያት ይደረድራሉ፡፡ እንዲሁም ለሰዎች የማይመች ግትር ባህሪ እና ቁጡነታቸዉ መገለጫቸዉ ነዉ፡፡ በዋናነት በጥርጣሬ የተሞሉ መሆናቸዉ ይገልጻቸዋል በተጨማሪም ሰዎችን ጠላቶቻቸዉ አድርገዉ መቁጠር፣እምነት ማጣት ከሰዎች ጋር መስራት እና መግባባት አለመቻል፣ ለቁጣ እና ጥል መቸኮል፣ ራስን ከማንኛዉም ማህበራዊ ግንኙነት ማራቅ እና ማግለል፣ ግትር፣ ተከራካሪ እና ማንንም የማይቀበሉ፣ ንግግርን ‹‹አይደለም›› ብለዉ የሚጀምሩ፣የራሳቸዉን ስህተት እና ችግር የማይረዱ እና ማይቀበሉ፣ ለራሳቸዉ ሆነ ለሰዉ ጊዜ የማይሰጡ፣ ከራሳቸው የተጣሉ እና
ሳይኮሎጂስቶች ድጋፍ እና እርዳታ ማግኘት ይቻላል፣ ሰዎችን ማፍቀር ያለዉን ጥቅም እንዲረዱ ማድረግ እና በዚህ ችግርየተጠቃን ግለሰብ ማግለል ሳይሆን በመዉደድ መርዳት ይቻላል። ነገር ጠቁሮ እና ጨልሞ የሚታያቸዉ ፔስሚስቶች(pessimist)
መከላከያዉ፡ በዚህ ችግር ዉስጥ ያለ ሰዉ ሁኔታዎች እና ችግሮች አስተምረዉት ራሱን ለመቀየር ዝግጁ ካልሆነ መርዳት እና መለወጥ አዳጋች ነዉ፡፡ሰዉን ሁሉ አለማመን እና መጠርጠር እንደመብቱ ስለሚቆጥር እንዲሁም ይህን ማንነት የገዛ ባህሪዉ በማድረጉ በልጅነቱ ያልተስተካከል እና ያልተገራ ማንነት እጅግ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
እርዳታዉ፡ በዚህ ችግር ያለን ሰዉ ለመርዳት የግለሰቡ ፈቃደኛነት ከታከለበት ዉጤት ማምጣት ይቻላል። ነገር ግን አዳጋቹ ክፍል ግለሰቡ ሰዉን መጠርጠሩ ዋናዉ ችግር መሆኑን ማሳመን ነዉ፡፡ ከሰዎች ጋር እንዴት በሰላም መኖር እንዳለባቸዉ በማህበራዊ....