
28/03/2025
ዳኒ አልቬስ በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ያለው የግል አስተያየት፡-
"ንፅፅር የማደርግ ከሆነ... እኔ እንደ ተጫዋች በአጨዋወት ስልት ከሊዮ ሜሲ ይልቅ ወደ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እቀርባለሁ። አሁን ባርሳና ማድሪድ ውስጥ አይደለንም ። ምክንያቱም ስለዚህ ጉዳይ ሁል ጊዜ ማውራት ፣ 'አይ ለባርሳ ስለሚጫወት ስለ ማድሪድ ሰው ምንም ጥሩ ነገር መናገር አይችልም!' ያስብል ይሆናል። እኔ ግን መናገር እችላለሁ። እና ክሪስቲያኖ ብዙ ተሰጥኦ ለሌለን ሁሉ በምሳሌነት ይገልፃል ። በትጋት በመስራት ከምርጦች ጋር መወዳደር እንደሚቻል አሳይቶናል። ይህንን በምሳሌነት አሳይቷል፣ እኔም በጣም አከብረዋለሁ። እርስ በርሳችን በምንፎካከርበት ወቅት ይህን ልነግረው እድል አግኝቻለሁ። በትጋት፣ ጥረት በማድረግ ሁሉንም ነገር ያሳካ ወንድ እንዴት አላከብርም?!!! እራሴን ከእርሱ አንፃር ነው የምገልፀው።"
ምንጭ:-World soccer Talk
🇧🇷🤝🇵🇹