ትግራይ ሙስሊም ሚድያ

ትግራይ ሙስሊም ሚድያ This page is aimed to give all kinds of information specially related to Tigrian Muslims.

«እንትርፊ ናይ ባዕሉ ናይ ስልጣን ባህጊ ናይ ህዝቢ ሰላምን ድሕንነትን ዘየግድሶ ጉጅለ ነቲ ዝተፈጥረ ናይ ሰላምን ሓቢርካ ናይ ምስራሕን ተበግሶ ብምብራዝን ብምሕማስን ኣብ ህዝብና ህወከትን ግ...
18/02/2025

«እንትርፊ ናይ ባዕሉ ናይ ስልጣን ባህጊ ናይ ህዝቢ ሰላምን ድሕንነትን ዘየግድሶ ጉጅለ ነቲ ዝተፈጥረ ናይ ሰላምን ሓቢርካ ናይ ምስራሕን ተበግሶ ብምብራዝን ብምሕማስን ኣብ ህዝብና ህወከትን ግጭትን ንምፍጣር ኮነ ኢሉ ኣብ ምንቅስቓስ ከም ዘሎ ከም መንግስቲ ተረዲእና ኣለና።»

አቶ ጌታቸው ረዳ ፕሬዝዳንት ግዝያዊ ምምሕዳር ክልል ትግራይ

በትግራይ ሙስሊሙ የካቲት 11 ለማክበር ምን ምክንያት አለው?የትኛውም ህዝብ የነፃነት ትግል የጀመረበት ቀን አልያም ነፃነቱ ያገኘበት ቀን ያከብራል። ይህ የተለመደ ነው። ብዙ ሀገሮች ከቅኝ ግ...
17/02/2025

በትግራይ ሙስሊሙ የካቲት 11 ለማክበር ምን ምክንያት አለው?

የትኛውም ህዝብ የነፃነት ትግል የጀመረበት ቀን አልያም ነፃነቱ ያገኘበት ቀን ያከብራል። ይህ የተለመደ ነው። ብዙ ሀገሮች ከቅኝ ግዛት ነፃ ለማውጣት ትግል የጀመሩበት ቀን ወይም ነፃነታቸውን የተቀዳጁበት ቀን ያከብራሉ።

የሚገርመኝ ግን በትግራይ በተለይ ሙስሊሙ የካቲት 11 የሚያከብረው ምን ያሳካው ነገር ኑሮት ነው? በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብ ህወሓት ትግል የጀመረችበት ቀን ብሎ ቀኑን የሚያከብረው ምን ያገኘው ጥቅም አለው?

በትግራይ ክልል በቁጥራችን ማነስ ምክንያት  በሙስሊምነታችን ብቻ እንደሌላው በመንግስት ት/ቤት ውስጥ መማር አልቻልንም። ህገ መንግስቱ እኛን በብዛታቸው ከሚተማመኑ መጠበቅና ከለላ መሆን አልቻ...
17/02/2025

በትግራይ ክልል በቁጥራችን ማነስ ምክንያት በሙስሊምነታችን ብቻ እንደሌላው በመንግስት ት/ቤት ውስጥ መማር አልቻልንም። ህገ መንግስቱ እኛን በብዛታቸው ከሚተማመኑ መጠበቅና ከለላ መሆን አልቻለም። ትምህርት ሚኒስትሩ እኩል የትምህርት እድል እንድናገኝ ምንም ዓይነት ድጋፍ አላደረገልንም። በማን አለብኝነት 159 ተማሪዎች ከትምህርት ሲባረሩ ዝም ብሎ እየተመለከተ ይገኛል።

የፕሪቶሪውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ውይይት በመካሄድ ላይ ነው😀
16/02/2025

የፕሪቶሪውን የሰላም ስምምነት በተመለከተ በአፍሪካ ህብረት መሪነት ውይይት በመካሄድ ላይ ነው😀

አንዳንዶች ጀነራል ሳሞራ እነሱ በደገሱለት ጦርነት ውስጥ ዘው ብሎ አለመግባቱ፣ ሚልዮኖች እንዲያልቁ ምክንያት አለመሆኑ፣ «ጦርነት አያስፈልግም» ብሎ ሰሚ አጥቶ ከሁሉም ወገን ሳይሆን ቀርቶ ዝ...
16/02/2025

አንዳንዶች ጀነራል ሳሞራ እነሱ በደገሱለት ጦርነት ውስጥ ዘው ብሎ አለመግባቱ፣ ሚልዮኖች እንዲያልቁ ምክንያት አለመሆኑ፣ «ጦርነት አያስፈልግም» ብሎ ሰሚ አጥቶ ከሁሉም ወገን ሳይሆን ቀርቶ ዝምታን በመምረጡ በያዘው ጽኑ አቋሙ ብቻ በደምብ አድርጎ ስለረታቸውና ስለአሸነፋቸው የሚፅናኑት ህዝቡን እንደከዳ አድርገው ማውራትን ይዘዋል።

ክህደት ምን እንደሆነና ማን ህዝቡን እንደከዳ ግን 3ቱ ምስሎች ብቻ መመልከት በቂ ነው። ህወሓት ምን እያለች ነበር ሙስሊሙን ለትግል ስትጠራው የነበር? እስከዛሬ ድረስስ ምን እየሰራች ነው? ክህደት ይህ ነው።

የጀነራል ሳሞራ የኑስ «No War» ፅኑ አቋም ከደብረፅዮንና መንጀሪኖ ፉከራ ከአቦይ ስብሃት የሰሜን እዝ ሴራ «እኔ ጌታቸው አሰፋ ነኝ» እያለ ከሚያቅራራ ሚድያተኛ ለትግራይ ህዝብ ይጠቅም ነ...
16/02/2025

የጀነራል ሳሞራ የኑስ «No War» ፅኑ አቋም ከደብረፅዮንና መንጀሪኖ ፉከራ ከአቦይ ስብሃት የሰሜን እዝ ሴራ «እኔ ጌታቸው አሰፋ ነኝ» እያለ ከሚያቅራራ ሚድያተኛ ለትግራይ ህዝብ ይጠቅም ነበር። ሰውየው አሁንም «No War» እያለህ ነው።

ወ/ሮ መድህን ጀነራል ሳሞራ እያሰሰች ወደ ሚድያዋ የምታቀርበው የእሱ ያህል የሚሰማ ሰው ባለማግኘቷ ነው። ለገንዘቧ ነው።

16/02/2025

ህወሓት በባህሪው ያለጦርነት፣ ያለህዝብን ከህዝብ ጋር ማጋጨት፣ መከፋፈል ህልውናውን ማስቀጠል አይችልም። በቅርቡ አክሱም ት/ቤቶች ላይ እየሰራው ያለ ስራ አንዱ ማሳያ ነው።

የትግራይ ፖለቲካ ለሁሉም ምህረት የሌለው በሀሰት ስም አውጥቶ የሚያጠለሽ፣ ተቃራኒ ሀሳብ ያለውን በሙሉ በሃይል ጸጥ ማሰኘት የሚፈልግ ገፊና አግላይ ነው። ይህ በሁሉም ስራ ላይ የሚያውለው አጠ...
16/02/2025

የትግራይ ፖለቲካ ለሁሉም ምህረት የሌለው በሀሰት ስም አውጥቶ የሚያጠለሽ፣ ተቃራኒ ሀሳብ ያለውን በሙሉ በሃይል ጸጥ ማሰኘት የሚፈልግ ገፊና አግላይ ነው። ይህ በሁሉም ስራ ላይ የሚያውለው አጠቃላይ የሚመራበት መመሪያው ነው። በሙስሊም ሲሆን ደግሞ መመሪያው ይለጠጣል፤ ይብስበታል። ሰውየው ሙስሊም ከሆነ ሰማይና ምድሩ የሚያላግብ ሀሰት ያህል ይወራበታል። ስሙ እንዲጠፋና እንዲጠለሽ ይደረጋል። በሙስሊም ሲሆን የትግራይ ፖለቲካ ህመሙ እጅግ በጣም ይታማማል፣ ይብስበታል። ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ የገጠመውም ይህ ነው። የሚባለው በሙሉ ከሰራው ስራ ጋር የሚያያዝ አይደለም። ከስሙና ከሃይማኖቱ ጋር የሚያያዝ ነው።

ጀግናችን ማን ይምረጥልን? ጀግኖቻችን መምረጥ ያለባቸው የሌሎች የሃይማኖት ተከታዮች አይደለም። ጀግኖቻችን ለሀገርና ህዝብ በሚጠቅም አቋማቸው፣ በሚሰሩት ስራቸው መምረጥ ያለብን እኛው ነን። በዚህ መሰረት ጀነራል ሳሞራ ጀግናችን ነው። ሌላው ቢቀር ሚልዮኖች በጦርነት እንዲያልቁ ያላደረገ የውትድርና ሞያውና ኃላፊነቱ ጠንቅቆ የሚያውቅ ጀግናችን ነው።

በትግራይ ግዝያዊ ምክር ቤት ተመስርቷል። ምክር ቤቱ 7 ቋሚ ኮሚቴ ይኖሩታል። አጠቃላይ የወንበር መቀመጫ ብዛቱ ደግሞ 152 ነው። የመመሪያ ደንቡ በመመልከት ብቻ በትግራይ የዲሞክራሲ መንገድ ...
15/02/2025

በትግራይ ግዝያዊ ምክር ቤት ተመስርቷል። ምክር ቤቱ 7 ቋሚ ኮሚቴ ይኖሩታል። አጠቃላይ የወንበር መቀመጫ ብዛቱ ደግሞ 152 ነው። የመመሪያ ደንቡ በመመልከት ብቻ በትግራይ የዲሞክራሲ መንገድ ለመከተል ቆርጦ የተነሳ ያስመስለዋል። በትግራይ ሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች አቅፎ የያዘ፣ ያላገለለ ወይም የተወከሉበት መሆኑ አለመሆኑ ግን ለወደፊቱ የሚታይ ነው።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሟች አቶ መለስ ዜናዊ ህገ መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን የመመረጥ ግዝያቸው እንዳይገደብ በማድረጋቸው ምክንያት በሞት ነው ስልጣናቸውን የለቀቁት።

ቡድኑ እንደማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት የፃፈው ህግ አለው። እንደማንኛውም ይሰበሰባል፣ ጉባኤ ያካሂዳል። ስራ አስፈጻሚና ማእከላይ ኮሜቴ ይመርጣል። ሚድያ ጠርቶ መግለጫ ይሰጣል። አንድ የፖለቲካ...
15/02/2025

ቡድኑ እንደማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት የፃፈው ህግ አለው። እንደማንኛውም ይሰበሰባል፣ ጉባኤ ያካሂዳል። ስራ አስፈጻሚና ማእከላይ ኮሜቴ ይመርጣል። ሚድያ ጠርቶ መግለጫ ይሰጣል። አንድ የፖለቲካ ድርጅት ሊሰራው የሚገባውን ስራ አንድም ሳያስቀር ይሰራል።

ውስጡን ለማያውቅ፣ ሴራው ላልገባውና ጠለቅ ያለ እውቀት ለሚያንሰው ሰው ድርጅቱ ህግና ስርዓት ተከትሎ ስራውን የሚከውን ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅት ተመስሎ ነው የሚታየው።

ይህ ድርጅት በሌላ ትግራይ ወደ ገነት ከምትቀየር ይልቅ ራሱ እየገዛት ወደ ገሃነብ ብትቀየር የሚመርጥ በህጋዊነት ካባ ተከልሎ የሽብር ወንጀል በመፈጸምና በማስፈጸም 50 ዓመታትን ያስቆጠረ እድሜ ጠገብ አሸ.. ድርጅት ነው።

15/02/2025

«በትግራይ ከየት አከባቢ ስትወለድ ነው ትግራዋይ የምትሆነው? ማን ሲቀድልስኝና ሲባርክልኝ ነው እኔ ትግራዋይ የምሆነው?» በማለት አቶ ረዳኢ ሓለፎም ከአሁን ቀደም የተናገረው ንግግርም መረሳት የለበትም።

እነ ጠርጠራው ይሆኑ እንዴ በአከባቢ እየመረጡ ለወደዱለት ብቻ ትግዋይነትን የሚቀድሱለትና የሚባርኩለት?

15/02/2025

«ህወሓት እንድትከስም እያደረጋት ያለው ከእኔ በላይ ለድርጅቷና ለትግራይ ህዝብ የሚቆረቆረቆር ማንም የለም የሚል ትዕቢትና እብሪት (ego) ነው።»

ክብርት ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከ VOA Tigrigna ጋር እጅግ ወሳኝ ጉዳዮች ያነሱበት ቃለ መጠይቅ አድርገዋል።

በሰፈርህ የበደልና የጭቆና ዝናብ እያዘነብክ ሌላው ግን በአንተ ላይ ፍትሃዊ ይሆን ዘንድ ትጮሃለህ።በአክሱም በሙስሊምነታቸው ብቻ 159 ተማሪዎች ከትምህርት እያባረርክ፣ ፍትህ እንዳያገኙ የወረ...
15/02/2025

በሰፈርህ የበደልና የጭቆና ዝናብ እያዘነብክ ሌላው ግን በአንተ ላይ ፍትሃዊ ይሆን ዘንድ ትጮሃለህ።

በአክሱም በሙስሊምነታቸው ብቻ 159 ተማሪዎች ከትምህርት እያባረርክ፣ ፍትህ እንዳያገኙ የወረዳው ፍ/ቤት ዳኛን እያስፈራራህና ጫና እያደረግክ ነገር ግን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሚሰጠው ፍርድና ውሳኔ ያንገሸግሸሃል።

መቐለ ቀበሌ 17 የሚገኘው ጧኢፍ መስጂድ‼️በአሏህ ፈቃድ አክሱምም ከመስጂድና ሚናራው ጋር እርቅ ሰላም የምታወርድበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም‼️
14/02/2025

መቐለ ቀበሌ 17 የሚገኘው ጧኢፍ መስጂድ‼️

በአሏህ ፈቃድ አክሱምም ከመስጂድና ሚናራው ጋር እርቅ ሰላም የምታወርድበት ጊዜ እሩቅ አይሆንም‼️

በግልፅ ነው መነጋገር ያለብን‼️ህወሓት በኢትዮጵያ የአንድ ብሄር በትግራይ ደግሞ የአንድ ሃይማኖትና አከባቢ የበላይነት ለማረጋገጥ ብዙ የተገለ ድርጅት ነው። ነገር ግን ለመጥቀም ፈልጎ የታገለ...
14/02/2025

በግልፅ ነው መነጋገር ያለብን‼️

ህወሓት በኢትዮጵያ የአንድ ብሄር በትግራይ ደግሞ የአንድ ሃይማኖትና አከባቢ የበላይነት ለማረጋገጥ ብዙ የተገለ ድርጅት ነው። ነገር ግን ለመጥቀም ፈልጎ የታገለለትን የህ/ሰብ ክፍልም ቢሆን ያልጠቀመ ድርጅት ነው። ይህን እውነት ድርጅቱ ደጋፊ እንዳያገኝ በማሰብ ከመናገር ዝም ብንልና ደጋፊ እንኳ ቢያገኝ ድርጅቱን በመደገፉ የሚጎዳ፣ የሚበደል፣ የሚጨቆን እንጂ የሚጠቀም ማንም አይኖርም።

እርግጥ ነው ህወሓት ሃይማኖታዊና ከባቢያዊ ድርጅት ነው። ይህ ማለት ግን በድርጅቱ የአከባቢው ክርስትያን ቢሆን ተጠቅሟል ማለት አይደለም።

14/02/2025

«ይትረፍካ ምጅጋን»‼️

 #ህወሓት በፖለቲካ ድርጅትነት በትግራይም ይሁን በኢትዮጵያ ስልጣን ተቆጣጥሮ በመንግስትና በህግ ስም ህዝቡን በአከባቢና በሃይማኖት ሽብርና ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ለ 50 ዓመታት የኖረ ድርጅት ...
14/02/2025

#ህወሓት በፖለቲካ ድርጅትነት በትግራይም ይሁን በኢትዮጵያ ስልጣን ተቆጣጥሮ በመንግስትና በህግ ስም ህዝቡን በአከባቢና በሃይማኖት ሽብርና ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ለ 50 ዓመታት የኖረ ድርጅት ነው። ለብዙ ዓመታት መኖሩ ማለትም ህዝቡ ታግሎ አለማጥፋቱ መታየት የለበትም። ድርጅቱ ብዙ ዓመታት ቢኖርም በህግና ስርዓት ተመርቶ ለህዝቡ ሰላምና ፍትህ ሲሰራ ታይቶ አያውቅም።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በይፋ ተጀመረ። ግንባታውን ያስጀመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ናቸው።••••••••••••••••የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት  ...
09/02/2025

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ በይፋ ተጀመረ። ግንባታውን ያስጀመሩት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ናቸው።
••••••••••••••••

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በአፍሪካ ሕብረት መሠብሰቢያ አዳራሽ አካባቢ የሚገነባውን የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል የመጀመሪያ ዙር የግንባታ ሂደት አስጀምረዋል።

ፕሬዝደንቱ ፕሮጀክቱን ባስጀመሩበት መርሐ ግብር ላይ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከ2015 ዓ.ል ጀምሮ የፕሮጀክቱ ግንባታ በአግባቡ እንዲከወን የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ እንደቆየ አንስተዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሰያሚነት የተቋቋመውና ግንባታውን በበላይነት የሚመራው ኮሚቴ ላለፉት ሁለት አመት አጠቃላይ የቅድመ ዝግጅትና የጨረታ ስራዎችን ያለ ምንም ክፍያ ሲሰራ እንደቆየም የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጂ ኢብራሂም ጠቅሰዋል።

ሸይህ ሀጅ ኢብራሂም አክለውም የአለም አቀፉ ኢስላማዊ ድርጅት (ራቢጣ) ፕሮጀክቱን ለማስገንባት ቃል በገባው መሰረት ገንዘብ ለመልቀቅ የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰ ቢሆንም ጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕዝበ ሙስሊሙን ተደጋጋሚ ጥያቄ ለመመለስ በመጅሊሱ የውስጥ አቅም ግንባታው እንዳስጀመረ አመላክተዋል።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ተጠናቆ እውን እስኪሆን ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራም ፕሬዝደንቱ አረጋግጠዋል።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ አበይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በቡላቸው ግንባታውን ለመጀመር እረጅም ጊዜ የወሰደው ፕሮጅክቱን የሚመጥን ዲዛይን ለማዘጋጀትና ለመምረጥ ጊዜ በማስፈለጉ መሆኑን ጠቅሰው የግንባታው ምዕራፍ ያንን ሊያካክስ በሚችል መልኩ እንደሚፋጠን ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክት ለሀገርና ለህዝብ ትልቅ እሴት የሚጨምር በመሆኑን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅድሚያ እንደሚሰጠው የገለፁት ደግሞ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያ ሀጅ ከማል ሀሩን ናቸው።

ዋና ስራ ሥራ አስኪያጁ መሬቱ ከተገኘበት 2012 ዓ.ል ጀምሮ እስከ 2015 ምንም አይነት የስራ እንቅስቃሴ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሰው የለውጡ መጅሊስ ፕሮጀክቱ ካለው ሀገራዊ ፋይዳ አንጻር ትኩረት በመስጠት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤትና አብይ ኮሜቴ አዋቅሮ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም አንስተዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባላት እና በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደርን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ም/ቤት

Address

Riyadh

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ትግራይ ሙስሊም ሚድያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share