ኪቢሽ - KMC

ኪቢሽ - KMC ለአሁናዊ ፈጣን መረጃዎች የኢትዮጵያውያን ታማኝ ምንጭ ነን !!

ኤርትራ የኢትዮጵያን  ክስ "ወታደራዊ ጠብ አጫሪነት" ነው አለች ኢትዮጵያ ጦርነት ልትከፍትብኝ እየተዘጋጀት ነው ስትል  የከሰሰቻት ኤርትራ፤ ክሱን "ወታደራዊ ጠብ አጫሪነት" ስትል ውድቅ አደ...
09/10/2025

ኤርትራ የኢትዮጵያን ክስ "ወታደራዊ ጠብ አጫሪነት" ነው አለች

ኢትዮጵያ ጦርነት ልትከፍትብኝ እየተዘጋጀት ነው ስትል የከሰሰቻት ኤርትራ፤ ክሱን "ወታደራዊ ጠብ አጫሪነት" ስትል ውድቅ አደረገች።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል፤ «የቀድሞ ግዛትን ለማስመለስ ያለመ" ያሉትን ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ፣ ወታደራዊ የጠብ አጫሪነት የታከለበት ነው ሲሉ ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬቭ በላከው ደብዳቤ አስመራ ፣ ፅንፈኛ ካለው የህወሓት አንጃ ጋር ኢትዮጵያን ለመውጋት እየተዘጋጁ ነው ሲል ከሷል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞትዮስ የፈረሙበት ይህ ደብዳቤ፤ የፌደራል መንግሥት ወታደሮች ከአማጽያን ጋር በሚዋጉበት በአማራ ክልል «ሁለቱ አካላት የታጠቁ ቡድኖችን ይደግፋሉ፣ ያንቀሳቅሳሉ ይመራሉም" ሲልም ይወቅሳል።

26/09/2025

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ቤንያሚን ኔትኒያሁ (Benjamin Netanyahu) የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድርግ መድረኩን ሲይዙ የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት ተወካዮች አዳራሹን በጩኸት አደበላልቀው ገሚሶቹም ለቀው ወጥተዋል። ጉባኤውን የሚመሩት የወቅቱ የተመድ ሊቀመንበርም ልኡካኑ ዝም እንዲሉና አዳራሹን ለቀው እንዳይወጡ ሲማጸኑም ታይተዋል።

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን በሰሞንኛው የተመድ ጉባኤ ላይ በግልጽ አሳውቃለች፡፡ፕሬዝዳንት ታዬ በ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ቀይ ባሕርን እና ህንድ ...
26/09/2025

ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋን በሰሞንኛው የተመድ ጉባኤ ላይ በግልጽ አሳውቃለች፡፡

ፕሬዝዳንት ታዬ በ80ኛው የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ቀይ ባሕርን እና ህንድ ውቅያኖስን የሰው ልጆች "የጋራ ቅርስ" ሲሉ በመግለፅ፣ ሁሉም ሀገራት እኩል ተደራሽነት እንዲኖራቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

አያይዘውም ከፍተኛ ባሕርን የሰው ልጅ የጋራ ቅርስ አድርጎ የሚገልጸው እና ሁሉንም ሀገራት በእኩልነት የመጠቀም መብትን የሚያረጋግጠው የዓለም አቀፍ ሕግ እውን መሆን አለበት ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በአዋዛ ቱርክሜኒስታን ተካሄዶ በነበረው ሶስተኛው የባሕር በር የሌላቸው በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ጉባኤ ላይ የተናገሩትን በማስታወስ፣ "አንድም ሀገር በጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ምክንያት ከልማት ዕድሎች ሊገለል አይገባም" ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ በቀይ ባሕርና በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ለሚገኙ ሁሉም ሀገራት እኩል ልማትና ደህንነትን ለማረጋገጥ "ሁሉን አቀፍ አካሄድ" እንደምትከተል ገልፀው "ህጋዊ የፖሊሲ ግቧን በዲፕሎማሲያዊና በሰላማዊ ተሳትፎ እንደምታስቀጥል" ቃል ገብተዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሁለተኛ ትልቅ የሕዝብ ብዛት ያላት እና ከፍተኛ የባሕር ንግድ ያላት እንደመሆኗ በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ ደኀንነት ላይ ልዩ ትኩረት እንደምትሰጥ መግለፃቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የቅዱሳን ስዕላትን በመቅደድ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስታሰራጭ የነበረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡  ቤተልሄም ሚሊዮን ሳህሉ ሠሞኑን የቅዱሳን ስዕላት በመ...
26/09/2025

የቅዱሳን ስዕላትን በመቅደድ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስታሰራጭ የነበረችውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ቤተልሄም ሚሊዮን ሳህሉ ሠሞኑን የቅዱሳን ስዕላት በመቅደድ በማህበራዊ ሚዲያ ማሰራጨቷ ይታወቃል፡፡ ኃይማኖትን ማንቋሸሽ እና ማዋረድ ተገቢነት የሌለው እና በህግ የሚያስጠይቅ ህገ-ወጥ ተግባር በመሆኑ ፖሊስ ግለሰቧን በፈፀመችው ድርጊት መስከረም 16 ቀን 2018 ዓ/ም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ፍጹም እና ዘላቂ ሰላምን የምንሻ ከሆነ ይቅርታን እና ዕርቅን፣ እኩልነትን እና አንድነትን፣ ፍትህን እና ርትዕን ማረጋገጥ ይገባል አሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊ...
26/09/2025

ፍጹም እና ዘላቂ ሰላምን የምንሻ ከሆነ ይቅርታን እና ዕርቅን፣ እኩልነትን እና አንድነትን፣ ፍትህን እና ርትዕን ማረጋገጥ ይገባል አሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት።

የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች እየተከበረ ነው።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት፤ እንኳን ለ2018 ዓ.ም በዓለ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።

በእግዚአብሔር ኃይል በጢሰ እጣን አመልካችነት ከተቀበረበት ጉድጓድ የወጣው መስቀል እስከዛሬ ድረስ የእውነት መስካሪ እና የድኅነት ምልክት ሆኖ ቀጥሏል ነው ያሉት።

ዛሬ ላይ ሕገ እግዚአብሔር በድፍረት ይጣሳል፣ የዚህ ውጤትም ዓለምን በአጠቃላይ በመኖር እና ባለመኖር መካከል እየከተተ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ፍጹም እና ዘላቂ ሰላምን የምንሻ ከሆነ ይቅርታን እና ዕርቅን፣ እኩልነትን እና አንድነትን፣ ፍትህን እና ርትዕን ማረጋገጥ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የዘንድሮው የመስቀል በዓል አከባበር እግዚአብሔር የሰጠን የውሃ ጸጋችን ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለመጠቀም በአንድነት ባካሄድነው ተግባር ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድባችንን አጠናቀን ባስመረቅንበት ማግስት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ይህ ክስተት ለሀገራችን የዳግም ልደትን ያበሰረ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ያሉት ብጹዕነታቸው፤ በግድቡ ግንባታ ስራ ላይ ታሪካዊ አሻራቻውን ያሳረፉትንም ሁሉ ማመስገን እንደሚገባ ገልጸዋል።

በቀጣይ ሀገራችን ልትሰራቸው በዕቅድ የያዘቻቸውን ታላላቅ ስራዎች በፍጥነት እና በጥራት ተሰርተው ለሕዝባችን ጥቅም እንዲውሉ ሁላችንም መረባረብ ይኖርብናልም ነው ያሉት።

ታላላቅ እና ዘመን ተሻጋሪ እንዲሁም ችግር አስወጋጅ ስራዎች እውን ሊሆኑ የሚችሉት ሕዝቡ በአንድነት እና በሕብረት ሲሰራ እንደሆነ ገልጸው፤ በግድቡ የታየው ትብብር እና ተነሳሽነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠቁመዋል።

አለመግባባቶችን በዕርቅ እና በይቅርታ በማለፍ እኩልነትን፣ ፍትህን እና ርትዕን በማረጋገጥ እንዲሁም ለሰላም መስፈን ረዥም ጉዞ በመሄድ ሕዝቡን ወደ አንድነት ማምጣት እንደሚገባም አመላክተዋል።

የመስቀሉ መልዕክት የሰው ልጅን ሁሉ በሰላም፣ በሕይወት፣ በእኩልነት፣ በአንድነት ማኖር መሆኑን በመገንዘብ ከመጠፋፋት ይልቅ በጋራ መልማትን ምርጫ ማድረግ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

"የደመወዝ ጭማሪው አልተራዘመም፣ ተራዝሟል የሚል መረጃ የተሳሳተ ነው"ከያዝነው መስከረም ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ይፋ የተደረገው የደሞዝ ማሻሻያ አልተራዘመም፣ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳ...
21/09/2025

"የደመወዝ ጭማሪው አልተራዘመም፣ ተራዝሟል የሚል መረጃ የተሳሳተ ነው"

ከያዝነው መስከረም ወር ጀምሮ ለመንግሥት ሠራተኞች ይፋ የተደረገው የደሞዝ ማሻሻያ አልተራዘመም፣ከመስከረም ወር ጀምሮ ታሳቢ የተደረገ የደመወዝ ክፍያ ይፈፀማል።

"ተራዝሟል የሚለው መረጃ ከየት እንደመጣ አላውቅም። መረጃው ለህዝብ ይፋ ከተደረገ ጀምሮ ከመስከረም የሚጀምር የደሞዝ ጭማሪ ለማስፈፀም ስራ ስንሰራ ቆይተናል"- ሲሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባልደረባ ተናግረዋል።

በዚህም አዲስ የደሞዝ ማሻሻያ መሰረት ዝቅተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደሞዝ ከብር 4,760 ወደ ብር 6,ዐዐዐ እንዲያድግ መደረጉ ይታወሳል።

በተጨሜሪም ከፍተኛው የመንግሥት ሠራተኛ ደሞዝ ከብር 21,492 ወደ ብር 39,000 እንዲሁም የዲግሪ ተመራቂ መነሻ ደመወዝ ከብር 6,940 ወደ ብር 11,500 መደረጉ በወቅቱ ይፋ ተደርጎ ነበር።

ይህም ለደመወዝ የሚወጣውን ጠቅላላ ዓመታዊ የመንግሥት ወጪ 56ዐ ቢሊዮን ብር ያደርሰዋል ተብሏል መባሉን መሰረት ሚዲያ ዘግቧል

አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ፔጃችንን Follow ያድርጉ🙏

[ኪቢሽ-Media]

" ሀቢቢ come to Afghanistan "የአሜሪካኑ መሪ ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አፍጋኒስታን ባግራም የአየር ሰፈርን በፀባይ  ካልመለሰች ነገሮች ጥሩ አይሆኑም ሲል ለማስፈራራት ሞክሯል ።...
21/09/2025

" ሀቢቢ come to Afghanistan "

የአሜሪካኑ መሪ ዶናልድ ትራምፕ ትናንትና አፍጋኒስታን ባግራም የአየር ሰፈርን በፀባይ ካልመለሰች ነገሮች ጥሩ አይሆኑም ሲል ለማስፈራራት ሞክሯል ።...........
አሜሪካ አፍጋንን ለመቆጣጠር በሞከረችባቸው ሀያ አመታት ከአንድ ሚሊየን በላይ ወታደሮች አሰማርታለች ።

ከሁለት ትሪሊዮን ሶስት መቶ ቢሊየን ዶላር አውጥታለች ፡ የሰው ሀገር ሊወሩ የሄዱ በሺህ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን አጥታለች ።

ሆኖም አሜሪካን ይህን ሁሉ አድርጋ ፡ ለሀያ አመታት በእጇ አስገብታው የነበረውን የባግራም አየር ሰፈርን ይዛ መቆየት አልቻለችምና ለቅቃ ወጥታለች ።

በዚህ ወቅትም አሜሪካ ወደ አፍጋኒስታን ይዛቸው መጥታቸው የነበሩት የቢሊየን ዶላር መሳሪያዎች አፍጋኒስታን ትታው በመውጣቷ ፡ አሁን ላይ ጣሊባን ማለት እጅግ ዘመናዊ የጦርሜዳ መነፅር አንስቶ ብላክ ሃውክን የመሰለ ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች ባለቤት ነው ።

በወቅቱ አሜሪካን ትታቸው ሄዳ በጣሊባን እጅ የገቡ የጦር መሳሪያዎች ዝርዝር

22,174 ............ humvee ተሽከርካሪዎች ፡
634 ..............ባለጎማ ታንኮች
155 .................ማክስ ፕሮ ማይን ፕሩፍ ተሽከርካሪዎች
169 ................. MII17 ታንክ
42 ሺህ. ...............ተሽከርካሪዎች
8ሺህ ................ከባድ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች
162,043 ..........ወታደራዊ የሬዲዮ መገናኛዎች
16,035 ............በምሽትም የሚያሳዩ ወታደራዊ የጦር ሜዳ መነፅሮች
358,530 ...........ቀላል ጠመንጃዎች
64,363 .............አውቶማቲክ ጠመንጃዎች
126,295 ........... ሽጉጥ
176 ...............መድፍ
33 .................MI ሄሊኮፕተሮች
33 .................. black hawk ዘመናዊ የጦር ሄሊኮፐተሮች
43. ............. MD 530 ዘመናዊ ሄሊኮፕተሮች
4 - ...........C130 ወታደራዊ መጓጓዣ አውሮፕላኖች
23 .............. EMB አውሮፕላኖች
28 .............. ሴሲና አውሮፕላኖች
10................. ሴስና ተዋጊ አውሮፕላኖች በሙሉ አሁን የታሊባን ናቸው .......
አሁን ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ ፡ አሜሪካ ትሪሊዮን ዶላሮችና ፡ የቢሊዮኖች መሳሪያ ትታ ወደ ሄደችው ወደ አፍጋኒስታን በውድም ሆነ በጉልበት እመለሳለሁ እያለች ነው ።

ጣሊባን በበኩሉ ይህንን የትራምፕን ንግግር ከሰማ በኋላ ዳግም ልታስታጥቀው እንደምትመጣ በማሰብ ሀቢቢ come to Afghanistan እያለ ነው ።

አፍጋኖች ከትናንቱ የትራምፕ ፉከራ በኋላ አደለም አሁን በራሷ በአሜሪካን ይህን ያህል ታጥቀን በሩሲያ ክላሽንኮቭ ለሀያ አመታት ለአሜሪካን አልተንበረከክንም ፡ የአፍጋን ምድርን ትርገጥና እንተያያለን እያለ ነው ።

በዋሲሁን ተስፋዬ
[ኪቢሽ- Media ]

የባንክ እዳዋን በመክፈል ባሏ የሞተባትን የ3 ልጆች እናት ነፃ ያወጡት ሰው !!ያዕቆብ ዮዶሩ ይባላሉ። በሲዳማ ክልል ዳዬ ከተማ ለምትኖር ባለ ዕዳ እናት ባንክ ገብተው 408 ሺህ 410 ብር ...
10/06/2025

የባንክ እዳዋን በመክፈል ባሏ የሞተባትን የ3 ልጆች እናት ነፃ ያወጡት ሰው !!

ያዕቆብ ዮዶሩ ይባላሉ። በሲዳማ ክልል ዳዬ ከተማ ለምትኖር ባለ ዕዳ እናት ባንክ ገብተው 408 ሺህ 410 ብር ከ55 ሳንቲም ዕዳዋን ከፍለዋል።

የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ይህች ሴት ባሏ በሞት ከተለያት በኋላ ልጆቿን በብቸኝነት እያሳደገች ሲሆን የምትኖርበት ቤትም በባንክ ብድር ምክንያት ሊወረስባት ተቃርቦ እንደነበር ነው የተገለፀው።

የሐይማኖት አባት የሆኑት አቶ ያዕቆብ ዮዶሩ የተባሉት ሰው ይህች ሴት አማራጭ አጥታ ችግሯን ለጉባኤው ስታስረዳ ሰምተው ነው ለችግሯ መፍትሄ መሆን አለብኝ ያሉት።

ያኔም ጊዜ ሳይወስዱ አከባቢው ወዳለ የአዋሽ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል በመቅረብ፣ በእናቲቱ ላይ የተመዘገበውን
የ408 ሺህ 410 ብር ከ55 ሳንቲም ዕዳ ሙሉ በሙሉ ከፍለዋል።

በባንክ ተይዞ የነበረው የቤቱ ካርታ ፕላንም ለእናቲቱ ሰጥቷም ቤቷን ከመወረስ ቤተሰቧንም ከጭንቀት ታድገዋታል።

የዚህ መልካም ሰው ተግባርም አሁን ላይ በብዙዎች ዘንድ ውዳሴ እየተቸረው ይገኛል::

Address

Kampala

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኪቢሽ - KMC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ኪቢሽ - KMC:

Share